Paul's Letters Romans

Living Free From Sin

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 493 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በክርስቶስ ለሆንን በአዲስ ኪዳን ዉስጥ ሮሜ ዋና መፅሀፍት ፤ ጳዉሎስ ምዕራፍ 7 አማኞች በክርስቶስ ድነዉ እንኳን ቢሆንም በህግ ቁጥጥር ስር መሆንን በመጠየቅ ይጀምራል ፡፡ የበላይነትን ለመዉሰድ ስለ ሁለት ዉሾች ትግል የአንድ የቆየ/የዱሮ የአሜሪካ ነዋሪ አለ - አንድ ነጭ ዉሻ እና አንድ ጥቁር ዉሻ መካከል ፡፡ አንድ ሰዉ የትኛዉ ዉሻ አሸነፈ ብሎ በጠየቀዉ ጊዜ “ ምግብን የበላዉ አንዱ ፤ ምግብን ያላገኘዉ አንዱ በመጨረሻም በራብ ሞተ “ በማለት መለሰ ፡፡ ዮሐንስ 8 ኢየሱስ ከኃጢዓት ነፃ አዉጥቶናል ይላል ነገር ግን በስጋ ስጋዊ የሆነዉ የኃጢዓት ተፈጥሮአችን ወደ ኃጢዓት መልሶ ሊያስገባን መሞከሩን ይቀጥላል/አያቆምም ፡፡ ዉዥንብሩ የኃጢዓት ተፈጥሮ ካለን አሁንም ኃጢዓት አለብን የሚለዉ ነው ፤ ካልተጠነቀቅን በዚያ የኃጢዓት ተፈጥሮ ኃጢዓተኝነታችን ለመተቸት እንሞክራለን ፤ ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱስ ለኃጢዓት እንደሞትን ይናገራል ፡፡ ልቤ ከኃጢዓት ነፃ ሆነን እንደምንኖር ነዉ የሚናገረው ፡፡

ትምህርት

ሮሜ (7፡ 1-6)፡ ጳዉሎስ ከትዳር አንድ ምሳሌን በመጠቀም ከህግ ስር መሆን የሚለዉን ጉዳይ መረመረው (ቁጥር 1-2) ፡፡ ጳዉሎስ ያገባች ሴት በህይወት እስካለ ድረስ ከባሏ ጋር በህግ የታሰረች ነች አለ ፤ ከሞተ ግን ከዚያ ከተገባ የቃል ኪዳን ተፈታለች/ተለቅቃለች ፡፡ ባላ ሳይሞት በፊት ሌላ ባል ካገባች አመንዝራ ትሆናለች (ቁጥር 3) ምክንያቱም ሁለት ባል መኖር ህጋዊ ስላልሆነ ፤ ስለዚህም ኪዳኑ በሞት ብቻ የሚሰበር ነበር ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አማኞች በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ለኃጢዓት የሞቱ ይሆናሉ (ቁጥር 4) ፤ ያ ማለት ከክርስቶስ ጋር በኪዳን ትስስር/ግንኙነት ዉስጥ ስላለን ለእርሱ ብዙ ፍሬን ማፍራት እንችላለን (ቁጥር 5) - ፍቅርን፣ ደስታን፣ ሰላምን፣ ትዕግስትን፣ ርህራሄን፣ ቸርነትን፣ እምነትን፣ የዋህነትን እና ራስን መግዛትን (ገላ 5፡ 22-23) ፡፡ ከክርስቶስ በፊት በኃጢዓት ፍላጎታችን በነፃነት በመመላለስ/በማድረግ “ የሞትን ፍሬ አፈራን “ (ቁጥር 5) ፤ ነገር ግን አሁን በሞት(ሚስቲቱ ነፃ እንድትሆን ባልየዉ መሞት እንደ ነበረበት) ከዚያ ኪዳን ነፃ ወጥተናል፣ ለክርስቶስ ህያዋን ስንሆን አሁን በመንፈስ እናገለግላለን፡፡ ሞት ነበር፣ በዚህ ጉዳይ በባርነት ይዞን የነበረ የሚቀጥል ሞት ነው - ህጉ ነው (ቁጥር 6) ፡፡ የመንፈስ አዲስነት በዚያ ሞት ይመጣል ፡፡

ሮሜ (7፡ 7-12)፡ የጳዉሎስ ቀጣዩ ጥያቄ “ ህጉ በራሱ ኃጢዓት ነው ? “(ቁጥር 7) ብሎ መጠየቅ ነበር ፤ ጳዉሎስ የራሱን ጥያቄ “ በፍፁም አይደለም ! “ በማለት ይመልሳል ፤ ለምን ? ምክንያቱም ያለ ሕጉ ኃጢዓት ምን እንደ ነበር ስለማያውቅ ፡፡ ሕጉ ከኃጢዓት ዛፍ ላይ እንዳንወድቅ የሚጠብቀንን መከላከያ አካትቷል በተጨማሪም ወደ ኢየሱስ ያመለክቱናል - ወደ ቅዱስነቱና ወደ ፃድቅነቱ ያመለክተናል ፡፡ ኢየሱስ ከህግ በላይ ይዞን የሚሄደው የሚያፀድቅ ነበር ፤ ጳዉሎስ ህጉ እንደ ተነገረው የማሳመን ምሳሌን ተጠቀመ ፡፡ ጳዉሎስን ኃጢዓት በአታለለዉ እና በራሱ ህጉን ለመፈፀም አለመቻሉን ባስተዋለ ጊዜ ያ ሞት መጣ (ቁጥር 8-12) ፤ ሕጉ ቅዱስ ነው ፡፡

ገላትያ 2 ላይ በመሄድ ስለዚህ ነገር በህጉ እናዉራ ፤ የገላ (2፡ 15-21) መነሻ ሀሳብ ጴጥሮስ ወደ አንፆኪያ በመምጣት ከጳዉሎስ እና ካመኑ አሕዛቦች ጋር መብላቱ ነው ፤ ነገር ግን ጥቂት የአይሁድ “ ምሁራኖች “ ከኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜ ጴጥሮስ ከአሕዛቦች ራቀ ፡፡ በተገቢዉ ስርዓት የሚኖሩትን በተለይ የመገረዝን ድርጊት በመፈፀም የሚኖሩትን አይሁዶች ፈራ ፤ ጳዉሎስ ጴጥሮስን ከግብዝነት እንዲወጣ ነገረው ፡፡ ጳዉሎስ ሁለቱም በክርስቶስ ፀድቀዉ እንደ ነበር አመልክቷል/ተናግሯል ነገር ግን ጴጥሮስ ወደ ኃላ በህግ ስር ለመሆን በመሞከር በሚለዉ መሰረት እያደረገ ነበር፡፡ ካልተጠነቀቅን በመጀመሪያዉ ስፍራ ወደ መንፈሳዊ ሞት ወደ የሚወስዱንን ለመገንባት እየሞከርንን ነው ማለት ነው ፡፡ ትክክለኛዉን ነገር ለማድረግ እና በትክክለኛ ስርዓት ለመኖር እንሞክራለን ነገር ግን ፃድቅ በሆነዉ ላይ ትኩረታችንን እናጣለን ፡፡

ገላ (5፡ 1) “ በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን ፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ “ ይላል ፤ ነፃ ስለወጣን እንደ ገና መያዝ የለብንም ፡፡ እዚህ ጋር የተጠቀሰዉ “ የባርነት ቀንበር “ ህጉ ነው ፤ ዮሐ (15፡ 4-5) በእርሱ እንድንኖር እና እርሱም በእኛ እንደሚኖር የሚለዉን የኢየሱስን ትዕዛዝ ይመዘግባል ፡፡ ከክርስቶስ ዉጪ ምንም ማድረግ አንችልም (ቁጥር 5) ፤ ነገር ግን ካልተጠነቀቅን ተመልሰን በህጉ እና በህጋዊነት/በስርዓታዊነት ወጥመድ ዉስጥ እንወድቃለን ፡፡ ህጉን በራሳችን መጠበቅ ችለን ቢሆን ኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት አልነበረበትም ፡፡

ሮሜ (7፡ 13-25)፡ ከዚያም ጳዉሎስ “ እንግዲህ በጎ የሆነዉን ለእኔ ሞት ሆነብኝ ? “ በማለት ጠየቀ (ቁጥር 13) እንደ ገና የራሱን ጥያቄ መለሰ “ በፍፁም አይደለም ! “ ፤ ሞትን የሚያመጣ በህይወቱ ኃጢዓት ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ህጉ መንፈሳዊና ከእግዚአብሄር እንደ ሆነ ነገር ግን ለኃጢዓት ከተሰጠ ስጋ እንደ ተሰራ ገለፀ (ቁጥር 14) ፤ ጳዉሎስ የግጭቱ ምክንያት፡ “ የማደርገዉን አላዉቅምና ፤ የምጠላዉን ያን አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደዉን እርሱን አላደርገዉም ፡፡ የማልወደዉን ግን የማደርግ ከሆንሁ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ “ (ቁጥር 15-16) ፡፡ እዉነታዉ የክርስቶስ ሀሳብ በእኛ ዉስጥ አለ ፤ ጳዉሎስ ማድረግ የማይፈልገዉን ካደረገ በእርሱ በሚኖረዉ ኃጢዓት ምክንያት ነበር (ቁጥር 20) ፡፡ ጳዉሎስ “ እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰዉ ነኝ ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል ? “ በማለት ጮኸ (ቁጥር 24) ፡፡

መደምደሚያ

በህይወቱ ኃጢዓትን መቆጣጠር ያልቻለ ቆስቋላ ሰዉ በመሆን በዚህ ስፍራ ላይ ነኝ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር በመጓዝ በቤቴ ለልጆቼ ላሳየዉ እፈልጋለሁ ፤ ኢየሱስን በስራ ስፍራዬ ላይ ማጋራት እፈልጋለሁ ፡፡ በህይወቴ በኃጢዓት ይህን እንዴት ማድረግ እችላለሁ ? ገላ (5፡ 16-18) “ ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ ፡፡ ስጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በስጋ ላይ ይመኛልና እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም ፡፡ በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም “ ይላል ፡፡

ገላ (5፡ 19-21) የስጋ ስራዎችን ይዘረዝራል፡ “ የስጋ ስራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ ጣዖትን ማምለክ፣ ምዋርት፣ ጥል፣ ክርክር፣ ቅንዓት፣ ቁጣ፣ አድመኛነት፣ መለያየት፣ መናፍቅነት፣ ምቀኝነት፣ መግደል፣ ስካር፣ ዘፋኝነት ይህንም የሚመስል ነው “ ፤ ቁጥር (22-23) ደግሞ የመንፈስ ፍሬዎችን ይዘረዝራል፡ “ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የዉሃነት፣ ራስን መግዛት ነው “ ፡፡

በሮሜ 7 ለማድረግ ምርጫ እንዳለን እናገኛለን ፤ በመንፈስ ፍሬዎች እንጓዛለን ? ወይስ ተመልሰን በህግ ስር እንወድቃለን ? ገላ (5፡ 24-26) ይህን ሂደት ይገልፀዋል፡ “ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑት ስጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ ፡፡ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ ፡፡ እርስ በእርሳችን እየተነሳሳንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ “ ፡፡ በመንፈስ የመኖር እና የእርሱ ፍሬ ሊኖረን ችሎታ አለን ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ሮሜ 7 ካገባች በኋላ ከሌላ ወንድ ጋር ስለ ተቀላቀለች አንዲት ሴት ምን ይላል ? እንደ መፅኀፍ አገላለፅ የትዳር ኪዳን እንዴት የተቀደሰ ነው ? (ዘፍ 2፡ 24, ማቴ 19፡ 3-9, ኤፌ 5፡ 25-31)
  2. ምድራዊ ጋብቻ ከኢየሱስ (ሙሽራዉ) እና ከቤተ ክርስቲያን (ከሙሽራዋ) ጋር እንዴት ይነፃፀራል ? (ኢሳ 62፡ 5, ራዕ 19፡ 7)
  3. እንደ ሮሜ 7 አገላለፅ እንድንሞትላቸዉ የተመከሩ/የተነገሩ ነገሮች ምንድን ናቸዉ፣ ለምንስ ?
  4. ሮሜ 7 ስለ ህጉ ምን ይላል (ማቴ 5፡ 17-20) ? ህጉ መጥፎ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? በገለፃችሁበት መንገድ ለምን እንደ ገለፃችሁ አብራሩ ፡፡
  5. ጳዉሎስ በቁጥር 19 የተሰማዉ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? “ መልካም/ፃድቅ “ ሰዉ መሆን የምትችሉበት መንገድ አላችሁ ? (ማር 10፡ 18, ሉቃ 18፡ 19)
  6. በእኛ ዉስጥ እርስ በእርሳቸዉ የዘመቻ ጦርነት የሚያደርጉ ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው ? ከሞት እንዴት ነፃ ልንሆን እንችላለን ? (ዮሐ 3፡ 16, 8፡ 32, 14፡ 6)
  7. በሮሜ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Romans 7:4, 6

“Therefore, my brothers, you also were put to death in relation to the law through the crucified body of the Messiah, so that you may belong to another—to Him who was raised from the dead—that we may bear fruit for God . . . But now we have been released from the law, since we have died to what held us, so that we may serve in the new way of the Spirit and not in the old letter of the law.”

ኢየሱስን የግል አዳኝህ አድርገህ ስትቀበልና እርሱ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ስትመሰክር ፣ ያኔ አዲስ ፍጥረት ነህ ፡፡ ነጻ የወጣኸው ከህግ ፣ ከቀድሞው መንገድህና ከኃጢአት ነው ፡፡ ክርስቶስ ነጻ አውጥቶሃል ፡፡ በኢየሱስ ላይ ጸንተህ ቁም ፡፡ ጸንተህ ቁም ! ደህንነትህን ለማግኘት ስትታገልበት ወደ ነበረው እና የህግ ባሪያ ወደ ነበርክበት ወደ ቀድሞው መንገድ እንዳትመለስ ፡፡ ወደ ቀድሞ የኃጢአት ልምምድህ እንዳትመለስ ፡፡ ደግመህ በዚያ ባርነት ውስጥ እንዳትኖር ፡፡ ነጻ ወጥተሃል ፡፡ አንተ የክርስቶስ ነህ ፡፡

ነገር ግን ይከብዳል አይደል ? ጥሩ ማድረግ ትፈልጋለህ ነገር ግን ይከብድሃል ትፈተናለህ እናም በቃ ማድረግ እንደማትችል ይሰማሃል ፡፡ አስተውል ከኢየሱስ ጋር መራመድ ማለት ህግን ስለ መጠበቅ ደግሞም ጥሩ ለማድረግና መልካም ሆኖ ለመገኘት ጥረት ስለ ማድረግ አይደለም ፡፡ ይህ ከኢየሱስ ጋር ስለ መመላለስና በመንፈሱ ውስጥ ስለ መኖር ነው ፡፡ የጠራህ በእርሱ እንድትኖር ነው ፡፡ ከእርሱ ጋር ጊዜን አሳልፍ ፡፡ የእርሱም ፍቅር ይሞላህ ዘንድ ፍቀድ ፡፡ በእርሱ ስትኖር የዚህ አለምን ነገር ሳይሆን የመንፈስን ፍሬ ማፍራት ትጀምራለህ ፡፡ ከእርሱ ስትርቅ ፣ ትፈተናልህ በራስህም የመንፈስን ፍሬ ልታፈራ አትችልም ፤ እናም ይህ ፈተና እርሱ እንድትኖርበት የጠራህ ነጻነት አይደለም ፡፡ እርሱ ከህግ ነጻ ያወጣህ በነጻነት ትኖር ዘንድ ነው ፡፡ ዛሬ በእርሱ ኑር ደግሞም በስጋህ ሳይሆን በመንፈስ ተመላለስ ፡፡

“ እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ ……….አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም ። “

  • ሮሜ 7፡4 ፤ 7፡6

ተጨማሪ ጥቅስ

ዮሐንስ 15:4–5— “ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም ። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል ። “

ገላትያ 5:16–18— “ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ ። ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም ። በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም ። “

ገላትያ 5:22–23— “ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው ። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም ። “