Paul's Letters Romans

Why The Jews Rejected Jesus

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 496 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለአማኞች በፃፈዉ የጳዉሎስ መልዕክቶች ጥናት ላይ ነን ፤ ዛሬ ሮሜ 10 ላይ ነን ፡፡ ጳዉሎስ በሮም ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ላሉት አማኞች ከግሪክ ቆሮንቶስ ሆኖ ፃፈላቸው ፤ ጳዉሎስ ወደ ሮም ጉዞ አድርጎ ነበር ነገር ግን እንደ መንግስት እስረኛ ሆኖ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በዚህ ምዕራፍ በተለየየ መልኩ ስለ እስራኤላዊያን ፅፏል ፡፡ ጳዉሎስ ሮማዊ ዜጋ እና አይሁዳዊ ነበር ፤ በምዕራፍ 9 እስራኤላዊያን እነርሱ አድርገዉት በነበረዉ ነገር ሳይሆን በራሱ በእግዚአብሄር ምክንያት እንዴት የእግዚአብሄር ምርጥ ሕዝቦች እንደ ነበሩ ተመልክተናል ፤ በምዕራፍ 10 በአሁኑ ጊዜ የእስራኤል አለመቀበልን እንመለከታለን - ኢየሱስን እንደ እግዚአብሄር ልጅ እና እንደ መሲህ አለመቀበላቸዉን እንመለከታለን፡፡ በምዕራፍ 11 በእስራኤል የወደፊት መታደስ/መመለስ ላይ እንመለከታለን ፤ ለሮሜ ቃላችን የሚያፀድቅ/አፅዳቂ ነው ፡፡ አይሁዶች የመሲሁን መምጣት እየተጠባበቁ ነበር (ገላ 3፡ 24) ፤ ለዚያ ክስተት እግዚአብሄር መረጣቸዉ ነገር ግን ለእርሱ አይሆንም አሉት ፡፡

ዋረን ዋይርስቤ ምዕራፍ 10 ወደ ሰዎስት ዋና ዋና ክፍል በመክፈል አስቀምጧቸዋል፡ “ ያለመቀበላቸዉ ምክንያቶች (ቁጥር 10፡ 1-13)፣ ያለመቀበላቸዉ ማስተካከያ (10፡ 14-17)፣ ያለመቀበላቸዉ ዉጤት (10፡ 18-21) “ ፡፡

ትምህርት

ሮሜ (10፡ 1-13)፡ አይሁዶች ኢየሱስን ላለመቀበላቸዉ ምክንያቶቹ ምን ነበሩ ? መጀመሪያው አይሁዶች ድነት እንደማያስፈልጋቸዉ እንደሚሰማቸዉ ዋይርስቤ አጥብቆ ይናገራል (ቁጥር 1) ፡፡ ጌታን ስለማያዉቁ ሰዎች መፀለያችሁን እንዳታቆሙ ፡፡ ሁለተኛው አይሁዶች ለእግዚአብሄር የተነሳሱ/የቀኑ ነበሩ ነገር ግን በእዉቀት ዉስጥ በብዙ ስለ እግዚአብሄር ለማወቅ ለመማር መነሳሳቱ አልነበራቸዉም (ቁጥር 2) (ገላ 3፡ 24) ፡፡ ሰዎስተኛ ትዕቢት የተሞሉ እና በራሳቸዉ የፀደቁ ነበሩ (ቁጥር 3) ፡፡ አራተኛ የራሳቸዉን ህግ በሚገባ/በስትክክል አልተረዱትም (ቁጥር 4-13) ፡፡ በቁጥር 4 “ ፍፃሜ “ የሚለዉ ቃል “ መፈፀም “ ማለት ነው (ማቴ 5፡ 17, ሮሜ 8፡ 4) ፡፡

ሙሴ በህጉ የሚኖር በራሱ በህጉ የፀደቀ እንደሚሆን ፅፏል - የህጉ ስራ ያ ነው (ቁጥር 5) ፤ ይሁን እንጂ ፅድቅ በኢየሱስ እንደ አዳኝ እና እንደ ጌታ በማመን (ቁጥር 6-7) እና ኢየሱስ ከሞት የተነሳ እንደ ሆነ በማመን እና በመናገር ይመጣል (ቁጥር 8-9) ፡፡ ይህ እወጃ ከዉድቀት ስለሚያድነን ይህ እንዲሆን እንሰራለን፣ እርምጃ እንወስዳለን እንዲሁም እናደርጋለን ፡፡ በክርስቶስ የሚያምን ሁሉ ተቀባይነት ያለዉ ይሆናል (ቁጥር 10) ምክንያቱም በአይሁዶች እና በአሕዛብ መካከል ልዩነት ስሌለለ ድነታችን ባደረገዉ ነገር ላይ የተመሰረተ ነው (ቁጥር 11-12) ፡፡ ስሙን መጥራት አለብን (ቁጥር 13) ፤ በአሁኑም ጊዜ በእስራኤል ጥቂት ፐርሰንት የሚሆኑ አይሁዶች ብቻ ለኢየሱስ አዎ የሚሉ አሉ ፡፡

ሮሜ (10፡ 14-17)፡ ለአይሁዶች አለመቀበል ማስተካከያዉ ምንድን ነው ? ቁጥር 14 ላይ አይሁዶች ስለ እርሱ ሳይሰሙ እና በእርሱ ካላመኑ እንዴት ክርስቶስን ሊጠሩት ይችላሉ በማለት ይጠይቃል ፤ ቀጥሎም ጳዉሎስ “ ያለ ሰባኪስ እንዴት አድርገዉ ሊሰሙ ይችላሉ ? “ ብሎ ጠየቀ ፤ ጳዉሎስ በመቀጠል በቁጥር 15 በእግዚአብሄር ተለኮ ካልነበር በስተቀር እንዴት ለአይሁድ ሊሰብክ ይችላል በማለት ጠየቀ (ቁጥር 15) ፡፡ “ መልካሙን የምስራች የሚያወሩ እግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው “ (ኢሳ 52፡ 7-10, ናሆ 1፡ 15) ፡፡ እግዚአብሄር ዮናስን እንደ መልዕክተኛ ለነነዌ ድነትን እና ሰላምን እንዲሰብክ ላከው ፡፡ “ ነገር ግን ሁሉ ለምስራቹ ቃል አልታዘዙም ……ምስክርነታችንን ማን አመነ ? “ (ቁጥር 16) ፡፡ እምነት ከመስማት ይመጣል መስማት ደግሞ ስለ ክርስቶስ ከሚሰበከው (ቁጥር 17) ፡፡ ምናልባት ስለ ክርስቶስ ዜና በፍፁም ሰምተዉ አልነበር ይሆናል ፡፡

ሮሜ (10፡ 18-21)፡ ያለመቀበላቸዉ ዉጤት ምንድን ነው ? አይሁዶች ስለ ኢየሱስ መልካሙን ዜና ሰምተዋል ምክንያቱም ዜናዉ በአለም ዙሪያ ሁሉ ስለሄደ/ስለተሰማ (ቁጥር 18) ፡፡ እስራኤል ኢየሱስን ባለመቀበል ጥፋተኛ ስለ ነበረች መልዕክቱ ወደ አሕዛብ ሄደ (ቁጥር 19) ፤ አንድ ቀን አይሁዶች በአሕዛቦች ኢየሱስን መቀበል በመበሳጨት ይቀናሉ ፡፡ ኢሳያስ ፈልገዉት እና ጠይቀዉት ላልነበሩት ተገኝቶ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 20) ፤ የሆነ ነገር እንደ ነበር ለመመልከት እንኳን አላወቁም ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ቀኑን ሁሉ ስለ አይሁዶች እጆቹን ወደ ማይታዘዙት እና ወደ ሚቃወሙት ዘረጋ (ቁጥር 21) ፤ አሁንም ስለ ህዝቦቹ ይናፍቃል ፤ ስለሆነም የክርስቶስን ዜና ማድረሳችንን መቀጠል ኃላፊነታችን ነው ፡፡

መደምደሚያ

ዋይርስቤ ከዶር. ኢ. ሜይርስ ሀምሰን እንደተቀበለው ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን መላክ ያለባት አራት ምክንያቶችን ያጋራል፡ “ 1) ከላይ የመጣ ትዕዛዝ ስለሆነ - ወደ አለም ሁሉ ሂዱ (ማር 16፡ 15)፣ 2) ከልብ የሆነ ጥሪ/ጩኸት - ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሀለሁ (ሉቃ 16፡ 27)፣ 3) ያለምንም ጥሪ - ተሻገርና እርዳን (ሐዋ 16፡ 9) እና 4) በዉስጥ ያለዉ የሚያስገድደዉ ነገር - የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል (2ቆሮ 5፡ 14) “ ፡፡

የክርስቶስ ፍቅር በልባችሁ እንዳለ የምታምኑ ከሆነ መልካሙን ዜና እንድታደርሱ ያስገድዳችኋል ፡፡ ከላይ የሆነ ቃል ታገኛላችሁ፣ ከቃሉ፣ ከእናንተ አለም ዉጪ ከሆነዉ ከህልም እና ከራዕይ ታገኛላችሁ ነገር ግን ይህ በሚገባ/በእዉነት ከዉስጥ መዉጣት ያስፈልገዋል ፡፡ መሲሀችሁ የሚያፀድቀዉ እንደሆነ ካወቃችሁ/ካስተዋላችሁ ስለ ኢየሱስ ለሌሎች መናገርን ማቆም አትችሉም ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, Wiersbe’s Exposition Outlines on the New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), pp. 546-548.

  2. Wiersbe, p. 546.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1539.

  4. E. Meyers Hamson, quoted in Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 548.

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ እስራኤላዊያን ለእግዚአብሄር ቅናት እንደ ነበራቸዉ ገልፆአል ፤ ስተዉ የነበረዉ ምን ነበር ? (ሮሜ 10፡ 2)
  2. በአዲሱ ህያዉ ትርጓሜ ሮሜ (10፡ 4) “ የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የህግ ፍፃሜ ነው “ ይላል ፤ በእናንተ አገላለፅ ለመፅሀፍ ቅዱስ አዲስ የሆነ ሰዉ ሊረዳበት የሚችልበትን መንገድ ከዚህ ጥቅስ እዉነታዎችን ፃፉ ፤ ገላ (3፡ 24-25)
  3. በሮሜ (10፡ 8) ጳዉሎስ ከዘዳ (30፡ 14) ይጠቅሳል፡ “ ይህም የምንሰብከዉ የእምነት ቃል ነው “ ፤ “ ለዚህ የእምነት ቃል “ ሮሜ (10፡ 9-10) መግለጫ የሚሆነዉ እንዴት ነው ?
  4. “ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፋችሁ የምታዉጁት “ እንዴት እንደሆነ ግለፁለልጆቻችሁስ እየገለፃችኁላቸዉ ነበር ፡፡
  5. በሮሜ (10፡ 9-10) እና በመዝ (19፡ 14) መካከል ትስስር ታያላችሁ ? አዎ ከሆነ ግለፁት
  6. በሮሜ (10፡ 18) ከመዝ (19፡ 4) በመጥቀስ ጳዉሎስ ሁሉም መልካሙን ዜና እንደ ሰሙ ተናገረ ፤ መዝሙር 19 እና ሮሜ (1፡ 18-20) አንብቡ (ኢሳ 52፡ 10) ፡፡ ቀድሞ የታወጀ/የተነገረ ከሆነ መልካሙን ዜና ለማጋራት መሄድ ለምን አስፈለገን ? (ኢሳ 53፡ 1, ማር 16፡ 15, ሮሜ 10፡ 16, 2ጴጥ 3፡ 9)
  7. በሮሜ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Romans 10:12–13

“For there is no distinction between Jew and Greek, since the same Lord of all is rich to all who call on Him. For everyone who calls on the name of the Lord will be saved.”

የወንጌሉ መልዕክት ለሰዎች ሁሉ ነው ፡፡ የጌታ ኢየሱስን ስም ከጠራህ ትድናለህ ፡፡ ሆኖም ግን የእስራዔል ሰዎች ይህን መልዕክት አልተቀበሉትም ፡፡ ስለዚህ አሁን ምን ይሁን ? እነርሱ አሁንም እውነቱን በሚያስቀና መንገድ ምናልባትም ደግሞ መረዳት ስለጎደላቸው እንድቆጡ በሚያደርግ መንገድ ጭምር መስማት ያስፈልጋቸዋል ፡፡

ሰዎች የወንጌሉን መልዕክት ከልብህ መስማት ይፈልጋሉ ፡፡ ዛሬ ያን ማድረግ የአንተ ስራ ነው ፡፡ በአፍህ “ ኢየሱስ ጌታ “ እንደሆነ መመስከር ፤ በልብህ ደግሞ እግዚአብሔር ከሞት እንዳስነሳው ማመን አለብህ ፡፡ የአንተ ያማሩ እግሮች ካላደረሱት በቀር ፣ ሰዎች ይህን እውነት እንዴት ይሰማሉ ? ያአንተ ህይወት የእርሱን አስደናቂና ፣ ደስ የሚል ፍቅር ካላንጻባረቀው በቀር እንዴት የአዳኝን ፍቅር ሊያውቁ ይችላሉ ? አፍህን ክፈትና ይህን መልዕክት አካፍል ፡፡ በክርስቶስ ስላገኘኸው ሰላምና ነጻነት ተናገር ፡፡ ክርስቶስ ለሁሉም ነው የመጣው ፡፡ ለሁሉም ከዚህ በኋላ እውነቱን አንቀበልም እንዳይሉ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፍቅር እንድቀበሉ ጸልይ ፡፡ ዛሬ ከሆነ ሰው ጋር እንድትካፈል የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይበልህ ፡፡

“ በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው ፤ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና ። “

  • ሮሜ 10፡12-13

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 10:8–10— “ በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው ። ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና ፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና ። “

ሮሜ10:14–15— “ እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ ? መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? “

2ኛ ቆሮንቶስ 5:14— “ ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ “