Mourning For The Pierced One
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Pierced One Zechariah 9-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዘካሪያስ ብዙ የማጥኛ ጊዜን ልናሳልፍበት የሚገባን ችላ የተባለ መጽኃፍ ነው ምክንያቱም እነዚህ ምዕራፎች ስለ መሲሁ ብዙ መልዕክቶችን ስላካተቱ ፡፡ በዘካሪያስ ዉስጥ ለኢየሱስ ሐረጋችን የተወጋው የሚል ነው ፡፡ ክርስቶስን በተመለከቱ ጊዜ እንደወጉት በማስተዋል ያዝናሉ (ዘካ 12፡ 10) ፤ በተጨማሪም ከምርኮ ነፃሊወጡበት የሚችሉበት ብቸኛዉ መንገድ በወጉት ላይ በመመልከት ብቻ እንደሆነ ያስተዉላሉ ፡፡
ዛሬ ዘካርያስ (9-12) እንሸፍናለን ነገር ግን በማጠቃለያ እንጀምር ፡፡ ዘካርያስ ከሐጌ ጋር እስራኤል ቤተ መቅደሱን መልሳ እንድትገነባ የፈለገ ነቢይ ነበር ፡፡ በስምንቱ ራዕይ ዉስጥ እግዚአብሔር ለዘካርያስ የእስራኤልን አቅም አጥብቆ መልኩን ሳለለት ፤ ዘካርያስ ያ ቤዛነት እየመጣ እንደ ነበር ተናገረ ፡፡
ትምህርት
ዘካርያስ (9፡ 1-8)፡ ይህ ሸክም ወይም ፍርድ በሴድራክ፣ በደማስቆ፣ በሐማት፣ በጢሮስ እና በሲዶና ላይ ነበር (ቁጥር 1-4) ፡፡ በቁጥር (5-8) ፍርድ በፍልስጤም ከተሞች በአስቀሎና፣ በጋዛ፣ አቃሮን እና በሜደትራሊያ ዳርቻ ላይ በአይታ ላይ ተነግሮ/ታዉጆ ነበር ፡፡
ዘካርያስ (9፡ 9-10)፡ ቁጥር 9 በመጽኃፉ ዉስጥ መሲሁን ከሚገልፁ ጥቅሶች ዉስጥ አንዱ ነው ፡፡ ጄ.ቬርኖን ማክጊ እንዳለው “ ይህ ወደኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ የክርስቶስ የድል አድራጊነት አገባብ ነው (ማቴ 21፡ 5) “ ፡፡ ይህ ቁጥር የሆሳዕናን ቀን ይገልፃል ፤ ዮሐ (12፡ 15) “ አንቺ የጽዮን ልጅ አትፈሪ ፤ እነሆ ንጉስሽ በአህያ ዉርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል “ ይላል ፡፡ ማቴዎስ 21 እና ዮሐንስ 12 ከዘካርያስ 9 ጋር በምናወዳድር ጊዜ የተረሳ/የተሳተ ነገር አለ ፤ ሁለቱም የወንጌል ፅኁፎች “ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ “ ትተዉታል ፤ ይህ ክፍል በክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ይፈፀማል ፡፡ ልክ እንደሌሎቹ ነቢያት ዘካሪያስ “ ብዙ ቀድመዉ የሆኑና ገና አሁንም ያልሆኑ “ ትንቢቶችን አካትቷል ፡፡ በክርስቶስ ሁለተኛ መገለጥ/ምጽዓት ሰላም ከባህር እስከ ባህር እስከ ምድር ዳርቻ ድረሰ ለአሕዛብ ሁሉ ሰላም ይመጣል (ቁጥር 10) ፡፡ እስካሁን በሁሉም ሕዝብ ላይ ሰላምን አላየንም ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ ግን እናያለን ፡፡
ዘካርያስ (9፡ 11-17)፡ ዘካርያስ ኢየሱስ ሰላምን ለማምጣት/ለማድረግ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ ሕዝቡን እንደሚያወጣ እና እንደሚያድስ አብራርቷል ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ በሁሉም ሰዉ ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ አስደናቂ መልክ እና የሕዝቡ ነፃ መዉጣት እና ቤዛነት በአህያ ላይ በተቀመጠው ንጉስ ብቻ እንደተገኘ እናያለን ፡፡
ዘካርያስ (10፡ 1-8)፡ ከጊዜዉ ርዝማኔ የተነሳ አስሩ ነገዶች ጠፍተዉ ነበር ይሁዳም ተበታትኖ ነበር - ሁሉም እረኛ እንደሌላቸዉ በጎች ሆነዋል (ቁጥር 2) ፤ ነገር ግን “ ከይሁዳ የማዕዘን ድንጋይ ይመጣል/ይወጣል “ (ቁጥር 4) ፡፡ የተበታተኑትንም መልሶ ይሰበስባቸዋልይዋጋሉም ፤ ይህ ለመጀመሪያዉም ለሁለተኛዉም መምጣት ማጣቀሻ የሚሆን ይመስላል ፡፡ ሁልጊዜ ትንቢታዊ ቃል ክርስቶስ መልስ እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡ እግዚአብሔር የይሁዳን እና የዮሴፍን ቤት እንደሚያበረታቸዉ፣ እንደሚያድናቸው እና እንደሚመልሳቸው እንዲሁም “ እንዳልጣልኋቸዉ ይሆናሉ “ በማለት ቃል ገብቷል (ቁጥር 6) ፡፡ በእግዚአብሔር ፀጋና ምሕረት ሕዝቡን ይሰበስባል ፡፡ የመዓዘኑ ድንጋይ ክርስቶስ ነው ፡፡
ዘካርያስ (10፡ 9-12)፡ እንደ ገና ሕዝቡ በአሕዛብ መካከል የተበተኑ ቢሆኑም እንኳን እግዚአብሔር መልሶ ወደ ምድሪቱ እንደሚያመጣቸው ቃል ገባ ፡፡ ይህ ምዕራፍ እግዚአብሔር ሕዝቡን መልሶ ወደ ምድሪቱ እንደሚያመጣ ነው ፡፡
ዘካርያስ (11፡ 1-6)፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ በስትክክል ክርስቶስ በሕዝቡ የተገፋ/ችላ የተባለ ሲሆን ማየት ትጀምራላችሁ ፡፡ በቁጥር (1-6) ስለ ሐሰተኛ እረኞች ቋንቋ ማየት እንጀምራለን ፡፡ ሐሰተኛ እረኞች ሕዝብን አስተዋል ፤ ጄ.ቬርኖን ማክጊ ቁጥር 6 እንደ ድል አድራጊ ለሮሜ ማጣቀሻ ከሆነ ያደንቃል ፡፡
ዘካርያስ (11፡ 7-14)፡ እረኛው መንጋዉን ለመጠበቅ ሁለት በትሮችን ይጠቀማል፡ ሞገስ እና ህብረት (ቁጥር 7)፡፡ “ ሞገስ “ የሚለዉ ቃል ዉበትን ወይም ፀጋን ሊያመለክት ይችላል ፤ “ ህብረት “ የሚለዉ ቃል ማሰሪያን ሊያመለክት ያችላል ፡፡ ቁጥር 12-13 በግልፅ የይሁዳን ኢየሱስን አሳልፎ ስለመስጠት ናቸው ፡፡ ማቴ (26፡ 15) ይሁዳ በምላሹ ኢየሱስን ለካህናት አለቆች እንዲሰጥ 30 ሸቅል ብር እንደተከፈለው ይናገራል ፤ ተመሳሳይ ነገር በማቴ (37፡ 3-10) እና ሐዋ (1፡ 17-20) የተፃፈ ነው ፡፡ ይህ የንጉሱ መገፋት በዘካርያስ ላይ ተመዝግቧል/ተጽፏል ፡፡
በእነዚህ ሰዎስት ምዕራፎች የተገለፀዉን ሂደት/ለዉጥ አስተዉሉ ፤ ዘካርያስ 9 ስለሚመጣዉ ንጉስ አወራ ፤ ዘካርያስ 10 ለክርስቶስ እንደ ማዕዘን ድጋይ ማሳያዎችን ይዟል ፤ አሁን በዘካርያስ 11 ንጉሱ ክርስቶስ በሕዝቡ ተገፋ ፡፡
ዘካርያስ (11፡ 15-17)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ኃሰተኛዉ እረኛ ማነው ? ምናልባትም እነዚህ ቁጥሮች ስለ ኃሰተኛዉ ክርስቶስ የሚያወሩ ናቸው ፡፡
ዘካርያስ (12፡ 1-5)፡ ይህ ምዕራፍ ጡዘት ነው ! ቁጥር 1 ስለ እግዚአብሔር ኃይል የሚያስደንቅ ኃይልን ያቀርባል ፡፡ እንደ ዋይርስቤ ገለፃ መሰረት ቁጥር 2 በግልፅ ኢየሩሳሌም የተጠቃች እንደምትሆን ይናገራል ፡፡ በዚህ ምሳሌ ኢየሩሳሌም ሌሎች እርሷን በማጥቃት መንገዳገድ የሚጀምሩበት ፅዋ ትሆናለች ፤ አሕዛቦች ኢየሩሳሌምን ለመዋጥ ያቅዳሉ ነገር ግን እርሷን ሲያጥለቀልቁ ወደ መንገዳገዳቸው እና ዉድቀታቸዉ ይመራቸዋል ፡፡ ኢየሩሳሌምን ለማንሳት የሚሞክሩም በራሳቸዉ የተጎዱ ይሆናሉ (ቁጥር 3) ፤ በሌላ አባባል በግል እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጠብቃል ማለት ነው - ይህም በእርግጠኝነት “ በመጨረሻው “ ዘመን የሚሆን ይመስላል ፡፡ በቁጥር 4 ላይ የሚገኘው “ በዚያ ቀን “ የሚለዉ ሐረግ የጌታን ቀን ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋለ ንግግር ነው ፡፡ ይህ ዉጊያ በሚከናወንበት ጊዜ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ጠላቶች ላይ ዉዝግብን፣ እብደትን እና እዉርነትን ይፈጥራል (ቁጥር 4) ፡፡ ዋይርስቤ “ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕዝቡን በመከላከል እና ጠላቶቹን በማሸነፍ ኃይሉን ያሳያል “ በማለት አጠቃሎታል ፡፡
ዘካርያስ (12፡ 6-9)፡ በኢየሩሳሌም ላይ የሚሆነዉ ከበባ በይሁዳም ላይ ይሆናል ፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር የይሁዳን መሪዎች እንደ ትንታግ እና ፋና ነበልባል ያደርጋቸዋል (ቁጥር 6) ፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል በሕዝቡ በኩል ይገለጣል/ይታያል ፡፡ ይሁዳን የሚያጠቁ እንደ ደረቅ ቃርሚያ ቃል በቃል የተቃጠሉ ይሆናሉ ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር መጀመሪያ ይሁዳን ያድነዋል (ቁጥር 7) ፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይከላከላል (ቁጥር 8)፡፡ ደካማዉ እንኳን አስር ሺዎችን እንደገደለዉ እንደዳዊት ይሆናል (1ሳሙ 18፡ 7-8) ፤ የእግዚአብሔር መለዓክ በዉጊያ/በጦርነት 185,000 አሶራዊያንን ገድሏል (ኢሳ 37፡ 36) ፤ ጠላቶቹ ሁሉ ይጠፋሉ ፡፡ ቁጥር 9 ሁሉንም ነገር - እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጣዉን ሕዝብ ሁሉ ያጠፋዋል በማለት ያጠቃልላል ፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ የአርማጌድዮን ጦርነት ተገልፆ አይተነዋል ፡፡
ዘካርያስ (12፡ 10-14)፡ ከዚያም ጦርነቱ ድል ከተደረገ በኋላ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ላይ የፀጋ እና የፀሎት መንፈስን ያፈስሳል የወጉትንም ይመለከቱታል (ቁጥር 10) ፡፡ ይህ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ አንዱ ኃይለኛ ንግግር ነው ፤ እስከዚህ ጊዜ ድረስ የአይሁድ ሰዎች ኢየሱስን አልተቀበሉም/ችላ ብለዋል ፡፡ አሁን ኢየሱስን እንደሰቀሉት በማስተዋል በምሬት በማልቀስ ስለ እርሱ ያዝናሉ ፤ ይህ በሚሆን ጊዜ ክርስቶስ እየተናገረዉ ስላለዉ መጨረሻ ለመድረስ በህይወት ዘመናችን ከዚህ በፊት አይተነዉ የማናውቀዉ አይነት እዉነተኛ መነቃቃት ይሆናል ፡፡ የአይሁድ ሰዎች መሲሁን እንደወጉት ያስተዉላሉ ፡፡ ራዕ (1፡ 7) ተመልሶ ሲመጣ ሁሉም ሰዉ እንደሚያየው የወጉት እንኳን ሳይቀሩ እንደሚያዩት እና እንደሚያዝኑ ይናገራል ፡፡ ጳዉሎስ በሮሜ (11፡ 25-27) ስለዚህ ነገር ፅፏል ፤ በመጨረሻም አሕዛብ ሁሉ ወንጌልን በሰሙ ጊዜ እስራኤላዊ ሁሉ ይድናል ፡፡ በመከራዉ እና በእግዚአብሔር ቀን በሆነ ስፍራ ላይ የአሕዛብ ሙላት ይሆናል ፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የአይሁዶችን አይን ይከፍታል ልባቸዉንም የሚያስተዉል ያደርጋል መሲሁን ወግተዉት እንደ ነበር ያያሉ ፤ ከዚያም በብዙ እንደ መሲሀቸው ወደ ክርስቶስ ይመለሳሉ ፡፡
መደምደሚያ
ዘካርያስ 12 እስካሁን ስላልመጣዉ የእግዚአብሔር ታላቅ እንቅስቃሴ ያመለክታል - የአይሁድ ሰዎች ለዮሹዋ/ለጌታ የሚያለቅሱበትን ጊዜ ፡፡
J. Vernon McGee, Thru the Bible Commentary Series: Zechariah (Nashville: Thomas Nelson, Inc., 1991), n. p.
McGee, n. p.
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), p. 1519.
Wiersbe, p. 1519.
ጥያቄዎች
-
ዘካ (9፡ 9) ንጉሱ በአህያ ሁርንጫ ላይ ተቀምጦ እንደሚመጣ ይናገራል ፤ ይህ በመጽኃፍ የት ላይ ተፈፀመ (ማር 11፡ 1-11) ? ለምን በአህያ ሁርንጫ ይመጣል ለምን በፈረስ አይመጣም ?
-
ዘካ (10፡ 2) ለአዲስ አማኝ እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
-
በዘካ (10፡ 6) እግዚአብሔር እስራኤልን እመልሳለሁ አለ ፤ በቁጥር (8-9) እግዚአብሔር እንደሚያድናቸዉ እና እንደ ገና ወደ እስራኤል እንደሚመለሱ ተናገረ ፡፡ በግል አስተያየታችሁ ይህ ወደ ተጀመረ ወደኃላ ይስባል ? ለምን ወይስ ለምን አይስብም ?
-
በዘካርያስ (11፡ 12) ለመሲሁ ዋጋ ሕዝቡ 30ሸቅል ብር ሰጡ ፤ በመጽኃፍ ላይ ያ መጠን ጥቅም ላይ የዋለበት ሁለት ሌላ ምሳሌዎች አሉ (ዘጸ 21፡ 32, ማቴ 27፡ 9) ፤ በእነዚህ መካከል ልዩነቶቹ ምንድን ናቸው ? ይህ በዘካርያስ በግልፅ ተመዝጎቦ ሳለ ለምን ማቴዎስ ለኤርምያስ ይህን ማሳያ ጠቀሰ ?
-
ዘካ (12፡ 10) በምን መንገድ ኢየሱስን ያመለክታል ? ይህ ጥቅስ የፍርሀትን ስሜት ወይስ የድል አድራጊነትን ይፈጥራል ? እንዴት አድርጎ ?
-
በዘካርያስ (9-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Zechariah 12:10
“Then, I will pour out a spirit of grace and prayer on the house of David and the residents of Jerusalem, and they will look at Me whom they pierced. They will mourn for Him as one mourns for an only child and weep bitterly for Him as one weeps for a firstborn.”
ዘካርያስ አይሁዶች አንድ ቀን መሲሁን እንደ ወጉት እንደሚያውቁ ተነበየ፡፡ ያዝናሉ ያለቅሳሉም፡፡ እርሱም እንደሆነ ያውቃሉ፡፡ ስላለመታዘዛቸው ደግሞም እረኛውን የማዕዘን ድንጋዩን እርሱን ባለመቀበላቸው ያዝናሉ፡፡ የእግዚአብሔርን ልብ ስለወጉም ያለቅሳሉ፡፡ አዎን አንድ ቀን ኢየሱስ በደመናት ላይ ተመልሶ ይመጣል፤ ሁሉም ሲጠብቁት የነበረው እርሱ እንደሆነም ያውቃሉ፡፡
እስኪ ራሳችሁን ጠይቁ ፡- እናንተም እንደ እስራኤላውያን እምቢ በማለት ባለመታዘዝ ተራምዳችኋል? ኢየሱስ መሲሁ በመሆኑ ትገረማላችሁን? ጌታ ለእርሱ ፍቅር፣ እውነት እና ሰላም እንድትነቁና እርሱን ወደ ህይወታችሁ እንድትቀበሉት ይፈልጋል፡፡ እንደ እስራኤላውያን አትጠብቁ፡፡ በራሳችሁ መንገድ እየሄዳችሁ መሲሁን ከፊታችሁ እንደምታገኙት አትጠብቁ፡፡ ንቁና እውነቱን ተቀበሉ፡፡ እዚህ አለላችሁ፡፡ አዎን ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል፡፡ ነጻ እንድትወጡና በሰላም እንድትኖሩ እርሱ እውነቱን እንድታውቁ ይፈልጋል፡፡ ጌታ ፈጽሞ አይተዋችሁም፡፡ እርሱ ይወዳችኋል፡፡ የህይወታችሁ የማዕዘን ድንጋይ ይሆን ዘንድ ደግሞም የሚመራችሁ ታላቅ እረኛ እንድሆንላችሁ ፍቀዱለት፡፡ መሲሀችሁ አድርጉት፡፡ ዛሬ እርሱን ተቀበሉት፡፡
“በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።”
- ዘካርያስ 12፡10
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘካርያስ 10:4–5 — “ከእርሱ ዘንድ የማዕዘኑ ድንጋይ፥ ከእርሱም ዘንድ ችንካሩ፥ ከእርሱም ዘንድ የሰልፉ ቀስት፥ ከእርሱም ዘንድ አስገባሪው ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ። በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ።”
ሮሜ 11:25–27 — “ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል።ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው። “
ራዕይ 1:7 — “እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።