Minor Prophets Zechariah

Finding The Messiah In Zechariah

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Pierced One Zechariah 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 707 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እነዚህ ምዕራፎች ስለተወጋዉ ሞት የእስራኤል ሀዘን ይዳስሳሉ ፤ በተጨማሪም ስለ ዘመናት መጨረሻ እና እንዴት ኢየሱስ ቅርንጫፍ እንደ ሆነ ያወራሉ ፡፡ በትንቢታዊ ቋንቋ ዘካርያስ ስለተፈጥሮ፣ ስለ ወቅታዉ ሁኔታ ከዚያም ወደ መለኮታዊ ምን እንደ ነበር ዞር በማለት ፅፏል ፡፡ ትዕቢትና ቸልተኝነት ትንቢቱን የሚቀበሉበት የሕዝቡ የተደጋገሙ አመለካከቶች ነበሩ ፡፡ ሕግና ነቢያት ሁሉም እንደ መሲህ ወደ ኢየሱስ እና ተመልሶ ወደመምጣቱ ያመለክታሉ ፤ ነገር ግን ሕዝቡ አልተረዱትም ፡፡ “ በቶሎ ማርጀት እና በቶሎ አለማስተዋል “ የሚለዉ የኔዘርላንድዊያን አባባል ለሕዝቡ አመለካከት ይመጥናል ፡፡

ትምህርት

ዘካርያስ (13፡ 1-4)፡ የአይሁድ ሰዎች በትክክል ክርስቶስ ማን እንደ ነበር የሚያዉቁበት ጊዜ ይመጣል ፤ አይሁዶች መሲሁ ማን እንደ ነበር በሚያስተዉሉ ጊዜ በመታጠብ የነፁ ይሆናሉ ፡፡

ምድሪቱን ማንፃጽ፣ ነቢያትን እና ርኩስ መናፍስትን የተወገዱ እንደሚሆኑ በቁጥር 2 የተተነበዬ ነው ፡፡ በሮሜ 11 ጳዉሎስ የአይሁድ ሰዎች ልብ ስለመደንደኑ አዉርቷል ፤ ነገር ግን ነፃ አዉጪዉ ኃጢዓታቸዉን የሚያስወግድበት ጊዜ ይመጣል ፡፡

በቁጥር 3 የፍጥረት ሁሉ ጌታ የምድሪቱን ጣኦታት ያጠፋል ፡፡ ጣዖቶቹ ኃሰተኞች እና ባድ መጽናናጽን ያቀረቡ ነበሩ ፡፡ ጣዖት ሕዝቡ ሊያየዉ የሚችል ተጨባጭ የሆነ ነገርን ያቀርባል ፤ ጣዖት የእግዚአብሔርን መገኘት ማስታወሻ አይነት ነገሮችን ይወክላሉ ፡፡ ሕዝብ አጥቶት ስለ ነበረው ነገር ይናፍቃል ፡፡ 2ነገ (18፡ 3-4) ሕዝቅያስ የእስራኤል ሕዝብን ጣዖቶች እንዳጠፋቸዉ ይናገራል ፤ ሕዝቡ የእስራኤላዊያንን መጽናናት እና ፈዉስን ያመጡ ነገሮችን ማስታወስ ጀመሩ እንጂ እግዚአብሔርን አላመለኩም ፡፡ ሕዝቡ በኑሮአቸዉ የእግዚአብሔር መገኘት የነበረባቸዉን ክስተቶች አስታዉሰዉ ነበር እንጂ እግዚአብሔርን አላስታወሱም ፡፡

በምዕረፍ 5 ዘካርያስ በኃሰት የሚምሉት የተወገዱ እንደሚሆኑ አዉርቷል (ቁጥር 1-4) ፤ እነዚህ ሐሰተኛ ነቢያት ነበሩ፡፡ ሐሰተኛ ነቢያቶች እና ያለፁት/የረከሱት የተወገዱ ይሆናሉ ፡፡

ዘካርያስ (13፡ 5-8)፡ ዘካርያስ የሐሰተኛ ነቢያቶች መጨረሻ ምን እንደሚሆን ማሳወቁን ቀጠለ ፡፡ የሐሰተኛ ነቢያቶች ቤተሰብ ያስወግዷቸዋል ፤ እነዚህ ሐሰተኛ ነቢያቶች በረከትን ለማግኘት እየሞከሩ ነበር ነገር ግን ከእግዚአብሔር የመጣ በረከት አይደለም ፡፡ በቁጥር 5 እግዚአብሔር የሐሰተኛ ነቢያት ጉዳዮችን እያጠፋ ነበር ፡፡

ቁጥር 6 እና ቁጥር 7 የተገናኙ ናቸው ፡፡ ዘካርያስ ስለ ሐሰተኛ ነቢያቶች እያወራ ነበር ነገር ግን ስለ መሲሁ ወደማዉራት ተቀየረ ፡፡ በቁጥር 8 ዘካርያስ ሁለት ሰዎስተኛዉ የሚሆነዉ ሕዝብ እንደሚሞት ነገር ግን አንድ ሰዎስተኛዉ የሚሆነዉ እንደሚተርፍ ተናገረ ፤ ይህ አንድ ሰዎስተኛው የሚተርፉትን ቅሬታዎች ይወክላል ፡፡ ዘካርያስ እረኛዉ ከተወገድ በጎቹ እንደሚበተኑ ገልፆአል ፤ እነዚህ ቁጥሮች የሕዝቡን እና የመሲሁን ምስል/መልክ ዳስሰዋል ፡፡ በማቴ (26፡ 3) የእግዚአብሔር ቃል ደቀ መዛሙርቱ የተበታተኑ እንደሚሆኑ ያወራል ከዘካርያስም ላይ የተወሰደ ነበር፡፡

እግዚአብሔር በተደጋጋሚ የእስራኤልን ቅሬታዎች አድኗል ፤ በዘካርያስ ላይ ያለዉ ማጣቀሻ የወቅቱን ሁኔታ እና በፍርድ ጊዜ ይመጣ ስለ ነበረዉ ነገር ይዳስሳል ፡፡

ዘካርያስ (14፡ 1-15)፡ ዘካርያስ ይመጣ ስለ ነበረው የመከራ ጊዜ መድረስ/መዳሰስ ጀመረ ፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚበቀል ቃል ገባ ፡፡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርህራሄ እና ምህረት አለው ፡፡ ዘካርያስ እግዚአብሔር በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በማረፍ ሸለቆን ለመስራት ወደ ሁለት እንደሚከፍለው ተናገረ ፡፡ ሕዝቡ በተራራዉ ሸለቆ ላይ ይሸሻሉ (ቁጥር 1-5) ፡፡

በራዕይ (1፡ 4-8) እግዚአብሔር ክርስቶስ እንደሚመለስ እና አይን ሁሉ እንደሚያየው ቃል ገብቷል ፡፡ የምድር ቤተሰብ ሁሉ ለእርሱ ያዝናሉ ፤ እነዚህ ጥቅሶች ከዘካርያስ የተወሰዱ ነበሩ ፡፡ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል በእግዚአብሔር ብቻ የታወቀም ቀን ይሆናል (ቁጥር 6-7) ፡፡ በቁጥር 8 ዘካርያስ ዉኃ ከኢየሩሳሌም እንደሚፈስስ እና ግማሹ ወደ ሙት/ጨዉ ባህር እንደሚሄድ ግማሹ ደግሞ ወደ ሜዴትራሊያ ባህር እንደሚሄድ ገልፆአል ፡፡ ያህዌ በምድር ሁሉ ላይ ንጉስ ይሆናል ፡፡ ሕዝቅኤል ጨዉ/ሙት ባህር እንኳን ከሕይወት ጋር የተገናኘ ስፍራ እንደሚሆን ተናግሯል ፡፡

ክርስቶስ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ ነገሮች መልካም አይሆንም ፤ ክርስቶስ በሚመጣ ጊዜ ነገሮች ትክክል ይሆናሉ ፡፡

መደምደሚያ

በዘካ (14፡ 16-21) መጽኃፍ ታላቁ ጦርነት ከተካሄደ በኋላ አሕዛብ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩት ይናገራል፡፡ ጭብጡ ክርስቶስ የፍጥረት ሁሉ ጌታ ንጉስ ይሆናል የሚለዉ ነው ፡፡ ሕዝቡ ወደ ዳስ በዓል ይሄዳል ፡፡ “ የእግዚአብሔር ቅዱስ “ ቃል በፈረሶች ሆድ ላይ እንኳን ይሆናል ፡፡

በዚያ ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከነዓናዊያን አይኖሩም ፤ ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ ሁሉም ነገር መሆን እንዳለበት ይሆናል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በዘካ (13፡ 6) “ በእጅህ ላይ እነዚህ ቁስሎች ምንድን ናቸዉ ? “ ብለው ለምን ይጠይቃሉ ?
  2. ዘካ (13፡ 8-9) በቀጥታ እንደሚሆን ታምናላችሁ ? “ ክፍል “ የሚለዉ እቃን ወይስ ሰዉን ያመለክታል ? ለምን እንደዛ እንደሚሆን ምን ታስባላችሁ ?
  3. ዘካ (14፡ 4) የደብረ ዘይት ተራራ እንደሚከፈል እና እንደ ማምለጫ መንገድ እንደሚለያይ ይናገራል ፤ በመጽኃፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ እግዚአብሔር እንደ ማምለጫ መንገድ የሆነ ነገርን ከፍሏል (ዘጸ 14፡ 21-22)?
  4. በዘካርያስ (13-14) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Zechariah 14:3

“Then the LORD will go out to fight against those nations as He fights on a day of battle.”

ነቢዩ ዘካርያስም ሲያጠቃልል ሰለ እግዚአብሔር ቀንና ኢየሱስ ውጊያን እንደሚዋጋ እግሮቹም ከኢየሩሳሌም ትይዩ ባለው የደብረ ዘይት ተራራ ላይ እንደሚቆሙ ያየውን ራዕይ ተናገረ፡፡ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል፤ የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል። ጌታ ሲመጣ ከዚያም በኋላ ርኩሰት አይኖርም፡፡ ሁሉም የጌታን ስም ይጠራል፡፡ ሃሌሉያ! ኢየሱስ ይመለሳል፡፡ ጌታ የሚመጣበትን ቀን ጠብቁ!

እነሆ ጌታ በመካከላችሁ እንደ ኃይለኛ ተዋጊ ይነግሳል፡፡ ተመልሶ በሚመጣበትም ቀን እናንተን ስለሚወዳችሁ ስለ እናንተ ይዋጋል፡፡ እርሱም ያሸንፋል፡፡ እርሱም ከዘላለም እስከ ለዘላለም ይነግሳል፡፡ ህዝቡም ከዚያ ወድያ አይረክሱም፡፡ ጣዖታትም ይጠፋሉ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፡፡ በመጨረሻም ክርስቶስ መሲሁ ሲመጣ ሁሉም ፡- “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል ይላሉ! ” ምድርም ሁሉ እርሱ መሲሁ እንደሆነ ያያል፡፡ መንገዱን አዘጋጁ ወደ ፊትም በመሄድ ዓለም ሁሉ ያውቅ ዘንድ ስሙን አውጁ፡፡

“እግዚአብሔርም ይወጣል፥ በሰልፍም ቀን እንደ ተዋጋ ከእነዚያ አሕዛብ ጋር ይዋጋል።”

  • ዘካርያስ 14፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘካርያስ 14:11 — “ሰዎችም ይኖሩባታል፥ ከዚያም ወዲያ እርግማን አይሆንም፤ ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትኖራለች።”

ዘካርያስ 14:21 — “በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ይሆናሉ፤ የሚሠዉትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ ከእነዚያም ወስደው ይቀቅሉባቸዋል፤ በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቤት ከነዓናዊው ከእንግዲህ ወዲያ አይገኝም።”

ራዕይ 4:11 — “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።”