The Temple Of The Lord
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Greater Temple Haggai 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ በጥናታችን ዘጠነኛዉ ክፍል ላይ ነን ! ቀጣይ በራዕይ መጽሐፋ እናጠናቅቃለን ፡፡ እስካሁን በዘጠን ታናናሽ ነቢያት ዉስጥ አልፈናል ፡፡ አብዛኞቻችን ብዙ ጊዜ እንዳላጠናን ለመገመት ፍቃደኛ ነኝ ፤ ዕብ (12፡ 26) በአዲስ ኪዳን ሐጌን የጠቀሰ ብቸኛዉ ስፍራ ነው ፡፡ ስለ ሐጌ ፀኃፊ ጥቂት ነገር የታወቀ ነው ፤ በዕዝ (5፡ 1 እና 6፡ 14) የተጠቀሰ በጠቸማሪም ሁለቱም ዘካሪያስንም ጠቅሰዉታል ፡፡ ስለ ሐጌ ስራ የተመዘገበ ነገር የለም በብሉይ ኪዳን በስሙ የተጠቀሰ ብቸኛዉም ሰው ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ሐጌ (2፡ 3) ከመጥፋቱ በፊት ሐጌ ስለ ሰለሞን ቤተ መቅደስ ክብር አይቶ እንደ ነበር እንደሚያመለክት ይህን መልዕክት በሚፅፍ ጊዜም ቢያንስ 70 አመት እድሜ እንደሚያደርገው “ ይናገራል ፡፡ በሐጌ ዉስ ለኢየሱስ ሐረጋችን/ቃላችን የሚበልጠዉ ቤተ መቅደስ የሚል ነው ፡፡
የሐጌ ትንቢት በፋርስ ንጉስ በዳርዮስ በሁለተኛዉ አመት በአራት ወር የጊዜ መዋቅር ዉስጥ ተፈፀመ/ሆነ (ከክርስቶስ ልደት 521-486 በፊት) ፤ ሐጌ ከዘሩባቤል ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ከ18 አመታት ቀደም ብሎ የሆነ ይመስላል ፡፡ ከምርኮ በኋላ ከክርስቶስ ልደት 583 በፊት እስራኤል በዘሩባቤል ሲቪል መሪነት እና በኢያሱ መንፈሳዊ መሪነት ወደ ቤቱ እንዲመለስ ተፈቅዶለት ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ ከክርስቶስ ልደት 536 በፊት ቤተ መቅደሱን መልሰዉ መገንባት እንደ ጀመሩ ነገር ግን ከጎረቤቶቻቸዉ ተቃዉሞ እና በአይሁዶች ችላ ማለት ስራዉ የተተወ እንዲሆን ምክንያት እንደሆነ ፤ ከአስራ ስድስት አመታት በኋላ ሐጌ እና ዘካሪያስ በእግዚአብሔር ሕዝቡን 1) ቤተ መቅደሱን መልሰዉ እንዲሰሩ እና በተጨማሪም 2) ለመንፈሳዊነት ቅድሚያ መስጠትን እንዲያድሱ እንዲያነሳሱ የታዘዙ እንደ ነበሩ “ ይገልፃል ፡፡
በሐጉ ዉስጥ ፍሬ ነገሩ “ ቤተ መቅደሱን መልሰን እንገንባ “ የሚል ነው ፡፡ በእርግጥ ሐጌ ልክ እንደ መንፈሳዊ ኮንትራክተር/ተቋራጭ ነበር ፡፡ እግዚአብሔር መንፈሳዊ ነገርን ቅድሚያ ባለስጠታቸው ምክንያት እህላቸዉ እንዲወድቅ/እንዲጠፋ አድርጎ ርኃብን በማምጣት አነሳሳቸው ፡፡ ሁልጊዜ ቤተ መቅደሱ የእግዚአብሔርን መገኘት ይወክላል ፤ ይሁን እንጂ ቤተ መቅደሱ በጠፋ ጊዜ ሕዝቡ የእግዚአብሔር ክብር ተለይቷቸዉ እንደ ነበር ያምናሉ ፡፡ የቤተ መቅደሱ መልሶ መሰራት/መገንባት የእግዚአብሔርን መገኘት ወደ ኑሮአቸዉ ዉስጥ መልሶ ለመቀበል አስፈላጊ ነበር ፤ የቤተ መቅደሱ መልሶ መገንባት ወደ ሚበልጠዉ ቤተ መቅደስ አመልክቷል ፡፡ የሐጌን ጽኁፍ በተሸለ ለመረዳት እንዲረዳን በቤተ መቅደሱ ሂደት/ለዉጥ ላይ ማትኮር እፈልጋለሁ ፡፡
ማክአርቱር የመጽሐፍ ቅዱሱን ቤተ መቅደስ ዝርዝር ያስቀምጣል፡
- የድንኳኑ ማደሪያ በመጽኃፍ ዉስ የመጀመሪያዉ ቤተ መቅደስ የነበር እና ከክርስቶስ መወለድ 1444 በፊት አካባቢ ተሰራ (ዘጸ 25፡ 30, ዘሌ 10፡ 1-7) ፡፡
- የሰለሞን ቤተ መቅደስ በዳዊት ልጅ በንጉስ ሰለሞን ተሰራ (ከክርስቶስ ልደት 966-586 በፊት) ፤ ዳዊት የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ለመስራት ፈለገ ነገር ግን ይህን እንዲያደርግ ሰለሞንን መረጠው (2ሳሙ 7፡ 1-29) ፡፡
- የዘሩባቤል ቤተ መቅደስ በሐጌ እና በዘካሪያስ በሁለቱም የተተነበዬ ሲሆን ከክርስቶስ ልደት (516 -169 በፊት) መካከል የተሰራ ነበር (ዕዝ 3፡ 1-8) ፡፡
- የሄሮድስ ቤተ መቅደስ የዘሩባቤል ቤተ መቅደስ የጥገና እና የዕድሳት ፕሮጀክት ነበር (ከክርስቶስ መወለድ 19 በፊት - ከክርስቶስ ሞት 70 በኋላ) ፤ ይህ በሮም የጠፋ ነበር (ማር 13፡ 2, ዮሐ 2፡ 20) ፡፡
- የአሁኑ ቤተ መቅደስ በጊዜአዊነት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆነዉ የአማኞች ሰዉነት ፤ ያም በመሲሁ ተመልሶ መምጣት ይቀየራል (1ቆሮ 6፡ 19-20) ፡፡
- የራዕይ 11 ቤተ መቅደስ በታላቁ መከራ ጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚዉ/አዉሬዉ የሚቀመጥበት ስፍራ ነው (ዳን 9፡ 27, ማቴ 24፡ 15) ፡፡
- የሕዝቅኤል የሺዉ አመት ቤተ መቅደስ በሺዉ አመት ዉስጥ ይገነባል/ይሰራል ፡፡ በሕዝቅኤል መጽኃፍ ዉስጥ የተገለፀ ሲሆን በመሲሁ ይገነባል/ይሰራል (ሕዝ 40፡ 1- 42፡ 20) ፡፡
- የመገኘቱ የዘላለም ቤተ መቅደስ እስካሁን ከተሰሩት ቤተ መቅደሶች የሚበልጥ ሲሆን መንፈሳዊ ቤተ መቅደስም ይሆናል (ራዕ 21፡ 22) ፡፡
ይህን ሁሉ ለምን ገለጥን ? ምክንያቱም በትክክል ሐጌ ወደ ዘሩባቤል ቤተ መቅደስ እያመለከተ ስለነበርና በተጨማሪም ስለ ሕዝቅኤል/ስለ ዘላለማዊዉ ቤተ መቅደስ መግለጥ ጀምሮ ስለ ነበር ፡፡
ትምህርት
ሐጌ (1፡ 1-11)፡ ጄ.ቬርኖን ማክጊ ቁጥር (1-11) “ ለሕዝቡ ፈተናዎች “ እንደ ነበሩ ይገልፃል ፡፡ ሕዝቡ ቤተ መቅደሱ ፈራርሱ ተቀምጦ ሳለ በቁሳዊ ብልፅግናቸው ቤታቸዉ ተረጋግተዉ እየኖሩ ነበር ፡፡ ምናልባትም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሐጌ በቅዱስ ባዕላት ጊዜ እንዲያደርስ መጣ ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን መልሶ መስራታቸዉን ትተዉታል አለ ፤ ይልቁንም የሱ ቤት ፈርሶ በታሸጉ ቤቶቻቸው በምቾት መኖርን መረጡ (ቁጥር 1-4) ፡፡ ሐጌ እስራኤላዊያን በፍጹም ረክቶዉ እንዳልነበርና ሌላ ተጨማሪ እንደሚፈልጉ ገልፆአል ፡፡ እግዚአብሔር እንዲከበር ወደ ተራሮች በመሄድ መልሰው እንጨትን ይዘዉ በመመለስ ቤተ መቅደሱን መልሰዉ እንዲሰሩ ነገራቸው ፡፡ እግዚአብሔር ቤቱ ተመልሶ ተሰርቶ ስላልነበር በዘራቸዉ/በእህላቸዉ ላይ ጥፋትን አምጥቶ እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 9) ፡፡ እግዚአብሔር እህላቸዉን የገደለዉን ድርቅን በመፍጠር ጠልን ከእነርሱ ከለከለ (ቁጥር 10-11) ፡፡
ሐጌ (1፡ 12-15)፡ በሐጌ ቃል ዉስጥ የሆነ ነገር ሕዝቡን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ክበር እንደሚያስፈልጋቸው ወንጅሏቸዋል ፡፡ ንጉስ ዘሩባቤል፣ ታላቁ ካህን ኢያሱ እና በአጠቃላይ ቅሬታ የሆነዉ ሕዝብ ታዘዙ (ቁጥር 12) ፡፡ ሐጌ ሕዝቡን እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደ ነበር አሳሰባቸው ! እግዚአብሔርም የዘሩባቤልን፣ የኢያሱን እና የሁሉንም ሕዝብ መንፈስ አነሳሳ (ቁጥር 14) ፡፡ ያ ማለት የእግዚአብሔርን ቤት መልሶ ለመስራት የተነሳሱ ሆኑ ማለት እንደሆነ አስባለሁ ፡፡ “ በንጉሱም በዳርዮስ በሁለተኛዉ አመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን “ በአዲሱ ቤተ መቅደስ ላይ ስራቸዉን ጀመሩ (ቁጥር 15) ፡፡
ሐጌ (2፡ 1-9)፡ ከአንድ ወር በኋላ ሕዝቡ መልሶ በመስራት ስራዉ ተስፋ እየቆረጡ ነበር ፤ እግዚአብሔር ሐጌን በሌላ መልዕክት ላከዉ - የበረቱ እና የታዘዙ እንዲሆኑ (ቁጥር 1-4) ፡፡ እግዚአብሔር እንደ ገና ሕዝቡን መንፈሱ ከእነርሱ ጋር እንደ ነበር አስታወሳቸው/አሳወቃቸው (ቁጥር 5) ፡፡ የሰራዊት ሁሉ ጌታ እንደ ገና ሰማያትን፣ ምድርን፣ ባህርን እና በምድር ላይ ያለን ሕዝብ ሁሉ እንደሚያናዉጥ እና ወደ ቤቱም ክብርን እንደሚያመጣ ቃል ገባ (ቁጥር 6-7) ፤ ይህ የሺዉ አመት መንግስት መልክ ነው ፡፡ እግዚአብሔር አዲሱን ቤተ መቅደስ “ ከመጀመሪያዉ እንደሚበልጥ “ ገለፀው ማለትም ከዘሩባቤል ቤተ መቅደስ እንደሚበልጥ (ቁጥር 8-9) ፤ ይህ በራዕ (21፡ 22) ያለዉ የሚበልጠዉቤተ መቅደስ ጥላ ነበር ፡፡
ሐጌ (2፡ 10-19)፡ ከሰባት ወር በኋላ(በዘጠነኛዉ ወር) እግዚአብሔር እንደ ገና መልዕክቱን እንዲያደርስ ሐጌን ሰጠው ፡፡ መጀመሪያ እግዚአብሔር ሐጌን ለእርሱ ተለይቶ የነበረው ያልተቀደሰዉን ነገር ነከቶ የነበረ ቅዱስ እንደሚሆን ወይም ጠይቅ አለው ፤ መልሱም አይሆንም ነበር ፡፡ ሁለተኛዉ ጥያቄ ሬሳ በመንካት ረክሶ የነበረን ነገርን ነክቶ የነበረም የረከሰ ይሆናልን በማለት እንዲጠይቅ ነበር ፤ መልሱም አዎን ነበር ፡፡ ቅድስና አልተላለፈም ነገር ግን አለመቀደስ/መርከስ ተላልፏል ፡፡ ሐጌ የሕዝቡ ስራና ያቀረቡት ሁሉም ነገር ቅዱስ ስላልነበሩ የረከሰ እንደ ነበር ገለፀ ፤ ይሁን እንጂ በዚያን ቀን የቤተ መቅደስ መሰረት ስለጣሉና እግዚአብሔርን አክብረዉ ስለ ነበር እግዚአብሔር እንደሚባርካቸዉ ቃል ገባላቸው ፡፡ ምንም እንኳን በጎተራ ዘር ባይኖራቸዉም በዛፎች ላይ የሚያድግ ምንም ባይኖራቸውም እግዚአብሔር በብልጽግና ይባርካቸዋል ፡፡
ሐጌ (2፡ 20-23)፡ እግዚአብሔር የነገስታትን ዙፋን እንደሚገለብጥ እና የአሕዛብን መንግስት ኃይል እንደሚያጠፋ ቃል ገባ ፤ለሕዝቡም በዘሩባቤል መለኮታዊ መሪነትን ይሰጣል ፡፡
መደምደሚያ
ስለ ሐጌ በጣም የሚያስገርመዉ ነገር ወደ ቤተ መቅደሶቹ ዝርዝር መመለሱ ፤ ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን መገንባት አልፈለጉም ፡፡ ተጠቅመዉባቸዉ በነበሩት ባለፉት የምቾት ቀናቶች ወስጥ መቀመጥን ፈለጉ ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለመሄድ ራሳቸዉን በተነሱ ጊዜ የተሸለ እና የሚበልጥ ነገር ነበረው ፡፡ በመጨረሻም የምናየው እነዚህ ሁሉ ነገሮች ኢየሱስ በሚመለስ ጊዜ እንደሚመጡ ነው (ራዕ 21፡ 22) ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1042.
MacArthur, p. 1042.
MacArthur, p. 1042.
MacArthur, p. 1047.
J. Vernon McGee, “Outline of Haggai”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/haggai/haggai-outline.cfm.
ጥያቄዎች
-
በሐጌ ( 1፡ 1-2) ነቢዩ ሐጌ ለይሁዳ አስተዳዳሪ ለዘሩባቤል እና ለታላቁ ካህን ለኢያሱ መልዕክትን ከእግዚአብሔር ተቀበለ ፤ ሐጌ ሕዝቡ ምን እያለ እንደ ነበር ነገራቸው ? ሕዝቡ ምንን በማድረግ ቢዚይ ሆኖ ነበር (ሐጌ 1፡ 4, 9) ?
-
የእግዚአብሔር ቤት ችላ ተብሎ ሕዝቡ የራሱን ቤት እንዴት እየሰራ ነበር (ሕዝ 34፡ 2, 1ጢሞ 1፡ 3-4) ? (በአሁኑ ጊዜ ተመሳሳይ ሁኔታ የሚሆነው አንዳንድ ፓስተሮች የእግዚአብሔርን መንግስት መገንባት በመተው የራሳቸዉ አገልግሎት በሚገነቡ ጊዜ ነው) ፡፡
-
የእግዚአብሔርን ቤት መልሶ መገንባትን ችላ በማለታቸው የሕዝቡ ዉጤት ምን ነበር (ሐጌ 1፡ 6, 10-11) ? በአሁኑ ጊዜ የክርስቶስ አካል የሆነቸዉን ቤተ ክርስቲያንን ከመስራት ይልቅ የተለዬ “ መንግስትን “ በመገንባት ቢዝ በሆኑት ላይ ምን ዉጤትን ትመለከታላችሁ ? (ሮሜ 12፡ 5, 1ቆሮ 12፡ 12-27, ኤፌ 3፡ 6, 5፡ 23, ቆላ 1፡ 18)
-
ከይሁዳ መሪዎች እና ቅሬታዎች ከእግዚአብሔር ለሆነዉ መልዕክት ከሰጡት ምላሻቸዉ እንዴት ልንማር እንችላለን (ሐጌ 1፡ 12) ? ይህ ለእግዚአብሔር ቁጣ እና ቅጣት ምላሽ የምትሰጡበት ነው ?
-
በሐጌ (2፡ 4) ያለዉ የእግዚአብሔር መልዕክት እናንተን መናገር ቢጀምር እንዴት ይሰማችኋል ወይም ምላሽ ትሰጣላችሁ ?
-
በሐጌ (2፡ 9) ያለዉ ከእግዚአብሔር የሆነዉ ቃል ስለ መሲሁ መምጣት እና ስለ አዲሱ ኪዳን ትንቢታዊ መልዕክት ነዉ ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ?
-
በሐጌ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Haggai 2:18
“Consider carefully from this day forward; from the twenty-fourth day of the ninth month, from the day the foundation of the LORD’s temple was laid; consider it carefully.”
ነቢዩ ሐጌ ከባቢሎን ግዞት በኋላ ለህዝቡ ስለ አኗኗራቸው ተናገረ፡፡ እርሱም ቤተ መቅደሱ ከፈረሰ በኋላ መልሰው ይገነቡት ዘንድ አዘዛቸው፡፡ ነቢዩ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ” የሚለውን የእግዚአብሔርን ቃልም አጸና፡፡ እርሱም ህዝቡ አካሄዳቸው እንዴት እንደሆነ በጥንቃቄ እንድመረምሩ አሳሰባቸው፡፡ የእነርሱ በታማኝነት እና በመታዘዝ ለመኖር መወሰን ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ነበር ፡፡ እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ከመመለስ ይልቅ ለሌላ ነገር ቅድምያ ሰጥተው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለእነርሱ ትልቅ ቤተ መቅደስ አዘጋጅቶላቸው ነበር ነገር ግን ይህ እንዲሆን እነርሱ ወደ እግዚአብሔር መመለስና መንገዳቸውን በጥንቃቄ መመርመር ነበረባቸው ፡፡
ልክ ሐጌ ለእስራኤላውያን እንደተናገረው ሁሉ ፣ ለእናንተም እንዲሁ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሊባርካችሁና ሊመልሳችሁ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህም አካሄዳችሁን መርምሩ፡፡ በዚህ በፈተና የተሞላ እና ደግሞም ሰይጣን ሊያባብልና ሊያታልላችሁ በሚሰራበት ዓለም ውሰጥ እንዴት እንደምትኖሩ መጠንቀቅ አለባችሁ፡፡ በጸሎት እግዚአብሔርን ፈልጉ፡፡ ይገልጥላችሁ እና ያረጋግጥላችሁ ዘንድ ጸልዩ፡፡ በትህትና ተራመዱ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፡፡ እርሱ በእናንተ ውስጥ ፍቅሩን ያዲስ ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ኢየሱስ እርሱ ሰላም ነውና ሰላምን ይሰጣችኋል፡፡ ዛሬ ውሳኔያችሁን፣ ድርጊቶቻችሁን፣ ንግግራችሁን በጥንቃቄ ገምግሙ እናም አካሂያዳችሁን ከጌታ ጋር አድርጉ፡፡ ይህ ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ነው ፡፡ እርሱ ለእናንተ ከዚህም የበለጠ የላቀ ነገር አለው፡፡
“ ከዛሬው ከዘጠነኛው ወር ከሀያ አራተኛው ቀን ጀምራችሁ የሚመጣውን ዘመን ልብ አድርጉ፤ የእግዚአብሔር መቅደስ መሠረት ከተተከለበት ቀን ጀምሮ ልብ አድርጉ።”
- ሐጌ 2፡18
ተጨማሪ ጥቅስ
ሐጌ 2:9 — “ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡”
ሐጌ 2:15–17 — “አሁንም ድንጋይ በድንጋይ ላይ በእግዚአብሔር መቅደስ ሳይነባበር፥ ከዛሬ ጀምራችሁ ወዳለፈው ዘመን ልብ አድርጉ።በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፤ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ላይ በዋግና በአረማሞ በበረዶም መታኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡”
ኤፌሶን 5:15–17 — “እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።