Love In Unity Without Judgement
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሮሜ መፅኀፍ መሲሁን (ኢየሱስን) የሚገልጠዉ አንድ ቃል በእግዚአብሄር ፊት ያፀደቀን የሚያፀድቅ/አፅዳቂ ነው ፡፡ በምዕራፍ 14 ላይ ይዘቱ/ሀሳቡ ከደካማ እና ጠንካራ አማኞች ጋር ስላለዉ መስተጋብር ነው ፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ “ አንዱን ከሌላው “ የሚያገናኘዉን ትዕዛዝ እናያለን ፡፡
ማክአርቱር የዚህን ምዕራፍ የኃላ ታሪክ/መነሻ ሀሳብ “ የበሰለ(ጠንካራ) አማኝ - አይሁድ ወይም አሕዛብ ሁለቱም ቢሆን ከደካማ ወይም በደንብ ክርስትና ካልገባዉ አማኝ ጋር ጠብ/ግጭት በተፈጠረ “ ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እንደ ማስተካካየነት ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር ይህን ግጭት ለመግለፅ በመቀጠልል “ ጠንካራ የአይሁድ አማኞች በክርስቶስ ያላቸዉን ነፃነት ስለተረዱ የሙሴ ህግ የበዓላት አከባበር መስፈርቶች በቀጣይነት የሚይዙ እንዳልነበሩ አስተዉለዋል ፤ ክርስትና የገባቸዉ አሕዛቦች ጣዖቶች አማልዕክቶች እንዳልሆኑ ስለተረዱ ለእነርሱ ተሰዉቶ የነበረዉን ስጋ መብላት ይችላሉ ፤ ይሁን እንጂ በሁለቱም ጉዳይ ደካሞች ወንድሞቻቸው አዕምሮ ታዉኮ ነበር እንዲሁምአሳባቸዉን(ለማድረግ አንድ ሰዉ ራሱን የሚያስለምደዉን መጥፎ ነገር) ለመቃወምም እንኳን የጓጉ ነበሩ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱርየደከሙት አማኞች የሚታገሉበት/የሚጋጩበትን ጉዳዮች “ ደካሞች የአይሁድ አማኞች በሚያስቸግር ሁኔታ የቀድሞዉን ኪዳን ክልከላዎች እና ስርዓቶችን ሙሉ በሙሉ ትተዉ ስለ ነበር ከአመጋገብ ህግ ጋር፣ ሰንበትን ከማክበር ጋር እና በቤተ መቅደስ መስዋዕትን ከማቅረብ ጋር እንዲጣበቁ እንዳስገደደ ተሰማው ፤ የደከሙት የአሕዛብ አማኞች በጣዖት አምልኮና በኃይማኖታዊዉ ስርዓት የቀጠሉ ስለ ነበሩ በኋላ ቀርነት ከደቆሞዉ ጋር የሚገናኝ ማንኛዉም ነገር ለጣዖት ተሰዉቶ የነበረን ስጋን መብላትን እና በገብያ ስፍራ መሸጥን ጨምሮ በኃጢዓት እንደ በከለዉ ተሰማው “ ፡፡ ይህ በእምነት የተለያየዉ መረዳት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ሊያጠፋ ወደ ሚችል ግጭት እየመራ ነበር ፡፡
ትምህርት
ሮሜ (14፡ 1-12)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶች “ አንዱ ሌላዉን ይቀበል/እርስ በእርስ ተቀባበሉ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ሁሉንም ተቀበሉ በእምነት የደከሙትንም እንኳን ቢሆን ስለ ድነት ያልሆነ ጉዳዮች ላይ ባለመከራከር (ቁጥር 1) ፡፡ ለምሳሌ ሮሜ 12 በደንብ ባልጠነከሩ እና በአዲስ አማኞች በስርዓት ስለማይረዱት ነገር እና አብዛኛዉን ጊዜ ሰዎች ስጦታ አላቸዉ ወይም የላቸዉም በሚል ፍርድ/ዉሳኔ ላይ ጉባኤን በሚከፍል ጉዳይ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ላይ ማስረጃዎችን ይሰጣል ፡፡ የምግብ ጉዳይ የፀብ መንስኤ አይሆንም ምክንያቱም አማኞች ማንኛዉንም ነገር ለመብላት ነፃ ናቸው (ቁጥር 2) ፡፡ የተለያየ የግል አስተያየት ያላቸው እርስ በእርሳቸዉ መፈራረድ የለባቸውም ምክንያቱም እግዚአብሄር ሁለቱንም ስለተቀበላቸው (ቁጥር 3) ፤ እርግጥ ነው የጌታቸዉ የሆኑትን መተቸት አንችልም (ቁጥር 4) ፡፡ የትኛዉ የሳምንቱ ቀን ቅዱስ ነዉ በሚለዉ ላይ አንዳንዶች የተለዬ የግል አስተያየት አላቸው ስለዚያም ፍርድ/መፈራረድ የለም (ቁጥር 5) ፤ ቀኑ ጌታን ለማክበር ይከበራል ፤ ምግቡም በጌታ የተሰጠ ነው (ቁጥር 6) ፡፡ የጌታ ስለሆንን ለጌታ እንኖራለን እንሞታለንም (ቁጥር 7-8)፡
“ ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያዉም ሆኖአልና “ (ቁጥር 9) ፤ ማክአርቱር ይህን “ ክርስቶስ ከኃጢዓት ነፃ ሊያወጣን ብቻ ሳይሆን የሞተዉ ለራሱ አገልጋዮች ሊያደርገንም (ሮሜ 6፡ 22)፣ በመገኘቱ በቅዱሳን ላይ እና በምድር ላይ ባሉት ሁሉ ላይ ራሱን እንደ ሉዓላዊ ለማድረግም ነው “ በማለት ይገልፀዋል (ፊል 2፡ 11, 1ጢሞ 6፡ 15, ራዕ 17፡ 14, 19፡ 16) ፡፡ ቁጥር 10-11 የጳዉሎስን ትምህርት ያጠቃልላል - ክርስቶስ ስለ ሁላችን ስለሞተ እርስ በእርስ ለመተቻቸት ወይም ለመፈራረድ ምክንያት ወይም ስልጣን የለንም ፤ ሁሉም ለእግዚአብሄር ምስጋናና ክብር ይሰጣሉ (ኢሳ 45፡ 23, 49፡ 18, ፊል 2፡ 10, ራዕ 20፡ 11-15) ፡፡ ሁላችንም ለመዳኘት በእግዚአብሄር ፊት እንቆማለን (ቁጥር 12) ፤ ስለዚህ እርስ በእርሳችን እንቀባበል ፡፡
ሮሜ (14፡ 13-23)፡ ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ እርስ በእርስ መደጋገፍ/መበረታት “ በማለት ያጠቃልለዋል ፡፡ ቁጥር 13 እርስ በእርስ አትፈራረዱ/አትተቻቹ ወይም በአንዱ በሌላዊ ፊት ማሰናከያን አያስቀምጥ ይላል (1ቆሮ 8፡ 1) ፡፡ ጳዉሎስ ምንም ነገር በራሱ የረከሰ አይደለም ነገር ግን አንድ ሰዉ የሆነን ነገር ርኩስ እንደሆነ ካሰበ ለእርሱ ርኩስ ነዉ በማለት እንደ ገና ተናገረ (ቁጥር 14-16) ፡፡ ይህ ከክርስቶስ በመለኮታዊ መገለጥ ለጳዉሎስ የተሰጠው ነበር ፡፡ በቁጥር 17 ጳዉሎስ ኃሳቡን የእግዚአብሄር መንግስት ስለፅድቅ አንጂ ስለ መብልና መጠጥ የምታስተዳድር አይደለችም በማለት ያጠነክራል ፡፡
እንደ እግዚአብሄር ዜጋ በክርስቶስ ፀድቀናል ፡፡ “ በመንፈስ ቅዱስ ፅድቅ፣ ሰላም እና ደስታ ያለን ነን “ (ቁጥር 17) ፡፡ ፅድቅ ማለት የተቀደሰ ህይወት መኖር ማለት ነው (ኤፌ 6፡ 14) ፤ ሰላም ማለት “ በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ከእግዚአብሄር እና ከሌሎች ጋር ያለ በፀጥታ የመዉደድ የአማኞች ባህሪይ ነው (ገላ5፡ 22) “ ፡፡ ማክአርቱር “ በመንፈስ ቅዱስ መደሰት “ “ ምንም አይነት ሁኔታን ወይም ችግርን ሳያተኩር በእግዚአብሄር ሉዓላዊነት ላይ የተደገፈ የአንድ ሰዉ እግዚአብሄር የማመስገን እና የማክበር የጠበቀ/የሚያጣብቅ አመለካከት የያዘ የመንፈስ ፍሬ ነው (ገላ 5፡ 22, 1ተሰ 1፡ 6) “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ሌሎች በእግዚአብሄር ተቀባይ ለመሆን ከሚያደርጉት ይልቅ በእነዚህ በመንፈስ ፍሬዎች ላይ እናተኩር (ቁጥር 18) ፤ ይህ በአንድነት መስራት በሚችሉት እና እርስ በእርስ በሚሰራሩት በደካማ/በደንብ ክርስትና ባልገባቸዉ አማኞች እና በጠንካራ/ክርስትና በደንብ በገባቸዉ አማኞች መካከል ችግሮችን ያስወግዳል (ቁጥር 19) ፡፡ በምናደርገዉ ነገር ሌሎች እንዲሰናከሉ ምክንያት መሆን የለብንም (ቁጥር 20-21) ፡፡ አማኞች ስለ እግዚአብሄር መነጋገር ነዉ እንጂ ያለባቸዉ በሌሎች ላይ እምነታቸዉን ማስገደድ የለባቸውም (ቁጥር 22) ፡፡
መደምደሚያ
ዋይርስቤ ይህን ምዕራፍ “ አማኞች ስለ ብዙ ጉዳዮች የተለያዩ እምነቶች ይይዛሉ ነገር ግን በፍቅር መያያዝ አለባቸው “ በሚለዉ ቃል ያጠቃልለዋል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1550.
MacArthur, p. 1550.
MacArthur, p. 1551.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 558.
MacArthur, p. 1552.
Wiersbe, p. 560.
MacArthur, p. 1552.
MacArthur, p. 1552.
Wiersbe, p. 561.
ጥያቄዎች
-
በሮሜ (14፡ 1-3) ጳዉሎስ በሚያጣሉ/በሚያከራክሩ ጉዳይ ላይ አንዴ በሌላዉ ላይ ፍርድን እንዳናደርግ ያዝዘናል ፤ የሚያጣሉ/የሚያከራክሩ ጉዳዮች ምንድን ናቸው ? በአሁኑም ስዓት ይህ ዝንባሌ በቤተ ክርስቲያን ላይ እንዳለ ታስባላችሁ ?
-
ሮሜ (14፡ 9) አንብቡ ፤ ክርስቶስ የህያዋን እና የግዑዛን ጌታ ነዉ ማለት ምን ማለት ነው ? (ፊል 2፡ 8-11)
-
ጳዉሎስ ሮማዊያንን አንዱ ሌላዉን በሌላዉ ላይ እንዳይፈርድ አዘዛቸው፣ በዚያ ፋንታስ ምን ያደርጉ ነበር (ሮሜ 14፡ 13) ? ከሮሜ (16፡ 17) ጋር ለማገናኘት ጳዉሎስ እንዴት አለ ?
-
በሮሜ (14፡ 14) መሰረት ጳዉሎስ በራሱ ምንም ነገር ርኩስ እንዳልሆነ አሳመነ ፤ እየጠቀሰ የነበረው ምን አይነት ነገር ነበር ? (ሮሜ 14፡ 20-21)
-
ሮሜ (14፡ 17) የእግዚአብሄር መንግስት ምን አካተተ ይላል ? እንደ እግዚአብሄር መንግስት አካል በጥቃቅን ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ሮሜ (14፡ 19) እንደምንስተዉ ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ ይህን ሂደት እንዴት ልንቀይረዉ እንችላለን ?
-
በሮሜ (12፡ 1) ጥቅም ላይ የዋለው ቃላት በሮሜ (14፡ 18)(ለእግዚአብሄር ተቀባይነት ያለዉ እና የሚያስደስት) ተመሳሳይ ቃላት ጥቅም ላይ ዉሏል ፤ እንዴት እንደሚገናኙ ግለፁ
-
በሮሜ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Romans 14:17–19
“For the kingdom of God is not eating and drinking, but righteousness, peace, and joy in the Holy Spirit. Whoever serves Christ in this way is acceptable to God and approved by men. So then, we must pursue what promotes peace and what builds up one another.”
ጌታ የጠራችሁ እርስ በእርሳችሁ እንድትቀባበሉ ነው ፡፡ ልክ ስጦታን ወይም ደግሞ አስተያየትን እንደምትቀበሉ ሁሉ ፣ እርስ በእርሳችሁም ተቀባበሉ ፡፡ ክርስቶስ እንደሚወደው እናንተም እንደዛው እንድትወዱ ያስፈልጋል ፡፡ አትፍረዱ ፡፡ ሌሎች በእምነት ዳካማ ሆነው ሳሉ በአስተያየቶች ላይ አትከራካሩ ፡፡ አትተቹ ፡፡ በወንድማችሁ መንገድ ላይ አደናቃፊ ወይም ደግሞ የወጥመድ ጉድጓድ አትሁኑ ፡፡ ያ ብዙ “ እመቢታ አለመስማማት “ ነው ፡፡ ሆኖም ግን በእዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንደ ክርስቶስ አማኝ ለጽድቅ ፣ ለሰላም ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ ደስ ሊላችሁ ተጠርታችኋል ፡፡ ስለዚህም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስትመላለሱ የክርስቶስን ፍቅር የሚሳዩትን ፍሬዎች ታፈራላችሁ ፡፡
ጽድቅ ፣ ሰላምና ደስታ አንድነትን ያስገኛሉ ደግሞም ብርታትን ይጨምራሉ ፡፡ እግዚአብሔር በመንግስቱ ውስጥ እንደ ዳኛ እንድትመላለሱ አልጠየቃችሁም ፡፡ እግዚአብሔር ብቻውን ስልጣንን እና ዳኝነትን ይዟል ፡፡ እርሱ በቃ የጠየቃችሁ በእርሱ እና በፍቅሩ ስትኖሩ የሚገለጠውን የመንፈሱን ፍሬ እንድታፈሩ ብቻ ነው ፡፡ ዛሬ በክርስቶስ አካል ወስጥ ባለው ልዩነት ምክንያት አመንትታችሁ እንዳትወድቁ ፡፡ እርስ በእርሳችሁ ለመዋደድና ለመቀባበል ናፍቁ ፡፡ እናም ከዚያ የምትፈልጉት ሰላም ፣ደስታ እና ጸድቅ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይትረፈረፋል ፡፡
“ የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና ። እንደዚህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛልና፥ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው ። እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል ። “
- ሮሜ 14፡17-19
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ 14:1— “ በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ ። “
ሮሜ 14:13— “ እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንፈራረድ፤ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቍረጡ ። “
ቆላስይስ 3:14— “ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።