Paul's Final Greetings
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሮሜ በሚገባ ስለ ወንጌል ነው ፡፡ ይህ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ በሮም ላለች ቤተ ክርስቲያን እዉነት እንደሚሆን የሚያዉቁትን እንዴት በተግባር መኖር እንዳለባቸዉ የሚገልፅበትን ቃል ስለ ማድረሱ ነው ፡፡ በሮሜ 16 ጳዉሎስ በሕይወቱ ላይ አስፈላጊ/ጠቃሚ ነገርን የተጫዎቱትን ሰዎች ይጠቅሳል ፡፡ ይህ ምዕራፍ እንደ መደምደሚያ ነው - በፊልም ወይም በድርጊት መጨረሻ ላይ ተመስጋዮች እንደሚዘረዘሩት ፡፡
ትምህርት
ሮሜ (16፡ 1-2)፡ ጳዉሎስ ፌበንን መልዕክቱን በዚያ ላሉ አማኞች እንድታደርስ በማመን ወደ ሮም አዘዛት ፤ ለሮም ቤተ ክርስቲያን በሚገባ የእዉነት የመልካም ዜና አድራሽ ነበረች ፡፡ ጳዉሎስም እንዲቀበሏት እና “ ህዝቡን በሚጠቅም መንገድ እንዲረዷት “ አሳሰባቸው (ቁጥር 2) ፡፡ በሌላ ቋንቋ ለማረፊያ፣ ለምግብ እና ከሌሎች አማኞች ጋር ህብረት እድታደርግ የመቀመጫ ስፍራንእንድታገኝ እርግጠኛ ለመሆን አሳሰባቸዉ ማለት ነው ፤ አስባችሁታል - ፌበን ከ66 የመፅኀፍ ቅዱስ መፅኀፍት ዉስጥ አንዱን ብትይዝም ፍንጭ አልነበራትም !
ሮሜ (16፡ 3-16)፡ ጳዉሎስ ስለ እርሱ ህይወታቸዉን አደጋ ላይ በመጣል አብረዉት ይሰሩት ለነበሩት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታን ላከ ፤ ከእርሱ እና ከአሕዛብ አብያተ ክርስቲያናትም ምስጋናን ገለጸላቸው (ቁጥር 4) ፡፡ ጳዉሎስ ሮማዉያንን በቤታቸዉ ላለች ቤተ ክርስቲያን እና በእስያ ወደ ክርስቶስ በመዞር የመጀመሪያ ለሆነው ለአጤኔጦን ሰላምታ እንዲያቀርቡለት አሳሰባቸው (ቁጥር 5) ፡፡ ጳዉሎስ ሰላምታን ለማሪያም (ቁጥር 6) እና ቀድመዉ ለተከተሉት እና ለእስረኞቹ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን አደረገ (ቁጥር 7) ፡፡ ለጵልያጦንም (ቁጥር 8)፣ ለኢሩባኖን እና ለስንጣክን (ቁጥር 9)፣ ለኤጤሌን እና ለአርስጣባል ቤተሰቦች (ቁጥር 10)፣ ለሄሮድዮና እና ለከንርቀሱ ቤተሰቦች (ቁጥር 11)፣ ለፕሮፊሞናና፣ ለጢሮፊሞሳ፣ ለጠርሲዳ (ቁጥር 12)፣ ለሩፎን እና ለእናቱ (ቁጥር 13)፣ ለአስቀሪጦና፣ ለአፍለሶንጳ፣ ለሄሮሜን፣ ለጳጥሮባም፣ ለሄርማን (ቁጥር 14)፣ ለፍሌጎን፣ ለዩልያ፣ ለኔርያና ለእህቷ ለአልንጦንም (ቁጥር 15) ሰላምታን አቀረበ ፡፡ ጳዉሎስ እነዚህን ሰዎች በክርስቶስ አገልግሎት ብዙ ፈፅመዉ ስለ ነበር እንደ ጠንካራ ሰራተኛ አከበራቸው ፡፡ እነዚህን ቤተ ክርስቲያን እንደ መሰረተ እንደ መስራች ጳዉሎስ በሮም ላሉ አማኞች ሰላምታቸዉን ላከ (ቁጥር 16) ፡፡
ሮሜ (16፡ 17-18)፡ ጳዉሎስ በመመልከት “ የተማሩትን ትምህርት ከሚቃወሙት መለያየትንና ማሰናከያን የሚያስተምሩትን “ እንዲያስወግዱ ይነግራቸዋል (ቁጥር 17) ፤ ከእነርሱ ተጠንቀቁ ምክንያቱም የሚያገለግሉት ክርስቶስን ሳይሆን ራሳቸዉን ስለሆነ ነው (18) ፡፡ መልካም በሚመስል መልኩ ስለሚያወሩ ትክክል ሳላልሆኑ ተጠንቀቁ ፡፡
ሮሜ (16፡ 19-20)፡ ጳዉሎስ በመባረኩ በተደጋጋሚ “ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን “ የሚለዉን ሀረግ ይጠቀማል (1ቆሮ 16፡ 23, 2ቆሮ 13፡ 13, ገላ 6፡ 18, ኤፌ 6፡ 24, ፊል 4፡ 23, ቆላ 4፡ 18, 1ተሰ 5፡ 28, 2ተሰ 3፡ 18, 1ጢሞ 6፡ 21, 2ጢሞ 4፡ 22, ቲቶ 3፡ 15, ፊል 15፡ 25) ፡፡
ሮሜ (16፡ 21-24)፡ እነዚህ ጳዉሎስ ሰላምታ ያቀረበላቸዉ ሰዎች ነበሩ ነገር ግን ብቻዉን አልነበረም ፡፡ ጢሞቲዎስ የጳዉሎስ የስራ ባልደረባ ነበር ፤ ሊቂዮስ፣ ኢያሶን እና ሱሲጴጥሮስ ዘመዶች ነበሩ (ቁጥር 21) ፡፡ ይህን መልዕክት የፃፈው ጤርጥዮስ የጳዉሎስ ፀሀፊ ነበር (ቁጥር 22) ፤ ጋዮስ የቤተ ክርስቲያን እና የጳዉሎስ አስተናጋጅ ሲሆን ፤ ገንዘብ ያዥዉ ኤርስጦስ ሲሆን ቁአስጥሮስ ደግሞ ምናልባትም ጳዉሎስ ካሳመናቸዉ ዉስጥ አንዱ ነበር ፤ ይህ ቡድን በሮም ቤተ ክርስቲያን ለቀሩት አማኞች ሰላም ያለ ነበር ፡፡
ሮሜ (16፡ 25-27)፡ ማክአርቱር “ ለረጅም ዘመናት ተደብቆ የቆየዉን ሚስጥር “ (ቁጥር 25) “ እግዚአብሄር ለአሕዛብ እንዲሁም ለአይሁዶች በሚሰጠዉ ሚስጥር “ ይገልፀዋል ፤ በቀድሞዉ ጊዜ ተደብቆ የነበረ እና አሁን ደግሞ እንዲታወቅ የተደረገ ነገር ነዉ ፡፡
ይህ ሐዋሪያው ጳዉሎስ በጉዞዉ ላይ የሆነ ስፍራ ላይ ለማወቅ አግኝቶቷቸዉ የነበሩ ሰዎች ቡድን ደብዳቤዉ በደረሰ ጊዜ በሮም እንደሚሆኑ የሚያዉቋቸዉ ነበሩ ፤ ይህየኬይሊ እምነት ከእግዚአብሄር እንደሆነ ለአገልግሎት ሞደልነት መፅኀፍ ቅዱሳዊ መሰረትን ይሰጣል ፡፡ በኢየሱስ ህይወት ላይ ስንመለከት በገሊላ ባህር ዙሪያ 12,000 እስ 15,000 ህዝብ ነበር ፤ በዚያ ሕዝብ ዉስጥ ኢየሱስ 12 ሰዎች ላይ አፈሰሰ (ኤንሲ የህዝቡ አንድ ፐርሰንት ስክዮር ሩት በሚለዉ ቀመር መሰረት ከተማዋን እንዴት እንደደረሳት በአሽቪሌ ከተቀበለዉ ከኬይሊ ታሪክ ጋር ይገናኛል ) ፡፡ ጳዉሎስ ለሮም በሚፅፍበት ጊዜ በከተማዋ ዉስጥ 1ሚሊዮን የሚያክል ህዝብ ነበር ፤ የዚያን ቁጥር አንድ ፐርሰንት ስክዮር ሩት በምትወስዱት ጊዜ ጳዉሎስ በሮም ከተማ ዉስጥ 100 ሰዎችንዉስጥ ማፍሰስ አስፈልጎታል ፡፡ ጳዉሎስ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ 100 ሰዎችን ባይዘረዝርም የሰዎቹን ቁጥር በቤት ዉስጥ ባሉ ቤተ ክርስቲያን እና በቤት ስላሉ ሰዎች ስትደምሩ እስከ 100 ሰዎች ያክል ስትደምሩ ትደነቃላችሁ ፡፡
ይህ ከክርስቶስ የተማረዉ የጳዉሎስ አቀራረብ ነው ፤ ጳዉሎስ ወደ ሰዎቹ ላይ ማፍሰስ/በደንብ ማዝለቅ እንዳለበት ያውቃል ፡፡ ዉጤታማ አገልግሎት ብዛት ያለዉን ሕዝብ መስበክ አይደለም ፤ በእግዚአብሄር ስራ ላይ በሚንቀሳቀሱ ሰዎች ላይ ማፍሰስ/በደንብ ማስተማር ነዉ እንጂ ፡፡ ቁልፉ ሰዎችን ደቀ መዝሙር ማድረግ ነው ፤ ይህ ጳዉሎስ አድርጎት የነበረው ነው ፡፡ በርናባስበጳዉሎስ እና በማርቆስ ላይ በደንብ እንዲሞሉ አድርጓቸዋል ፤ በተመሳሳይ ጊዜ ጳዉሎስ ጵርስቅላና አቂላም ላይ በደንብ የተሞሉ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ፡፡ ሐዋ (18፡ 24-28) ጵርስቅላና አቂላም አጵሎስን በደንብ እንዲገባዉ አደረጉት ፤ ከዚያም አጵሎስ ወንጌልን ወደ አካይያ ይዞ ሄደ ፡፡ ጳዉሎስ በቲቶ እና ጢሞቲዎስ ላይ ትምህርትን አፈሰሰ ፡፡ በ 2ጢሞ (2፡ 2) ጳዉሎስ ጢሞቲዎስን ወንጌልን “ ለታመኑና ሌሎችን ማስተማር ለሚችሉ “ እንዲናገር ነገረው ፡፡ የመጨረሻ ግቡ የቀረቱ በራሳቸዉ እንዲቆሙ እና በደቀ መዛሙርቱ በኩል ወንጌል መቀጠል እንዲችል ነው ፤ በተጨናነቀ ህዝብ ላይ በመጨናነቅ ከመስበክ/ከማስተማር ይልቅ ከፊት ለፊታችን ባለ አንድ ትክክለኛ ሰዉ ለይ ትምህርትን ለማፍሰስ ማሰብ /መጨነቅ ያስፈልገናል ፡፡ ከፊታችን ባሉት ትክክለኛ ሰዎች ላይ ትምህርትን ስናፈስስ በተመሳሳይ እነርሱም ይህን ማድረግ ይችላሉ ፤ በርናባስ ጳዉሎስ የተባለዉ ሳዉል ላይ ትምህርትን ለማስተማር ፍራቱን ተቆጣጥሮ እንደ ነበር እናስታዉሳለን ፡፡ ጳዉሎስ በግልፅ አለምን የቀየረ አንድ ሰዉ ነበር ይሁን እንጂ ማንም ሰዉ ስለ በርናባስ ምንም አይልም ፤ ይሁን እንጂ በርናባስ እጁን በጳዉሎስ ላይ ለማስቀመጥ እና ስለ እርሱ ለመፀለይ ለጌታ የታዘዘ ባይሆንም ስለ ጌታ ሌሎች ስለሚሰሙ ያውቃል፡፡ በዚህ ምዕራፍ ላይ የተዘረዘሩት ሰዎች ጳዉሎስ ያስተማራቸዉ/በደንብ የሞላቸዉ ነበሩ ምክንያቱም መጀመሪያ ጳዉሎስን በርናባስ ስለሞላው ፡፡
መደምደሚያ
ከሌሎች ጋር የወንጌልን መልዕክት ለመነጋገር ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ስታገኙ በእነርሱ ላይ በደንብ ማስተማር/ማፍሰስን መቀጠል አለብን ፡፡ ይህን ለምንድነዉ የምናደርገው ? ምክንያቱም ህይወታችን የተቀየረዉ በሚያፀድቀዉ ስለሆነ ፡፡ በሮሜ መፅኀፍ ኢየሱስ ኃጢዓታችንን በማንፃት እንደ አዳኝ አገለገለ ፤ በመስቀል ላይ በመሞት አፀደቀን ፡፡ ቅሪቶቹ የያዙት መልዕክት ያ ነው ፡፡ ይህ የሚያስደንቅ የመዳን ምልክ በምትይዙ ጊዜ ለሁሉም ሰዉ መናገር ትችላላችሁ - በአንድ ጊዜ ለአንድ ሰው ፡፡
John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1560.
ጥያቄዎች
-
በሮሜ (16፡ 17-18) ጳዉሎስ ለመከፋፈል ምክንያት የሚሆኑ ሰዎችን እንዲያስወግዱ ያስጠነቅቃል ፤ ለመከፋፈል ምክንያት የሆነ ሰዉ ታውቃላችሁ ? አስወግዳችኋቸዋል ? ብዙ ከፋፍለዋልስ ?
-
በሮሜ (16፡ 19) ጳዉሎስ ለማለት የሞከረዉን እንዴት ትገልፁታላችሁ ? ይህ ለምን አስፈላጊ ይሆናል ? (መዝ 19፡ 7, 1ቆሮ 15፡ 33, 2ጢሞ 3፡ 15)
-
በሮሜ 16 በአብዛኛው ጳዉሎስ ለሰዎች ሰላምታን ላከ ፤ በእናንተ አስተያየት ለዚህ የተለዬ ምክንያት ነበረዉ ወይስ ዝም ብሎ ጳዉሎስ ሰላም እያለ ነው ?
-
በሮሜ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Romans 16:3–6
“Give my greetings to Prisca and Aquila, my coworkers in Christ Jesus, who risked their own necks for my life. Not only do I thank them, but so do all the Gentile churches. Greet also the church that meets in their home. Greet my dear friend Epaenetus, who is the first convert to Christ from Asia.Greet Mary, who has worked very hard for you.”
ጳውሎስ ወንጌልን በማድረስ ላይ ሳለ አግኝቷቸው የነበረውን ብዙ የሮሜ ክርስቲያኖችን ሰላምታ አቀረበላቸው ፡፡ እርሱ በእነዚህ የተለዩ ሰዎች ላይ ያለውን አፍስሷል ደግሞም በቤታቸው ጊዜን አሳልፏል ፡፡ እነርሱ ወንጌልን የበለጠ ማስፋት ማስቀጠል ይችሉ ዘንድ ጳውሎስ የምስራቹን ወንጌል መልካሙን ዜና ለእነርሱ አካፈለ ፡፡
አንተም ተመሳሳይ ለሆነ ነገር ማለትም ፡- የወንጌሉን መልዕክት በዙሪያህ ባሉ ሰዎች ላይ ልትዘራ ተጠርተሃል ፡፡ አንተ ይህን ስታደርግ ፣ እነርሱ ደግሞ በዙሪያቸው ወዳሉ ሰዎች ወንጌሉን ያደርሳሉ እና በቃ እንድህ እንድህ እያለ ይቀጥላል ፡፡ ያ ኢየሱስ እንዴት ያገለግል እንደነበር እንድሁም ህይወትን የሚቀይረውን የወንጌሉን እውነት በማድረስ ደረጃ ጳውሎስ የኢየሱስን አገልግሎት ምሳሌ አንዴት እንደተከተለ ያሳየናል ፡፡ ጥያቄው አልተመለሰም ፡- የስም ዝርዝርህ ምን ይመስላል ? ስለ ኢየሱስ ጸጋ መልዕክትን የምታከፍለው ሰውስ ? ምናልባት ልጆችህ ፣ የልጅ ልጆችህ ፣ ጎረቤቶችህ ወይም የስራ አጋሮችህ ? ሰዎችን እንደ ኢየሱስ ስትወድና በህይወትህ ስለ ተገለጠው የእርሱ ጸጋ ለሌሎቸ ስትናገር ብዙ ነፈሳትን ትታደጋለህ ፡፡ ይህ የተወሳሰበ ፕሮግራም ወይም ኮንፈረንስ አይደለም ፤ ነገር ግን ይህ በቃ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረት ሰዎችን መውደድ ነው ፡፡ በል አሁን ሄደህ ሰዎቸን ውደድ ፡፡
“ በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ ፤ እነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ፥ የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑአቸው ናቸው እንጂ እኔ ብቻ አይደለሁም ፤ በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእስያ ለክርስቶስ በኵራት ለሆነው ለምወደው ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ ። ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ ። “
- ሮሜ 16፡3-6
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ 16:19–20— “ መታዘዛችሁ ለሁሉ ተወርቶአልና፤ እንግዲህ በእናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ለበጎ ነገር ጥበበኞች ለክፉም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ ። የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን ። “
ሮሜ16:25— “ እንግዲህ ያበረታችሁ ለሚችለው፥ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው ፡፡ “
2ኛ ጢሞቴዎስ 2:2— “ ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።