Paul's Letters Romans

A Living Sacrifice, The Body Of Christ

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 498 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ጳዉሎስ በሮም ባይሆንም በዚያ ወዳሉት አማኞች ለማፍሰስ ይህን ደብዳቤ/መልዕክት ፃፈ ፤ በሮሜ (12-16) “ ጳዉሎስ ከሮሜ (1-11) የመጣዉን ስነ መለኮታዊ እዉነቶች አማኞች እንዴት መኖር እንዳለባቸዉ ተግባራዊ በታላቅ ጥልቀት ይገልፃል ፤ እግዚአብሄር ጳዉሎስ በታላቅ መታዘዝ ምላሽ እንዲሰጡ የሚመክራቸዉ ብዙ አማኞች በደግነት ተሰጥተዉታል “ ፡፡ እዉነት ይሆናል ብለን የምናዉቀዉን ነገር ልንታዘዘዉ እንችላለን ? በዚህ ክፍል ዉስጥ ጳዉሎስ በህይወት ዉስጥ እንዴት እንደሚያልፉ በሂደቱ ዉስጥ አስኬዳቸው ፤ በእነዚህ እዉነቶች ስትሄዱ በእያንዳንዷ የመንገድ እርምጃችሁ ክርስቶስ አብሯችሁ ይሆናል ፡፡

ትምህርት

ሮሜ (12፡ 1)፡ ዋይርስቤ በዚህ ምዕራፍ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቁጥሮች ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ግንኙነት ይዳስሳሉ ፡፡ ይህ ለሁሉም አማኞች ለሴትም ለወንድም ለሁለቱም ይሰራል ፡፡ “ አሳሰበ “ የሚለዉ ቃል “ ለመነ “ በማለት ሊተረጎም የሚችል ሲሆን ትርጉሙም “ ለመርዳት በአጠገብ ዝግ/ቀስ የሚል “ ማለት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ በአሮጌዉ ኪዳን እግዚአብሄር የሚሞቱ እንስሳቶችን መስዋዕት ተቀብሏል ፤ ነገር ግን በክርስቶስ የመጨረሻ መስዋዕትነት ምክንያት የብሉይ ኪዳን መስዋዕት ከዚህ በኋላ ተፅዕኖ የለዉም “ አለ ፡፡ አሁን ሰዉነታችንን እናቀርባለን - በቀጥታ ሰዉነታችንን ለሞት በመሰዊያዉ ላይ እናስቀምጣለን ማለት አይደለም ራሳችንን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሄር አሳልፈን እንሰጣለን ማለት ነዉ እንጂ ፤ ያን እንዴት እናደርጋለን ? ህያዉ መስዋዕት ማለት እየቀጠለ ያለ ማለት ነው - በምሄድበት ሁሉ፣ በምናገርበት ስፍራ ሁሉ፣ በምሰማዉ ወይም በምመለከተዉ ነገር ሁሉ ምንም ነገር መልሶ ባለመያዝ ለእርሱ ክብር ለማምጣት ሁሉንም ነገር እስጣለሁ ማለት ነው ፤ መፅኃፍም ያ ለእግዚአብሄር ቅዱስ እና የሚያስደስት መስዋዕት ነዉ ይላል ፡፡ ማክአርቱር “ በእግዚአብሄር ቁጥጥር ስር የአማኞች ያልተዋጀ ሰዉነታቸው ለፅድቅ መሳሪያነት ለእርሱ የተሰጡ መሆን አለባቸው “ በማለት ይቀጥላል ፡፡ ይህ መንፈሳዊ አምልኮአችን ነው (ቁጥር 1) ፡፡

ሮሜ (12፡ 2)፡ ለጌታ ህያዉ መስዋዕት ስንሆን የዚህ ጊዜ ከዘመኑ፣ ከባህሉ እና ከልማዱ ጋር የተስማማን ልንሆን አንችልም ፤ ይልቁንም በእግዚአብሄር ቃል የተለወጥን እንሆናለን ፡፡ ይህን በማድረግ ወደ አንድ አካባቢ በምንገባ ጊዜ ምን መልካም፣ የሚያስደስት እና ፍፁም የእግዚአብሄር ፍቃድ እንደ ሆነ እንለያለን ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል አይምሮአችሁን ስለሚያድስላችሁ ወደ አንድ አካባቢ በምንመጣ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የመለየት ስጦታን ስለሚሰጠን ለእግዚአብሄር ምን ማድረግ እንዳለብን መለየት እንድንችል ያደርገናል ፡፡ ማክአርቱር የጳዉሎስ መልዕክት እነዚህ አማኞች በአይምሮአቸዉ መታደስ ያልተለወጡ የነበሩ እና ከሮም አካባቢ ጋር የተመቻቹ ሆነዉ እንደ ነበር ያመለክታል አለ ፤ ጳዉሎስ ለምድራዊ ዘመናቸው ዋጋ መስጠትን እንዲያቆሙ ፈለገ ፡፡ ሰዉ ወደ ቤታችሁ ወይም ወደ መኪናችሁ ሲመጣ አለምን ወይስ ጌታን ስታንፀባርቁ ያዩአችኋል ? “ መለወጥ “ የሚለዉ ቃል “ ሙሉ የቅርፅ ለዉጥ “ ማለት ሲሆን “ በዉጪ መልክ መቀየርን ላይ መቀየርን አያሳስብም “ ፡፡

ሮሜ (12፡ 3-16)፡ እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት/ትስስር/ዝምድና ስላለን እነዚህ ቁጥሮች ከሌሎች ጋር ያለንን ግንኙነት ይዳስሳሉ ፡፡ ቁጥር 3 አማኞችን ራስን በሌሎች ላይ ከፍ ከፍ እንዳያደርጉ ያስጠነቅቃል ፤ ኢየሱስ በፍፁም ይህን ስላላደረገ እኛም ማድረግ የለብንም ፡፡ ይልቁንም እርስ በእርሳችን መቀባበልን ማሰብ አለብን ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰውበእግዚአብሄር መንግስት ዉስጥ ልዩነትን ስለሚያደርግ ፡፡ ይህ የእምነት መጠን የሚያድን እምነት አይደለም ነገር ግን እንደ ማክአርቱር ገለፃ “ ትክክለኛ ተመጣጣኝ የመንፈሳዊ ስጦታ - ወይም መለኮታዊ ስጦታ እና ችሎታ - መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱን አማኝ ስለሚሰጠው በክርስቶስ አካል ዉስጥ ድርሻዉን እንደሚፈፅም “ ነዉ የሚናገረው ፡፡ ለእያንዳንዱ አማኝ የተሰጠው የእምነት መጠን የተለዬ ይሆናል ነገር ግን ሚናችንን ለመፈፀም የሚያስፈልግ መጠን ነው ፡፡ ቁጥር 4-5 የእግዚአብሄርን አላማ ለመፈፀም እንደ ክርስቶስ አካል አማኞች እንደ አንድ ሆነዉ የሚሰሩበትን መንገድ ይገልፃል ፤ ቁጥር 6-8 እግዚአብሄር ለአማኞች የሰጣቸዉን የተለዩዩ ስጦታዎችን ስለሰጣቸው እያንዳንዳቸው ለእግዚአብሄር መንግስት አስተዋፅዖ እንደሚያደርጉ ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር ትንቢት “ የወደፊቱን መናገር “ ማለት ነዉ ይላል ፡፡

ሁሉም አማኞች የተለዬ ሚና አለው ፤ ማገልገል የሚችሉ፣ ማስተማር የሚችሉ እና ትንቢታዊ ቃል መስጠት የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጉናል ፤ 1ቆሮ (14፡ 3) “ ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትምለሰዉ ይናገራል “ ይላል ፤ እነዚህ ሰዎስት ነገሮች ትንቢት ለሚናገሩ ሰዎች መጠበቂያ ናቸው ፡፡ የመምከር ስጦታ ሌሎችን የእግዚአብሄርን እዉነት ወደ መታዘዝ እና መከተል ይጠራል ፤ ኃጢዓትንም በተመለከተ የሆነን ሰዉ ለማስተካከል ወይም ለማስጠንቀቅ ይጠቅማል ፡፡ የመስጠት ስጦታ ርካሽ/ቀላል አይደለም፣ ጠባብ አይደለም እንዲሁም በስምምነት ወይም በግዴታ የሚሰጥ አይደለም ፡፡ ስትሰጡ በለጋስነት በመስጠት እግዚአብሄርን አክብሩት ፡፡ የመምራት ስጦታ ማለት “ ከፊት መቆም “ ማለት ነው ፡፡ ጳዉሎስ ይህንን በጎቹን የሚመራ ወይም የሚነዳን ሰው ለመግለፅ የማስተዳደር ፀጋ በማለት ጠርቶታል ፤ ማክአርቱር እንዳለው “ በአዲስ ኪዳን ይህ ቃል በቤት እና በቤተ ክርስቲያን ላይ መሪነትን ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋለ ነው “ ፡፡ ምህረትን ማሳየት ማለት ለሰዎች ጥንቃቄ ማድረግ እና በደስተኝነት ነገሮችን ማድረግ ማለት ነው ፡፡ እነዚህ ሁሉ የክርስቶስ አካል አካሎች ያስፈልጉናል ፤ ከሌሎች የሚበልጥ አንድም የለም ፡፡

ቁጥር 9 ከዚህ ዉስጥ ማንኛዉንም መዋሸት/ማሳሳት እንደማንችል ያመለክታል ፤ ቁጥር 10 መዋደድ እና መከባበርን እርስ በእርስ እንድንደራረግ ይነግረናል ፡፡ ቁጥር 11 እግዚአብሄርን በትጋት እንድናገለግል እና በመንፈስ የምንቃጠል እንድንሆን ይነግረናል ወይም ደግሞ “ በመንፈስ የነደድን ፤ ይህ ዓረፍተ ነገር የሚበቃ ነገር ለማምረት ጉልበት ለማምረት የተትረፈረፈ ሙቀት መኖርን ይመክራል ነገር ግን ከቁጥጥር ዉጪ የሆነ የበዛ ሙቀት አይደለም“፡፡ ቁጥር 12-17 ስለ አንድነት ያወራል ፤ በአንድነት በምታስተዉሉ ጊዜ እርስ በእርሳችን እንደምናስፈልግ እና ከሌላዉ አካል በጣም የሚጠቅም አንድ አካል እንደሌለ እናስታዉላለን ፡፡ የክርስቶስ አካል እነዚህ ሁሉ አካላት ያስፈልጓታል ፡፡ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ስለ ራሱ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነዉን ሁሉ በትህትና ልትይዝ ያስፈልጋታል ፡፡

ሮሜ (12፡ 17-21)፡ ዋይርስቤ እነዚህ ቁጥሮች ከጠላቶቻችን ጋር ስለሚኖረዉ ግንኙነት ይገልፃሉ ፡፡

መደምደሚያ

የኔልሰን ማብራሪያ ራሳችንን ከሌሎች ለማወዳደር ያለንን ዝንባሌ ለመግለፅ “ የዉድድር አባዜ/አዙሪት “ የሚል የሚያስቅ ዓ.ነገርን ይጠቀማል ፡፡ ከእኛ የተሻለ ዋጋ እንዳላቸዉ ስናስብ፣ ከእያ የተሸሉ እንደሆኑ ስናስብ ወይም ደግሞ ከእነርሱ የተሸልን እንደሆንን ስናስብ ይህን እናደርጋለን ፡፡ በሌሎች ላይ ከማትኮር ይልቅ የተሻለዉ ጥያቄ እግዚአብሄር እኛን እንዴት ያየናል የሚለዉ ነው ፤ ይህን ስናደርግ ማንም አይገልፀንም/አይገምተንም - እግዚአብሄር ይገልፀናል እንጂ ፡፡ አይምሮአችንን በክርስቶስ በማደስ የተገለፅን እና በአብ ፈቃድ የምንጓዝ እንሆናለን ፡፡ ያን ስናደርግ ስጦታዉን መግለፅ እንችላለን ፡፡

  1. John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1544.

  2. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 441.

  3. MacArthur, p. 1544.

  4. MacArthur, p. 1545.

  5. MacArthur, p. 1545.

  6. MacArthur, p. 1545.

  7. MacArthur, p. 1545.

  8. Wiersbe, p. 442.

  9. MacArthur, p. 1545.

  10. MacArthur, p. 1546.

  11. MacArthur, p. 1546.

  12. MacArthur, p. 1546.

  13. MacArthur, p. 1546.

  14. Wiersbe, p. 443.

  15. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1448.

ጥያቄዎች

  1. በሮሜ (12፡ 1) ጳዉሎስ “ ሰዉነታችሁን ህያዉና ቅዱስ አድርጋችሁ አቅርቡ “ ሲል ምን ማለቱ ነው ? (1ሳሙ 15፡ 22, መዝ 40፡ 6-8, አሞ 5፡ 21-24)
  2. እንደ ክርስቲያን በአለም ዉስጥ ከአለም ጋር ሳንመሳሰል እንዴት እንኖራለን ? ክርስቶስን በድርጊታችን እንዴት እንወክለዋለን ? (ዮሐ 4፡ 7-9, 8፡ 3-11, ሉቃ 15፡ 1-7)
  3. በሮሜ 12 መሰረት እግዚአብሄር የሰጠን አንዳንድ ስጦታዎች ምንድን ናቸው ? እግዚአብሄር ምን ስጦታን ሰጣችሁ ? ቤተ ክርስቲያንን ለማነቃቃት/ለማጠናከር ስጦታችሁን እንዴት ትጠቀሙበታላችሁ ?
  4. ሮሜ 12 ስለ በቀል ምን ይላል በጠላቶቻችሁ ላይ አፀፋ የምትሰጡትስ እንዴት ነው ? በህይወታችሁ ይህን ለማድረግ ቀላል ነው ?
  5. ሮሜ (12፡ 18) “ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ “ ይላል ፤ እንደ አዳኛችን እና እንደ ጌታችንከኢየሱስ ጋር ምን አይነት ሰላም ሊኖረን ይችላል ? (ኢሳ 26፡ 2-3, ዮሐ 14፡ 26-27, 1ጴጥ 3፡ 9)
  6. በሮሜ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Romans 12:1–2

“Therefore, brothers, by the mercies of God, I urge you to present your bodies as a living sacrifice, holy and pleasing to God; this is your spiritual worship. Do not be conformed to this age, but be transformed by the renewing of your mind, so that you may discern what is the good, pleasing, and perfect will of God.”

እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳዔ አማካኝነት ለአንተ ምህረቱን አሳይቷል ፡፡ በኢየሱስ ምክንያት በእምነት ጸድቀሃል ፡፡ ልክ አንተ ከእግዚአብሔር ምህረት እንደተቀበልክ ሁሉ ፣ አሁን ደግሞ ለሌሎች ምህረትን ታደርግ ዘንድ የአንተ ተራ ነው ……… በራስህ ብርታት አይደለም ይልቁንም በየቀኑ እግዚአብሔርን በማምለክህና በአዕምሮህ መታደስ የተነሳ ከምታገኘው ብርታት እንጂ ፡፡ ይህ ማለት ቃሉን ማንበብ ፣ በጸሎት ጊዜን ማሳለፍ እናም እግዚአብሔርን ማመስገንና መክበር ማለት ነው ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ ሲሰራ ፣ ህይወትህ ይለወጣል ደግሞም የጌታን ምህረት ለሌሎች ተሳይ ዘንድ ብርታትን ይሰጥሃል ፡፡

ለራስህ ታማኝ ሆነህ እስኪ እራስህ ን ጠይቅ ፡- እግዚአብሔርን በማምለክ በየቀኑ አዕምሮህን ታድሳለህን ? ደክምህና ዝለህ ከሆነ ምናልባት ቆም ብለህ እግዚአብሔርን ለማምለክ ጊዜው ነው ፡፡ ባለህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ውደድ ፡፡ ይህ የየቀኑ ህያው መስዋዕት ነው ፡፡ ከዚያ የእግዚአብሔርን ፍቃድ መለየት ትችላለህ ፡፡ በዚህ መንገድ እርሱ በአንተ ወደ እራሱ ህዝብ ሊያፈስ የሚፈልገውን ምህረትና ፍቅር መሳየት ትችል ዘንድ በእርሱ ኃይል እና በእርሱ መንፈስ ትሞላለህ ፡፡ ከዚያም አለም የእርሱን ታላቅ ፍቅር ያውቃል ፡፡

“ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው ። እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው ። “

  • ሮሜ 12፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 12:9–12 — “ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ ፤ በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ ፤ ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ ፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ “

1ኛ ቆሮንቶስ 6:19–20 — “ ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ ። “

ዕብራውያን 13:15–16 — “ እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት ። ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና ። “