Justification Through Faith
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አሁን በሮሜ 4 ላይ ነን ! መጀመሪያ ሬድዮ ስሰራ በዕብራዉ መፅሀፍ ዉስጥ አስተምሬአለሁ ፤ ለማስተማር ዕብራዊ ጠንካራ እንደ ነበር አስብ ነበር ነገር ግን ያ የነበረው በሮሜ ዉስጥ ስላላስተማርኩ ነበር ፡፡ ሮሜ አብሮአቸዉ ሊሆን ይናፍቅ ለነበራቸዉ በሮሜ ለሚገኙ አማኞች የጳዉሎስ መልዕክት ነበር ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ቆይቶ ጳዉሎስ እንደ እስረኛ ሆኖ ይህን ወደ ሮም አደረገ/ላከ ፡፡ ቀደምት ሰዎች ወደ ሮም የሚሄደዉ ደብዳቤ በፌቨን የደረሰ ነበር ይላል ፤ በዚህ ትምህርት መጀመሪያ ላይ ጳዉሎስ ፍላጎቱ ሁሉም ሰዉ ስለ ወንጌል እንዲሰሙና ፃድቅ በእምነት እንደሚኖር እንደገለፀ አስታዉሱ (ሮሜ 1) ፡፡ ከጳዉሎስ የተላኩት ቃላቶቹ ዛሬ የምንኖርባቸዉ/የምንሄድባቸው ናቸው ፡፡
ትምህርት
ሮሜ (4፡ 1-3)፡ ጳዉሎስ ስለ አብርሃም ፅፏል ፤ በዚህ ክፍል ላይ ጳዉሎስ አብርሃምን ለመጥቀስ በሚገባ አስፈላጊ ሆኖ ያገኘዉ ለምን ነበር ? አይሁዶች የእግዚአብሄር ቃል ተሰጥቷቸዉ ነበር አብርሃምም በእግዚአብሄር ቃል ላይ ተጠቅሷል ፡፡ ዋይርስቤ “ አብርሃም በስራ ሳይሆን በእምነት የፀደቀ እንደ ነበር (ቁጥር 1-8) “ ፅፏል ፡፡ ክርስቶስ በዘመኑ መጥቶ/ሁሉን አድርጎ ባልነበረበት ጊዜ አብርሃም እንዴት ሊፀድቅ ይችላል ? ምክንያቱም አብርሃም የእግዚአብሄርን ቃል ስላመነ ፤ በእምነት እርሱን ለማፅደቅ ያ በቂ ነበር ፡፡
ጳዉሎስ ፅፎ ስለ ነበረዉ ሀሳብ በምትረዱ ጊዜ አብርሃም ለእነርሱ ምን ማለት እንደሆነ ይህን ፅሁፍ መረዳት ትችላላችሁ ፡፡ አብርኃም የእስራኤል አካላዊ አባታቸዉ ነበር (ዮሐ 8፡ 39) ፤ በተጨማሪም አብርሀም “ የሁላችንም “ አባት ነው (ሮሜ 4፡ 16) ፡፡ አብርኃም በስራዎቹ ፀድቆ ቢሆን የመመካት መብት ይኖረዉ ነበር ፡፡ ኮንስታብል “ አብርሃም በእግዚአብሄር ፊት ለመጎራት ምንም መነሻ/ስራ አልነበረዉም ምክንያቱም በስራ ሳይሆን በእምነት ፅድቅን ስለተቀበለ “ በማለት ፅፏል ፡፡ አብርሃም በማመኑ ምክንያት ፀድቆ ከነበር ምን አመነ ? ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገዉ፣ እንደሚባረክ እና ያ ተስፋ ቃል ወደ ፍሬ እንደሚመጣ አምኖ ነበር (ዘፍ 12፡ 1-4) ፡፡ ዘሩን ተቆጥሮ ወደ ማይዘለቅ ህዝብ የሚመራ አንድ ልጅ እንደሚኖረዉ አመነ (ዘፍ 12፡ 7, 15፡ 4) ፤ በቀላሉ ሲቀመጥ ከእግዚአብሄር የሆነዉን ቃል አመነ ማለት ነው ፡፡
ኮንስታብል “ በእግዚአብሄር ተስፋዎች ላይ መታመን መሰረቱ እምነት ሲሆን ዉጤቱ ፅድቅ ነው ፤ የእግዚአብሄር ተስፋ ይለያያል ፤ እነዚህ ተስፋዎች የእምነት ይዘት/ሁኔታ መሰረታቸዉ ነው ፤ ይሁን እንጂ የእምነት ግቡ አይለያይም ፤ ሁልጊዜ የእግዚአብሄር ሰዉ ነው ፡፡ ለእኛ የእግዚአብሄር ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ በመተካት እንደሞተ እና ስለ ኃጢዓተኞች የእግዚአብሄርን ፍላጎት እንዳሟላ ነው (3፡ 24-25) ፤ እግዚአብሄር የአብርሃምን እምነት “ ለእርሱ እንደፅድቅ አድርጎ ቆጠረለት “ (ቁጥር 3) ፡፡ እምነት ራሱ ፅድቅ አይደለም ፤ እምነት በራሱ ሽልማት የሚገባዉ አይደለም ፤ የእግዚአብሄር ፅድቅ ወደ እኛ እንዲደርስ ብቸኛዉ የማድረሻ ተሽከርካሪ ነው ፤ እኛንም የሚያደርሰን ብቸኛዉ ማድረሻም እንጂ “ በማለት ፅፏል ፡፡
በቁጥር 3 ጳዉሎስ “ አብርሃምም እግዚአብሄርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት “ በማለት ፅፏል ፤ ተቆጠረለት የሚለዉ ቃል ተመዘገበለት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር “ ተቆጠረ በፋይናንሻል እና በህጋዊ ሁኔታ በሁለቱም ጥቅም ላይ ዉሏል ፤ በምዕራፍ 4 ይህ ቃል ዘጠኝ ጊዜ ተከስቷል ፡፡ ማለትም የሌላ ሰዉ የሆነን ነገር በመዉሰድ በሌላ ሰዉ አካዉንት ላይ መመዝገብ ማለት ነው ፤ በአንድ በኩል ብቻ የሚደረግ ልዉዉጥ ማለት ነው፡፡ አብርሃም ይህን ለማግኘት/ለማጠራቀም ምንም ነገር አላደረገም ፤ በቀላሉ እግዚአብሄር መዘገበለት/ቆጠረለት ፡፡ እግዚአብሄር የራሱን ፅድቅ በመዉሰድ መጀመሪያ የእርሱ እንደ ነበር በማድረግ ለአብርሃም መዘገበለት/ቆጠረለት “ በማለት ፅፏል ፡፡ እግዚአብሄር ይህን ፅድቅ ለአብርሃም ሊመዘግብለት የቻለበት ብቸኛዉ መንገድ ማመኑ ብቻ ነው፡፡
ሮሜ (4፡ 4)፡ ኮንስታብል “ ስራ ሰዉ የሰራዉን ዋጋ ወይም የሚገባዉን ደሞዝ ያስገኛል ፤ እምነት ሰዉ ያመነዉን የማይገባዉን እና ዋጋዉ ያልሆነዉን ያገኛል “ በማለት ፅፏል ፡፡ አብርሃም ፅድቅ የተገባዉ እንዲሆን ያደረገዉ ምንም ነገር የለም ፤ ስላመነ ብቻ ተሰጠው ፡፡ እንደ አገልግሎት የት ላይ እንዳለን ግልፅ ለማድረግ ኤፌ (2፡ 8-9) እናብብ፡ “ ጸጋዉ በእምነት አድኖአችኋልና ፤ ይህም የእግዚአብሄር ስጦታ ነዉ እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም “ ፤ ድነትን ማግኘት አትችሉም ፡፡
ሮሜ (4፡ 5-7)፡ ጳውሎስ ለመጠቀም እንደወደደዉ ዳዊትም ቀድሞ የተለመደ የሚሆን ይመስላል ፤ ዳዊትም እግዚአብሄር ስለቆጠረዉ ፅድቅ ተናግሯል ፡፡ ዳዊት ስለ ምህረት በረከቶቹ ፅፏል ምክንያቱም ከእግዚአብሄር ፅድቅን ማግኘት እንደማይገባዉ ስለሚያውቅ (መዝ 32፡ 1-2) ፡፡
ሮሜ (4፡ 8)፡ ኃጢዓት ፅድቅን አያጠፋዉም ፤ በእግዚአብሄር የፀደቃችሁ ለመሆን አንዴ የክርስቶስን ምህረት ካገኛችሁ ፅድቅ የተወሰደ ሊሆን አይችልም ፡፡ ይህ ማታለል ነው ምክንያቱም እነዚህ ቃላቶች ከብሉይ ኪዳን ስለመጡ ፤ በብሉይ ኪዳን በእግዚአብሄር ያመኑ በእግዚአብሄር ቃል እምነት ፀድቀዋል ፤ ዛሬ እግዚአብሄር ልጁን ለእኛ እንዲሞት እንደላከዉ ባለዉ እምነታችን ፀድቀናል ፡፡
ሮሜ ( 4፡ 9-12)፡ ዋይርስቤ “ አብርሃም በህግ ሳይሆን በጸጋ የፀደቀ እንደ ነበር “ ፅፏል ፤ ሁሉም አብርሃም ከእግዚአብሄር ሰምቷቸዉ የነበሩት ነገሮች ከመገረዙ በፊት ሆነዋል ፤ ስለዚህ አይሁዳዊ ሰው “ ፅድቁ ህጉን ስለጠበቀ ነው ማለት አይችልም “ ፡፡ ከመገረዙ በፊት አምኗል ፤ ጳዉሎስ የጊዜ ቅደም ተከተሉን ያዉቀዋል ፤ እግዚአብሄር ምን እያደረገ እንደ ሆነ ያውቃል ፡፡ የእግዚአብሄር ቃልን ከተቀበለና ካመነ ከአስራ አራት አመት በኋላ ተገረዘ ፤ የአብርሃም መገረዝ እንደ ማህተም/ማረጋገጫ ያገለግላል ፡፡ አብርሃም የሚያምኑት አይሁዶች እና የሚያምኑት አሕዛቦች አባት ነበር (ገላ 3፡ 29) ፤ አብርሃም በፀጋ የፀደቀ ነበር ፡፡
ሮሜ (4፡ 13-15)፡ ህጉን በትክክል መጠበቅ የማይቻል ነገር ነው ፤ ለዚያም ነዉ ፅድቅን በእምነት መቀበል ያለባችሁ ፡፡
ሮሜ (4፡ 16-17)፡ እነዚህ ጥቅሶች ያለፉትን ጥቅሶች ያጠቃልሏቸዋል (ቁጥር 13-15) ፡፡ ኮንስታብል “ እግዚአብሄር ተስፋዉን ለአብርሃም ያለሁኔታ/ያለገደብ (በፀጋ መሰረት) የአሕዛብ አባት እንደሚያደርገዉ ሰጠው - ፓትርያርኩ ፀድቀዉ ከቆሙ በኋላ ፤ አብርሃም ህጉን በመጠበቅ ሳይሆን በቀላሉ በማመን ብቻ ተስፋዉን አገኘ “ በማለት ይፅፋል ፡፡
ሮሜ (4፡ 18-22)፡ ዋይርስቤ “ አብርሃም በሰዉ ጥረት ሳይሆን በትንሳኤዉ ኃይል ፀደቀ (ቁጥር 18-25) “ በማለት ፅፏል ፡፡ ለእግዚአብሄር ክብር በሚያመጣው ሁኔታዉ ምክንያት የአብርሃም እምነት አልተናወጠም ፤ የእግዚአብሄርን ተስፋ ሙሉ በሙሉ አመነ ፡፡ አብርሃም በይበልጥ ከእግዚአብሄር ጋር ሲጓዝ እምነቱ ጠነከረ ፡፡
ሮሜ (4፡ 23-25)፡ ጸሎቴ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ይህን ፈጣን እምነት ማየት እንድጀምር ነው ፡፡ ማክአርቱር “ አብርሃም በእምነት ከፀደቀ ሌላዉ ሁሉም ሰው በተመሳሳይ በእምነት ይፀድቃሉ “ በማለት ፅፏል ፡፡
መደምደሚያ
ለመረዳት ሰዎስት ቃላቶች አስፈላጊ/ጠቃሚዎች ናቸው፡
- መፅደቅ ያለፈ ጊዜ ከኃጢዓት ቅጣት ወዲያዉኑ መዳን ፡፡
- መቀደስ የአሁን ጊዜ ከኃጢዓት ኃይል ቀስ በቀስ መዳን ፡፡
- መክበር የወደፊት ጊዜ ከኃጢዓት መገኘት እስከ መጨረሻዉ መዳን ፡፡
ዛሬ ስለ መፅደቅ አዉርተናል ፡፡ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ መፅደቅ በእምነት እና በእግዚአብሄር በማመን በመምጣት ከኢየሱስ ወደ ሚመጣዉ ድነት አመለከተ ፡፡ ለእኛ ፅድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት፣ መቀበር እና ትንሳኤ የተፈፀመዉን ተስፋ በማመን የሚመጣ ነው ፡፡
Warren W. Wiersbe, Wiersbe’s Exposition Outlines on the New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 372.
Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Bible Study Expository Notes: Romans, p. 85; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/romans.pdf.
Constable, p. 86-87.
John MacArthur, The MacArthur Study Bible (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2013), p. 1691.
Constable, p. 87.
Wiersbe, p. 373.
Constable, p. 93.
Wiersbe, p. 374.
Wiersbe, p. 186.
Thomas Nelson, The Woman’s Study Bible, NIV (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2013), p. 1593.
ጥያቄዎች
-
ሮሜ (4፡ 3-6) የሚመስሉ ጥቅሶች እንዴት ከያዕ (2፡ 17-26) ጋር ይዛመዳል/ይገናኛል ?
-
አብርሃም እንዴት በእግዚአብሄር ፊት ፀደቀ ? በእርሱ ፊት እንዴት ፀደቅን ?
-
ስለ መገረዝ ከአይሁዶች የነበረዉ ክርክር ምን ነበር ? መገረዝ ለምን ነበር የተሰጠው ? (ሮሜ 4፡ 11)
-
በሮሜ (4፡ 17) እግዚአብሄር እንዴት ነዉ የተገለፀው ? (ዘፍ 17፡ 5, ዕብ 11፡ 11-12)
-
የአብርኃም እምነት ለምን እየጠነከረ ሄደ/አደገ ? ኢየሱስ ለምን ሞተ ? ለምንስ ነበር የተነሳው ?
-
በሮሜ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Romans 4:16–17a
“This is why the promise is by faith, so that it may be according to grace, to guarantee it to all the descendants—not only to those who are of the law but also to those who are of Abraham’s faith. He is the father of us all in God’s sight.”
አብርሃም እንደ ጻድቅ የተቆጠረውና ከኃጢአት መንጻትን ያገኘው በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ ባለው እምነት አማካኝት ነበረ ፡፡ አብርሃም አመነ ፡፡ አብርሃም የእግዚአብሔር ቃል እውነት እንደነበር አመነ ፡፡ አብርሃም ጽድቅን ለማግኘት አለፋም ነበር ይልቁንም ጽድቅን በእምነት አገኘው እንጅ ፡፡ አብርሃም የእግዚአብሔርን ተስፋ ባለማመን አልተጠራጠረም ይልቁንም በእምነቱ በረታ እግዚአብሔርንም አከበረ እንጅ ፡፡ እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ደግሞ ሊፈጽመው እንደሚችል ፈጽሞ በመረዳት ፣ እግዚአብሔር እንድያደርግ ያዘዘውን አደረገ ፡፡
ለጽድቅ የሚያበቃ ምንም አይነት የሰው ጥረት ፣ በጎ ስራ ወይም ደግሞ ህግን መጠበቅ የለም ፡፡ የዳንከው በእምነት በጸጋ አማካኝነት ነው ፡፡ በማመን ፡፡ እርሱን እና የእርሱን ተስፋ ስትቀበል፣ እግዚአብሔር በእምነት ያጸድቅሃል ፡፡ ትግሉን አቁም ፡፡ ህጎችን እና ትዕዛዛትን በመከተል በእግዚአብሔር ፊት የጽድቅን ቁመና ለማግኘት ከመሞከር አቁም ፡፡ በቃ ዝም ብለህ የእግዚአብሔርን ተስፋ በእምነት ተቀበል ፡፡ ዛሬ ልታየው በማትችለው ነገር ላይ እመን ደግሞም እግዚአብሔርንና የሰጠውን ተስፋ እመን ፡፡
“ ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው ፤ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው ። “
- ሮሜ 4፡16-17
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘፍጥረት 12:2 ፤ 12፡ 4— “ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን ………… አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፤ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ ። “
ሮሜ 4:20–21— “ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም ። “
ኤፌሶን 2:8–9— “ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።