Zechariah's Vision
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Pierced One Zechariah 1-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ ጥናታችንን በዘካሪያስ እንጀምራለን ፡፡ በዚህ ሳምንንት ይህ አራተኛዉ አዲስ መጽኃፍ ነው ! አብዛኞቹ ምሁራን መጽኃፉ በጸኃፊዉ በነቢዩ ዘካሪያስ እንደ ተሰየመ ይቀበላሉ ፡፡ ዘካሪያስ የሚለዉ ስም በብሉይ ኪዳን ከ29 ሰዎች በላይ ላይ ጥቅም ላይ ዉሎ የነበር እና ትርጓሜዉም “ እግዚአብሔር ያስታዉሳል/አይረሳም “ ማለት ነው ፡፡ ማክአርቱር ዘካሪያስን “ ስለመሲሁ በስፋት በመፃፍ ከኢሳይያስ ቀጥሎ ሁለተኛ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ በዘካሪያስ ዉስጥ ስለ መሲሁ በጣም ብዙ ነገር አለ ፡፡
ማክአርቱር ኤርምያስ እና ሕዝቅኤል እንደ ነበሩት ዘካሪያስ ካህን እንደ ነበር ያመለክታል፡ “ በቀደምት ጽሁፎች መሰረት የታላቁ ምኩራብ አባል ነበር፣ በነህምያ የተጀመረዉ እና በዕዝራ ይመራ የነበረው የ120 መማክርት አባል ነበር ፡፡ በኋላም ይህ መማክርት ሳንሄድሪን/ሸንጉ ተብሎ ወደሚጠራው የሕዝብ መሪ ሽማግሌዎች አድጓል “ ፡፡ ዘካሪያስ በባቢሎን ተወለደ አያቱን ባካተተዉ በመጀመሪያዉ ከምርኮ ከተመለሰዉ ቡድን ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ ፤ አንዳንድ ምሁራን የዘካርያስ አባት በራክዩ በወጣትነት እድሜዉ እንደ ሞተ እና በፍጹም እንደ ካህን በአባቱ ስፍራ በመተካት እንዳልተከተለ ያመለክታሉ ፡፡ የዘካሪያስ መጽኃፍ በስትክክል በዳርዮስ ሁለተኛ አመት ከክርስቶስ ልደት 520 በፊት እንደተፃፈ በዘካ (1፡ 1) ተቀምጧል ፡፡ ዘካሪያስ ሐጌ በነበረበት በተመሳሳይ ጊዜ ነቢይ ነበር ነገር ግን ከሐጌ የሚያንስ ነበር (ዘካ 2፡ 4) ፡፡ ዘካሪያስ እንደ ነቢይ ለምን ያክል ጊዜ እንዳገለገለ የሚታወቅ መረጃ የለም ፤ (ዘካ 7፡ 4) የተቀመጠው የመጨረሻው ትንቢቱ ከመጀመሪያዉ ትንቢቱ ሁለት አመት ያክል ከቆዬ በኋላ የተሰጠ ነበር ፤ ስለዚህ ሁለቱም ትንቢቶቹ የሐጌ ትንቢት ተሰጥቶ በነበረበት በተመሳሳይ ጊዜ የተሰጡ ነበሩ ፡፡
ከክርስቶስ ልደት በ538 በፊት በፋርስ አገዛዝ በቂሮስ ስር 50,000 ምርኮኞች ከባቢሎን ወደ እስራኤል እንዲመለሱ ተፈቀደላቸው ፡፡ በዚያም የተመለሱት ምርኮኞች በኢየሩሳሌም የቤተ መቅደሱን መልሶ ግንባታ ስራ ጀመሩ ፤ ቤተ መቅደሱ ከክርስቶስ ልደት 516 በፊት ተጠናቀቀ ፡፡ ማክአርቱር “ ዘካሪያስ እና ሐጌ ቤተ መቅደሱን መልሰዉ እንዲገነቡ ሕዝቡን እንዲያነሳሱ በእግዚአብሔር ታዘው እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡
ማክአርቱር ሁለቱን ነቢያቶች አወዳድሯቸዋል፡
“ የሐጌ የመጀመሪያ አላማ ቤተ መቅደሱን መልሶ መስራት ነበር፣ ስብከቱ የሕዝቡን ግዴለሽነት፣ ኃጢዓት እና በእግዚአብሔር አለመታመንን የመገሰፅ ድምፅ አለው ፤ ለመጀመር መነሳሳት/መነቃቃትን የተጠቀመ ሲሆን ዘካሪያስ በብዙ አዎንታዊ ማብራሪያዎች ሕዝቡን ወደ ንስኃ በመጥራት የወደፊቱን በረከት እንደ ገና በማረጋገጥ በመጠንከር እንዲቀጥሉ ለማበረታታት ጥቅም ላይ የዋለ ነበር “ ፡፡
ዘካሪያስ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ በጣምራዕያዊ የሆነ መጽኃፍ ሲሆን በተጨማሪም ስለሚመለሱ ምርኮኞች እንዲሁም ስለ ወደፊቱ መልዕክት ነበረው ፡፡
ትምህርት
ዘካሪያስ (1፡ 1-6)፡ እግዚአብሔር በዘካሪያስ አባቶች ተበሳጭቶ ስለ ነበር ወደ ነቢዩ ዘካሪያስ መጣ (ቁጥር 1-2) ፡፡ እግዚአብሔር እርሱ ወደ እነርሱ መመለስ ስለሚችል ወደ እርሱ እንዲመለሱ ሕዝቡን ተጣራ (ቁጥር 3) ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ እርሱ ለመመለስ የነቢያቶችን ማስጠንቀቂያ ያልተከተሉትን አባቶቻቸዉን እንዳይመስሉ ነገራቸው (ቁጥር 4) ፤ እግዚአብሔር አባቶቻቸዉ የት እንደ ነበሩና አለቀበል ያሉትን መልዕክት አድርሰዉ የነበሩት ነቢያቶች የት እንደ ነበሩ ጠየቀ (ቁጥር 5) ሁሉም ሞተዉ ነበር ፡፡
ዘካሪያስ (1፡ 7-11)፡ በቁጥር 7 ቋንቋዉ/ንግግሩ በመቀየር ዘካሪያስ በአንድ ምሽት የነበሩትን ራዕዮቹን መግለጽ ጀመረ ፡፡ ራዕይ ሰፊ/ጥልቅ እንቀልፍ ሲሆን እንደሚሆን እና ሕልም ደግሞ በሚተኛ ጊዜ እንደሚሆን እናስታዉሳለን፡፡ በራዕይ እግዚአብሔር ዘካሪያስን በፊቱ የሆነ ነገር ሲሆን አሳየው ፤ እነዚህ ራዕዮች ለሕዝቡ መጽናናትን ያመጣሉ ተብለዉ የታሰቡ ነበሩ ፡፡ የመጀመሪያዉ ራዕይ አንድ ሰው በባርሰነት ዛፎች ስር መጋላ ፈረስን ጋልቦ ነበር ፤ ከሰዉዬዉም በኋላ መጋላ፣ ሐመር እና አንባላይ ፈረሶች ነበሩ (ቁጥር 7-8) ፡፡ ማክአርቱር “ ቀለማቸዉ የጋላቢዎቹን ስራ እንደሚናገር፡ መጋላ/ቀይ ስለ ደም መፍሰስ እና ፍርድ እንደሚናገር፣ አንባላይ/ነጭ ስለ ድል እንደሚናገር እና ምናልባትም ሐመር የሌሎች ዉህደት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ዘካሪያስ እያዬዉ ስለ ነበረዉ ነገር ጠየቀ መልአኩም እንግርኃለሁ/እገልጽልኃለሁ አለው (ቁጥር 9) ፡፡ በቀዩ/በመጋላው ፈረስ ላይ ተቀምጦ የነበረዉ ሰዉዬ ፈረሶቹ ምድርን ሁሉ እንዲዞሩ በእግዚአብሔር የተላኩ እንደ ነበሩ ነገረው (ቁጥር 10) ፤ ማክአርቱር “ በአለማቀፍ ደረጃ እንደ ወታደራዊ አሰሳ እና ፍተሻ መገለጫ የመለዓክቱን እንቅስቃሴ በመወከል ፤ አላማዉም የጠላትን መንግስት/ግዛት ማረጋገጥ እና በጠላት ድል ላይ በመዉጣት ለእግዚአብሔር ፍቃድ ምላሽ መስጠት እንደ ሆነ “ ይገልፃቸዋል ፡፡ ለእግዚአብሔር መለዓክት (ምናልባት ስጋከመልበሱ በፊት ለክርስቶስ) አጠቃላይ ምድር ተረጋግታ እና ፀጥ ብላ እንደ ነበር ሪፖርት አደረጉ (ቁጥር 11) ፡፡ በዚህ ራዕይ ዉስጥ እግዚአብሔር ለእስራኤል ብልጽግናን ቃል ገባ ፡፡
ዘካሪያስ (1፡ 12-17)፡ የእግዚአብሔር መለዓክ እግዚአብሔርን ይሁዳን አለመማሩን እስከመቼ እንደሚቀጥል ጠየቀው (ቁጥር 12) ፤ ለመለዓኩም እግዚአብሔር በሚያጽናና ቃል መለሰለት (ቁጥር 13) ፡፡ ይህ ክርስቶስ ስጋ ከመልበሱ በፊት በኢየሱስ እና በአባቱ በእግዚአብሔር መካከል የተደረገ መስተጋብር/ንግግር ነው (ሮሜ 8፡ 34, ዕብ 7፡ 25) ፡፡ እግዚአብሔር አሁንም ይሁዳን እና ኢየሩሳሌምን እንደሚወዳቸዉ እና በእነርሱም ላይ መጥተዉ በነበሩት ሕዝቦችም እንደተበሳጨ ገለፀ (ቁጥር 14-15) ፡፡ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር መልሶ ወደ ኢየሩሳሌም እና ወደ ከተማዉ በጺዎን ላይ ብልጽግናን ያመጣል (ቁጥር 16-17) ፡፡ የባርሰነት ዛፎች ለዳስ በዓል ከሚዉል ጎጆ ጋር ግንኙነት ስለ ነበራቸው ይህ ራዕይ የእግዚአብሔርን የቀጠለ በረከት እና በሕዝቡ ላይ ያለዉን ጥበቃ ያመለክታል ፡፡ በኢሳይያስ 41 እና 55 የባርሰነት ዛፍ ከመሲሁ በረከትም ጋር የተገናኜ ነበር ፡፡
ዘካሪያስ (1፡ 18-20)፡ ሁለተኛዉ ራዕይ “ የኃይል እን የትዕቢት ምልክት “ ስለ ነበሩ ስለ አራት ቀንዶች ነበር ፤ ዘካሪያስ በእስራኤል ላይ ሁሉ የተበተኑ ምናልባትም ባቢሎንን፣ ሜደን -ፋርስን፣ ግሪክን እና ሮምን የሚያመለክቱ ቀንዶች እንደነበሩ ተነገረው (ቁጥር 18-19) ፡፡ ከዚያም ዘካሪያስ ይሁዳን በታትነዉ የነበሩትን ሕዝቦች ለማስፈራራት መጥተዉ የነበሩ አራት ጠራቢ ሰዎች ታዩት (ቁጥር 20-21) ፤ በዚህ እግዚአብሔር እስራኤልን ያጠቁትን ሕዝቦች እንደሚፈርድባቸዉ ቃል ገባ ፡፡
ዘካሪያስ 2፡ ሰዎስተኛዉ ራዕይ የመለኪያ ገመድን ስለያዘ አንድ ሰዉ ነበር (ቁጥር 1-3) ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር እቅድ ኢየሩሳሌምን መልሶ እንደሚሰራ እና መልሶ እንደሚያቋቁም እና እግዚአብሔር በዚያ እንደ ገና እንደሚያድር የሚያሳይ ነበር (ቁጥር 10-16) ፡፡
ዘካሪያስ 3፡ አራተኛዉ ራዕይ ስለ ታላቁ ካህን እና ስለ ቅርንጫፍ ነበር (ቁጥር 1-7) ፡፡ ይህ እግዚአብሔር በታላቁ ካህን እና በእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር እንደታደጋቸዉ የሚጠቀምበትን መንፃት ያሳያል (ቁጥር 8) ፡፡ ማክጊ “ ኢያሱም ሆነ እስራኤል የራሳቸዉን ጽድቅ እንደለበሱ በሰይጣን ተቃዉሞ ደርሶባቸዉ እንደ ነበር ፤ የክርስቶስን ጽድቅ መልበስ እንዳለባቸው ፤ በአሮጌዉ ልብስ ላይ አዲስ ልጣፍ እንኳን ብቁ እንደማይሆን “ ይገልፃል ፡፡ “ ቅርንጫፉ አገልጋዬ “ ለኢየሱስ ሌላ ማሳያ ሲሆን (ቁጥር 8) ቁጥር 10 የሚመጣዉን እድሜ ያመለክታል ፡፡
ዘካሪያስ 4፡ አምስተኛዉ ራዕይ እግዚአብሔር በዘሩባቤል ቤተ መቅደሱን መልሶ እንደሚገነባዉ ስለሚያሳይ የወርቅ መቅረዝ እና ስለ ሁለት የወይራ ዛፎች ነበር (ቁጥር 1-7) ፡፡
መደምደሚያ
ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር እቅድ መልሶ ይቋቋማል ፡፡ ዘካሪያስ (12፡ 10) “ በዳዊት ቤት ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ “ ይላል ፡፡ በቀረዉ በዘካሪያስ መጽኃፍ ዉስጥ ስንጓዝ ያንን እንገልጠዋለን ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1049.
MacArthur, p. 1049.
MacArthur, p. 1049-1050.
MacArthur, p. 1050.
MacArthur, p. 1053.
MacArthur, p. 1053.
MacArthur, p. 1052.
MacArthur, p. 1054.
J. Vernon McGee, “Outline of Nahum,” available at https://www.blueletterbible.org/Comm/mcgee_j_vernon/notes-outlines/nahum/nahum-outline.cfm.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሔር በዘካ (2፡ 5) “ እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ በዉስጥዋም ክብር እሆናለሁ “ ማለቱ ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ራዕ 21፡ 23, 22፡ 5)
-
ዘካ (2፡ 8) አንብቡ፡ “ የሚነካችሁ የአይኔን ብሌን የሚነካ ነው “ ፤ ብዙ ሰዎች እንድ እግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ ቤተ ክርስቲያን አይሁድን እንደተካች ያምናሉ ፤ የሚያምኑት እዉነት ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በዘካ (2፡ 10-11) እግዚአብሔር ሕዝቡን እየመጣ እንደ ነበርና በመካከላቸዉ እንደሚኖር ነገራቸው ፤ ይህ ወደ ሕዝቡ የመሲሁን በአካል መምጣት ቀድሞ እየተናገረ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ኢሳ 7፡ 14, 9፡ 6, ማቴ 1፡ 23, ዮሐ 1፡ 1, 14)
-
በዘካ (3፡ 3) በመለዓኩ ፊት ቆሞ እንደ ነበር ታላቁ ካህን ኢያሱ የቆሸሸ ልብስን ለብሶ ነበር ፤ ዘካር (3፡ 4) እና ኢሳ (64፡ 6) አንብቡ ፤ ዕነዚህ የቆሸሹ ልብሶች ይወክላሉ/ያመለክታሉ ?
-
በዘካርያስ (3፡ 8) መሰረት ታላቁ ካህን ኢያሱና ጓደኞቹ ምልክት ከነበሩ ምንን ይወክሉ/ያመለክቱ ነበር ?
-
በዘካ (4፡ 14) በእግዚአብሔር አጠገበ ቆመዉ የነበሩት ሁለቱ የተቀቡት እነማን እንደ ነበሩ ምን ታስባላችሁ ? (ዘካ 4፡ 2-3, 11-14, ራዕ 11፡ 1-4)
-
በዘካርያስ (1-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Zechariah 3:5–7
“Then I said, ‘Let them put a clean turban on his head.’ So a clean turban was placed on his head, and they clothed him in garments while the Angel of the LORD was standing nearby. Then the Angel of the LORD charged Joshua: ‘This is what the LORD of Hosts says: If you walk in My ways and keep My instructions, you will both rule My house and take care of My courts; I will also grant you access among these who are standing here.’”
እስራኤል ከግዞት ከተመለሰ በኋላ ፣ የእግዚአብሔር ቃል በራዕዮች ወደ ነቢዩ ዛካርያስ መጣ፡፡ ዘካርያስም በራዕይ ታላቁ ሊቀ ካህን እያሱ የጎደፈ ልብስ ለብሶ በህዝቡ ፊት ቆሞ ተመለከተ ፣ ይህም የእስራኤላውያንና የልነጻ ኃጢአታቸው ምልክት ነበር፡፡ ከዚያም ኢያሱ ንጹህ ልብስን ተቀበለ፡፡ ዘካርያስም ይህ የተስፋና የመመለስ ምልክት እስራኤላውያን አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረጉ እንደሚሆንላቸው ተናገረ፡፡ ዘካርያስ ህዝቡ ቤተ መቅደሱን እንደገና ሲሰሩ በፍጹም ልባቸው እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ ተናገራቸው፡፡
ኢየሱስ ስለ መተላለፋችሁ ደቋል፤ የእርሱም ጸጋ ዕድፋሙን ልብሳችሁን፣ ኃጢአታችሁንና በደላችሁን ያጥባል፡፡ ማንም ኢየሱስን አዳኝ አድርጎ የሚቀበልና ራሱን በማዋረድ ኃጢአቱን የሚናዘዝ ይቅርታን ያገኛል፡፡ ከዚያም ጌታ ያለምንም ዋጋ በነጻ የጸድቅን መጎናጸፊያ ይሰጣችኋል፡፡ ስለዚህም በእምነት በትህትና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡና የእርሱን ጸጋና ምህረት ተቀበሉ፡፡ አዲሱ ልብስ የሚደረብላችሁ በቆሸሸው በአሮጌው ላይ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ፈጽሞ ዕድፋሙን የኃፍረትና የበደል ልብስ ያስወግዳል፡፡ እናንተ የንጉሥ ልጆች፣ ወራሾች ናችሁ ደግሞም ከእግዚአብሔር ከአብ ጋር ግንኙነት አላችሁ፡፡ ውዶች ብሎ ይጠራችኋል፡፡ እርሱ ይወዳችኋል፡፡ ዛሬ በላያችሁ ላይ በጥንቃቄ የተጠመጠመ ንጹህ ነጭ መጎናጸፊያ እንዳለ እያሰባችሁ፣ የእርሱን ስጦታ ተቀበሉ፡፡
“ ደግሞ፦ ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉ አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር።የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያሱ እንዲህ ሲል አዳኘበት።የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።”
ዘካርያስ 3፡5-7
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዘካርያስ 3:3–4 — “ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው። እርሱንም፦ እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው።”
- ገላትያ 2:20 “ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።”
- ራዕይ 19:8 — “ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።