Paul's Letters Romans

Israel's Rejection Not Total

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 497 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለሮሜ 9, 10, እና 11 አጠቃላይ ጭብጡ/ፍሬ ሀሳቡ ስለ እስራኤል ነው ፡፡ ዛሬ እግዚአብሄር በመረጣቸዉ ህዝቦቹ በእስራኤል አለማድረጉን/ስራ አለመስራቱን የሚያሳየዉን ይህን ክፍል እናጠናቅቃለን ፡፡ ሮሜ 9 እንደ እግዚአብሄር ሕዝብ ስለ እስራኤል የቀደመ ምርጫን ያወራል ፤ ሮሜ 10 የእስራኤል የአሁኑን እግዚአብሄርን አልቀበልም ስለ ማለት ያወራል ፡፡ በዛሬዉ ትምህርታችን ሮሜ 11 ደግሞ ስለ እስራኤል የወደፊት መታደስ ያወራል ፡፡ ሁሉም ነገር እያለ እግዚአብሄር በእስራኤል አልሰራም ፤ ሮሜ 11 ስናነብ ዋረን ዋይርስቤ ሮሜ 11 “ በአሁኑ ጊዜ ለቤተ ክርስቲያን መጠቀም አንችልም ምክንያቱም ጳዉሎስ ለአንድ ሕዝብ አንድ በአንድ ወደፊት የሚሆንን እየገለፀ ስለሆነ “ ይላል ፡፡

ብዙ አመታትን ሰዎች በእስራኤል ሀገርነት ግራ ተጋብተዋል፣ ተወዛግበዉ እና እንቆቅልሽ ሆኖባቸዋል ፡፡ የሮማን መንግስት እስራኤልን “ ኃይማኖታዊ ህገወጥ “ በማለት ጠርቷታል ፤ ታሪክ አዋቂዉ አርኖልድ ቶይንቤ እስራኤላዊያንን “ የቀድሞ ስልጣኔዎች “ በማለት ጠርቷቸዋል ፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት የተባበሩት መንግስታት ምርጫን በማድረግ የቤተ መቅደሱ ተራራ በፍፁም የአይሁድ ህዝቦች እንዳይደለ ወስኗል ፤ በእኛም ዘመን እንኳን ሰዎች የእስራኤልን ሚና/ተግባር እያሳሳቱ/በትክክል እየተረዱት አይደለም ፤ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ያሉ ሰዎች ስራችን እና ታሪካችን ከአይሁድ ሰዎች እንደሆነ ማስተዋል ያስፈልገናል ፡፡ በሮሜ (15፡ 25-27) በኢየሩሳሌም ያሉትን ድሆች ለማገልገል በመፈለጋቸው የመሲሁን መንፈሳዊ ጥቅም ተቀብለዉ የነበሩትን የአሕዛቦች ስብስብ ጳዉሎስ ተመለከተ (ሮሜ 15፡ 25-27) ፡፡ ክርስቲያን ከማንቋሸሽ/ከመናቅ ይልቅ አይሁዶችን ሊያገለግል ኃላፊነት አለበት ፡፡

ትምህርት

ሮሜ (11፡ 1-4)፡ ጳዉሎስ ስለ እራሱ በማዉራት ጀመረ ፤ እግዚአብሄር እስራኤልን ትቶ ከነበረ ከቢንያም ወገን እስራኤላዊ በነበረዉ በጳዉሎስ ምን እናደርጋለን ? በመቀጠል በቁጥር 2-10 ጳዉሎስ በነቢዩ ኤልያስ መሰረት ክርክሩን ይቀጥላል ፤ ቁጥር 2 እግዚአብሄር ህዝቡን አልተዋቸዉም/አልጣላቸዉም ይላል ፡፡ ኤልያስ በእስራኤል ላይ እግዚአብሄርን በለመነዉ ጊዜ እግዚአብሄር ለበዖል ያልሰገዱ ለራሱ 7,000 ሰዎች አስቀርቻለሁ አለው ( ቁጥር 2-4) ፤ እነዚህ 7,000 ሰዎች የመለዉ ሀረጊቱ ባይሆኑም ለእግዚአብሄር የተለዩ ቅሬታዎች ነበሩ ፡፡ በሮሜ (9፡ 27) ጳዉሎስ የእስራኤል ቅሬታዉ ይድናል ያለዉን ኢሳያስን ይጠቅሳል ፡፡

ሮሜ (11፡ 5-8)፡ ቀጥሎም ጳዉሎስ በእርሱ ዘመን “ በጸጋ የተመረጡ ቅሬታዎች “ (ቁጥር 5) በእግዚአብሄር የተመረጡ እንደ ነበሩ ያሸጋግረዋል ፡፡ በእስራኤል ዉስጥ ያሉት ቅሬታዎች ድነትን ሲያገኙ (ቁጥር 7) የቀሩት የማያዩ እና የደነደኑ ነበሩ ፡፡ ጳዉሎስ “ ዓይኖቻቸዉ እንዳያዩ ጆሮቻቸዉም እንዳይሰሙ እግዚአብሄር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸዉ “ ብሎ ሲፅፍ ኢሳ (29፡ 10) ጠቀሰ ፡፡ በዘዳ (29፡ 4) ሙሴ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን እንዲያዩ አይንን እንዲሰሙ ደግሞ ጆሮን አልሰጣቸዉ ብሏል ፡፡

ሮሜ (11፡ 9-10)፡ ቀጥሎም ጳዉሎስ በመዝ (69፡ 22-23) ካለዉ ከዳዊት ቃል ይጠቅሳል ፡፡ እንደ ዋይርስቤ ንግግር መሰረት የእስራኤል በረከቶች ሸክም እና ፍርድ ሆኑ ፤ “ መንፈሳዊ በረከቶቻቸው ወደ ክርስቶስ ይመሯቸዋል ይሁን እንጂ ከዚያ ይልቅ ከክርስቶስ የሚያርቋቸው ወጥመድ ሆኑባቸው “ ፡፡

ሮሜ (11፡ 11-15)፡ የአይሁድ ሰዎች በመሰናከላቸዉ ምክንያት እስራኤልን ለማስቀናት ድነት ወደ አሕዛብ መጣ ( ቁጥር 11) ፡፡ ባለጠግነታቸዉ ወደ አሕዛብ ቢመጣ የአይሁድ ሙላት በተፈፀመ ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቡት (ቁጥር 12) ፤ ጳዉሎስ በፍቃደኝነት አገልግሎቱ ለአሕዛብ እንደ ነበር አጉልቶ እያሳዬ ስለ ነበር አይሁዶች ስለሚቀኑ ከእነርሱ ዉስጥ ጥቂቶቹ ሊድኑ ይችላሉ (ቁጥር 13-14) ፡፡ መቀበላቸው ከሙት ህይወትን ያመጣል (ቁጥር 15) ፤ በእዚህ በአሕዛብ ወቅት መሆናችን እግዚአብሄር በህዝቡ በእስራኤል ያደርጋል/ይፈፅማል ማለት አይደለም ፡፡

ሮሜ (11፡ 16-17)፡ ለእግዚአብሄር የሚቀርበዉ የሊጥ/የቡሆ የመጀመሪያዉ ክፍል ምልክት ስለሆነ ከአጠቃላዩ የቀረዉም ቅዱስ ሊሆን ይቻለዋል (ቁጥር 16) ፤ በበኩራት ፍሬ ድግስ/በዓል ላይ ካህኑ ሁሉም ምርት/እህል የእሩሱ እንደ ነበር ለመወከል አንድ ነዶን ያቀርባል ፤ “ ስሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ቅዱሳን ናቸው “ (ቁጥር 16) ከሚለዉ ጋር ተመሳሳይ አስተሳሰብ ነበር ፡፡ ስሮች ሌላዉን ሁሉንም ነገር ይወክላሉ ፤ ዋይርስቤ እንዳለው “ እግዚአብሄር ድርሱን ሲቀበል ሁሉንም ቀድሶታል “ ፡፡ እግዚአብሄር የህዝቡን መሰረት አብርሃምን ተቀብሎታል ፤ የይስሐቅ እና የያዕቆብ ኃጢዓት እያለ አሁንም እግዚአብሄር ቀሪዉን እስራኤልን ተቀብሏል ፡፡ ተቆርጠዉ የነበሩት ቅርንጫፎች ያላመኑት የአይሁድ ሰዎች ነበሩ (ቁጥር 17) ፤ አሕዛቦች “ የወይራ ዘይት ከሚወጣው ስር ዉስጥ “ (ቁጥር 17) ተካፋይ የሆነን የበርሃ ወይራ ዘይትን የተወከሉ ናቸው ፡፡ ተመልሰን ቁጥር 16 ላይ ስንመለከት ቅዱሱ ስር የፓትሪያሪኩ ጥሪ ስለ ነበር ሁሉም ቅርንጫፎች ቅዱስ ናቸው ፤ ችግሩ አንዳንድ ቅርንጫ ፎች መሰበራቸው ነው ፡፡ የዚህ መልኩ/ስዕሉ የተፈጥሮዉ ባልሆኑ ብዙ ቅርንጫፎች መተካት ምክንያት አብዛኛዎቹ የተፈጥሮ ቅርንጫፎች ተሰብረዋል ፡፡

ሮሜ (11፡ 25-27)፡ “ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው “ (ቁጥር 25) ፤ ቁጥሩ ስንት እንደሆነ አናዉቅም ፡፡ ወደ ሁሉም ሀገር፣ ሕዝብ፣ ጎሳ እና ነገድ በመሄድ እንደሚያስፈልገን እናዉቃለን ፡፡ በአንዳንድ በኩል ድንዛዜ ሆነባቸዉ ማለት እግዚአብሄር የመረጣቸዉ ሁሉም አሕዛቦች ጌታ እንደሆነ ወደ ማወቅ እስኪመጡ ድረስ ብዙ የተቆረጡ የተፈጥሮ ቅርንጫፎች ይኖራሉ ማለት ነው ፡፡ የእግዚአብሄር እቅድ ከአይሁዶች መካከል የደነዘዙትን ስለሚያካትት አሕዛቦች የመንግስቱ አካል ይሆናሉ ፤ “ እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል “ (ቁጥር 26) ፡፡ ይህን ሀሳብ ለመናገር ጳዉሎስ ኢሳ (59፡ 20-21) ይጠቅሳል ፡፡ ነፃ አዉጪዉ ኢየሱስ ከፂዎን ስለሚመጣ ኃጢዓታቸዉን ከእነርሱ ያስወግደዋል/ያርቀዋል (ቁጥር 26-27) ፤ እግዚአብሄር ተስፋዉን የሚጠብቅ ነው ፡፡ የአሕዛብ ሙላት በሚሆን ጊዜ እስራኤል ሁሉ ይድናል ፡፡

ሮሜ (11፡ 28-32)፡ “ እግዚአብሄር በጸጋዉ ስጦታና በመጥራቱ አይፀፀትማና “ (ቁጥር 29) ፤ በሚል (3፡ 6) እግዚአብሄር “ እኔ እግዚአብሄር አልለወጥም “ ይላል ፤ እግዚአብሄር አይለወጥም ! የአይሁዶች አለመታዘዝ በእግዚአብሄር ምህረት እንዲድኑ ፈቀደላቸው በምላሹም በኢየሱስ የሚያምኑ አይሁዶች እንዲድኑ ይፈቅድላቸዋል (ቁጥር 30-31) ፡፡

የአሕዛብ ሙላት እስኪሆን ድረስ በአይሁዶች ላይ በከፊል የሆነ ድንዛዜ አለ ፡፡ በዚህ ሂደት ላይ የሆነ ስፍራ ላይ መሲሁን ኢየሱስን በኑሮአችን ላይ በሚያዩት ጊዜ ምን እንዳደረጉ ማስተዋል ይጀምራሉ ፡፡ ዘካ (12፡ 10) አይሁዶች ለወጉት በምሬት /በኃይል በማዘን መሲሁ ላይ ይመለከታሉ ይላል ፤ በዚያ ክስተት ላይ በማቴ (23፡ 39) መሰረት “ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው “ ይላሉ ፡፡ ያ በሚሆን ጊዜ የመሲሁ የኢየሱስን ተመልሶ መምጣት እናያለን ፤ ዘካሪያስ 14 ስለ ህዝቦቹ ተመልሶ ሲመጣ ኢየሱስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ እግሮቹን እንደሚያሳርፍ እና ወደ ሁለት እንደሚከፈል ይነግረናል ፡፡

መደምደሚያ

ሮሜ 9-11 እግዚአብሄር በህዝቦች በእስራኤላዊያ እንዳልሰራ ያሳየናል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 438.

  2. Wiersbe, p. 438.

  3. Wiersbe, p. 439.

  4. Wiersbe, p. 439.

  5. Wiersbe, p. 439.

  6. Wiersbe, pp. 439-440.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር ህዝቦቹን እስራኤላዊያንን ጥሏቸዋል (ሮሜ 11፡ 1, 15, 26-29) ? አሁን በእግዚአብሄር የተመረጥን ህዝቦች ነን ? (ሮሜ 2፡ 29, 11፡ 24-26)
  2. ሮሜ (11፡ 11) “ ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ “ ስል ምን ማለቱ ነው ? (ሮሜ 11፡ 14-15)
  3. አሕዛቦች እንደ በርሃ የወይራ ዛፍ ሲጠቀሱ አይሁዶች ደግሞ አብሮ እንደ በቀለ የዘይት ቅርንጫ ተጠቅሰዋል የወይራ ዛፉ ስር ማን ነው ? (ኤር 11፡ 16-17, ሆሴ 14፡ 4-6, ሮሜ 11፡ 16-18)
  4. በሮሜ (11፡ 21) የተጠቀሱት የተፈጥሮ ቅርንጫፎች የተቆረጡ እንዲሆን ምክንያቱ ምንድን ነው (ሮሜ 11፡ 17, 20, 23) ? እንዳያምኑ ምን አደረጋቸው ? (ዮሐ 3፡ 16-18, ሮሜ 10፡ 9-10)
  5. እግዚአብሄር ለሆነ ነገር ባለቤት እንዳደረጋችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል (ኢዮ 41፡ 11, ሮሜ 11፡ 35) ? ሮሜ (11፡ 36) ስታነቡ ከእርሱ የሆነዉን፣ በእርሱ የሆነዉን እና ለእርሱ በሆነዉ ሁሉም ነገር ላይ ትታገላላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አትታገሉም ?
  6. በሮሜ 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Romans 11:11–12

“I ask, then, have they stumbled in order to fall? Absolutely not! On the contrary, by their stumbling, salvation has come to the Gentiles to make Israel jealous. Now if their stumbling brings riches for the world, and their failure riches for the Gentiles, how much more will their full number bring!”

እግዚአብሔር ከተመረጡ ህዝቦቹ ከአይሁዶች ጋር አልጨረሰም ፡፡ እግዚአብሔር በሁለቱም ላይ ማለትም በአህዛብም በአይሁድም ላይ ምህረቱ አላበቃም ፡፡ አህዛብ የክርስቶስን ፍቅር በማሳየት ሲያስቀኑዋቸው ፣ አይሁድ ወደ ማዕዘን ድንጋዩ ወደ ኢየሱስ ይመጣሉ ፡፡ ስለዚህ አህዛብ ለሆኑት ማለትም አይሁድ ላልሆኑት ሁሉ ጥሪ አለ እርሱም ፡- እምነታቸውን አይሁድን ለቅናት በሚያነሳሳ መንገድ እንድያራመዱ ነው ፡፡ የኢየሱስ ጸጋና ፍቅር ምንኛ አስደናቂ እንደሆነ ፤ መንገዱም እንዴት እንደሚያስፈራ ደግሞም ባለጠግነቱን ፤ ጥበብ እውቀቱንም ያዩ ዘንድ አስችሏቸው ፡፡ ዛሬ አይሁድ መሲሃቸውን እንደ መሲህ መቀበል እንድፈልጉ በሚያደርግ መንገድ ኑሮችሁን ለኢየሱስ ኑሩ ፡፡

ስለ እግዚአብሔር ደግነት ሊባል የሚችል ብዙ ነገር አለ ፡፡ እርሱ የራሱን ህዝብ ወደ ራሱ ተጣርቷል ፤ ስለዚህም እርሱ አልጨረሰም ፡፡ ምናልባትም እነርሱ በህይወታቸው አንዱን ፣ እውነት በቻ የሆነውን የማዕዘን ራስ የሆነውን ፣ ህያውን ድንጋይ ኢየሱስን ያዩት ይሆናል ፡፡ ነገር ሁሉ ከእርሱ ፣ በእርሱ ደግሞም ለእርሱ ነውና ፡፡ እርሱን በሚያከብር መልኩ ህይወታችሁን በክርስቶስ ኑሩ ፡፡ ምናልባት እርሱ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ ፣ ክርስቶስ ይፈጸም ይሆናል ፡፡

“ እንግዲህ፦ የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነውን? እላለሁ። አይደለም፤ ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ ። ዳሩ ግን በደላቸው ለዓለም ባለ ጠግነት መሸነፋቸውም ለአሕዛብ ባለ ጠግነት ከሆነ፥ ይልቁንስ መሙላታቸው እንዴት ይሆን ? “

  • ሮሜ 11፡11-12

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘካርያስ 12:10— “ በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል ። “

ማቴዎስ 23:37, 39 — “ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም ……….. እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም ። “

ሮሜ 11:33, 36— “ የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም ፡፡ ……… ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን ። “