Paul's Letters Romans

Our Relationship to Authorities; Putting On Christ

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 499 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለሮሜ መፅሀፍ ቃላችን የሚያፀድቅ/አፅዳቂ ነው ፡፡ ኢየሱስ ኃጢዓታችንን አንፆቶታል ፤ አንዴ እምነታችንን በክርስቶስ ላይ ስናደርግ ፀድቀናል ፡፡ በሮሜ (12-16) የሮሜ (1-11) የእምነት መሰረታዊ ስነ መለኮታዊ እዉነቶችን እንዴት መኖር እንደምንችል እናያለን ፡፡ በሮሜ 12 ከእግዚአብሄር ጋር ስላለን ግንኙነት፣ ከሌሎች አማኞች ጋር ስላለን እና ከጠላቶቻችን ጋር ስላለን ግንኙት አዉርተናል ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ባለን ግንኙነታችን የእግዚአብሄርን ፍቃድ እንድናደርግ የሚፈቅድልን የታደሰ አይምሮ አለን ፤ ከሌሎች አማኞች ጋር ባለን ግንኙነታችን ከሌላ ሰዉ የተሸልን እንዳልሆንን እና ራሳችንን ከሌላ አስበልጠን ማሰብ እንደማንችል ተምረናል ፤ ሁላችንም በክርስቶስ አካል ዉስጥ አስፈላጊ ድርሻን እንጫወታለን ፡፡ ከጠላቶቻችን ጋር ባለን ግንኙነታችን ልናበላቸው፣ ልንወዳቸዉ፣ ልንባርካቸው. ለእነርሱ ልንፀልይላቸዉ እና ልናስብላቸዉ እንደሚገባ ተምረናል ፡፡ ከክርስቶስ ጋር ባለን ግንኙነት ምክንያት እነዚህ ሁሉ ቀላል ናቸው ፡፡ በዋረን ዋይርስቤ ንግግር መሰረት ሙሉዉን ምዕራፍ አስራ ሰዎስት ከመንግስት ጋር ስላለን ግንኙነት ይዳስሳል ፡፡ ጳዉሎስ ይህን መፅሀፍ ሲፅፍ ኔሮ በስልጣን ላይ ነበር ፤ ጳዉሎስ አማኞችን ለመንግስት ባለስልጣናት እንዲታዘዙ አበረታታቸው ፡፡ እግዚአብሄር ይህን በስፍራዉ ስላስቀመጠው ሁሉም አማኝ ለባለስልጣኖች የታዘዘ/የተገዛ መሆን አለበት ፡፡

ትምህርት

ሮሜ (13፡ 1)፡ አማኞች በእግዚአብሄር ለተቋቋሙት/ለተሸሙት ለሚያስተዳድሩ ባለስልጣነት መገዛት/መታዘዝ አለባቸው ፡፡ ባንወዳቸዉም ወይም ባንስማማባቸዉም እንኳን ለእነርሱ መገዛት አለብን ምክንያቱም በስፍራዉ ላይ እግዚአብሄር ስላስቀመጣቸው ፡፡ መጠየቅ ያለብን ጥያቄ መታዘዛችን ምን አይነት መሆን አለበት ነው ? እዉነታዉ መታዘዝ በፍፁም ቀላል አይደለም ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የሰዉ ተፈጥሮ በተለይም መንግስት ብቁ ካልሆነ፣ ሙሰኛ እና የሚጫን ከሆነ ወደ ተቃዉሞ እና አመፅ ያዘነብላል “ ብሏል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ለስልጣን ስለ መገዛት ለመረዳት አራት ነገሮችን አቅርቧል ፤ የመጀመሪያው እግዚአብሄር የመጨረሻዉ ባለስልጣን መሆኑን መረዳት ነው ፤ መንግስታት እንደ አንድ ተቋም አላማዉን ለማገልገል በእግዚአብሄር የተመሰረቱ ናቸው ፡፡ እግዚአብሄር መሪዎችን ያስነሳል ያስወግዳልም ፡፡

ሮሜ (13፡ 2)፡ ስልጣንን የሚቃወሙ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ስለሚቃወሙ ፍርድ ያገኛቸዋል (ቁጥር 2) ፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ መሰረት ልንረዳዉ የሚያስፈልገዉ ሁለተኛዉ ነገር “ ተከታዮች እና መሪዎች ሁለቱም በመጨረሻ ለእግዚአብሄር ተጠያቂነት “ እንዳለባቸዉ ነው ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ለሰዉ ስልጣን መገዛት ለእግዚአብሄር ስልጣን ተገዢነታችንን ያንፀባርቃል “ በማለት ይቀጥላል ፡፡

ሮሜ (13፡ 3-4)፡ የኔልሰን ማብራሪያ ሰዎስተኛዉን “ እግዚአብሄር መልካሙን አላማዉን ለመፈፀም መንግስትን እንደሚጠቀምበት “ እንደሆነ ይናገራል ፤ ይህን እግዚአብሄር ስለሰራው መንግስት ለሰዎች በመጠንቀቅ ያስተዳድራል ይቆጣጠራል ይራዳልም እንጂ በእነርሱ ላይ አይሰለጥንም ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ መንግስታት ያለምንም ጥያቄ መልካም ነገር የሚያደርጉትን ያሳድዳሉ “ በማለት ይቀጥላል ፤ ያን ጳዉሎስ በኔሮ ደርሶበታል ፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ ግን ወንጀለኞች እና ህግን የማያከብሩት መንግስትን መፍራት የሚገባቸዉ ናቸው ፤ በሌላ አነጋገር በስርዓት/በትክክለኛዉ መንገድ እስከ ቆየን ድረስ ደህና/ሰላም ነን ፤ ስህተት ስናደርግ ደግሞ የፈራን ልንሆን ያስፈልገናል ምክንያቱም መንግስ እንደ እግዚአብሄር ተበቃይ ስህተት በሚያደርገዉ ላይ ቁጣን ስለሚያመጣበት (ቁጥር 4) ፡፡

ሮሜ (13፡ 5)፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚናገረዉ አራተኛው “ መታዘዝ በዉስጥ እና እንዲሁም ህግን የማመን ጉዳይ ነው “ ፤ “ የመታዘዝ ፍላጎታችን ቅጣትን ከመፍራት ያለፈ መሆን አለበት ፤ እንደ አማኝ የስልጣናት ሁሉ የበላይ የሆነዉን ራሱን እግዚአብሄርን እናገለግላለን …. እግዚአብሄር የከለከለዉን መንግስት እንድናደርግ ባዘዘን ጊዜ ብቻ አንታዘዝም “ ፤ ይህ ወደ ሮሜ 12 ይመልሰናል ፡፡ አንዳንዶቻችን ከዚህ አለም ጋር ተስማምተናል ምክንያቱም የእግዚአብሄር ቃል ትክክል እና ስህተት የሆነዉን እንድንለይ የሚለንን ስለማናውቅ ፤ የእግዚአብሄርን ቃል ካላወቅን ከአለም ጋር እንጣበቃለን ፡፡

ሮሜ (13፡ 6-7)፡ በዚህም ምክንያት ግብራችንን መክፈል አለብን ምክንያቱም የእግዚአብሄር ቃል እዉነት እንደሆነ ስለምናምን፣ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሄር ባለስልጣናት እንደሆኑ ስለምናምን እና የእግዚአብሄር ቃል ግብራችሁን ክፈሉ ስለሚለን ፡፡ ግብርን ከመክፈል በተጨማሪ ለሚገባቸዉ ቀረጥን እንከፍላለን፣ ክብር እና አክብሮት ለሚገባቸዉ ክብርና አክብሮት እንድናሳይ ታዝዘናል (ቁጥር 7) ፡፡

ሮሜ (13፡ 8-10)፡ እነዚህ ቁጥሮች መንግስትን ከመታዘዝ ወደ ሌሎችን ስለ መዉደድ መሸጋገሪያ ናቸው፡ “ መዉደድ የህግ ፍፃሜ ነዉና “ (ቁጥር 10) ፤ ስለዚህ ለመንግስት እና ለሀገር ግንኙነታችን ምንድን ነዉ መሆን ያለበት ? እነርሱን መዉደድ ፡፡

ሮሜ (13፡ 11-14)፡ ይህን ስለ ኢየሱስ እናደርጋለን ፡፡ ሰዎችን የመጥላት እና እነርሱን ያለመዉደድ እና ስርዓቱን ለማጭበርበር የመሞከር ጨዋታን መጫወት አንችልም ፡፡ ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል ! መጀመሪያ ካመነዉ ጊዜ ይበልጥ መዳናችን ቀርቧል (ቁጥር 11) ፤ ከአለም ጋር የተስማማ በመሆን ይህን ጨዋታ መጫወት አንችልም ፡፡ በመንቃት አይምሮአችንን ማደስ ይጠበቅብናል ፤ እንዴት ፍቅር ማሳየት እንደምንችል እግዚአብሄርን መጠየቅ አለብን ፡፡ በሌሎች ላይ ክፉ ለመሆን፣ በመንግስታችን ላይ ተቃራኒ ለመሆን እና ከእኛ በተለዬ መንገድ በመረጡት ወዳጆቻችን ላይ ተቃራኒ ለመሆን ጊዜ የለንም ፡፡ እንደ አማኝ ድርጊታችንን በአንድ ላይ ማድረግ አለብን ፤ “ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት “ (ቁጥር 14) ፡፡ ክርስቶስን ለዚህ አለም ለማንፀባረቅ ተጠርተናል ፤ የስጋን ፍላጎት ለመፈፀም ምንም እቅድ አታቅዱ - ከአለም ጋር የተመሳስል መሆን የለብንም ፡፡ ይልቁንም ክርስቶስን በመልበስ፣ እዉነትን በመልበስ፣ ፅድቅን በመልበስ፣ ሰላምን በመልበስክርስቶስን እንገልጣለን ፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ስንለብስ በተመሳሳይ በመንግስትም ይህንን እናደርጋለን ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር የመጨረሻዉ ባለስልጣን ነው ፡፡ እንደ ተከታይ እና እንደ መሪ በመጨረሻም ለእርሱ ተጠያቂነት አለብን ፤ እግዚአብሄር በምድር ላይ መልካሙን አላማ እንዲያደርጉለት መንግስታትን ይጠቀማል ፡፡ የነገሩ መጨረሻ በሰላም ነው ፤ የትም ስፍራ ላይ ብንሆን ለእግዚአብሄር ቃል ታዛዥ መሆን አለብን ፤ ያ ማለት ልክ እንደ ኢየሱስ እነርሱን (ባለስልጣናትን) መዉደድ ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 443.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1449.

  3. Nelson’s Commentary, p. 1449.

  4. Nelson’s Commentary, p. 1449.

  5. Nelson’s Commentary, p. 1449.

  6. Nelson’s Commentary, p. 1449.

  7. Nelson’s Commentary, p. 1449.

  8. Nelson’s Commentary, p. 1449.

  9. Nelson’s Commentary, p. 1449.

ጥያቄዎች

  1. በሮሜ 13 መሰረት የመንግስት ባለስልጣናትን ለምንድን ነዉ ማክበር ያለብን ? ለሚያስተዳድረዉ ባለስልጣን ከግል ስሜት ጋር በተያያዘ በሚሆን ጊዜ የክርስቲያን ተገቢዉ ተግባር እንዴት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? መታመናችሁን በፖለቲሺያን ወይስ በእግዚአብሄር ላይ ታስቀምጣላችሁ ? ስለዚህ አስቡ
  2. የሰዉን ህግ አለማክበር ልክ ሆኖ ያውቃል ? ለምን ወይስ ለምን አያውቅም ? (አስ 3፡ 2-4, ዳን 3፡ 9-18, 6፡ 11-13, ሐዋ 4፡ 18-20)
  3. አብዛኛዎቹን ትዕዛዛት ከመጣስ በመጠበቅ “ ወዳጆቻችንን “ እንዴት ልንወድ እንችላለን ?
  4. ፍቅር ምንድን ወይስ ማነዉ ? (ሮሜ 13፡ 10, 1ቆሮ 13፡ 4-8, 1ዮሐ 4፡ 8, 10, 18)
  5. በሮሜ (13፡ 12) መሰረት የምን ቀን ነዉ የቀረበው ? (2ጴጥ 3፡ 10-18)
  6. በሮሜ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Romans 13:1

“Everyone must submit to the governing authorities, for there is no authority except from God, and those that exist are instituted by God.”

እንደ አማኝ በሁሉም ነገር ላይ የመጨረሻ ስልጣን ያለውን እግዚአብሔርን ታገለግላለህ ፡፡ ደግሞም እንደ አማኝ ለመንግስት ባለስልጣናት መገዛት አለብህ ምክንያቱም ሹመትን የሰጣቸው እግዚአብሔር ሰለሆነ ፡፡ እግዚአብሔርን እንደ ገዥህ ካከበርክ ስለዚህም የሚመሩ ባለስልጣናትንም ማክበር አለብህ ፡፡ ጌታን ስትከተል ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበስ ፡፡ ልክ ልብስን እንደምትለብስ ሁሉ ይህን በማድረግ እውነትን ፣ ሰላምንና ጽድቅን ትለብሳለህ ፡፡ ሰዎች አንተን ሲያዩ ፣ የክርስቶስን ባህሪያት ማየት አለባቸው ፡፡ ለሰዎች ሁሉ ፍቅርን ታሳያለህ ፣ በመንግስት የስልጣን ቦታ ላይ ለተቀመጡትም ጭምር ፡፡

የሚመሩህን ባለስልጣናት ውደዳቸው ፡፡ ጸልይላቸው ፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም የእርሱን ፍቅር ያውቁ ዘንድ ይሻል ፡፡ የአንተ ድርሻ ልክ እንደ ኢየሱስ መውደድ እንድሁም በአንተ የወንጌሉን እውነት ያውቁ ዘንድ ከመንግስት ባላስልጣናት ጋር ስትገናኝ ኢየሱስን መምሰል ቢሆንስ ? ትዕቢትና የስጋ ምኞት ጣልቃ እንድገቡ አትፍቀድ ፡፡ እግዚአብሔርን እንደ መጨረሻ ገዥህ አድርገህ ታመን በትህትናም የክርስቶስን ፍቅር ፈጽም ፡፡ በመልክህ ክርስቶስን ምሰል ፡፡ ሌሎችን ውደድ ፣ ጎረቤቶችህን ውደድ ደግሞም የመንግስት አመራር በመሆን በስልጣን ላይ ያሉትንም ውደድ ፡፡ በአንተ ውስጥ ያለውን ኢየሱስን ለማወቅ ሲፈልጉ በዚህ መንገድ ነው አለም በትክክል የሚለወጠው ፡፡

“ ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው ። “ - ሮሜ 13፡1

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሮሜ 13:7— “ ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ። “
  • ሮሜ 13:14— “ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ ። “
  • 1ኛ ጢሞቴዎስ 2:1–2 — “ እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ ። “