No Condemnation Through Christ
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ብዙ ምሁራን ሮሜ 8 ከመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ በጣም የሚያምረዉ መፅሀፍ እንደ ሆነ ይናገራሉ ፡፡ ለምን ? መጀመሪያው በምዕራፉ ዉስጥ ኩነኔና ፍርድ የለም ፤ ህጉን እና መንፈሱን የሚያነፃፅር ነው ፡፡ ምዕራፉ ወደ አራት ክፍል ሊከፈል ይችላል፡ 1) ከፍርድ ነፃ መዉጣት/መሆን - ኩነኔ የለም (ቁጥር 1-4) ፤ 2) ከመሸነፍ/ከሽንፈት ነፃ መዉጣት/መሆን - ግዴታ የለም (ቁጥር 5-17) ፤ 3) ተስፋ ከመቁረጥ ነፃ መዉጣት/መሆን - ፍርሃት የለም (ቁጥር 8-30) እና 4) ከፍርሃት ነፃ መዉጣት - መለያየት የለም (ቁጥር 31-39) ፡፡
ትምህርት
ሮሜ (8፡ 1-4)፡ “ ኩነኔ “ የሚለዉ ቃል ስለ ሆነ ነገር ወይም ስለ ሆነ ሰዉ ኃይለኛ ተቃዉሞን የሚገልፅ ነው ፤ ነገር ግን በክርስቶስ ላሉት ኃይለኛ ተቃዉሞ የለባቸዉም ምክንያቱም የሚያፀድቀዉ ቅጣታቸዉን አስወግዶላቸዋል (ቁጥር 1) ፡፡ አማኞች በኑሮአችን ከማንኛዉም የኃጢዓት ቅጣት ነፃ ወጥተናል (ቁጥር 2) ፤ የሕይወት መንፈስ ነፃ አድርጎናል ፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ ከነገሮች ነፃ ብንወጣም በዚያ ነፃነት እንዴት እንደምንሰራ/እንደምንቀሳቀስ አናዉቅም ፡፡ ለምሳሌ ሸዋሺንክ ሪደምሽን በሚለዉ ፊልም ዉስጥ የሞርጋን ፈሪማን ገፀ ባህሪይ ከእስር ቤት ነፃ ወጥቶ የተቀመጠ ነበር ነገር ግን እንዴት በዚያ ነፃነት እንደሚንቀሳቀስ አላወቀም ምክንያቱም በእስር ቤት ዉስጥ ህይወቱን ያስተዳድረዉ ከነበረዉ ህግ ጋር ስለተጣበቀ ፡፡
ህጉ በስጋ ደካማ ሆኖ ነበር እግዚአብሄር እንዲያደርግ የሚፈልገዉን ሊያደርግ አልቻለም ፡፡ ህጉ ቅዱስ እንድንሆን በተሰጠን መንገድ/ትራክ ላይ እንድንሮጥ እና ድንበር እንዲሆነን ተቀመጠ ፡፡ እነዚያን ድንበሮች እምቢ ማለትን መምረጥ በኑሮአችን ዉስጥ የህጉ መኖርን ደካማ ያደርገዋል ፡፡ ልጅ እያለሁ በልጆች ስኪ ት/ቤት ዉስጥ የአንድ ስኪ ተቆጣጣሪ ነበርኩ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከትንንሾች ጋር በዳገት/ቁልቁለት ላይ የምንሆንበት ቀን አስቸጋሪ ነበር ፤ ልጆች ባለመኖራቸዉ መልካም/ፍፁም ስራ ስለሚሆን ካለፈ በኋላ እንቀልዳለን ፤ ይሁን እንጂ ሙሉ ለሙሉ አላማችን ስለ እነርሱ በዚያ መሆን ነበር ፡፡ በተመሳሳይ ህጉ እንዲያግዘን ተሰጠን ነገር ግን በመሳት ደካማ አደረገን ፡፡
“ እንደ ስጋ ፈቃድ የማይሄዱት “ የሚለዉ ሀረግ በአብዛኛዉ ባልተፃፉ ጥቂት አስተማማኝ እዉነቶች ዉስጥ አይደለም ፡፡ በክርስቶስ ህይወት እንዲኖረን በመንፈስ ለመኖር ለመገናኘት የሚመስል ሁኔታን ዝንባሌ ስዕል የሚስል ፤ ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት ምንም መፈፀም አይጠበቅብንም ፡፡ በክርስቶስ ኩነኔ የለም ፤ እግዚአብሄር ይወደናል ፤ ነፃ አዉጥቶናል ያለንበትም ስፍራ ላይ ያገኘናል (ሮሜ 5፡ 8) ፡፡ ከፍርድ ነፃ ነን ኩነኔም የለብንም ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ኃጢዓቶቻችን ዝርዝሮችን በማድረግ በልጆቹ ላይ ፍርድን አላደረገም ፡፡
ሮሜ (8፡ 5-17)፡ እንደ አማኝ በክርስቶስ በማደግ ሂደት ዉስጥ ሁላችንም “ ሂደት ዉስጥ ነን “ ፤ በዚህ ጥቅስ በዚህ ቁጥር ዉስጥ አንዳንድ ምሁራን የዳኑትን ወይም ያልዳኑትን በመለየት ጉዳይ ይጀምራሉ ፤ ይህ እዉነት ቢሆንም ሁሉም አማኞች “ በሂደት ዉስጥ “ እንደሆኑና ሁልጊዜ በክርስቶስ እንደሚድጉ በአይምሮአችን ዉስጥ ማስታወስ ይጠበቅብናል ፡፡
ቁጥር 5 አማኞችን ወደ ሁለት ቡድን ይከፍላቸዋል - ስለ ስጋ ነገር የሚያስቡ እና ስለ መንፈስ ነገር የሚያስቡ በማለት ፡፡ አማኝ በሆንኩኝ ጊዜ በአይምሮዬ ዉስጥ ሌሎችን መዳኘት አጠራጣሪ ምልክ የሌለዉ እንደ ነበር የማሰብ ኃሳብ በአይምሮዬ ዉስጥ እንደ ነበር አስታውሳለሁ ፡፡ እግዚአብሄር እነዚያን ሁሉ ነገሮች ከህይወቴ ለምን እንዳልወሰደ በራሴ እደነቃለሁ ፤ እያደረኩ በነበረው በመደነቄ በጥቂት ተሸንፌ ነበር ፡፡
ዮሐ (15፡ 1-4) ስለ አንድ የወይን ዛፍ ቅርንጫፍ መቁረጥ/መከርከም ያወራል ፡፡ ፍሬ ከቅርንጫፎች ድጋፍ ያድጋል ፤ እነዚያን ቅርንጫፎች መከርከም ጊዜን ይወስዳል ፤ በአንድ ምሽት አያድጉም ፡፡ ከቤታችን ግቢ ዉስጥ የሚያምር ዛፍ አለን ፤ ብዙ ቅርንጫፎችን በመቁረጤ አንድ አመት መጠበቅ ይጠበቅብናል ያ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ወጥተው የከረከምኳቸዉ ሞልተው እናያለን ፡፡ ዛፉ ሲሞላ ምርጥ ፍሬ ማፍራት እንደምፈልገው ይሞላል/ይሆናል ፡፡ (ገላ 5፡ 22-24 - የመንፈስ ፍሬዎች ያድጋሉ ) ፡፡
በመንፈስ መሆን ሰላም እና ህይወት ነው በስጋ መሆን ግን በእግዚአብሄር ዘንድ የተጠላ ነው (ቁጥር 6-7) ፡፡ በእምነቴ ሳድግ ሀሳቤን በክርስቶስ ነገር ላይ ማድረግን ተማርኩኝ ፤ ለእኔ ኃጢዓት የሞተ እንደ ሆነ አወኩኝ ነገር ግንይህ አይምሮዬን እና አካሌን በመንፈስ እንደ ገና ማሰልጠን እንደ ነበር ይመስል ነበር ፡፡ ሀሳቦች፣ ቀልዶች፣ ፍላጎቶች እና ስሜቶች አሁንም በአይምሮዬ ዉስጥ ይሄዳሉ ነገር ግን ለኃጢዓት እንደ ሞትከኝ እና በክርስቶስ ህይወት እንደ ነበረኝ ሳዉቅ አስወጥቼ መጣል ቻልኩኝ ፡፡ ከጊዜ ብዛት ትንንሽ የሆኑ ዉጊያዎችን ማሸነፍ ስለቀጠልኩኝ ከሽንፈት ነፃ የሆነዉን ነፃነት ቀመስኩኝ ፡፡ ትንንሽ ዊጊያዎችን ማሸነፍ እንደምችል እና ለእነርሱም የመገዛት ግዴታ እንዳልነበረብኝ አዉቃለሁ (ኤፌ 5፡ 7-10) ፡፡ በዉስጣችን የእግዚአብሄር መንፈስ ከሌለን ክርስቶስ የእኛ ወገን አይደለም (ቁጥር 9) ፤ ስለዚህ እንደ አማኝ በስጋ አይደለንም ፡፡ በክርስቶስ የህይወት መንፈስ እና ፅድቁ በእኛ ዉስጥ ነው ፡፡
ኢየሱስን ከሞት ያስነሳዉ መንፈስ በእኛ ዉስጥ በመኖር ህይወትን ይሰጠናል (ቁጥር 11) ፡፡ ለስጋ ሳይሆንለመንፈስ ባለ እዳዎች ነን (ቁጥር 12) ፤ ለኃጢዓት ባሪያዎች አይደለንም ምንም እዳ አያደርግብንም ፡፡ በስጋ ሀሳብ የምንኖር ከሆነ እንሞታለን ነገር ግን በመንፈስ በመሄድ ስጋችንን ለሞት በማስቀመጥ መኖር እንችላለን (ቁጥር 13) ፡፡ በመንፈስ ስንመራ የእግዚአብሄር ልጆች ስለምንባል (ቁጥር 14-17) እንደ አብ/አባት ልጆች ኑሮአችንን እንኖራለን - ወደ ፅድቅ በመንፈስ እንዲመራን የሚፈልገዉ ልጆች እንባላለን ፡፡ ልጆቻችንን እና በዙሪያችን ያሉትን የምንመራ መሆን አለብን ፤ ከክርስቶስ ጋር ወዳለ ግንኙነት እንመራቸዋለን፣ በመንፈስ በመኖር ምሳሌ በመሆን፣ የአካሄድ ልምዳችንን በማጋራት፣ ተመሳሳይ ነገር እንዲያደርጉ በማስተማር ደጋግሞ በመሞከር እናስተምራቸዉ/እናሰለጥናቸዋለን ፡፡
ሮሜ (8፡ 18-30)፡ የዚህ የአሁኑ ዘመን መከራ ማለፊያዎች ናቸው (2ቆሮ 4፡ 17-18) - የሚሄድና የሚመጣ ነው (ቁጥር 18) ፡፡ ሁላችንም የእግዚአብሄርን ልጅ ሁለተኛ መምጣትን እየጠበቅን ነው (ቁጥር 19) ፤ እግዚአብሄር ይመጣል ፤ ፍጥረቶቹም ከከንቱ ነገር ባርነት ነፃ እንዲወጡ እቅድ አለው (ቁጥር 20-21) ፡፡ ሁሉም የእግዚአብሄር ፍጥረት ሰዉን ሁሉ ጨምሮ በአንድ ላይ በመቃተት እየጠበቁ ነው (ቁጥር 22-23) ፡፡ ዋይርስቤ “ የአሁኑ የሚያስቃስት ባርነት ለነገዉ የከበረ ነፃነት የሚቀየር እንደሆነ !“ ይፅፋል ፡፡ እግዚአብሄር በመንፈስ እንድንጓዝ ስለሚፈልግ ተመልሶ ለመምጣቱ በመዘጋጀት እንደ አላማዉ መጓዝ እንችላለን (ቁጥር 24-25) ፡፡ በምንደክም ጊዜ መንፈስ ይረዳናል ስለ እኛም ስለ ቃላትም/ስለምንፀልየው በጥልቅ መቃተት ይማልቅልናል (ቁጥር 26-27) ፡፡ በመታዘዝ ለኢየሱስ ጌትነት በሙሉ ስንቀርብ ሁሉም ነገር ለበጎ ያደርገዋል (ቁጥር 28) ፤ እግዚአብሄር የክርስቶስን መልክ እንድንመስል በማረጋገጥ ጠርቶናል (ቁጥር 29) ፡፡ እግዚአብሄር ኢየሱስ መልሶ መምጣት ላይ እንድንደርስ እንድንዘጋጅ እያደረገን ነው (ቁጥር 30) ፡፡
ሮሜ (8፡ 31-39)፡ በቁጥር 31 ጳዉሎስ “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል ?” እነዚህን ኃይለኛ ቃላቶችን ሰጥቶናል ፤ እግዚአብሄር በሚያስፈልገን ሁሉም ነገር ስላሰለጠነን ተመልሶ ለመምጣቱ ዝግጁዎች መሆን እንችላለን (ቁጥር 32) ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር ለፍጥረቶቹ፣ ለህዝቡ እና ተመልሶ ለመምጣቱ እቅድ አለው ፤ በኩነኔ ወይም በፍራት እንጓዝም ፡፡ ለእኛና ለመንግስቱ አላማዉን ለመፈፀም በእግዚአብሄር መንፈስ እንጓዛለን ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 540.
ጥያቄዎች
-
ሮሜ (8፡ 1) ስለ ኩነኔ ይናገራል ፤ በኩነኔ/በፍርድ ስር ሆናችሁ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታዉቃላችሁ ? አዎ ካላችሁ ራሳችሁን አስመልጣችኋል ? ካልሆነ ደግሞ ያንን ሸክም ኢየሱስ ከእናንተ እንዲያስወግድ ለመጠየቅ ትንሽ ደቂቃ ዉሰዱ
-
ሮሜ (8፡ 4) “ እንደ ስጋ ፈቃድ ሳይሆን እንደ መንፈስ ፍቃድ ስለመጓዝ “ ያወራል ፤ ለእናንተ “ እንደ ስጋ ፈቃድ መጓዝ “ ምን ይመስላል ? በመንፈስ መጓዝስ ?
-
ሮሜ (8፡ 18) በዚህ ያለዉ መከራ/ስቃይ ከሚመጣዉ ክብር ጋር ሲወዳደር “ ያነሰ/ምንመ እንደ ሆነ “ ይናገራል ፤ እንዲህ አይነቱ መከራ/ስቃይ ሌላ የት ስፍራ ላይ ነዉ የተጠቀሰው ? (2ቆሮ 4፡ 17, ያዕ 1፡ 12, 1ጴጥ 5፡ 10)
-
ሮሜ (8፡ 28) ከኤር (29፡ 11) ጋር እንዴት ታወዳድሩታላችሁ ? ልዩነቶቻቸዉ ወይም አንድነቶቻቸዉ ምንድን ናቸው ?
-
ሮሜ (8፡ 38-39) ለልባችሁ እንዴት ይናገራችኋል ? ከእግዚአብሄር ጋር ፍቅራችሁ ይህን እንደሚመስል ታዩታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታዩትም ?
-
በሮሜ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Romans 8:37–39
“No, in all these things we are more than victorious through Him who loved us. For I am persuaded that not even death or life, angels or rulers, things present or things to come, hostile powers, height or depth, or any other created thing will have the power to separate us from the love of God that is in Christ Jesus our Lord!”
ስለ እግዚአብሔር መንፈስ ማሰብ ህይወትንና ሰላምን ይሰጣል በሌላ በኩል ስለ ስጋ ማሰብ ግን ሞትን ያመጣል ፡፡ ስለዚህ አሳብህን በመንፈስ ላይ አድርግ ፡፡ በመንፈስ ኃይል ተመላለስ ፡፡ እናም በመንፈስ እየተመላለስክ መከራ እና ችግር ሲመጣ ምላሽ በስጋህ ሳይሆን በመንፈስ ትሰጣለህ ፡፡ ምንም እንኳ በመከራ በመጎዳት ውስጥ ብታልፍም ፣ በመንፈስ የሰላምና የደስታ ፍሬዎችን ትቀበላለህ ፡፡ በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ትመላለሳለህ ፡፡ እግዚአብሔርን ለሚወዱት እና እንደ አሳቡ ለተጠሩት ነገርን ሁሉ አያይዞ ለበጎ እንደሚያደረግላቸው ፣ በእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ በመታመን ትመላለሳለህ ፡፡ ይህ በመንፈስ መመላለስ ነው ፡፡
እንደ አማኝ ህይወትን በሽንፈት ሳይሆን በአሸናፊነት ትኖራለህ ! በሚወድህና ህይወቱን በሰጠህ በክርስቶስ ከአሸናፊዎች ሁሉ ትበልጣለህ ፡፡ በመንፈስ ስትመላለስ ፣ ከእግዚአብሔር ፍቅር ይለይህ ዘንድ ምንም ነገር እንደማይችል በማመን ትመላለሳለህ ፡፡ ምንም ነገር ፡፡ ስለዚህ ተሸንፈህ እንዳትኖር ፡፡ ትከሻህን መለስ አድርገህ ፣ አይኖችህን በፊትህ ባለው ክርስቶስ ላይ አድርገህ በትንሳዔው ኃይል እየተመላለስክ ኑር ፡፡ በክርስቶስ ድልን ትቀዳጃለህ ፡፡ ሰላም በተሞላውና ህይወትን በሚሰጠው በእርሱ መንፈስ ተመላለስ ፡፡ ጸንተህ ቁም በክርስቶስም ፍቅር ውስጥ ኑር ፡፡
“ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ። ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ ። “
- ሮሜ 8፡37-39
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ 8:5–6— “ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው ። “
ሮሜ 8:28— “ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ። “
1ኛ ቆሮንቶስ 15:57— “ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።