Revelation Revelation

John's Vision Of The Risen Lord

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 709 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሁሉም መጽኃፍ ዉስጥ መሲሁን ለመመልከት በመፈለጋችን በመጽሃፍ ቅዱስ ዉስጥ ለሁለት አመት ያክል አሳልፈናል ፡፡ በማቴ (5፡ 17) ኢየሱስ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ አለ ፡፡ በሁሉም በመጽኃፍ ቅዱስ መጽኃፍ ዉስጥ ኢየሱስ እያንዳንዱን ሊፈጽም እንደመጣ አይተናል ፤ በራዕይ መጽኃፍ ዉስጥ ስንጓዝ በአንድ በማገኛኘት ያጠናናቸዉን ሁሉንም ነገሮች የማየት እድል አለን ፡፡ በራዕይ መጽኃፍ ዉስጥ ለመሲሁ ቃላችን እኔ የሚል ነው ፤ ራዕ (1፡ 8) “ ያለዉና የነበረው የሚመጣዉም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ ፡- አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ ይላል “ ፡፡ ኢየሱስ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተሳሰረ (ዘጸ 3፡ 14) ፡፡

የመጽኃፉ ርዕስ መገለጥ ሳይሆን ራዕይ ነው ፤ ይህ የማያቋርጥ የክርስቶስ ራዕይ ነው ፡፡ ራዕይን ማክአርቱር “ እንዳልተሸፈነ፣ እንዳልተደበቀ ወይም እንደ ይፋ/ገሀድ የወጣ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ በራዕይ ዉስጥ ያልተሸፈነዉ ክርስቶስ ነው ፤ የራዕይን መጽኃፍ የማንረዳበት ምክንያት በአዉዳቸዉ 65 የመጽኃፍ ቅዱስ መጽኃፍት ስለማንረዳ እንደሆነ አምናለሁ ፡፡ ማክአርቱር በራዕይ ላይ የሚገኘዉን አለመሸፈን/የተገለጠ መሆንን “ የመንፈሳዊ እዉነትን እንደ መገለጥ፣ የእግዚአብሔር ልጅን እንደ መገለጥ፣ የክርስቶስን መገለጥ እና የከበረ ሁለተኛ በመምጣቱ እንደ ተገለጠ “ ይገልፀዋል ፤ “ በእያንዳንዱ ጥቅም ላይ ራዕይ የሆነ አካል የደበቀዉ ነገር የተገለጠ መሆኑን እንደሚያመለክት ፤ ይህ መፅኃፍ የሚገልጠዉ ወይም የሚያሳየው በክርብ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሆነ “ በመናገር ይቀጥላል ፡፡ ኢየሱስ ከአይሁዶች ተደብቆ/ተሰዉሮ ነበር ነገር ግን በሁለተኛዉ መምጣቱ ይገለጥላቸዋል ፡፡

ፀኃፊው የዮሐንስ ወንጌልን፣ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዮሐንስን የፃፈዉ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ነው ፡፡ ዮሐንስ ራሱን እንደ ፀኃፊ ለይቷል በተጨማሪም የቀድሞ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ማርትየር፣ ኢረኒየስ፣ የአሌክሳንድሪያ ክሊንመንት እና ቴርቱሊያ የዮሐንስን ፀኃፊነት/ባለቤትነት ይደግፋሉ ፡፡ “ ከመጽኃፊ የመጀመሪያ አንባቢዎች ዉስጥ አብዛኞቹ በሁለቱም ሐዋሪያዊ ባለቤትነት ባደረጉት በጀስቲን ማርትየር እና ኢረኒየስ የሕይወት ዘመንም ነበሩ “ ፡፡ በዮሐንስ በወንጌሉ እና በራዕይ የአፃፃፍ ስታይሉ መካከል አንደንድ ልዩነቶች ቢኖሩም ተመሳሳይነቶችም አሉ ፤ ሁለቱም መጽኃፍት ኢየሱስን “ እንደ ቃል “ ያመለክታሉ በተጨማሪም ሁለቱም መጽኃፍት “ ዘካ (12፡ 10) ከዘመን በተለዬ ቢተረጉሙም እርስ በእርስ ግን ይስማማሉ “ ፡፡

ምሁራን መጽኃፉ መቼ ተፅፎ እንደ ነበር በስምምነት አይደሉም/አልተስማሙም ፡፡ ማክአርቱር በዶሚቲያን ኢምፓየር አስተዳደር (ከክርስቶስ ሞት 81-96 በኋላ) መጨረሻ አካባቢ ከክርስቶስ ሞት (94-96 በኋላ መካከል) የተፃፈ እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡ በሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ ዝለት/ዉድቀት ስለ ደረሰባቸው (ራዕይ 2-3) ምናልባቱም መጽኃፉ ከዚያ በፊት ሊፃፍ አይችልም ፡፡ በ60ዎቹ አካባቢ ቤተ ክርስቲያኖች ጠንካሮች ነበሩ ፤ ማክአርቱር “ በዚያ በጳዉሎስ አገልግሎት እና በኔሮ ዘመን መካከል ያለዉ ግልፅ ጊዜ በጣም አጭር ስለ ነበር እንዲህ አይነቱ ፈጣን ዉድቀት እንዲሆን ምክንያት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ የረዘመዉ የጊዜ ስፋትምበጳዉሎስ መልዕክት ያልተጠቀሰዉን ከእነዚህ ተመሳሳይ ቤተ ክርስቲያን አንድ ወይም ከዚያ በላይ ያልተጠቀሱት እንኳን ኒኮታያን ተብሎ የሚታወቅን የተጠላን ክህደት/መናፍቅነትን እንደሚያስነሱ “ ይገልፃል ፡፡

ዮሐንስ በመጽኃፉ መጀመሪያ ላይ ድረስ በሕይወት የነበረ ብቸኛዉ ሐዋሪያ ነበር ፤ በዚህን ጊዜ ዮሐንስ አርጅቶ እና ስለ ክርስቶስ በታማኝነት በመስበኩ በፍጥሞ ደሴት በግዞት/ተሰዶዶ ነበር ፡፡ በዚያም እያለ ዮሐንስየሚመጣዉን አለም የሚያቀርብ የማያቋርጥ ራዕይን ተቀበለ ፡፡ ታስሮ በነበረበት ጊዜ ዮሐንስ አሁንም በኤፌሶን እያገለገለ ነበር ፤ ይህ የቀድመ ታሪክ የዮሐንስ የሚመጣዉን የስደት እና ተመልሶ የሚመጣዉ እኔ የሚለዉን ተስፋ ለመግለፅ ይረዳል፡፡

የራዕይ መፅኃፍ ቋንቋው ትንቢታዊ ስለሆነ ትልቅ/ሰፊ ነው ፡፡ ጭብጡ/ፍሬ ኃሳቡ ስለ መለዓክት እና ስለ መጨረሻው ዘመን ስነ መለኮታዊ ማስረጃዎችን እንዲሁም ደግሞ “ የአለምን የመጨረሻ የፖለቲካ አቋም፣ የሰዉ ልጅን የመጨረሻ የዉጊያ ታሪክ፣ የክርስቶስ ተቃዋሚዉን/የአዉሬዉን የጊዜ ቆይታ እና የመጨረሻ ሽንፈቱን፣ የክርስቶስን በምድር ላይ የ1,000 አመት መንግስትን፣ የሰማይን እና የዘላለም ሁኔታን ክብርን እና የክፉዎች እና የፃድቃን የመጨረሻ መዳረሻን/ሁኔታን “ ያካትታል ፡፡

ማክአርተር ራዕይን ለመተርጎም አራት አቀራረቦችን አስቀምጧል፡ 1) ወደፊት አሻግሮ ባለመመልከት የጊዜዉን ታሪካዊ ክስተቶችን እንደ መግለጫነት በራዕይ ላይ በሚመለከት የቅድመ መግለጫ አቀራረብ፣ 2) ታሪካዊ አቀራረብ ራዕይን በምልክት/በዉክልና እንደ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ስዕል ያየዋል፣ 3) ሀሳባዊዉ አቀራረብ ራዕይን በመልካም እና በክፉ መካከል እንዳለ እንደ ሰማያዊ ዉጊያ ያየዋል እንዲሁም 4) የወደፊት ናፋቂ አቀራረብ ደግሞ ምዕራፍ (6-22) የወደፊት ስለሆነ ነገር በመረዳት በምልክት ምን እንደሚመጣ ያቀርባል ፡፡ ማክአርቱር አራተኛዉ አመለካከት ብቻ “ የራዕይ አቀራረብ/ጥያቄ ትንቢታዊ እንደሚሆን ትክክለ እንደ ሆነ እና መጽኃፉን እንደ ምዕራፍ (1-3) እና እንደቀረው መጽኃፍ በተመሳሳይ አዉዳዊ ታሪካዊ ዘዴ እንደሚተረጉም “ አመልክቷል ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (1፡ 1-8)፡ “ ራዕይ ክርስቶስን በደስታዉ/በክብሩ ይገልጠዋል፡ 1) በላቀ ክብር (ቁጥር 7-20)፣ 2) እንደ ጌታዋ በቤተ ክርስቲያን ላይ (ምዕራፍ 2, 3)፣ 3) በሁለተኛዉ መምጣቱ ያለ አግባብ ከነገሰባት ከሰይጣን ምድርን መልሶ በመዉሰድ የራሱን መንግስት ይመሰርታል (ምዕራፍ 4-20) እና 4) የዘላለሙን ስርዓት/ሁኔታ እንደሚያበራ (ምዕራፍ 21, 22) “ ፡፡ ዮሐንስ እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠውን ከዚያም ኢየሱስ በመለዓክቱ በኩል ከዮሐንስ ጋር የተጋራዉን አይቶት የነበረዉን እንዲመሰክር ተነገረው (ቁጥር 1-2) ፡፡ በራዕይ ዉስጥ ለመጨረሻው ዘመን የሚያዘጋጁን ሰባት “ ብፁዑነቶች “ አሉ (1፡ 3, 14፡ 13, 16፡ 15, 19፡ 9, 20፡ 6, 22፡ 7, 14) ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሔርመጽኃፉን ለሚያነቡ እና መልዕክቱን ለሚታዘዙት የተለዬ በረከትን እንዳዘጋጀ/ቃል እንደ ገባ “ ያመለክታል (ቁጥር 3) ፡፡

መጽኃፉ በእስያ ለሰባቱ አባያተ ክርስቲያናትን ተደረሳያን ያደረገ ነበር፡ ኤፌሶን፣ ሰምርኔስ፣ ጴርጋሞን፣ ትያጥሮን፣ ሰርዴስ፣ ፌልድልፍያ እና ሎዶቅያ (ቁጥር 4) ፡፡ “ ሰባቱ መናፍስት “ የሚለዉ ሐረግ ኢሳ (11፡ 2) እና “ የመንፈስ ቅዱስን ሰባቱን ጥቅል አገልግሎቶች “ ወይም በዘካ (4፡ 1-10) ሰባቱን መቅረዝ ሊይጠቅስ/ሊያመለክት ይችላል ፡፡ ክርስቶስከሞት የተነሳ (ቁጥር 5) እና ክብሩና ገዢነቱ ለዘላለም የሆነ የእግዚአብሔር በኩር ነው (ቁጥር 6) ፡፡ ቁጥር 7 ሁሉም ሰዉ ስለሚያዩት ንጥቀትን ሳይሆን በደመና ክብር የኢየሱስን ሁለተኛ ተመልሶ መምጣትን (በብሉይ ኪዳን ሻካህናይ ግሎሪን) ይጠቅሳል ፡፡ የወጉት ሁሉ (አይሁዶች) ያዩታል ፤ እግዚአብሄር ከሁሉም የሚበልጥ የዘላለም አምላክ ነው (ቁጥር 8) ፡፡

ራዕይ (1፡ 9-20)፡ እነዚህ ጥቅሶች በዮሐንስ ራዕይ የክርስቶስን የሚያምር የሚያስደንቅ መልክ ያሳያሉ ፡፡ ዮሐንስ ዮሐንስ በእግዚአብሔር መንፈስ መገኘት ዉስጥ እንደ ነበር እንደ መለከት አይነት ድምጽ ሰማ ፤ ራዕዩን እንዲጽፈዉ እና በእስያ ላሉት አብያተ ክርስቲያናት እንዲልከዉ ተነገረው ፡፡ ምናልባትም ሰባቱ መቅረዞች ቤተ ክርስቲያንን ያመለክቷሉ (ቁጥር 12) ክርስቶስም እንደ ሊቀ ካህን በወርቅ መታጠቂያ ካባን የለበሰ ነው (ቁጥር 13) ፡፡ ፀጉር ነጭ ነበር (ዳንኤል 7) እና አይኖቹም ወደ ቤተ ክርስቲያን ዘልቀዉ የሚመለከቱ ልክ እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ (ቁጥር 14) ፤ ድምጹም ወደ ብዙ የዉኃዎች ድምጽ ተቀየረ (ቁጥር 15) ፡፡ በቁጥር 15 ላይ ፍርድ የሚታይ ሲሆን ክርስቶስ ሰባቱን ከዋክብት በእጁ ይዞአቸዉ ታይቷል (ቁጥር 16) ፡፡ ዮሐንስ ልክ እንደ ሞተ ሰዉ በኢየሱስ እግር ስር በመዉደቅ ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 17) ፤ ኢየሱስም ራሱን እኔ ፊተኛና ኋለኛ ሞቶ እንደ ነበር ነገር ግን ለዘላለም ህያዉ እንደ ሆነ በመናገር ለዬ (ቁጥር 18) ፡፡ እግዚአብሔር ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት (ለሰባቱ መቅረዞች) የመለዓክ መልዕክተኞቹን (ሰባቱን ከዋክብት) ስለሚልክ የሚያስፈራ ምንም ነገር አይኖርም (ቁጥር 19-20) ፡፡

መደምደሚያ

ይህ ለቀረዉ ለራዕይ መጽሃፍ ደረጃን ያስቀምጣል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1989.

  2. MacArthur, p. 1989.

  3. MacArthur, p. 1989.

  4. MacArthur, p. 1989.

  5. MacArthur, p. 1989.

  6. MacArthur, p. 1989-1990.

  7. MacArthur, p. 1990.

  8. MacArthur, p. 1990-1991.

  9. MacArthur, p. 1991.

  10. MacArthur, p. 1991.

  11. MacArthur, p. 1992.

  12. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p.567.

  13. MacArthur, p. 1993.

ጥያቄዎች

  1. ይህ መጽሃፍ የኢየሱስ ክርስቶስ ራዕይ ነው (ራዕ 1፡ 1) ፤ በሁሉም ገፅ ላይ የተገለጠዉን ለምን መመልከት እንዳለብን ምን ታስባላችሁ ? በራዕይ (1፡ 19) ዮሐንስ አይቶት የነበረዉ ምን እንደ ነበር እና ምን እንደሚፈጥር እንዲጽፈው ታዘዘ
  2. በራዕ (1፡ 3) መጽኃፍ “ ጊዜዉ ቀርቧል “ ይላል ፤ ያኔ ጊዜው “ ቅርብ “ ከነበር አሁን ምን ያክል ቀርቧል ? ጊዜዉ ከጌታ መመለስ በፊት በማጠር እያደገ እንደሆነ ትስማማላችሁ ? ይህ ኢየሱስ ነገ ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል ማሰብ እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጋችኋል ? ተዘጋጅታችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አልተዘጋጃችሁም ?
  3. ራዕ (1፡ 7) እንዴት እንደሚሆን ምን ታስባላችሁ ? እንዲያዩት “ ለሁሉም አይን “ የተቻለ እንደሚሆን ወይም ባንቀላፉት ብቻ ማለት እንደ ሆነ ታስባላችሁ ? ስለዚያ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በራዕ (1፡ 16) ከሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ አስፈላጊነት ምንድን ነው ? በመጽሃፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ይህ ሰይፍ ተጠቅሷል ? (ኤፌ 6፡ 17, ዕብ 4፡ 12)
  5. በራዕ (1፡ 18) እንዳለው ኢየሱስ የሲዖልን መክፈቻ የት ስፍራ ላይ ተቀበለ/አገኘ ? (ኤፌ 4፡ 8-9, 1ጴጥ 3፡ 19-20, ራዕ 20፡ 1-2)
  6. በራዕይ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 1:3

“The one who reads this is blessed, and those who hear the words of this prophecy and keep what is written in it are blessed, because the time is near!”

እግዚአብሔር ለሐዋርያው ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ይመሰክር ዘንድ ራዕይን ሰጠው፡፡ የራዕይ መጽሐፍ ጌታ ለዮሐንስ ስለሰጠው ራዕይ ይናገራል፡፡ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው፡፡

ምናልባት የራዕይ መጽሐፍ ለእናንተ እንደማይሰራ ታስቡ ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ ከእናንተ አስተሳሰብ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ ምናልባት ስለ ራዕይ መጽሐፍ መሰብ ስትጀምሩ ፍርሀት ይሰማችሁ ይሆናል፡፡ሆኖም ግን ዮሐንስ አንባቢዎቹን እንዲህ በማለት ይመክራል፡- ዘመኑ ቀርቦልና በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን የሚጠብቁ ብጹዓን ናቸው፡፡ ዮሐንስ ይህንን ስለ ኢየሱስ በኃይል በመመስከር ተከተለ፡፡ ዛሬ የዮሐንስን ክርስቶስን አገላለጽ ስታነቡ እግዚአብሔር ራዕዩን ትረዱ ዘንድ ልባችሁን እንድያሰፋ ጸልዩ፡፡ ኢየሱስ የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የታመነ ምስክር ነው፣ እርሱ ከሙታን በኩርና የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነው፡፡ ኢየሱስ ይወዳችኋል ከኃጢአትም ያነጻችኋል፡፡ እርሱ ለአምላኩና ለአባቱ መንግሥትና ካህናት አድርጓችኋል፡፡ ኢየሱስ በደመናት ላይ ይመጣል፡፡ እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነው፡፡ እርሱ የሚኖር ነው፤ እርሱ ዘላለማዊ ነው፤ እርሱ የሞትና የሲዖል መክፈቻ አለው፡፡ ኃይለኛውን የኢየሱስን ስም አመስግኑ! ወደ መገኘቱ እርሱን ለማምለክ ስትገቡ በፊቱ ውደቁ፡፡

“ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው። ”

- ራዕይ 1፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ማቴዎስ 5:6 — “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።”
  • ራዕይ 1:4–6 — “ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።”
  • ራዕይ 1:17–18 — “ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።”