Sun Of Righteousness
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Sun of Righteousness Malachi 1-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ብሉይ ኪዳን በማቴ (5፡ 17) የተነቃቃ/የተነሳ ነበር፡ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ ፡፡ በታናናሽ ነቢያት ዉስጥ ኢየሱስ እንዴት ትንቢቶችን ሊፈጽም እንደመጣ አይተናል ፤ ኢየሱስ በአጠቃላይ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ ማስረጃ ነው ፡፡
ሚልክያስ በቅደም ተከተል እና በታሪካዊ ቅደም ተከተል የመጨረስ መጽኃፍ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ለ400 አመታት ዝም ያለ ከመሆኑ በፊት በሚልክያስ በኩል በመልዕክቱ የብሉይ ኪዳንን ቀኖና ሕግ ዘጋ ፡፡ የሚልክያስ ስም “ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ “ ማለት ነው ፡፡ እንደ ማክአርቱር ገለፃ የአይሁድ ወግ ሚልክያስን ለአይሁድ ሽማግሌዎች ጀማሪ በታላቁ ምኩራብ አስቀመጡት ፡፡
ሚልክያስ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአምስተኛው ክፍለ ዘመን ዘግየት ብሎ ትንቢትን ተናገረ ፡፡ ብዙ ምሁራን የሚልክያስ አገልግሎት ከክርስቶስ ልደት 433- 424 አካባቢ በፊት ከነህምያ መመለስ ጋር እንደሚጣጣም ያምናሉ ፤ መስዋዕት በሚልክያስ ዘመን ጊዜ በአካላዊዉ ቤተ መቅደስ ላይ የሚደረግ ነበር ፡፡ ሐጌ እና ዘካርያስ ሕዝቡን ቤተ መቅደሱን መገንባታቸዉን እንዲጨርሱት አበረታተዋቸዉ ነበር ፤ ሚልክያስ በዚህ የዘሩባቤል ቤተ መቅደስ ተብሎ በሚጠራዉ በሁለተኛው ቤተ መቅደስ መስዋዕት የተደረገ እንደሆነ ገልፆአል (ሚል 1፡ 7-11) ፡፡ ሁለተኛው ቤተ መቅደስ ከክርስቶስ ልደት 516 በፊት ያበቃ ነበር ፤ ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ ከተጠናቀቀ ከ 100 አመት ካነሰ ጊዜ በኋላ ማክአርቱር ካህናቱ “ የተበላሹ እና በራሳቸዉ የሚደሰቱ “ እንደሆኑ ፅፏል ፡፡
ከተበላሸ መስዋዕት በተጨማሪ እስራኤላዊያን የአሕዛብ ሚስቶችን እየወሰዱ ነበር፣ አስራትን አይከፍሉም ነበር በተጨማሪም ማህበራዊ ስህተት መፈፀም ነበር ፡፡ ይህ የእስራኤላዊያን ታሪክ ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ መልሶ ተቀምጦ እንደ ነበረው ለእነርሱ በተመሳሳይ ኃጢዓት የመዉደቅ እና እንደገና የማመጽ ታሪክ ነው ፡፡ ሚልክያስ በነህምያ ወደ ፋርስ መመለስ ጊዜ ትንቢትን ከተናገረ ነህምያ በመመለሱ ላይ የደረሳቸዉ ኃጢዓቶች (ነህ 13፡ 6) በሚልክያስ 3 የተገለፁት ይሆናሉ ፡፡
በሚልክያስ አገልግሎት ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት 50,000 የሚደርሱ ስደተኞች ይኖራሉ ፡፡ ቤተ መቅደሱ መልሶ ተገንብቶ ነበር የመስዋዕት ስርዓቱም እንደ ገና ተቋቁሞ ነበር ፤ ነገር ግን ወደ ምድሪቱ ከተመለሱ ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ጠንካራ/የደነደነ ልብን አሳደገ ፤ ሚልክያስ ሕዝቡን በመገሰፅ ወደ ንስኃ ጠራቸው ፡፡ እንደ ብሉይ ኪዳን መዝጊያ/መደምዲያ ማክአርቱር “ ከ2,000 አመት በላይ የብሉይ ኪዳን ታሪክ ሲከናወን አብርኃም እንደ ደመደመው ከከበሩት ተስፋዎች/ኪዳኖች የአብርኃም፣ የዳዊት እና አዲሱ ኪዳን ማንኛቸዉም እንዳልተፈፀሙ “ ፅፏል ፡፡ የሚልክያስ የመጀመሪያዉ ትንቢቱ እስራኤል ስለ ኃጢዓቷ ንስኃ እስክትገባ ድረስ መሲሁ እንደማይመለስ ነበር ፡፡
ትምህርት
ሚልክያስ (1፡ 1-5)፡ ሚልክያስ ለእስራኤል በእግዚአብሔር ፍቅር መልክ ይጀምራል/ይከፍታል (ቁጥር 1-5) ፡፡ እግዚአብሔር ከኤሳዉ ይልቅ/በላይ እንዴት ያዕቆብን እንደመረጠ ያመለክታል ፡፡ በሚልክያስ ዘመን እንኳን የእግዚአብሔር ፍርድ በኤሳዉ ዘር በኤዶም ላይ በመሆን ለእስራኤል ጥበቃዉን አሳይቷል ፡፡
ሚልክያስ (1፡ 6-14)፡ የእግዚአብሔር ቅሬታ በሕዝቡ ላይ ካህናቱን ያካትታል ፤ እግዚአብሔር ክሱን እንዳቀረቡ ሕዝቡ በስላቅ ምላሽን ሰጡ (ቁጥር 6-7) ፡፡ ካህናቶች የክብርን ጌታ ለእግዚአብሔር አንካሳ እና እዉር የእንስሳ መስዋዕትን በማምጣት ዘርፈዉት ነበር ፤ በቁጥር 8 እግዚአብሔር እንዲህ አይነቱን መስዋዕት ለአለቆቸው እንዲያቀርቡ፡ “ በዉኑ በአንተ ደስ ይለዋልን ወይስ ፊቴን ይቀበላልን ? “ በማለት ሞገታቸው ፡፡ ጄ.ቬርኖን ማክጊ “ የእስራኤል ልብ ተበክሎ “ እንደ ነበር አመለከተ ፡፡ ከዚህም የተነሳ እስራኤል የእግዚአብሔርን ሞገስ ለመቀበል አይጠብቅም ፡፡ እግዚአብሔር እስራኤል የቤተ መቅደሶን በሮች እንኳን የሚዘጋ እንደሌለ እስከመናገር ሄደ ፤ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በአሕዛብ መካከል ስሙን ያለ አግባብ ስለወከሉ (ቁጥር 11) “ ከእጃቸዉም ቁርባን አይቀበልም ! “ (ቁጥር 10) ፡፡ ሕዝቡ እግዚአብሔር በእነርሱ የሰለች እስኪሆን ድረስ ወደ ኋላ ተንሸራጸው/ተመልሰዉ ነበር ፡፡
ሚልክያስ 2፡ እግዚአብሔር ካህናቱን ሕዝቡን በተሳሳተ እየመሩበት ከነበረዉ መንገድ አንፃር አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 1-7) ፡፡ ካህናቱ ከእግዚአብሔር ተመልሰዉ ስለ ነበር እግዚአብሔር ከእነርሱ ፊቱን መልሶ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 8-9) ፡፡
ሚልክያስ (3፡ 1-7)፡ በቁጥር 1 የተመላከተው “ መልዕክተኛ “ መጥምቁ ዮሐንስ ይሆናል ፤ የእርሱ ሚና/ተግባሩ ከክርስቶስ በፊት መንገዱን መጥረግ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ይህን ፅሁፍ በማቴ (11፡ 10) ጠቅሶታል፡ “ እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልዕክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ፤ ተብሎ የተፃፈለት ይህ ነዉና “ ፡፡ መልዕክተኛዉ ከደረሰ በኋላ ጌታ ራሱ በቤተ መቅደሱ ላይ “ በቶሎ እንደሚመጣ “ ቃል ገብቷል (ቁጥር 1) ፡፡ የጌታ ስራ ድርሻ ሕዝቡን እና የክህነት አገልጋዮችን/ካህናቱን ማንፃት ይሆናል ፤ ይህ ባደረገ ጊዜ እስራኤል “ እንደ ዱሮዉ እና እንደ ቀደሙት አመታት እግዚአብሔርን የሚያስደስት “ (ቁጥር 4) መስዋዕት ያቀርባል ፤ ይህ የኢየሱስ መስዋዕት ግልፅ ማሳያ/ማጣቀሻ ነበር ፡፡ እግዚአብሔር ኪዳኑን/ቃሉን የሚጠብቅ አምላክ ስለሆነ በመጨረሻም ሕዝቡን ነፃ ያወጣል (ቁጥር 7) ፡፡
ሚልክያስ (3፡ 8-12)፡ እግዚአብሔር በተጨማሪም አስራታቸዉን ባለማምጣት ሕዝቡን ከሰሳቸው (ቁጥር 8-10)፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በአዘዛቸዉ መንገድ የሚሰጡ ከሆነ እግዚአብሔር “ አሕዛቦች ብፁዓን/እድለኞች ብለዉ በሚጠሯቸው “ (ቁጥር 12) መንገድ እንደሚባርካቸዉ ቃል ገብቷል ፡፡ ካልሆነ ግን እግዚአብሔር ፍርዱን በእነርሱ ላይ ያመጣል ፡፡
ሚልክያስ (3፡ 13-18)፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እግዚአብሔር ማገልገል “ እንዴት ጥቅም የለሽ “ ይሆናል በማለት በይበልጥ ተከራክረዉት/ተከላክለዉት ነበር ፡፡ እንደ ማስረጃም እንዴት ክፉ ሰዎች እንደ በለፀጉ አዉርተዋል (ቁጥር 14-15) ፤ ነገር ግን ክሱን የሰሙ ቡድኖች ነበሩ “ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸዉ ተነጋገሩ “ (ቁጥር 16) ፡፡ እግዚአብሔር ለእርሱ ስለ ክብራቸው በማስተዋል “ ሰዉም የሚያገለግለዉን ልጁን እንደሚምር እንዲሁ እምራቸዋለሁ “ (ቁጥር 17) በማለት ቃል ገባ ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ እግዚአብሔር ንስኃ ለሚገቡት በሚያሳየው ርህራሄ/ ምህረት በፃድቃን እና በኃጢዓተኞች መካከል ያለዉን እዉነተኛ ልዩነት ያያሉ ፡፡
ሚልክያስ (4፡ 1-4)፡ የሚልክያስ የመጨረሻው ምዕራፍ የእግዚአብሔር ቀን ፍርድን በማሳየት ይጀምራል ፡፡ እግዚአብሔር “ ትዕቢተኞች እና ኃጢዓትን/ክፋትን የሚያደርጉ ሁሉ “ እንደሚበሉ ቃል ገብቷል (ቁጥር 1) ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ግን “ በመዉጣት እንደ ሰባም እምቦሳ ይፈነጫሉ “ (ቁጥር 2) ፡፡ ሚልክያስ (4፡ 2) ከሚልክያስ የሚመጣዉ ሐረጋችን ጥቅስ ነው፡ የጽድቅ ፀሐይ ፡፡
ሚልክያስ (4፡ 5-6)፡ ሚልክያስ የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ከመምጣቱ በፊት ኤልያስ ወደ ሕዝቡ ይመጣል በሚል ተስፋ ዘጋ ፤ ስራዉም “ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል “ (ቁጥር 6) ፡፡ ካልመጣ እግዚአብሔር ምድሪቱን ይረግማ ፡፡
መደምደሚያ
እስራኤል ሁለት ምርጫ ነበራት ፤ የተበላሹ መስዋዕቶችን በማቅረብ እና ከሚስቶቻቸዉ ፊታቸዉን በማዞር ከእርሱ በመራቅ መቀጠል ወይም ደግሞ እግዚአብሔርን በመፍራት እና የሚመጣዉን የጽድቅ ፀሐይ በመመልከት የታመኑ ቅሬታዎች መሆን ይችላሉ ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ በረከቱን በማፍሰስ ቤተሰብን እና ልባቸዉን በመመለስ ወደ እርሱ እምነት ይመለሳል !
ይህ ብሉይ ኪዳንን ይደመድማል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1077.
MacArthur, pp. 1077-1078.
MacArthur, pp. 1077-1078.
MacArthur, pp. 1077-1078.
J. Vernon McGee, Thru the Bible Commentary Series: Malachi (Nashville: Thomas Nelson, Inc., 1991), n. p.
ጥያቄዎች
-
ሚል (1፡ 11) በሐዋሪያት ስራ 10 ለአሕዛብ የተነገረዉን ወንጌል ያመለክታል ?
-
በሚልክያስ 1 ለእርሱ ተሰጥተዉ ከነበሩት ቁርባኖች/መስዋዕቶች ጋር ምን ጉዳይ እንደ ነበረዉ እግዚአብሔር ምን አለ ?
-
እግዚአብሔር “ ፍችን እጠላለሁ “ አለ ሚል (2፡ 16) ፤ እግዚአብሔር ፍችን ፍቃድን ሰጥቷል ? አዎ ከሆነ በምን ሁኔታ ? (ማቴ 5፡ 32, 1ቆሮ 7፡ 12-16)
-
በሚል (3፡ 10) እግዚአብሔር ሕዝቡ አስራቱን ወደ “ ጎተራ “ እንዲያገቡ አዘዘ ፤ በሚልክያስ ዘመን ጎተራዉ ቤተ መቅደሱ ነው ፤ በአሁኑ ጊዜ ጎተራው ነፍሳችሁ በተቀመጠበት ስፍራ ይሆናል ፤ አስራት ትከፍላላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አትከፍሉም ? እግዚአብሔር “ ስለ እናንተ በላተኞችን እየገሰፀ የነበረበትን “ የምታዉቁት ጊዜ አለ ? (ሚል 3፡ 11)
-
በሚል (4፡ 5) እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስ የተላከ እንደሚሆን ተናገረ ፤ በመጽኃፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ የኤልያስ መምጣት ተጠቅሷል ? (ማቴ 17፡ 10-12, ራዕ 11፡ 3)
-
በሚልክያስ (1-4) በኬይል ላንስ ማርቲን በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Malachi 4:2–3
“‘But for you who fear My name, the sun of righteousness will rise with healing in its wings, and you will go out and playfully jump like calves from the stall. You will trample the wicked, for they will be ashes under the soles of your feet on the day I am preparing,’ says the LORD of Hosts.”
እግዚአብሔር ህዝቡ የእርሱን ገበታ “ የተናቀ ነው “ በማለት ሲናገሩ ሰማ፡፡ ህዝቡም “ እግዚአብሔርን አርክሰናልን ? እንዴት ነው መመለስ የምንችለው ? በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድን ነው ? በማለት ይጠይቃሉ፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ ንግግራቸው፣ ድርጊታቸውና አሳባቸው እግዚአብሔርን ስለ መበደሉ ግዴለሾች ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን በእግዚአብሔር ቀን ሁሉም ትዕቢተኞችና ኃጢአተኞች ገለባ ሲሆኑ ያያል፡፡ ነገር ግን ስሙን ለሚፈሩ ለእነርሱ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላቸዋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እነርሱም ይወጣሉ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ይፈነጫሉ።
እንደ እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ስታፌዙ ይሰማችኋል፡፡ አዎን እርሱ አመጻችሁን ያያል፡፡ እርሱ አሳባችሁን ያውቃል፡፡ ወደ እርሱም ካልተመለሳችሁ በእርሱ እሳት ትበላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን እግዚአብሔርን ለሚፈልጉና እርሱን ለሚፈሩ ደስታና አምልኮ ተዘጋጂቷል! የእግዚአብሔር ቀን ደርሷል፡፡ እግዚአብሔርን በዘፈቀደ በትዕቢት መጠየቅ አቁሙ፡፡ እስከመቼ ድረስ ከእርሱ ጋር አብራችሁ እንደምትቀጥሉ መጠየቅ አቁሙ፡፡ እርሱ ያያችኋል፤ እርሱ ይሰማችኋል፤ እርሱ ያውቃችኋል ደግሞም እርሱ ልባችሁ ለእርሱ እንድማረክ ይፈልጋል፡፡ ይሄ ነው በቃ ፡፡ ከዚያም ደስታ፣ ሰላም እና ደህንነት ይኖራችኋል፡፡ ኢየሱስ ይበቃል ይህ እውነት እንደ እንቦሳ ጥጃ በደስታ እንድትዘሉ ያደርጋችኋል፡፡
“ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡”
- ሚልክያስ 4፡2-3
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 16:11 — “የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።”
መዝሙር 73:25–28 — “በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ?የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው።እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው።ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።”
ሚልክያስ 3:13–14 – “ቃላችሁ በእኔ ላይ ድፍረት ሆኖአል፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ እናንተ ግን፦ በአንተ ላይ ደፍረን የተናገርነው በምንድር ነው? ብላችኋል።እናንተም፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙንስ በመጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።