Dead To Sin
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ጳዉሎስ ፅፎላቸዉ የነበረዉን አብዛኞቹን ቤተ ክርስቲያኖች ቀድሞ ቢጎበኝም ጳዉሎስ ይህንን መልዕክት ሲፅፍላቸው በሮም ያለችዉን ቤተ ክርስቲያን አልጎበኘም ነበር ፡፡ ምናልባትም ሮሜን ለመሳብ/ለማሳመን እንደ ማስተማሪያ ዘዴ ጳዉሎስ ሮሜን ሲፅፍ ብዙ የተጋነኑ/የሚያሳምኑ ጥያቄዎችን ተጠቅሟል ፡፡ ምዕራፍ 6 ከእነዚህ አሳማኝ/የተጋነኑ ጥያቄዎች በአንዱ የምዕራፉ ዋና ኃሻብ በሆነዉ ይጀምራል፡ ክርስቲያን ለኃጢዓት የሞተ ነው ፡፡ ይህ ኃሳብ ጳዉሎስ በምዕራፍ 5 ኢየሱስ ኃጢዓታችንን በመዉሰድ ከኃጢዓት አነፃን የሚለዉን ጉዳይ የተከተለ ነው ፡፡
ዋረን ዋይርስቤ ጳዉሎስ በምዕራፍ 6 ላይ በዋቀረው/በቀናጀዉ ክርክር ዙሪያ ሰዎስት ነጥቦችን/ጭብጦችን ፅፏል፡
- ማወቅ (6፡ 1-10)
- ማሰብ/ማሰላሰል (6፡ 11)
- ማፍራት (6፡ 12-23)
ትምህርት
ሮሜ (6፡ 11)፡ ይህ የምዕራፍ 6 ጭብጥ/ዋና ጥቅስ ነው ፡፡ ጳዉሎስ በኃይል ክርስቲያን ለኃጢዓት እንደ ሞተ ይናገራል ፤ እንደዚያ ሲሆን ለእግዚአብሄር ህያዋን እንሆናለን ፡፡
ሮሜ (6፡ 1)፡ የመክፈቻዉ ማሳመኛ ጥያቄ “ እንግዲህ/ስለዚህ ምን እንላለን ? “ “ እንግዲህ “ እንደሚለዉ ቃል ያገለግላል ፡፡ ጳዉሎስ ከምዕራፍ 5 መደምደሚያዉ ክርክርን/ነገርን መሰረተ “ በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ ፤ ዳሩ ግን ኃጢዓት በበዛበት ኃጢዓት በሞት እንደ ነገሰ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግስ ዘንድ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ “ (ሮሜ 5፡ 20-21) ፡፡ በቀድሞ ቤተ ክርስቲያን ጥቂቶች የፀጋ መብዛት ኃጢዓትን ካመነጨ ኃጢዓትን ማስወገድ ለመሞከር ምክንያት እንዳልነበር አስበዋል ፡፡ ኃጢዓት ሲበዛ የበዛ ፀጋ ያስፈልጋል/መኖር አለበት ማለት ስለሆነ ፀጋ መልካም ነገር ነበር ፡፡
ሮሜ (6፡ 2-5)፡ ጳዉሎስ አጥብቆ ክርስቶስ ለኃጢዓት እንድንሞት እንዳደረገን ያመለክታል ፤ ስለሆነም ክርስቲያን በኃጢዓት ለመኖር የሚቀጥል ፍላጎት ሊኖረዉ አይገባም ማለት ፡፡ ቁጥር 3 ጳዉሎስ “ ወይስ አታዉቁምን “ በሚለዉ ሀረግ ይጀምራል ፤ ይህ ማለት ሮማዉያን በኃሳብ ደረጃ ለኃጢዓት ሞተዉ እንደነበር የሚለዉን እዉነት እንደሚያዉቁ ነገር ግን ወደ ሙሉ መረዳት መጥተዉ እንዳልነበር ይገልፃል ፡፡ ከኃጢዓት ነፃ መዉጣት ከኢየሱስ ጋር በሮማዉያን ግንኙነት መጣ ፤ በተመሳሳይ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳዉ የእግዚአብሄር ክብር በኢየሱስ ባላቸዉ እምነት ምክንያት በአዲስ ህይወት መንገድ መጓዝ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ፡፡ እዚህ ጋር ጳዉሎስ “ ክብር “ ብሎ የሚጠቀመዉ ቃል ከአልዓዛር ሞት በኋላ ኢየሱስ ማርታን “ ኢየሱስም ብታምኚስ የእግዚአብሄር ክብር እንድታዩ አልነገርሁሽምን “ (ዮሐ 11፡ 40) ብሎ በተናገራት ጊዜ ዮሐንስ በዮሐንስ 11 ከተጠቀመዉ ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ወንድሟ ከሞት ሲነሳ ማርታ የእግዚአብሄርን ክብር አይታለች፣ ሮማዉያን በመስቀል ላይ በኢየሱስ የንስኃ ሞት በኩል ከኃጢዓታቸዉ ኃይል ነፃ በወጡ ጊዜ የእግዚአብሄር ክብር በመታየት ላይ ነበር ፡፡ ለኃጢዓት ሲሞቱ በመስቀል ላይ ከሞተዉ ከኢየሱስ አካላዊ ሞት ጋር ይመሳሰላሉ፣ ከሞት በአካል በኢየሱስ መነሳት ምክንያት አዲስ አይነት ህይወት ለመኖር ይችላሉ ፡፡ ኢየሱስ “ ሌባዉ ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም ፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸዉም መጣሁ “ አለ (ዮሐ 10፡ 10) ፡፡ የሮማዉያን ሞት ለኃጢዓት ኢየሱስ ቃል ገብቶት ወደ ነበረዉ የተትረፈረፈ ህይወት የሚመራ ማለት ነበር ፡፡
ሮሜ (6፡ 6-7)፡ በሮማዉያን ላይ የነበረዉ የኃጢዓት ጉልበት በኢየሱስ ስራ ተወዶ ነበር ፤ ኃጢዓት የሆነ ድርጊት ከዚህ በኋላ እነርሱን የመያዝ ኃይል የለዉም ፡፡ ኤፌሶን “ እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም ፤ በእርግጥ ሰምታችሁታልና እዉነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል ፤ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋዉን አሮጌዉን ሰው አስወግዱ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ ለእዉነትም በሚሆን ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሄር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰዉ ልበሱ “ ይላል (ኤፌ 4፡ 20-24) ፡፡
ሮሜ (6፡ 8-11)፡ እንደ ገና ጳዉሎስ በአካል የኢየሱስን መሞትና መነሳት እዉነታን አመለከተ ፡፡ በዚህ ጊዜ የተነሳዉ/የትንሳኤዉ ኢየሱስ በፍፁም ሞትን እንደማይቀምስ የሚለዉን እዉነት አብራራ ፤ በተመሳሳይ መንገድ ሮማዉያንም “ በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆነዉ ለእግዚአብሄር ሕያዋን እንደ ሆኑ ራሳቸዉን መቁጠር አለባቸው “ (ቁጥር 11) ፤ ይህ የምዕራፉ የዋይርስቤ “ ሀሳብ “ ነበር ፡፡ ሮማዉያን በትክክል ለኃጢዓት የሞቱ ለመሆን ሮማዉያን ለኃጢዓት እንደ ሞቱ ራሳቸዉን መቁጠር/መመልከት ነበረባቸው ፡፡ ለእነርሱ ኢየሱስ አድርጎላቸዉ የነበረዉን መረዳት እና እንደ እርሱ ተከታይነታቸው ለእነርሱ ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ነበረባቸው ፡፡
ሮሜ (6፡ 12)፡ ለኃጢዓት እንደሞቱ ራሳቸዉን መቁጠራቸው አሁን ሮማዉያንን ለጌታ እንዲያፈሩ ያደርጋቸዉ ነበር ፤ ለተቀደሰ/ለፅድቅ አላማ ለጌታ ራሳቸዉን ያቀርባሉ ፡፡ አይምሮአቸው ቅዱስ ባልሆነ ነገር የተወሰደ/የተበታተነ አይሆንም ለእግዚአብሄር የተሰጠ ይሆናል እንጂ ፤ አይኖቻቸው በአለም ነገር የተሳበ/የተማረከ አይሆንም ነገር ግን እግዚአብሄር ለእነርሱ ያለዉን ነገር የሚመለከት/የሚያስተዉሉ ይሆናል ማለት ነው ፡፡
ሮሜ (6፡ 15-23)፡ ጳዉሎስ ምዕራፉን የጀመረባቸዉን የማሳመኛ ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ መለሳቸው ፡፡ ሮማዉያን ኃጢዓትን ማድረግን መቀጠል ከመረጡ ለኃጢዓት ባሪያ እንደሆኑ ራሳቸዉን ያሳያሉ ፡፡ ሙሉ ለሙሉ ራሳቸዉን ለክርስቶስ ሲያስማርኩ ለፅድቅ ራሳቸዉን እንደ ባሪያ ያቀርባሉ ፡፡ ፅድቅ ካልሆነ ነገር ተቀብለዉት የነበረዉ ፍሬ ዛሬ ያፍሩበታል ፤ ራሳቸዉን እንደ ፅድቅ አገልጋይ/ባሪያ ሲያቀርቡ መቀደስን እና የዘላለም ህይወትን ይቀበላሉ ፡፡ ኃጢዓት የእግዚአብሄርን ፍሬ የሚያመነጭበት ምንም መንገድ አልነበረም ፤ ኃጢዓት ሁልጊዜ የሚያመጣዉ ሞት ነው ፡፡ የእግዚአብሄር የዘላለም ህይወት ስጦታ እግዚአብሄርን በመታመን እና ራስን እንደ ፅድቅ ባሪያ በማቅረብ ብቻ የሚገኝ ነበር/ነው ፡፡
መደምደሚያ
በእዉቀታችን ለኃጢዓት እንደሞትን እናዉቃለን ነገር ግን ጳዉሎስ በሚገባ ለኃጢዓት በመሞት ለክርስቶስ ህያዉ ሆኖ መኖር ምን ማለት እንደ ሆነ በሚገባ እንድንመለከት ይሞግተናል ፤ ቀጥሎም ለክርስቶስእንዴት እንደምናፈራ እንድንመለከት ይሞግተናል ፡፡ ጌታ ለፅድቅ አላማ እንዲጠቀምብን እንዴት ራሳችንን ማቅረብ እናቀርባለን ? ተስፋ የገባልንን የተትረፈረፈ ህይወት ለመያዝ እንደ ጌታችን ክርስቶስን እንዴት እንከታተላለን ?
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007) pp. 423-424.
Wiersbe, p. 424.
3 Wiersbe, p. 424.
ጥያቄዎች
-
እንደ መፅሀፍ አገላለፅ ኢየሱስን እንደ ጌታ አድርገዉ ከተቀበለ በኋላ በኃጢዓት ዉስጥ መኖርን መቀጠል ማስተዋል ነው ? ከዚያ በኋላ እንዴት መኖር አለባችሁ (ገላ 2፡ 19-20) ?
-
የመጠመቅን ምልክትነትን ግለፁ ፤ እንደ አዲስ አማኝ ይህ ምን ይነግረናል ? ( ሕዝ 36፡ 26, 2ቆሮ 5፡ 17, ኤፌ 4፡ 24)
-
በክርስቶስ ከሆናችሁ የኃጢዓት ባሪያ/አገልጋይ ለምን መሆን የለባችሁ ? ዛሬ በዚህ እዉነት እየተጓዛችሁ ነው ?
-
በሟች ሰዉነታችሁ ኃጢዓት እንዳይነግስበት እንዴት ትከላከላላችሁ (ሮሜ 12፡ 1) ? ራሳችሁን ለእግዚአብሄር እንዴት ነዉ የምታቀርቡት (ቆላ 3፡ 5, 1ጴጥ 2፡ 24) ? በመዝሙር 51 የዳዊት ኃጢዓት ሙሉ ሰዉነቱን እንዴት እንዳጠቃዉ አንብቡ ፡፡
-
በሮሜ (6፡ 23) የማያረጁ/የማይደበዝዙ ሁለት እዉነቶች ምንድን ናቸው ? መፅሀፍ ዘላለማዊ ህይወት ምን ማለት እንደሆነ ምን ይላል ? (ዮሐ 10፡ 10, 17፡ 3)
-
በሮሜ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Romans 6:11
“So, you too consider yourselves dead to sin but alive to God in Christ Jesus.”
ሁሉም ኃጢአትን ሰርቱዋል ከእግዚአብሔርም ክብር ጉድለት የተነሳ ወድቋል ፡፡ ሰዎች በተለያየ የኃጢአት ባርነት ውስጥ ይኖራሉ ፡- ሀሰተኛ አማልዕክት ፣ ጣዖት ፣ ሱስ ፣ ትዕቢት ፣ እና ሌላም ፡፡ ሰዎች ለኃጢአት እንደ ባሪያ ሆነው ይኖራሉ ፡፡ ልክ ባሪያ ለገዥው እንደሚታዘዘው ሁሉ ለኃጢአት ባሪያም የሆነ ሰው ኃጢአት የሚያዘውን ሁሉ ይታዘዛል ፡፡ ሆኖም ግን ለጽድቅ ባሪያ ከሆንክ ፣ ጌታህ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ትታዘዛለህ ፡፡
በክርስቶስ ነጻ ወጥተሃል ከእንግድህም ለኃጢአት ባሪያ አይደለህም ፡፡ በክርስቶስ ለኃጢአት ሞተሃል ወደ ጽድቅም በሚመራህ በእርሱ ትኖራለህ ፡፡ ክርስቶስ የመጣው ከኃጢአት ባርነት ነጻ ሊያወጣህ ነው ፡፡ እርሱ ማግኘት የማይገባህን የዘላለምን ህይወት በጸጋ ሰጠህ ፡፡ ጸንተህ ቁም ፡፡ በባርነት ቀንበር እትያዝ ይልቁንም አዕምሮህንና መንፈስህን በክርስቶስ አዲስ ፡፡ በክርስቶስ ህያው ነህ ! ህያው ነህ !
“ እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ ። “
- ሮሜ 6፡11
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ 6:16–18— “ ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ ። ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ። “
ሮሜ 6:23— “ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው ። “
ኤፌሶን 4:20–24— “ እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም ፤ በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል ፤ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።