Receiving The Prophetic Word
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Pierced One Zechariah 5-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የዘካሪያስ መጽኃፍን በማስተማር ዉስጥ በትንሹ በሌላ አቅጣጫ ማስፋት እፈልጋለሁ ፡፡ የሪቫይቭ ት/ቤት ሀሳብ/አላማ ኢየሱስ እንዴት እንደሚታይ በተለይም በብሉይ ኪዳን መጽኃፍ በእያንዳንዱ መጽኃፍ መግለጥ ነው ፡፡ በዘካሪያስ በአጠቃላይ በመጽኃፉ ዉስጥ ኢየሱስን እንደ ተወጋው እናየዋለን ፡፡
ዘካ (1፡ 1-6) ደግማችሁ አንብቡት ፤ ይህ ሁሉም ነቢያቶች ሁለቱም ታላላቅ እና ታናናሽ ነቢያቶች ስለሚመጣዉ የእግዚአብሔር ፍርድ እና ስለ ወደፊቱ ተስፋ አመልክተዋል ፡፡ የዘካሪያስ የመጀመሪያዎቹን አምስት ራዕዮች አይተናል፡
- ዘካሪያስ አንድ ሰዉ በባርሰነት ዛፍ ስር መጋላ ፈረስን ምድርን ከሚዞሩ አራት ፈረሰኞች ከመጋላ፣ ከሀመር እና ከአባላይ ፈረሶች ጋር ጋልቦ አየው ፡፡ ሰላማቸዉ በሕዝቡ ላይ የተፈጠረ ስለ ነበር እግዚአብሔርን ደስተኛ ያላደረገ ሰላምን በመላዉ ምድሪቱ ላይ አገኙ (ዘካ 1፡ 7-8) ፡፡
- ዘካሪያስ አራት ቀንዶችን እና አራት ጠራቢዎችን አዬ (ዘካ 1፡ 18-20) ፡፡
- ዘካሪያስ መለኪያ ገመድን የያዘ አንድ ሰዉ አዬ (ዘካ 2፡ 1-3) ፡፡
- ዘካሪያስ ታላቁን ካህን እና ቅርንጫፍን አዬ (ዘካ 3፡ 1-8) ፡፡
- ዘካሪያስ የወርቅ መቅረዝን አዬ (ዘካ 4፡ 1-14) ፡፡
ዘካሪያስ በግልፅ ወደፊቱ ተስፋ ያመለክታል ፡፡ ዘካ (12፡ 10) ኢየሱስን እንደ ተወጋ ያመለክታል፡ “ በዳዊትም ቤት ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል ሰዉም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኃዘን ያዝኑለታል “ ፡፡
ትምህርት
ዘካርያስ (5፡ 1-4)፡ የዘካሪያስ ስድስተኛዉ ራዕይ ስለሚበርር የመፅኃፍ ጥቅል ነበር ፡፡ ጥቅሉም እርዝመቱ 30 ጫማ ስፋቱ ደግሞ 15 ጫማ ሲሆን በአየር ላይም እየተንሳፈፈ ነበር ፤ ዘካሪያስ ይህ ምን እንደ ነበር ጠየቀ ፡፡ ጥቅልሉም ኃጢዓት ሰርተዉ የነበሩትን እና በኃሰት ይምሉ የነበሩትን ስም እና የሚመጣዉን የእግዚአብሔርን እርግማን በማመልከት ዘርዝሯል ፡፡ ጥቅሉ ወደ ቤታቸዉ በመግባት ሙሉ በሙሉ ያጠፋል ፡፡
ዘካርያስ (5፡ 5-11)፡ የዘካሪያስ ሰባተኛዉ ራዕይ ኢፍ ስለመስፈሪያ ቅርጫት ነበር ፡፡ እንደ ገና ዘካሪያስ ምን እንደ ነበር ጠየቀ ፡፡ መለዓኩ የሕዝቡን ክፋት/መርገም ክፉዎችን የምትወክለዉን በኢፍ መስፈሪያዉ ቅርጫት ዉስጥ የተቀመጠችዉን አንዲት ሴት ለመግለጥ የእርሳሱን መክደኛ አነሳው ፡፡ መለዓኩ ሴቲቱን መልሶ ወደ ኢፍ መስፈሪያዉ ቅርጫት ዉስጥ በመግፋት መልሶ ሸፈናት ፤ ከዚያም ሁለት ሴቶች የኢፍ መስፈሪያዉን ቅርጫት በሰማይ እና በምድር መካከል ባነሳው የሽመላ ክንፍ በሚመስል ንፋስ ተጠጉ ፡፡ የኢፍ መስፈሪያዉን ቅርጫትም በምሰሶ ላይ እንደ ተቀደሰ ስፍራ የተቀመጠ እንዲሆን ወሰዱት ፡፡ ከምድሪቱ ላይ ክፋትን እያስወገዱ እና እያራቁ ነበር፡፡
ዘካርያስ (6፡ 1-8)፡ እነዚህ ተኝቶ ያለማቸው ህልሞች ሳይሆኑ ዘካሪያስ እያንቀላፋ እንደ ነበር ያያቸዉ ራዕዮች ነበሩ፡፡ ኢዮ (33፡ 14-17) “ እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል ፤ ሰዉ ግን አያስተዉለዉም ፡፡ በሕልም በሌሊት ራዕይ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ በዚያን ጊዜ የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል በተግሳጹም ያስደነግጣቸዋል ሰዉን ከክፉ ስራው ይመልሰው ዘንድ ከሰዉም ትዕቢትን ይሰዉር ዘንድ “ ፡፡
በመጽኃፍ ላይ ስለ ህልም ብዙ ምሳሌዎች አሉ፡ ዮሴፍ የፈርዖንን ህልም ተረጎመ፣ ዮሴፍ የናዝሪቱ የኢየሱስን ደህንነት እንዲጠብቅ ወደ ግብፅ እንዲሸሽ የተጠነቀቀ ነበር፣ ዳንኤል በንጉስ ናቡከደነፆር ፊት የወሰደዉ ህልም ነበረው ፡፡ ዘካሪያስ እነዚህን ስምንንቱንም ራዕዮች በአንድ ምሽት ተሰጠው ፡፡
የመጀመሪያዉ ራዕይ በዘካርያስ 1 ስለ አራት ሰረገሎች እና ፈረሶች ነበር፣ ስምንተኛዉና የመጨረሻው ስለ ተመሳሳይ ነገር ነበር ፡፡ ከነሀስ በተሰሩ ሁለት ተራሮች መካከል አራት ሰረገላዎች ሲመጡ አዬ ፤ እያንዳንዳቸው ሰረገሎች የተለያዬ ቀለም/መልክ ነበራቸው - የመጀመሪያው በመጋላ፣ የሁለተኛው ጥቁር፣ የሰዎስተኛው ነጭ/አምባላይ እና የአራተኛው በቅጠላቅጠል ፈረሶች ፡፡ እነዚህ ከጌታ ፊት ከቆሙበት በኋላ ወደ አለም ሁሉ የወጡ አራት የሰማይ መናፍስት ነበሩ ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሔር በህልም፣ በራዕይ እና በትንቢታዊ ቃል እግዚአብሔር እናንተን መናገር እንዲጀምር ለማወቅ የሚያስፈልጓችሁን ሰባት ተግባራዊ ነገሮችን እንድንመለከት እፈልጋለሁ፡
የጌታን ቃል ለመቀበል ክፍት መሆን (ዘካ 1፡ 7-8, 4፡ 1) ፡፡ ዘካሪያስ እግዚአብሄር ይለዉ የነበረዉን ቃል ለመስማት ፍቃደኛ ነበር ፤ ተመልሶ ለመተኛት አልሄደም ፡፡
ክፍት የሆነ ተቀባይ መሆን ፡፡
ስለ እግዚአብሔር ቃል ለመጠየቅ በሚገባ ትሁት መሆን (ዘካ 1፡ 9) ፡፡ ዘካሪያስ ስላየዉ ነገር ምን ማለት እንደሆነ ለመጠየቅ አላመነታም ፡፡
ትሁት ጠያቂ መሆን ፡፡
የእግዚአብሔርን ቃል ለመመዝገብ ታማኝ መሆን (ዘካሪያስ 1-6) ፡፡ ዘካርያስ ሁሉንም ነገር በሙሉ ዝርዝር በጥንቃቄ ፅፏል ፡፡
ታማኝ መዝጋቢ/ፀኃፊ መሆን ፡፡
ለቃሉ እዉነተኛ መሆን (ዘካ 5፡ 1-4) ፡፡ አለመጨመር፣ አለመቀነስ ወይም ደግሞ አለማስጌጥ ፤ ዘካርያስ እንዴትም ተቀባይነት ቢሆንም በስትክክል ሪፖርት አደረገ ፡፡
የተመሰገን አድራሽ መሆን ፡፡
ስለመሲሁ ቃል ጠንቃቃ መሆን (ዘካ 6፡ 9-14) ፡፡ ዘካሪያስ ስለሚመጣዉ መሲህ ትንቢታዉ ቃልን በማድረስ ይመጣ ስለነበረው ነገር አወጀ ፡፡
ንቁ/ጠንቃቃ ምስክር መሆን ፡፡
የቃሉን ተግባራዊ አፈፃፀም አስተዋይ መሆን (ዘካ 5፡ 17 -7፡ 1-6, 9-10) ፡፡ ትንቢታዊ ቃል ተግባራዊ አፈፃጸም አለው ፡፡ ተግባራዊ በሆኑ ትንቢታዉ ቃሎች ጠንቃቃ መሆ ፡፡
በተግባር የተገለፀ/ተግባራዊ ነቢይ መሆን ፡፡
ህይወት ተናጋሪ መሆን ! ሕይወትን መናገር ፡፡ ያ የእግዚአብሔር ተስፋ መበልፀግ የሚጀምርበት ስፍራ ነው፡፡
ህይወትን የሚናገር መሆን ፡፡
የምዕራፉ የቀረዉ ክፍል እግዚአብሔር ምድሪቱን እንደሚፈዉስ፣ እድላቸዉን እንደሚታደስ እና ልጆች እንደ ገና በመንገድ ላይ እንደሚሮጡ/እንደሚጫወቱ ይናገራል ፡፡ በዚህ እንደሚመላለስ ልበ ክፍት፣ ትሁት፣ ታማኝ፣ ተግባራዊ፣ እዉነተኛ እና ሕይወት ተናጋሪ ሁኑ ፡፡
ጥያቄዎች
-
የዘካርያስ የመጨረሶቹ ሰዎስት ራዕዮች ትርጓሜ ምን ነበር ? (ዘካ 5፡ 1-6፡ 8)
-
ዘዉዱ በኢያሱ ራስ ላይ ከተቀመጠ በዘካ (6፡ 12) ለቅርንጫፍ/ለቁጥቋጦው ማጣቀሻ የሚሆነዉ ማነው ? (ኢሳ 11፡ 1, ዘካ 3፡ 8, ዮሐ 12፡ 13-15, 1ጢሞ 6፡ 13-16)
-
በዘካ (6፡ 12-15) ስለ መሲሁ የተሰጡት አንዳንድ እዉነታዎች ምንድን ናቸው ?
-
በዘካ (6፡ 13) ቁጥቋጦው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንደሚገነባ ተስፋ ተገብቷል ፤ ሁለተኛዉን የምድራዊዉን ቤተ መቅደስ ግንባታ/ስራ ማን ጨረሰው፣ የሺዉ ዘመን ቤተ መቅደስንስ ማን ይሰራዋል/ይገነባዋል ? (ኢሳ 2፡ 2-4, ሐጌ 2፡ 6-9, ዘካ 4፡ 9-10)
-
በዘካርያስ 8 የኢየሩሳሌም ከተማ እንዴት የተገለጠች/የታወቀች ነች (ዘካ 8፡ 3, 8,16) ? ኢየሩሳሌም በእነዚህ ነገሮች መቼ የተጠራች ትሆናለች ? ልክ እንደተባለዉ ከተማዋ በእነዚህ ለምን ተገለጠች/ታወቀች ? (ኢሳ 6፡ 3, ዮሐ 14፡ 6)
-
በዘካርያስ (5-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Zechariah 8:19
“The LORD of Hosts says this: The fast of the fourth month, the fast of the fifth, the fast of the seventh, and the fast of the tenth will become times of joy, gladness, and cheerful festivals for the house of Judah. Therefore, love truth and peace.”
ዘካርያስ እንደ ነቢይ ከግዞት ከተመለሱ በኋላ በእስራኤል ላሉ በእግዚአብሔር ለተመረጡት ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር በህልሞችና በራዕዮች ትንቢታዊ የሆኑ የፍርድ ደግሞም እንዲሁ የበረከትና የተስፋ መልዕክቶችን ሰጠው፡፡ ህዝቡ በግዞት ሆነው በሚጾሙበት ጊዜ እግዚአብሔር ልባቸው እንደ ዓለት ጠንካራ እንደሆነ አይቶ ነበርና እንዲህ ይጠይቃቸዋል “ በውኑ ለኔ ጾም ጾማችሁልኝን? እግዚአብሔር ቅሬታዎቹን በመታዘዝ እንድራመዱና ለእግዚአብሔር በመገዛት በንጹህ ልብ እንድጾሙ ያዛቸዋል፡፡ ይህንንም ሲያደርጉ ደስታንና ሀሴትን እንደሚያገኙ ቃል ይገባላቸዋል ፡፡
ጾም ልባችሁን፣ አሳባችሁንና ነፍሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት እንድታነጹ ያበረታችኋል፡፡ ጾም በህይወታችሁ ውስጥ ያሉትን ተጨማሪ ነገሮች እንድትተው በማድረግና ብርታትን ፣ የመንፈስ ጥንካሬንና ተስፋን እንድታገኙ ከልባችሁ በእግዚአብሔር ላይ ትኩረትን እንድታደርጉ በማድረግ ወደ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንድትገቡ ያደርጋችኋል፡፡ ዛሬ ስለ ጾም ጸልዩ፡፡ አሳባችሁን ፍላጎታችሁን ሁሉ ለጾም ንጹህ አድርጉ፣ ከዚያም በመታዘዝ ጾማችሁን ጀምሩ፡፡ ክብደት ለመቀነስ አትጹሙ፤ ጊዜያችሁን በደንብ ለመጠቀም ወይም የሆነን ሰው ለማስደሰት አትጹሙ፡፡ በንጹህና በታዛዥ ልብ ጹሙ፡፡ እውነትንና ሰላምን ውደዱ ደግሞም እግዚአብሔር በመካከላችሁ በኃይል እንደሚሰራ እመኑ፡፡
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”
- ዘካርያስ 8፡19
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘጸአት 34:28 — “በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ እንጀራም አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። በጽላቶቹም አሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።”
ዘካርያስ 7:4–6 — “ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?በምትበሉበትና በምትጠጡበትስ ጊዜ፥ ለራሳችሁ የምትበሉና የምትጠጡ አይደላችሁምን?”
ሉቃስ 4:2–4 — “አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።ዲያብሎስም፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ይህን ድንጋይ፦ እንጀራ ሁን ብለህ እዘዝ አለው።ኢየሱስም፦ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።