Paul's Letters Romans

The Jerusalem Collection

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 501 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሮሜ 14 “ አንዱ የሌላዉን “ ተከታታይነት የያዘ ነው ፤ አማኞች “ እርስ በእርሳቸው /አንዱ ሌላዉን “ እንዲነቃቁ፣ እንዲበረታቱ እና እንዲሰራሩ ታዘዋል ፡፡ ሮሜ 15 አማኞችን “ እርስ በእርስ እንዲመሰጋገኑ “ ይመክራቸዋል ፡፡

ትምህርት

ሮሜ (15፡ 1-4)፡ ሌሎችን ስለ ማገልገል ስናስብ ለመስራት የምንፈልጋቸዉን ነገሮች፡- ሳህኖችን ማጠብ፣ ሳርን መቁረጥ እና በቤት ዙሪያ ያለን መልቀም ወ.ዘ.ተ ብቻ ለማድረግ በማሰብ አናዘነብልም ፤ ነገር ግን ሌሎችን በመንፈሳዊ ጉዳይ ማገልገል ለእኛ ምን ይመስላል ? ዮሐንስ ማክአርቱር በዚህ ፅሁፍ ላይ “ መሸከም “ የሚለዉን ቃል አንድ የዉሃ እንስራ መሸከምን (ማር 14፡ 13)፣ ሰዉን መሸከም (ሐዋ 21፡ 35) እና ግዴታን የመሸከም ስዕልን (ሐዋ 15፡ 10) ለመግለፅ ከምንጠቀምበት ቃል ጋር ተመሳሳይ እንደ ሆነ አመለከት ፡፡ የጳዉሎስ ምክር ለሮማዉያን በክርስቶስ ወንድሞቻቸዉ እና እህቶቻቸዉ ለነበሩት ሸክምን ለማቅለል የሚረዳዉን የሚችሉትን ማንኛዉንም ነገር እንዲያደርጉ ነበር ፡፡ ሸክምን መሸከም የተለመደ ተግባርን በማድረግ ከመርዳት፣ የማፅናኛ ቃላትን ከማቃፈል ወይም ከእነርሱ ፊት ሌላ ሰዉን ከሚያስደስተዉ ማንኛዉም ነገር የቀለለ ነው ፡፡

ኢየሱስ በእርሱ ፊት ሌሎችን የማገልገል የመጨረሻዉ ማሳያ ነበር ፤ ነገር ግን ሮማዉያንም በመፅሀፍት ዉስጥ በተመሳሳይ መንገድአንዱ ለሌላዉ የሚጠነቀቁበትን መበረታታት ያገኛሉ ፡፡ ሮማዉያን በራሳቸዉ ላይ ያላቸዉን ትኩረቶች እንዲሁም ለሌሎች ትኩረት እንዳያደርጉ የሚያደርጓቸዉን የቀን ተቀን ድርጊቶቻቸዉን ጨምሮ በማንሳት ትኩረታቸዉን በሌሌች ፍላጎት፣ አስፈላጊ ነገሮች እና ምኞቶች ላይ አደረጉ ፡፡

ሮሜ (15፡ 8-13)፡ ዋይርስቤ ይህ የሮሜ ክፍልለአሕዛብ በኢየሱስ አገልግሎት ላይ የሰፋ እንደሆነ ይፅፋል ፤ ኢየሱስ የአይሁድ ሰዎችን ስላገለገላቸው አሕዛቦችም ወደ እርሱ በእምነት ይመጣሉ ፡፡ የሁለቱም ቡድን ሰዎች በክርስቶስ ስራ የተካተቱ ነበሩ ፡፡

ሮሜ (15፡ 14-24)፡ ዋይርስቤ ከኢየሱስ አገልግሎት ወደ አሕዛብ፣ ከጳዉሎስ አገልግሎት ወደ አሕዛብ የነበረዉ ሽግግር ያስቀምጣል ፡፡ በአገልግሎት የጳዉሎስ አላማ የክርስቶስን ወንጌል በተቻለዉ መጠን ለብዙ ሰዎች መናገር ነበር ፤ ያም ብቻ አልነበረም የጳዉሎስ ፍላጎት ማንም ስለ ኢየሱስ ሰምቶበት ወደ ማያቀዉ ስፍራ ወንጌልን ማድረስም ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በሮሜ የነበሩትን አማኞች በፍፁም አልጎበኛቸዉም ነበር ፤ ሁል ጊዜ በሌላ ስፍራ ባላው ስራዉ ወይም በማይታሰብ ሁኔታዎች ተከልክሏል ፤ ይሁን እንጂ አሁን ወንጌልን በስፔን ለመናገር ሲሄድ ሮምን ለመጎብኘት አቀደ ፡፡

ሮሜ (15፡ 25-29)፡ የጳዉሎስ አገልግሎት ለአሕዛብ ነበር ነገር ግን ዋይርስቤ አሕዛቦች ደግሞ አይሁዶችን እንደሚያገለግሉ ያመለክታል ፡፡ ጳዉሎስ ለሮማዉያን መልዕክቱን እንደ ፃፈው በእዚያ ለነበሩት አማኞች በሜቆዶንያና አካይያ ካሉት አማኞች ስጦታን በመያዝ ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዘ ነበር ፡፡ በሜቆዶንያና በአካይያ ያሉት አማኞች በኢየሩሳሌም ላሉት አማኞች መዋጮ ለማድረግ ለምን ፈለጉ ? ለአሕዛብ መልዕክተኛ የነበረዉ ጳዉሎስ ከአሕዛብ አማኞች ወደ አይሁድ አማኞች ስጦታን ለመዉሰድ ለምን አሰበ/ተመለከተ ? በሜቆዶንያና በአካይያ የነበሩት አማኞች “ ለእነርሱ ባለ ዕዳዎች “ ስለነበሩ (ቀጥር 27) ፡፡ አሁን አሕዛቦች በኢየሩሳሌም እንደ ነበሩት አማኞች ተመሳሳይ የቤተሰብ አካል ነበሩ ፤ ከአይሁዶች መንፈሳዊ ጥቅም በስም ከክርስቶስ ከሆነዉ ድነት መንፈሳዊ ጥቅሞችን ተጋርተዉ ስለ ነበር አሁን አሁንም በኢየሩሳሌም ከአይሁድ አማኞች ጋር ቁሳዊ እቃዎቻቸዉን ይጋራሉ ፡፡

ሮሜ (15፡ 30-33)፡ ጳዉሎስ በኢየሩሳሌም ላሉት የቤተ ክርስቲያንን ስጦታ እንዳያደርስ ሊከለክሉት ከሚችሉት “ በይሁዳ ካሉ አላማኞች “ እንዲጠበቅ እንዲፀልዩለት ጠየቀ ፤ በተጨማሪም ሮማዉያንን ለመጎብኝት ያለዉ እቅድ በመጨረሻም የተሳካ እንዲሆንለት እንዲፀልዩለት ጠየቀ ፡፡

የኢየሩሳሌም መሰባሰብ፡ የገንዘብ ስጦታው በግሪክ እና በአንዳንድ ኢሲያ የተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች በመሰብሰብ በጳዉሎስ መሪነት ስር በኢየሩሳለም ወዳለችዉ ላሳደገቻቸዉ እናት ቤተ ክርስቲያን ላኩ ፤ ይህ ስጦታ በኢየሩሳሌም ያለችዉ እናት ቤተ ክርስቲያን በመላዉ አለም ለአሕዛቦች በጳዉሎስ አገልግሎት ታላቅ ሚና እንደተጫወተች እንዲታወቅ ያደርጋል ፡፡ ጳዉሎስ የአሕዛቦችን ዋጋ መልሶ በገንዘብም በመንፈሳዊ ነገርም ወደ ኢየሩሳሌም ላይ ኢንቨስት ማድረጋቸዉን ተረድቷል ፡፡ ጳዉሎስ ይህን መሰብሰብ ለማድረግ ሰዎስት ፍላጎት ነበረው፡

  1. ድሆችን ለመርዳት ፤ ጳዉሎስ በኢየሩሳሌም ያሉትን ድሀ ክርስቲያኖች አሕዛቦችን በክርስቶስ እንዳገኘበት የእግዚአብሄር ፍቅር ማሳያነት መርዳት ፈለገ ፤ በተጨማሪም ጳዉሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ስለመሰብሰብ ፅፏል፡ “ ትዕዛዝ እንደምሰጥ አልልም ነገር ግን በሌሎች ትጋት በኩል የፍቅራችሁን እዉነተኛነት ደግሞ ልመረምር እላለሁ “ (2ቆሮ 8፡ 8) “ የዚህ ረድኤት አገልግሎት ለቅዱሳን የሚጎድላቸውን በሙሉ የሚሰጥ ብቻ አይደለምና ነገር ግን ደግሞ በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሄር ይበዛል ፤ በዚህ አገልግሎት ስለ ተፈተናችሁ በክርስቶስ በክርስቶስ ወንጌል በማመናችሁ ስለሚሆን መታዘዝ እነርሱንና ሁሉንም ስለምትረዱበት ልግስና እግዚአብሄርን ያከብራሉ ራሳቸዉም ስለ እናንተ ሲያማልዱ በእናንተ ላይ ከሚሆነዉ ከሚበልጠዉ ከእግዚአብሄር ጸጋ የተነሳ ይናፍቁአችኋል ፡፡ ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሄር ይመስገን “ (2ቆሮ 9፡ 12-15) ፡፡

ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ፤ ጳዉሎስ በኢየሩሳሌም ለነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን ምንም እንኳን የአሕዛብ አማኞች ህጉን ባይጠብቁትም አንድ ወንጌል ብቻ እንደ ነበር፣ አንድ ጌታ እና በዚህም ምክንያትአንድ ቤተ ክርስቲያን ብቻ እንደ ነበር ለማሳየት ጓጉቶ ነበር ፡፡

ለማስቀነታ ለማነሳሳት ፤ ጳዉሎስ ወንጌልን ለአሕዛብ ለመናገር የተጠራ ቢሆንም የአይሁድ ወንድሞቹ በአሕዛብ ላይ በሆነዉ ነገር በቅናት በመነሳሳት ወደ ክርስቶስ ሲመጡ ለማየት ፍላጎቱን ጠበቀ ፡፡

መደምደሚያ

የጳዉሎስ ለኢየሩሳሌም ርዳታ/ገንዘብ የማሰባሰብ ተግባር በሐዋሪያት ስራ ሁለተኛዉ አጋማሽ ላይ እና በአብዛኛዎች መልዕክቶቹ ላይ ተስፋፍቷል ፡፡ በ 2ቆሮንቶስ ለዚህ እርዳታ መሰብሰብ በቆሮንቶሳዊያን በልግስና/በቸርነት ስለ መስጠት ጳዉሎስ ይመካል ፡፡ እንደ መንፈሳዊ በረከት ምንጫችን መልሳችሁ በኢየሩሳሌም ላይ ለመዝራት ፍላጎቱ ካላችሁ ለማድረግ አታመናቱ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1553.

  2. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 448.

  3. Wiersbe, p. 448.

  4. Wiersbe, p. 449.

  5. Scot McKNIGHT, “Collection for the Saints,” in Hawthorne, G.F., Martin, R.P. & Reid, D.G., eds. Dictionary of Paul and His Letters (Downers Grove: IVP, 1993), pp. 143–147

ጥያቄዎች

  1. በሮሜ (15፡ 2) ጳዉሎስ “ እያንዳንዳችን እንድናንጸዉ እርሱን ለመጠቀም ባልንጀራችንን ደስ እናሰኝ “ በማለት ይፅፋል ፤ ይህን ትዕዛዝ እንዴት በተግባር ላይ ልናዉለዉ እንችላለን ? የሆነ ሰው በጌታ አንጾአችኋል /አበርትቷችኋል ? እንዴት አድርጎ ?
  2. ሮሜ (15፡ 12) እንዴት ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ? ኢሳያስ “ የዳዊት ስር “ በማለቱ ምን እያለ ነበር ? (ኢሳ 11፡ 1-5)
  3. ጳዉሎስ በሮሜ (15፡ 20) ምን ማለቱ ነው ? ሮሜ (15፡ 21) ለሰዉ እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
  4. በሮሜ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Romans 15:13

“Now may the God of hope fill you with all joy and peace as you believe in Him so that you may overflow with hope by the power of the Holy Spirit.”

ተስፋ ምንድን ነው ? ተስፋ የሆነ ነገር እንድሆን መፈለግ ወይም ደግሞ የሆነ ነገርን መሆን መጠባበቅ ማለት ነው ፡፡ ልክ ፡- “ እንደሚሻልህ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ “ “ ቀዶ ጥገናው በጥሩ ሁኔታ እንደሚጠናቀቅ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ “ ስራውን እንደምታገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ “ በእርሱ ስታምን በደስታና በሰላም የሚሞላህ ፣ እርሱ የተስፋ አምላክ ነው ፡፡ ለሆነ ነገር ተስፋ እያደረክ ከሆነ ፣ ከጌታ ጋር ሁን ፣ በእርሱ እረፍ ደግሞም በፍቅሩ ኑር ፡፡ ጌታን ጠብቅ ታመንም ፡፡ በክርስቶስ ተስፋን በማድረግ ላይ ሳለህ ደስታና ሰላም ይኖርሃል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንደምትትረፈረፍ ጌታ ተናግሯል ፡፡ እስኪ በአምሮህ አስብ የኩሽናው ዕቃ ማጠቢያ በውሃ ሲጥለቀለቅ እና በወለሉ ላይ ሁሉ ሲፈስ ፡፡

በክርስቶስ አካል ውስጥ አንድነትን ተስፋ ስታደርግ ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ውጣ ፡፡ ለህይወትህ የእርሱን ፍጻሜ በጌታ ተስፋ ስታደርግ ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ውጣ ፡፡ ምንም እንኳ ጳውሎስ ወደ ሮም ለመሄድ አጥብቆ ቢፈልግ ደግሞም ተስፋን ቢያደርግም የጳውሎስ የጉዞ እቅድ ግን ብዙ ጊዜ ተቀይሮ ነበር ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ቅዱሳኑን እንድያገለግል ጳውሎስን በኃይል ወደ ተጠቀመበት ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ሌላ እቅድ ነበረው ፡፡ በክርስቶስ በሚገኘው ተስፋ ላይ ስትመለከት የመጨረሻ ውጤቱ ምንም ይሁን ፣ ከእግዚአብሔር ፍቃድ ጋር ተስማምተሃልና ፣ ሰላምና ደስታ ይኖርሃል ፡፡ ዛሬ ተስፋህን በጌታ ላይ ብቻ አድርግ !

“ የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ ። “ - ሮሜ 15፡13

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 33:20–22— “ ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች፥ ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውና ። ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥ በቅዱስ ስሙም ታምነናልና ። አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን፥ በአንተ እንደ ታመንን ። “
  • ሮሜ 15:22–25— “ ስለዚህ ደግሞ ወደ እናንተ እንዳልመጣ ብዙ ጊዜ ተከለከልሁ ። አሁን ግን በዚህ አገር ስፍራ ወደ ፊት ስለሌለኝ፥ ከብዙ ዓመትም ጀምሬ ወደ እናንተ ልመጣ ናፍቆት ስላለኝ ፥ ወደ እስጳንያ በሄድሁ ጊዜ ሳልፍ እናንተን እንዳይ፥ አስቀድሜም ጥቂት ብጠግባችሁ ወደዚያ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ ። አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ ። “
  • ዕብራውያን 10:23— “የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ “