Paul's Letters Romans

God Fulfills His Promise

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 495 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ታላቅ ስማንንት ስለሆነ በእነዚህ በቀጣዮቹ በሮሜ ምዕራፎች ዉስጥ ለማስተማር ጓጉቻለሁ/ስሜቴ ተነሳስቷል ፡፡ በሮሜ (9-11) ጳዉሎስ ስለ እስራኤል የወደፊት ሁኔታ ያወራል ፡፡ እነዚህ ምዕራፎች አሁንም እግዚአብሄር ለእስራኤል ስላለዉ እቅዶች ናቸው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች አሁንም እግዚአብሄር ለእስራኤል እቅድ መኖሩን ዋጋ አይሰጡትም ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እስራኤልን አልተካችም ፤ እግዚአብሄር አሁንም ለእስራኤል እና ለአይሁድ ሰዎች እቅድ አለው ፡፡

ሰዎስቱንም ምዕራፎች ሁሉንም አወያያለሁ ነገር ግን ምዕራፍ 9 እከፋፍለዋለሁ ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ የሮሜ (9-11) መልክ የሚስሉ ሰዎስት ነገሮችን ይለያል፡ “ በሮሜ 9 ላይ ያለዉ ማብራሪያ በእስራኤል የቀደመ ምርጫ ላይ ነው፣ በሮሜ 10 በአሁኑ የእስራኤል መገፋት ላይ ሲሆን ሮሜ 11 በእስራኤል የወደፊት መልሶ መታደስ ላይ ነው “ ፡፡ ከእነዚህ ምዕራፎች በአንዱ ላይ ብቻ የምታተኩሩ ከሆነ ትልቁን ስዕል ትስቱታላችሁ ፡፡

በሮሜ 8 መጨረሻዉ ላይ እግዚአብሄር ለአማኞች እቅድ አለዉ ይላል ፡፡ የእግዚአብሄርን ሰዎች ከእርሱ ፍቅር ምንም ነገር ሊለያቸዉ አይችልም ፤ ያ እዉነት ከሆነ ልጁን ስላልተቀበሉት ስለ አይሁድ ሰዎች ልትደነቁ ይገባችኋል ፡፡ እግዚአብሄር ስላለዉ አንድ ነገር ያን ማለት እንደሆነ እንዲታያችሁ በእግዚአብሄር ጥቂት ባህሪያት ዉስጥ ማለፍን/መሄድ እፈልጋለሁ ፡፡

ትምህርት

ሮሜ (9፡ 1-3)፡ መጀመሪያ “ ስለ እግዚአብሄር ታማኝነት “ እናወራለን ፤ እግዚአብሄር ተስፋዉን ይጠብቃል ፡፡ ምን እያለ እንደሆነ ማለት ነው ፤ መንፈስ ቅዱስ በተቆጣጠረ ጊዜ ሀሳብ/አይምሮ የታመነ ሊሆን ይችላል ፡፡ ጳዉሎስ የጭንቀት እና የኃዘን ስሜቱን ከጥልቅ ስሜቱ ተናገረ ፤ ጳዉሎስ ወንድሞቹን ያድን ወይም ደግሞ ይጠቅም ከሆነ ሲዖል ድረስ ለመዉረድ ፍቃደኛ ነበር ፡፡ ቀላል እንዳልሆነ እናዉቃለን ነገር ግን የጳዉሎስ ልብ ሁሉንም ነገር ለመስጠት ሙሉ ለሙሉ ስለ እግዚአብሄር እና ስለ ህዝቡ ነው ፡፡

ሮሜ (9፡ 4-5)፡ ጳዉሎስ ለእስራኤል የሆኑትን ተስፋዎች ሁሉ መግለፅ ጀመረ ፤ ማክአርቱር የእስራኤላዊያንን እዉነታዎች ይከፋፍላቸዋል፡

  • እስራኤላዊያን፡ “ ስሙን እግዚአብሄር ወደ እስራኤል በቀየረው በያዕቆብ ዉስጥ የአብርሃም ዘር (ዘፍ 32፡ 28) “ ፡፡

እንደ ልጅ መሆን/ጉድፈቻ፡ “ ለሁሉም ሰዉ አንድ አይሁዳዊ ሆኖ በመወለድ የሚሰጥ የድነት ሁኔታ ሳይሆን ነገር ግንእንደ ምስክሮች ህዝብ እንዲያገለግሉ በሉዓላዊነቱ ሙሉዉን ህዝብ የተለየ ጥሪዉን፣ ኪዳኑን እና በረከቱን እንዲቀበሉ መረጣቸው /ለያቸው (ዘጸ 4፡ 22, 19፡ 6, ኢሳ 46፡ 3-5, ሆሴ 11፡ 1) “ ፡፡

ክብር፡ “ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሄርን መገኘት የሳለዉ ክብር በእስራኤላዊያን ነበር ፤ ክብሩ ለአምላክ/ለያህዌ ዙፋን ክፍል በሚያገለግለዉ በድንኳኑ ማደርያ እና በቤተ መቅደሱ በሁለቱም ዉስጥ ነኃይል በቅድስተ ቅዱሳኑ ዉስጥ ነበር (ዘጸ 16፡ 10, 24፡ 16-17, 29፡ 42-43, ዘሌ 9፡ 23-24) “ ፡፡

ኪዳን፡ “ ኪዳን ህጋዊ የሆነ ፅኑ ቃል ኪዳን፣ ስምምነት ወይም ዉል ነው ፡፡ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ ኪዳን የሚለዉ ቃል በብዙ ቅርፅ ሰዎስት ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ ነው ፡፡ ሁሉም ነገር ግን አንዱ የእግዚአብሄር ኪዳን ከሰዉ ጋር ዘላለማዊ እና ከአንድ ወገን ብቻ የሆነ ነው - ያም የተስፋዉ ተጠቃሚ ከሆነዉ ምላሽ ወይም ድርጊት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን እግዚአብሄር በራሱ ባህሪይ መሰረት ሊያሳካዉ ቃል የገባዉ ነገር ነው “ ፡፡ ከሰዉ ጋር ስድስት ኪዳኖች ነበሩ፡

ከኖህ ጋር የተደረገዉ ኪዳን (ዘፍ 9፡ 8-17) ፡፡

ከአብርሃም ጋር የተደረገዉ ኪዳን (ዘፍ 12፡ 1-3) ፡፡

በሲና ተራራ ላይ በሙሴ በኩል የተሰጠዉ የህግ ኪዳን (ዘጸ 19-31, ዘዳ 29-30) ፡፡

የክህነት ኪዳን (ዘኁ 25፡ 10-13) ፡፡

በዳዊት ታላቅ ልጅ የተደረገዉ የዘላለም መንግስት ኪዳን ( 2ሳሙ 7፡ 8-16) ፡፡

አዲሱ ኪዳን (ኤር 31፡ 31-34, ሕዝ 37፡ 26, ዕብ 8፡ 6-13)

ሁሉም የሙሴ ኪዳኖች ዘላለማዊ እና በአንድ ወገን ብቻ የተደረጉ ናቸው ፤ በእስራኤል ኃጢዓት ምክንያት የሙሴ ኪዳን ቆሸሸ /ተበላሸ ነገር ግን በአዲስ ኪዳን ተተካ (ዕብ 8፡ 7-13) ፡፡

አገልግሎት፡ የቤተ መቅደስ አገልግሎት “ እግዚአብሄር ለሙሴ የተገለጠበትን ሁሉንም የመስዋዕትነትን አከባበር ያመለክታል (ዘጸ 29፡ 43-46) “ ፡፡

ተስፋዉ/ቃል ኪዳኑ፡ “ ምናልባትም ይህ ከእስራኤል በመዉጣት የዘላለም ህይወትን እና የዘላለም መንግስትን ስለሚያመጣዉ ተስፋ የተገባዉን መሲህ ያመለክታል (ሐዋ 2፡ 39, 13፡ 32-34, 26፡ 6) ፡፡

ሮሜ (9፡ 5)፡ መሲሁ ከአይሁድ በስጋ የአይሁድ አባቶች ልጅ/ትዉልድ ነበር ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንጂ እግዚአብሄር እንዳልሆነ የሚናገሩ ብዙ ኃይማኖቶች አሉ ፤ ቁጥር 5 በግልፅ በሁሉም ላይ አምላክ እንደ ሆነ ይገልፃል ፤ ከዚያ የበለጠ ግልፅ የሆነ አይገኝም ፡፡ ኢየሱስ በሰዉ ስጋ የተገለጠ አምላክ ነው ፡፡ አይሁዶችን የምናከብራቸዉ እና የምናበረታታቸዉ ለምንድን ነው ? ምክንያቱም መሲሁ ከእነርሱ ዉስጥ ስለመጣ ፡፡

ሮሜ (9፡ 6-8)፡ የእግዚአብሄር ቃል የተሸረ አልነበረም ፤ ጳዉሎስ “ እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና “ በማለት ፅፏል ፡፡ ይህ አብርሃም ሚስቱ አገልጋይ ልጁን እስማኤልን ከወለደችለት ከአጋር ልጅ ስለነበረዉ ነው ፤ ነግር ግን ያ የእግዚአብሄር እቅድ አልነበረም ፡፡ ስለሆነም ሁሉም የአብርሃም ልጆች የእግዚአብሄር እቅድ አካል አያደሉም ፡፡ ማክአርቱር “ የአብርሃም ልጆች ሁሉም በስጋ የእግዚአብሄር ህዝቦች - የእስራኤል ህዝብ/ብሄራዊ ካልተባሉ በይስሀቅ በኩል የሆኑት ሁሉም እዉነተኛ የአብርሃም ልጆች እዉነተኛ የእግዚአብሄር መንፈሳዊ ልጆች በመሆን ለአብርሃም መንፈሳዊ ልጆች ተስፋ የተገባዉን የሚቀበሉም አይደሉም “ በማለት ፅፏል ፡፡

ሮሜ (9፡ 9-13)፡ የእግዚአብሄር ተስፋ ወደ አብርሃም መጣ ከዚያም ወደ ይስሐቅ ሄደ ቀጥሎም ወደ ያዕቆብ ሄደ ፡፡ ማክአርቱር “ የእግዚአብሄር ያዕቆብን ምርጫ ብቻዉን በሉዓላዊ እቅዱ ዉስጥ አኖረው፣ ለድነት ፍፁም የሆነ ምሳሌ ነው “ በማለት ፅፏል ፡፡

ሮሜ (9፡ 14-18)፡ እነዚህ ጥቅሶች “ በእግዚአብሄር ፅድቅ ላይ “ ይመለከታሉ ፤ እግዚአብሄር ምህረትን እና ርህራሄን የሚያሳያቸዉን/የሚያደርግላቸዉን ይወስናል ፡፡

ሮሜ (9፡ 19-29)፡ እነዚህ ቁጥሮች “ የእግዚአብሄርን ፍትህ/እዉነተኝነት “ ላይ ያተኩራሉ ፤ እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሄር ምርጫ ላይ የተመሰረቱ ናቸው ፡፡ ፅድቁና ታማኝነቱ ፡፡ በዚህ ዉስጥ እየበረርን እንደሆነ አዉቃለሁ ነገር ግን እግዚአብሄር ቁጣዉን ለማሳየት፣ ኃይሉን የታወቀ ለማድረግ በሚያሳየዉ ላይ የከበረዉን ምህረቱን በማስቀመጥ በትዕግስት እየጠበቀ ነው ፡፡ ቀጥሎም ጳዉሎስ እግዚአብሄር ፍቅሩን ለአሕዛብ ያፈስስ እንደ ነበር ለማሳየት ከሆሴዕ መፅኀፍ ጥቅሶችን ተጠቀመ ፤ ይሁን እንጂ ይህ ማለት እግዚአብሄር በአይሁድ ሰዎች ይፈፅመዋል ማለት አይደለም ፡፡

ሮሜ (9፡ 30-33)፡ እነዚህ ቁጥሮች “ በእግዚአብሄር ፀጋ “ ላይ ያተኮሩ ናቸው ፤ እስራኤል በመሲሁ ተሰናከለች ፤ በእስራኤል አለመቀበል ምክንያት እናንተ እና እኔ አህዛቦች ሁሉ የመዳን እድል አለን ፡፡

መደምደሚያ

አይሁዶች በመሲሁ መሰናከላቸዉ፣ በመስቀሉ የመሰናከላቸዉ እዉነት ቀድሞ እስራኤላዊያን ተመርጠዉ እንደ ነበር የነበረዉን እዉነት አይሰርዝም/አያጠፋም ፤ ምክንያቱም ይህ እግዚአብሄርን ስለማይቀይረው ፤ እሱ ታማኝ ነው፣ ፃድቅ ነው እንዲሁም ቅንነቱን እና ፀጋዉን አፍስሳል ፡፡ በመሰናላቸዉ ምክንያት ወንጌልን የመስማት እድል አለን ፡፡ ነገ ያ ለአይሁድ እና ለአሕዛብ ምን እንደሚመስል እንመለከታለን ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, Wiersbe’s Exposition Outlines on the New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 542.

  2. Wiersbe, p. 543.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1535.

  4. MacArthur, p. 1535.

  5. MacArthur, p. 1535.

  6. MacArthur, p. 1535.

  7. MacArthur, p. 1535.

  8. MacArthur, p. 1536.

  9. MacArthur, p. 1536.

  10. MacArthur, p.1537.

  11. MacArthur, p.1537.

  12. Wiersbe, p. 543.

  13. Wiersbe, p. 544.

  14. Wiersbe, p. 545.

ጥያቄዎች

  1. ሮሜ 9፡ 8 የእግዚአብሄር ልጅ ስለመሆን ይናገራል ፤ በስጋ ልጆች እና በእግዚአብሄር ልጆች መካከል ያሉት ልዩነቶች ምንድን ናቸው ? ምን ተስፋ የተነገረ ሆነ ? (ዘፍ 12፡ 7, ገላ 3፡ 16)
  2. ሮሜ 9፡ 17 በምታነቡ ጊዜ የእግዚአብሄርን ህዝብ ነፃ ለማዉጣት ሲል እግዚአብሄር ፈርዖንን በስልጣን ስፍራ በማስቀመጥ ልብ እንዳደነደነዉ ታስባላችሁ ? (ዘጸ 4፡ 21)
  3. በሮሜ (9፡ 33) እግዚአብሄር ለምን የማሰናከያ ድንጋይን እንዳስቀመጠ ምን ታስባላችሁ (ኢሳ 8፡ 14-15, 28፡ 16) ? እስካሁን በማደናቀፊያዉ ድንጋይ ተሰናክላችኋል ? ምንስ አደረጋችሁ ?
  4. በሮሜ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Romans 9:23–24

“And what if He did this to make known the riches of His glory on objects of mercy that He prepared beforehand for glory— on us, the ones He also called, not only from the Jews but also from the Gentiles?”

በመጀመሪያ ልጅነት ፣ የእርሱም መገኘት ፣ የሕግም መሰጠት ፣ ኪዳንም ፣ የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ለሆኑት ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር እቅድ አሳብ ነበረው ፡፡ እግዚአብሔር ታማኝነቱን ፣ ፍርዱን ፣ ጽድቁንና መኃሪነቱን ለእስራኤል ህዝብ አሳይቷል ፡፡ ሆኖም ግን እነርሱ ህያው በሆነው ድንጋይ ፣ በማሰናከያው ዓለት ፡- በኢየሱስ ተደናቀፉ ፡፡ ኢየሱስ መሲሃቸው እንደሆነ ሳያውቁት ቀሩ ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ለእነርሱ ባለው ጸጋ ሳይሆን ከህግ ስር መኖርን ቀጠሉ ፡፡ ይሁን እንጅ አሁንም እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው ፡፡ ሀዝቡ የእርሱን ፍቃድ በማይከተሉበት ጊዜ እንኳ ሳይቀር እግዚአብሔር ምህረቱን ከማፍሰስ አያቋርጥም ፡፡ እርሱ በስራ ላይ ነው ባህሪውም አይለዋወጥም ፤ እርሱ የሰጠውን ተስፋ ይፈጽማል ፡፡

እግዚአብሔር ታላቅነቱን ለማሳየት አንተ ልታያቸው በማትችላቸው መንገዶች በአህዛብም ይሁን በአይሁድ ዘንድ እየሰራ ነው ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር በአንተ የሚሰራው ምንድን ነው ? እግዚአብሔር በትክክል ሊሰራ የሚፈልገውን ነገር ልትስተው ትችላለህን ? ምናልባት ይሆናል ፤ ነገር ግን በእምነት በምህረት ፣ በፍቅር ፣ በፍርድ ፣ በጽድቅና በጸጋ አምላክ እመን ፡፡ አሳቡ ይፈጸማል ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ስትራመድ ፣ ከእርሱ ጋር አትተላለፍም ፡፡ ፍቅሩ ታጋሽ ነው ፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ አምላክህ ነው ፡፡ የእርሱ አሳብ እንደሚፈጸም እመን ፡፡

“ አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው በምሕረት ዕቃዎች ላይ የክብሩን ባለ ጠግነት ይገልጥ ዘንድ ፡- የምሕረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፥ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን ።

  • ሮሜ 9 ፡23-24

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 9:4— “ እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና ፡፡ “

ሮሜ 9:32–33— “ ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ ። “

2ኛ ጴጥሮስ 3:9— “ ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል ።