No Differences Between Jews and Gentiles
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ ሳምንት ከመኃልየ መኃለይ ዘሰለሞን መነሳሳት እና ስሜት ወንጌል ለአይሁዶች እና ለአሕዛብ ምን እንደሆነ እና ሁለቱም እንዴት ፍርድ እንደሚገጥማቸዉ ወደሚያራዉ የጳዉሎስ ስነ መለኮታዊ ዉይይት የተደረገ ጥብቅ/ኃይለኛ ለዉጥ ነው ፡፡ በሮሜ 3 በጣም ብዙ ነገር አለ ፤ በመጀመሪያዎቹ ስምንንት ቁጥሮች ላይ ብቻ እናተኩራለን ፡፡ በዚህ ክፍል ዉስጥ ጳዉሎስ ሰዎች ቀድመዉ ወንጌል ለምን ለአይሁዶች እና ለአሕዛብ እንደተመሳሰለ ይነጋገሩበት ስለ ነበረዉ ይደርሳል/ያወራል ፡፡
ትምህርት
ሮሜ (3፡ 1-2)፡ በቁጥር 1 ጳዉሎስ አይሁዶች በመገረዛቸዉ ምን ጥቅም እንዳላቸዉ ይጠይቃል ፤ በትክክለ አንድ ሰዉ አይሁዳዊ መሆኑ ወይም አልመሆን ችግር ነበረዉ የሚለዉን እየተናገረ ነበር - አይሁዳዊ የሞሆን ሀሳቡ ወይም አላማዉ ምን ነበር ? በቁጥር 2 ላይ ጳዉሎስ የራሱን ጥያቄ መለሰ - አይሁዳዊ የመሆን ጥቅሙ “ በሁሉም መነገድ ከፍ ያለ ነበር “ ፤ መጀመሪያው አይሁዶች እግዚአብሄር የተናገረዉ ቃል አደራ ተሰጥቷቸዉ ነበር (ቁጥር 2) ፤ እግዚአብሄር አይሁዶችን በመላዉ ብሉይ ኪዳን ዉስጥ መለኮታዊ የሆነ መልዕክቱን ሰጥቷቸዋል ፡፡ እንደ ሮሜ (9፡ 4-5) አገላለፅ አይሁዶች እስራኤላዊያን ነበሩ - በእግዚአብሄር የተመረጡ ሕዝቦች፣ የእግዚአብሄር የጉድፈቻ ልጆቹ፣ ከእግዚአብሄር ጋር ባለዉ ኪዳን ዉስጥ የገቡ፣ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ በእግዚአብሄር ፊት ያመልኩ የነበሩ ሕዝቦች እና ከሁሉም ነገር በላይ በሆነዉ በመሲሁ የዘር ሀረግ ዉስጥ የተጋሩ ናቸው ፡፡ የመገረዝ ጥቅም አይሁዶች ከእግዚአብሄር በሆኑት በእነዚህ ሁሉ ስጦታዎች አደራ ተሰጥቶአቸዉ ስለ ነበር ነው ፡፡ አይሁዶች የእግዚአብሄርን ቃል ወደ እኛ እንዲያስተላልፉ ተሰጥቷቸዋል (ሐዋ 7፡ 38, ገላ 3፡ 8, 2ጢሞ 3፡ 15, ዕብ 5፡ 12, 1ጴጥ 4፡ 11) ፡፡
ሮሜ (3፡ 3-4)፡ በቁጥር 3 የጳዉሎስ ሁለተኛዉ ጥያቄ - የእስራኤል አለማመን ወይም አለመታመን ለእነርሱ የእግዚአብሄርን ተስፋ ያጠፋዋል ? ጥያቄው ባለመታመናቸዉ ምክንያት እግዚአብሄር ተስፋዉን ይቀይራል ብሎ ይጠይቃል ፡፡ ዶር. ቶም ኮንስታብል ጳዉሎስ የእስራኤል አለመታመን መቼ እንደጀመረ ለማመልከት እየሞከረ እንደ ነበረዉ እግዚአብሄር እስራኤልን ህጉን በሰጠ ጊዜ በሲና ላይ ወክለዉ ከነበሩት ታምነዉ እንደነበር የቆዩ ሁለቱን ካሌብን እና ኢያሱን ብቻ እንዳገኛቸዉ ይገልፃል ፡፡ ይሁን እንጂ “ ያላመነዉ ትዉልድ በምድርበዳ የሞተ ቢሆንም አሁንም እግዚአብሄር ተስፋ ገብቶት እንደ ነበረዉ ሁሉንም ሕዝብ ወደ ከንዓን አመጣቸው “ ፡፡
ማክአርቱር “ ሰዉ ሁሉ እግዚአብሄር ለተስፋዉ የታመነ እንዳልነበር ይስማሙ ከነበር ሁሉም ዉሸታሞች እና እግዚአብሄር ብቻ እዉነተኛ እንደሆነ እንደሚያረጋግጥ “ ይፅፋል ፤ በተጨማሪም ማክአርቱር “ ባለማመናቸዉ ምክንያት እያንዳንዳቸዉ አይሁዶች ተስፋዎችን መቀበል ባይችሉም እንኳን እግዚአብሄር ለህዝቡ ያደረገዉን ሁሉንም ተስፋዎቹን እንደ ሚፈፅማቸዉ “ ይገልፃል ፡፡ የእግዚአብሄርን ተስፋዎች ለመቀበል ለአይሁዶች በየግላቸዉ ወደ ንስኃና እምነት መምጣት አለባቸው ፡፡ በቁጥር 4 ጳዉሎስ ስለ እግዚአብሄር ፃድቅነት እና ታማኝነት/እዉነተኛነት ተጨማሪ ማስረጃ ለመስጠት መዝ (51፡ 4) ደግሞ ተናግሯል፡ “ አንተን ብቻ በደልሁ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ በነገርህም ትጽድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ “ ፤ እግዚአብሄር በአይሁዶች አልሰራም ፤ ተስፋዎቹን ጠበቀ !
ሮሜ (3፡ 5-6)፡ በቁጥር 5 ጳዉሎስ ሰዎስተኛዉን ጥያቄዉን ይጠይቃል - የአይሁዶች ፃድቅ አለመሆን በይበልጥ የእግዚአብሄርን ፅድቅ የሚገልጠዉ ከሆነ እርሱ ፃድቅ አይደለም ወይስ በቁጣ ብቻ የሚቀጣ ነው ? ኃጢዓቴ ወደ እግዚአብሄር ፍፁምነት የሚያመለክት ከሆነ እግዚአብሄር በእኔ ላይ ቁጣዉን ለማሳየት ይህ ተገቢ/ትክክል ነው ? እግዚአብሄር ኃጢዓትን ስለኮነነዉ ለፍርድ ፃድቅ የሆኑ ወራሾች አይኖሩትም (ቁጥር 5) ፤ እንደዚያ ከሆነ እግዚአብሄር በአለም እንዴት ይፈርዳል ? ማክአርቱር ይህን ሀሳብ “ የድንጋዩን መልክ በይበልጥ የሚያምር ለማድረግ በጥቁር ልብስ ላይ አልማዝን የሚያሳይ አንጥረኛ ይስላል ፤ በቀላሉ የጠላቶቹን መፅኃፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ እዉነቶችን፣ ድክመትን በቀላሉ እየፃፈ ነው - የተፈጥሮአዊ ያልተሸሻለዉ አሳባቸዉ ዉጤት ነው “ በሚል ምሳሌ ይገልፀዋል ፡፡ የማክአርቱር ሀሳብ ኃጢዓታችን እግዚአብሄር ምን ያክል ቅዱስ እንደሆነ እንደሚያሳይ ነዉ ነገር ግን እግዚአብሄር የተሸለ ቅዱስ ለማድረግ ኃጢዓት ማድረግን መቀጠል ትክክል ነዉ ማለት አይደለም ፡፡
ሮሜ (3፡ 7-8)፡ የጳዉሎስ አራተኛ ጥያቄ - የእኔ ዉሸት የእግዚአብሄርን እዉነት ካላቀ ለምን ይፈርድብኛል ? ይህ ጥያቄ ከሰዎስተኛዉ ጥያቄ ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ የጳዉሎስ መልስ “ አይደለም ! “ የሚል ነበር ፤ እንደ ኃጢዓተኛ ነቀፌታቸው የሚገባቸዉ ነው ፡፡ ኮንስታብል “ ጳዉሎስ ይህን ተቃዉሞ በጣም የማይመሳሰል ትኩረት ሊደረግበት የሚያበቃ ዋጋ የሌለዉ አንደምታ ነዉ በማለት እንደገለፀው “ ይናገራል ፡፡ ይህ የአኗኗር ስታይል/ዘዴ ለምንድን ነዉ ያለን ? ቁጥር 9-20 ይህን ጥያቄ መግለጥ ይጀምራል ፡፡
ሮሜ (3፡ 9-20)፡ ጳዉሎስ አሕዛቦች ከአይሁዶች ጋር ተመሳሳይ የሆኑበትን ነገር ያስቀምጣል - ሁላችንም በኃጢዓት ስር ስለሆንን ፡፡ ቀጥሎም ይህ ፅሁፍ እንዴት ኃጢዓተኛች እና ፃድቅ እንዳልሆንን ይገልፃል ፤ ማክአርቱር ጳዉሎስ በቁጥር (10-18) የዘረዘራቸዉን 14 ክሶች ለይቷቸዋል፡
- ማንም ፃድቅ የለም (ቁጥር 10) ፡፡
- ማንም አስተዋይ የለም (ቁጥር 11) ፡፡
- እግዚአብሄርን የሚፈልግ የለም (ቁጥር 11) ፡፡
- ሁሉም ከእግዚአብሄር ዞር ብለዋል (ቁጥር 12) ፡፡
- ሁሉም በአንድነት የማይጠቅሙ ለመሆን ሰርተዋል (ቁጥር 12) ፡፡
- ማንም ደግ/ቸርነት የሚያደርግ የለም (ቁጥር 12) ፡፡
- ጉሮሮአቸዉ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው (ቁጥር 13) ፡፡
- ሁሉም ዋሽተዋልም ሸንግለዋልም (ቁጥር 13) ፡፡
- አፋቸዉ/አንደበታቸዉ በእባብ መርዝ የተሞላ ነው (ቁጥር 13) ፡፡
- አፋቸዉ እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል (ቁጥር 14) ፡፡
- እግሮቻቸዉ ደምን ያፈሳሉ (ቁጥር 15) ፡፡
- መንገዳቸዉ ጥፋትንና ጉስቁልናን ይፈጥራል (ቁጥር 16) ፡፡
- የሰላምን መንገድ አያዉቁም (ቁጥር 17) ፡፡
- እግዚአብሄርን መፍራት የላቸዉም (ቁጥር 18) ፡፡
ሮሜ (3፡ 21-31)፡ አይሁድ እና አሕዛቦች ሁለቱም ኃጢዓተኞች ናቸው ፤ እግዚአብሄርም በሁሉም ላይ ይፈርዳል ፡፡ ዋይርስቤ “ መላዉ አለም አይሁዶችም አሕዛቦችም ጥፋተኞች እንደሆኑ ፤ የአይሁዶች አቋቋም ይመኩበት በነበረዉ ህግ የሚወቀሱ ሲሆን አሕዛቦች አቋቋም ደግሞ በተፈጥሮ እና በአይምሮአቸዉ እንደሚወቀስ “ ይናገራል ፡፡ ማንም በህግ ስራ የሚፀድቅ አይሆንም ነገር ግን በእግዚአብሄር ፅድቅ በመሆነዉ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ ፤ እምነታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስናደርግ በአይሁዶች እና በአሕዛብ መካከል ልዩነት የለም ፡፡ አሁንም እግዚአብሄር አሁንም ለሕዝቡ እንደ አዳኝና እንደ ጌታ በክርስቶስ በማመን የሚፈጽመዉ እቅድ አለው (ቁጥር 21-22) ፤ ቁጥር 23 ይህን “ ሁሉ ኃጢዓትን ሰርተዋልና የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎአቸዋልና “ በማለት ያጠቃልለዋል ፤ በኢየሱስ ክርሰቶስም በኩል ፀድቀዋል (ቁጥር 24) ፡፡
መደምደሚያ
ኢየሱስ በእርሱ ወደ ነፃነት ያመጣን አጽዳቂአችን ነው ፤ ነፃነታችን የመጣዉ በታላቅ ዋጋ መክፈል የመጣ ነው - ያን ነፃነት ለእኛ ለመግዛት ክርስቶስ ህይወቱን ሰጠ ፡፡ በክርስቶስ በኩል እግዚአብሄር የሰራነዉን ኃጢዓት አስወገደው (ቁጥር 25) ፡፡ በሕግ ሳይሆን በክርስቶስ ባለን እምነታችን በእግዚአብሄር ፊት ፃድቆች እንሆናለን (ቁጥር 26) ፡፡ ኢየሱስ የሚያፀድቅ/አጽዳቂ ነው ፡፡
Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Bible Study Expository Notes: Romans, p. 64; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/romans.pdf..
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1512.
MacArthur, p. 1512.
MacArthur, p. 1512.
Constable, p. 66.
MacArthur, p. 1514.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 522.
ጥያቄዎች
-
ለአይሁዶች ብሉይ ኪዳን መኖሩ ጥቅሙ ምን ነበር ? (ዘዳ 4፡ 5-8, ገላ 3፡ 8, 2ጢሞ 3፡ 15, 1ጴጥ 4፡ 11)
-
የማያምን ሰዉ መልካም ነዉ በሚለዉ ላይ ለመፍቀድ/ለማዉራት ለአማኝ ለምን ሞኝነት ይሆናል ? በቁጥር (9-12) አይሁዶች ከአሕዛብ የተሻሉ ናቸው ? ይህ ስለፅድቃችን ምን ይላል ?
-
መፅኀፍ ቅዱሳዊ እግዚአብሄርን መፍራት ምንን ይይዛል ? (መዝ 36፡ 1, ምሳ 1፡ 7, 9፡ 10, ሐዋ 5፡ 1-11)
-
ጳዉሎስ በአንድ ላይ የሁሉንም ሰዉ ፀባይ እና ባህሪይ የሚከስሱ 14 የብሉይ ኪዳንን ንግግሮች/ጥቅሶችን አስቀምጧል ፤ 14 ክሶች/ያልተደረጉት ነገሮች ምንድን ናቸው ? (ሮሜ 3፡ 10-18)
-
ሁሉም ኃጢዓትን የሰሩ እና ማንም ፃድቅ ባይሆንም እንኳን እግዚአብሄር ለሁሉም ለአይሁድም ለአሕዛብም ያቀረበዉ መልካም ዜና ምንድን ነው ?
-
በሮሜ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Romans 3:23–24
“For all have sinned and fall short of the glory of God. They are justified freely by His grace through the redemption that is in Christ Jesus.”
ሁሉም ሰው ፣ አይሁድም ፣ አህዛብም ኃጢአትን ሰርተዋል ፡፡ በህይወታቸው ከተገለጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ ውጪ ሁሉም ኃጢአተኞች ነው ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ፣ እርሱ ለህዝቡ ሁሉ እቅድ አለው ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር ጸጋ በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ቤዛነት በነጻ እንድሁ ይጸድቃል ፡፡ ይህም ማለት ህግን ስለመጠበቅ መመካት አትችልም ፡፡ በተጨማሪም ስለ መልካም ስራዎችህ መመካት አትችልም ፡፡
አንተ የኃጢአት ደመወዝ ከሆነው ከሞት ትድን ዘንድ ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞተ ፡፡ ኢየሱስ በአንተ ቦታ ሞተ ፡፡ እርሱ ጽድቅህ ነው ፡፡ ሁሉም ኃጢአትን ሰርተዋልና ኢየሱስ በእምነት የሁሉም ጽድቅ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ለህዝቡ እቀድ አሳብ እንዳለው እመን ፡፡ እናም ኢየሱስ ጽድቅህ መሆኑ የእግዚአብሔር የመጨረሻ ፣ የፍቅርና የደግነት እቅድ አካል ነው ፡፡ በኢየሱስ ነጻነትን ፣ ጸጋንና ዘላለማዊ ህይወትን አግኝተሃል ፡፡
“ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል ፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ ። “ - ሮሜ 3፡23-24
ተጨማሪ ጥቅስ
- ሮሜ 3:21–22— “ አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል ፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና ፡፡ “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 5:21— “ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው ። “
- ያዕቆብ 4:17— “ እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።