Paul's Letters Romans

Justified And Reconciled

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 491 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ጉዞአችንን/መንገዳችንን መስራት በሚያዝናና እና በኢየሱስ ለእምነታችን እንደ መሰረታዊ የሆነዉን በሮሜ መፅኀፍት ዉስጥ እንቀጥላለን ፤ የተማራችሁትን የሆነ ነገር በማሰላሰል ተግባራዊ እናደርጋለን ፡፡

ትምህርት

ሮሜ (5፡ 1-2)፡ ሮሜ 5 “ እንግዲህ “ በሚለዉ ንግግር ስለሚጀምር ሮሜ 4 እንዴት “ እንግዲህ “ ወደ ሚለዉ ንግግር እንደ መራን በመቆም ማሰብ አለብን ፤ ሮሜ (4፡ 3) “ አብርሃም እግዚአብሄር አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት “ ይላል ፤ ፅድቅ ይህ ነው - በኢየሱስ ክርስቶስ ፀድቀናል (ሮሜ 5፡ 1) ፡፡ በኤፌ (2፡ 8-9) ጳዉሎስ በእምነት በኩል እንደዳንን አብራርቷል ፤ ድነት ሊገኝ የማይችል ከእግዚአብሄር የሚሰጥ ሰጦታ ነው ፡፡ በድነት ዉስጥ እምነት ወሳኙ መንገድ ነው ፡፡ “ ያለ እምነት እግዚአብሄርን ማስደሰት አይቻልም “ (ዕብ 11፡ 6) ፡፡

በአገራችን ፍትህ እንዴት እንደጠነከረ ስናስብ ብዙጊዜ ስለ ፍርድ ስርዓቱ እናስባለን ፤ አንድ ጉዳይ በታችኛዉ/ዝቅ ባለዉ የፍርድ ስርዓት የተሰማ ይሆናል ነገር ግን ሁለቱም አካላት ደስተኞች ካልሆኑ ለከፍተኛዉ የፍርድ ስርዓት ይግባኝ ማለት ይችላሉ ፤ ይግባኙ አሜሪካ የበላይ/ከፍተኛ ፍርድ መስጫ ድረስ ይቀጥላል ነገር ግንየበላይ/ከፍተኛ ፍርድ ሰጪዉ ከወሰነበት/ከዳኘዉ የመጨረሻ ነው ፡፡ ከስሞች ዉስጥ አንዱ የእግዚአብሄር ስም ዳኛ/ፈራጅ ሲሆን በምድር ሁሉ ላይ የበላይ/የመጨረሻ ፈራጅ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ፍቅር እና ፍትሀዊም ነው ፤ ፍትሀዊ ይሆናል ምክንያቱም ካልሆነ የተበላሸ/ስህተት ስለሚሆን ፡፡ መፅደቅ/መንፃት የምንችልበት ብቸኛዉ መንገድ ለሌላ ሰዉ ስለ ኃጢዓት ዋጋ በመክፈል ብቻ ነው ፡፡ የ1828 ድህረ ገፆች መዝገበ ቃላት ፅድቅን/መንፃትን “ በክርስቶስ አስተሰረዪነት መዝገብ ላይ እንደ ፃድቅ በመቀበል እግዚአብሄር ኃጢዓተኞችን ይቅር ያለበት ነፃ የፀጋ ተግባር እንደ ሆነ “ ይገልፀዋል፡፡ ኢየሱስ የኃጢዓታችንን ዋጋ ስለከፈለልን በእምነት የክርስቶስን ፅድቅ እንቀበላለን ፡፡

ሮሜ 5 በእግዚአብሄር የፀደቁ የመሆን ብዙ ጥቅሞችን እና በረከቶችን ይሰጣል ፤ መጀመሪያው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም አለን (ቁጥር 1) ፤ ይህ ሰላም በእኛና በእግዚአብሄር መካከል የሚቀጥል ጠላትነት አይኖርም ማለት ነው ፡፡ ኤፌ (2፡ 13) ከእግዚአብሄር ርቀዉ የነበሩት በክርስቶስ ደም ወደ እርሱ አቀረባቸዉ በማለት ይገልፃል ፤ እርግጥ ነዉ ኢየሱስ ሰላማችን ነው (ኤፌ 2፡ 14) ፡፡ ይህ ሰለም ከእግዚአብሄር ጋር የቀጠልን ጠላቶች አይደለንም ማለት ነው ፤ ፊል (3፡ 18) “ ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነዉ ይመላለሳሉ “ ይላል ፡፡ ያዕ (4፡ 4) የአለም ወዳጅ መሆን ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር ጠላት ያደርጋቸዋል ፤ ኢያሱ ለማገልገል ይህን ቀን እንመርጣለን አለ (ኢያ 24፡ 15) ፡፡

ሁለተኛ በእምነት የእግዚአብሄርን ጸጋ እናገኛለን (ቁጥር 2) ፡፡ በሮሜ (1፡ 16-17) ጳዉሎስ የእግዚአብሄር ጽድቅ በእምነት የተገለጠ እንደሆነ እና ፅድቁን የተቀበሉ በእምነት እንደሚኖር ይገልፃል ፤ የፀደቁት በእምነት መኖርን ይመርጣሉ ምክንያቱም አብን የማግኘት መብት/መንገድ ስላላቸው ፤ ነገር ግን ወደ እግዚአብሄር የመቅረብ እድል እንዳለን ብቻ ማወቅ በቂ አይደለም መጠቀምም አለብን ፡፡ ስለ እምነታችን እርምጃዎችን መዉሰድ አለብን ፤ ለኢየሱስ ወይስ ደግሞ ለአለም ነዉ የምንኖረው ፡፡ ሰዎስተኛው “ በእግዚአብሄር ክብር ተስፋ እንደሰታለን “ (ቁጥር 2) ፤ ተስፋችን ተመልሶ እንደሚመጣ እና ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንደምንኖር በሚለዉ በኢየሱስ ተስፋ ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ ልንወስደዉ የሚገባን ትግስት/መታገስ ጊዜአዊ መታገስ ነው ፤ ይህ ህይወት እስኪያበቃ ድረስ የሚቆይ ብቻ ከዚያ ከኢየሱስ ጋር እንሆናለን ፡፡

ሮሜ (5፡ 3-5)፡ ጳዉሎስ ይህን መልዕክት ሲፅፍ በስደትና በመከራ ጊዜ ስለ ኢየሱስ እየታገሱ ስለ ነበሩት ፃፈ ፡፡ በመታገስ በእምነታችን ስንጓዝ የተፈተንን እንሆናለን ፤ ከኢየሱስ ጋር ስንጓዝ መከራና ስቃይ ይኖራል ፡፡ ጳዉሎስ ግን አማኞቹን በችግር ዉስጥ ቢሆኑም እንኳን እንዲደሰቱ ነገራቸው (ቁጥር 3) ፡፡ በችግር/በመከራ ዉስጥ በምናልፍ ጊዜ ጥንካሬን (መቻልን/ትጉ መሆንን) ይሰጠናል ፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜዎች ዉስጥ ተግተን ስንሰራ ባህሪን እና ተስፋን ያስገኝልናል (ቁጥር 4) ፡፡ ባህሪያችን በአስቸጋሪ ጊዜያት መንገዶች ዉስጥ ያደገ ነዉ በቀላል ጊዜያት ዉስጥ በፍፁም አያድግም ፡፡ በአስቸጋሪ ጊዜ በደንብ ኢየሱስን የምንይዝ/የለመድን ከሆንን በደንብ እምነታችን እርግጠና በመሆን ተስፋችን የጠነከረ ይሆናል ፡፡ ይህ ተስፋ በፍፁም አይጠፋም ምክንያቱም የእግዚአብሄር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ ልባችን ስለፈሰሰ (ቁጥር 5) ፡፡

ሮሜ (5፡ 6-8)፡ ጳዉሎስ ረዳት የሌለን ኃጢዓተኞች ነበርን ክርስቶስ ግን ስለ እኛ ሞተልን በማለት ያብራራል ፡፡ እግዚአብሄር ያደረገልንን ማስታወስ አስፈላጊ ስለሆነ እስካሁን እርሱን ያላወቁትን ማገልገል እንችላለን ፡፡ ጳዉሎስ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ብዙ ነገር ደርሶበታል ፤ በድንጋይ ተወግሯል፣ ተደብድቧል፣ በመርከብ አደጋ ተፈትኗል እንዲሁም በእፉኝት ተነድፏል ፤ ነገር ግን ለክርስቶስ ሁሉን በመተዉ ኖረ ምክንያቱም እግዚአብሄር እንደሚወደዉ እና ለህይወቱ እቅድ እንደነበረዉ ስለሚያዉቅ ፡፡ እምነት እና ፍርሃት አብረዉ መሄድ አይችሉም ፤ እምነት ፍርሃትን አርቀን እንድንወረዉር ችሎታን ይሰጠናል ፡፡ በፍርኃት እየተጓዛችሁ ከሆነ መከራ በሚመጣ ጊዜ ትሮጣላችሁ ፤ ነገር ግን በእምነት ከሆነ የምትጓዙት ትቋቋሙታላችሁ ፡፡

ሮሜ (5፡ 9-11)፡ በእምነት ከፀደቅን ከቁጣዉ እንድናለን (ቁጥር 9) ፤ በእምነት ያልዳኑት፣ ከክርስቶስ ዉጪ የሆኑት፣ የእግዚአብሄር ጠላት የሆኑት ግን የእግዚአብሄር ቁጣ ይደርስባቸዋል ፡፡ ይሁን እንጂ “ በልጁ ሞት ከእግዚአብሄር ጋር ታርቀናል “ (ቁጥር 10) ፡፡

አሁን እንደዳንን ካወቅን ኃላፊነታችን ምንድን ነው ? ኑሮአችንን በተለያየ መኖር እንችላለን ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ክርስቶስ እንዳደረገልን ስለምናዉቅ ፡፡ በ 2ቆሮ (5፡ 18) ጳዉሎስ “ እግዚአብሄር የማስታረቅ አገልግሎትን ሰጠን “ አለ ፤ ከእግዚአብሄር ጋር የታረቀ ሁሉም የማስታረቅ አገልግሎት ተሰጥቶታል ፤ በሰማይ ባለዉ እግዚአብሄር እና በምድር ላይ ባሉት ሰዎች መካከል እንቆማለን ፤ በኢየሱስ እንደ ጠበቃችን ለሰዉ ከእግዚአብሄር ጋር የታረቀ እንዲሆን በመካከል ላይ ነን ፡፡ ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ ሲጓዝ አላማዉ ማስታረቅ ነበር -አለምን መልሶ ከእግዚአብሄር ጋር ለማስታረቅ (2ቆሮ 5፡ 19) ፡፡ ኢየሱስ ችግሮቻቸዉን በማስቀጥ አልነቀፋቸዉም ፤ ይልቁንም እንዴት እንደሚድኑ ነገራቸው ፡፡ ወደ ሄደበት ወደ ሁሉም ስፍራ ኢየሱስ መልዕክተኛ እና ለጠፋዉ እና እየሞተ ላለዉ አለም አስታራቂ ነበር ፤ ከዚያም የመጨረሻዉን ማስታረቅ አደረገ - በመስቀል ላይ ሞተ ፡፡ አሁን ይህን የማስታረቅ ስራ ለእኛ አሳልፎ ሰጥቶናል ፤ እኛ የክርስቶስ አካሎች ይህ የማስታረቅ አገልግሎት ተሰጥቶናል ፡፡ አንድ ቃል ተሰጥቶናል - ለሚያምኑት ለመዳን የእግዚአብሄር ኃይል የሆነ ወንጌል የሚባል (ሮሜ 1፡ 16) ፤ እያንዳንዳችን ስለ ኢየሱስ የመናገር ኃላፊነት አለብን ፤ ስለ ክርስቶስ የምንለምን/የምንማለድ የክርስቶስ አምባሳደሮች ነን (2ቆሮ 5፡ 20) ፡፡

መደምደሚያ

ለኢየሱስ እንዴት እንደምንኖር፣ ማን እንደሆንን እና ማንነታችን ምን እንደሆነ የሚያወራ የሚያስደንቅ መፅሀፍ ነው ፤ ነገር ግን ይህ እንደ እዉቀት ብቻ እንዳትወስዱት ፡፡ እዉቀቱ እንዲቀይራችሁ ፍቀዱለት ያ ከሆነ በመሄድ ይህን በዙሪያችሁ ካሉ ሰዎች ጋር መጋራት ትችላላችሁ፣ መልሰዉም ከእግዚአብሄር ጋር መታረቅ ይችላሉም ፡፡

  1. Tim Kelley, “Spiritual Misalignments,” Available from https://www.oneplace.com/ministries/grace-thoughts/read/articles/spiritual-misalignments-8538.html..

ጥያቄዎች

  1. በእግዚአብሄር ፊት እንዴት ፀደቃችሁ ? (የመፅደቅ)የፀደቁ መሆን ዉጤቱ ምንድን ነው ? (ኤፌ 2፡ 14)
  2. ከፀደቃችሁ በኋላ ልታጧቸዉ እንደማትችሉ እርግጠኞች የምትሆኑባቸዉ አንዳንድ (ጥቂት) መንፈሳዊ በረከቶች ምንድን ናቸው ? (ሮሜ 5፡ 1-11)
  3. መፅደቅ ከህይወት መከራ ያመለጠ/ማምለጥ ነው (ዮሐ 16፡ 33) ? መከራ ወይም ችግር ከእግዚአብሄር ፍቅር ሊለየን ይችላል (ሮሜ 8፡ 35-39) ? ከመከራ ማምለጥ ካልቻላችሁ ጥቅማቸዉ/አላማቸዉ ምንድን ነው ? (ያዕ 2፡ 2-4, 1ጴጥ 1፡ 6-7)
  4. በሮሜ (5፡ 6-8) ላይ ለአንድ ደቂቃ አሰላስሉ ፤ ገና በኃጢዓት ዉስጥ እንደነበራችሁ ኢየሱስ ስለ እናንተ መሞቱን በምታስቡት ጊዜ ወደ አይምሮአችሁ ምን ይመጣል ? ልጆቹ ለሆኑት ምን ያክል እንደሚጨነቅ ምን ታስባላችሁ ?
  5. በሮሜ (5፡ 12-19) ሞትን ያመጣዉን አዳምና እና ህይወትን ያመጣዉን ኢየሱስን አወዳድሩ ፤ በቁጥር 20-21 ፀጋን ከህግ ጋር አወዳድሩ ፤ (ሮሜ 7፡ 8-12, ገላ 3፡ 19, 21-24)
  6. በሮሜ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Romans 5:1–2

“Therefore, since we have been declared righteous by faith, we have peace with God through our Lord Jesus Christ. We have also obtained access through Him by faith into this grace in which we stand, and we rejoice in the hope of the glory of God.”

ሰዎች በህይወታቸው ሰላምን ይናፍቃሉ ፡፡ በአራቱም የአለም ማዕዘናት ሰላምን ይፈልጋሉ ፡፡ ለምን ? ምክንያቱም እግዚአብሔር ሲፈጥርህ ይህ አለም ከሚያቀርብልህ ነገር የበለጠ እንድትሻ አድርጎ ስለሆነ ነው ፡፡ ሆኖም ግን ነፍስህ የምትናፍቀውን ሰላም በዚህ አለም ውስጥ ምንም ነገር ሊሰጥህ አይችልም ፡፡ ምናልባት በችግር ውስጥ ፣ በስደት ወይም ደግሞ በመከራ ውስጥ አያለፍክ ይሆናል እናም በዚህ መከራ ውስት ስታልፍ ፣ ሰላምን ትናፍቃለህ ፡፡ ነፍስህ የምትናፍቀው ያ ሰላም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡

ኢየሱስ የሰላምህ አለቃ ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀሃል ፡፡ አዎን ገና ኃጢአተኛ ሳለህ ፍቅሩን የገለጸልህ ኢየሱስ ፣ ያ ኢየሱስ እርሱ የአለም ሰላም ነው ፡፡ ሰላምን ስትፈልግ ፣ በእምነት ወደ ኢየሱስ ተመለስ እናም ጸጋውን ተቀበል ፡፡ በተስፋ መቁረጥ መሃል ብትሆን እንኳ እርሱ ሰላምህ ይሆናል ፡፡ በመከራ ውስጥ ስታልፍ ኢየሱስ ትዕግስትን ይሰጥሃል ፣ የተፈተነ ባህርይን ደግሞም ተስፋን ይሰጥሃል ፡፡ ፍቅሩ ለአንተ እየፈሰሰ ነው ፡፡ በነገር ሁሉ አመስግነው እናም አዕምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእርሱ ሰላም ልብህን ይጠብቃል ፡፡ ገደብን ጣስ እና ከኢየሱስ ጋር ተራመድ ፡፡ አስታውስ እርሱ ነፍስህ የምትናፍቀው ሰላም ነው ፡፡

“ እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ ፤ በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን ። “

  • ሮሜ 5፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 9:6— “ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል ። “

ሮሜ 5:3–5— “ ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን ፤ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም ።

2ኛ ተሰሎንቄ 3:16— “ የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን ። “