The First Four Church Letters
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ራዕይ የማጥናት እዉነታው መጽኃፉን ምን ያክል ጊዜ እንደምጣጠኑት ሳይሆን ሁል ጊዜ ወደኋላ በመመለስ ብዙ መማር መቻላችሁ ነው ፡፡ በምዕራፍ 2 በእስያ የሚሸፈኑ አራት አብያተ ክርስቲያናት አሉ ፡፡ በራዕይ ( 1፡ 19) ዮሐንስ “ ያሉትን እና የሚመጡት አይቷቸዉ የነበሩትን ነገሮች እንዲፅፋቸው “ ታዝዞ ነበር ፤ ነገሮቹ በቤተ ክርስቲያን ዘመን የነበሩ እና የኃይማኖትን የፀጋ ስርዓት የጣሱ ነበሩ (ኤፌ 3፡ 2) ፡፡ ያም የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን እና የአሁኗን ቤተ ክርስቲያን ያካትታል ፡፡ የራዕይ መጽኃፍ የእግዚአብሔርን መሪ እቅድንም በአንድ ላይ ይስላል ፡፡ እግዚአብሔር ተመልሶ መምጣት ወሰን ላይ ነው ፡፡ ከፍጥሞ ደሴት ዮሐንስ ስለ እያንዳንዳቸዉ ቤተ ክርስቲያን ከቀረበለት መረጃ የተነሳ ለመጎብኘት በዚያኑ መንገድ በእስያ ያሉትን እያንዳንዳቸዉን አብያተ ክርስቲያናት ደረሳቸው ፤ ዮሐንስ ለእያንዳንዳቸዉ ቤተ ክርስቲያን በሚፅፍ ጊዜ የተለየ መንገድን ተጠቅሟል፡ 1) የቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ፣ 2) የክርስቶስ ባህሪይ፣ 3) ቤተ ክርስቲያን ፈፅማዉ ስለ ነበረዉ መልካም ነገር አድናቆት፣ 4)ቤተ ክርስቲያን ፈፅማዉ ስለ ነበረዉ መጥፎ ነገር ክስ፣ 5) ቤተ ክርስቲያን ምን ማድረግ እንዳለባት ስለ ማስተካከያው፣ 6) መንፈስ ቅዱስ ምን እያለ እንደ ነበር እንድትሰማ ለቤተ ክርስቲያን ጥሪ እና 7) ቤተ ክርስቲያን ትፈፀመዉ ስለ ነበረዉ ነገር ፈተና ፡፡
የስነ መለኮታዊያን ሚና መጽኃፍን በማጥናት ማን ማለት እንደ ሆነ መተርጎም ነው ፡፡ 65 የመጽኃፍ ቅዱስ መጽኃፍትን ካጠናን በኋላ በእነዚህ ፅኁፎች ዉስጥ እግዚአብሔር ምን ማለቱ እንደ ሆነ የመጠየቅ መብት አለን ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (2፡ 1-7)፡ ያልታወቀ ስለ ራዕይ መጽኃፍ ዝርዝር ብዙ ነገር አለ ፡፡ ቁጥር 1 በኤፌሶን ያለችን ቤተ ክርስቲያንን በመድረስ ኢየሱስ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት በመያዝ በሰባቱ የወርቅ መቅረዞች (ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት) መካከል እንደተጓዘ ያመለክታል ፡፡ ዮሐንስ በኤፌሶን የቤተ ክርስቲያንን ስራ ያውቃል (ቁጥር 2) ፤ ስለ ክርስቶስ ሲሉ ምንን ለማድግ እንደተዘጋጁ እና ፍቃደኞች እንደ ነበሩ ያውቃል ፡፡ እርስ በእርሳቸው የተለያዩት ከእነዚህ ቤተ ክርስቲያናት ዉስጥ ሁሉም መልካም/ጥሩ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን የተወሰዱ እንደ ነበሩ አምናለሁ ፡፡ ቤተ ክርስቲያን መከራን ታግሳ የነበርና አሁን ቀጥላለች (ቁጥር 3) ፡፡
ይሁን እንጂ በኤፌሶን የነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን ከበፊቷ ፍቅር ተመልሳ/ዞራ ነበር (ቁጥር 4) ፤ አስደናቂ ቤተ ክርስቲያን ነበረች ነገር ግን ክርስቶስ ከማስቀደሟ ተመልሳ ነበር ፡፡ ዮሐንስ ከክርስቶስ ርቀዉ በመዉደቃቸው በመገሰፅ ንስኃ በመግባት ለእርሱ “ መጀመሪያ ወደሚሰሩት “ ስራቸዉ እንዲመለሱ አዘዛቸው (ቁጥር 5) ፡፡ በዚህ ጉዳይ “ ንስኃ መግባት “ ማለት በክርስቶስ ላይ በተቃራኒዉ ይደረጉ ከነበሩት ነገሮች በመመለስ ወደ ክርስቶስ መመለስ ማለት ነው ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ንስኃ ካልገባች ከቤተ ክርስቲያኗ ክርስቶስ መቅረዛቸዉን ያስወግዳል ፤ ያ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንን ይገድላል ፡፡ እግዚአብሔር ለማድረግ የማይፈቅደዉን ነገር አያስፈራራም ፡፡
በቁጥር 6 ለኒቆላዊያን ማጣቀሻ ተደርጓል ፤ ምናልባትም ይህ የተጠላ ስጥር እና ተገቢ ያልሆነ ወሲባዊ ተግባር፣ የሐሰተ አስተምሮ ማስተማር እና ለጣዖት ተሰዉቶ የነበረን ምግብ መብላት ነበሩ ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ በአስተምሮዉ ተይዛ ነበር ነገር ግን ለጠፉት ፍላጎት/መነሳሳት አልነበረም ፡፡ ስለ ክርስቶስ መከራዉን የሚቋቋሙ የዘላለም ሕይወት ተስፋ ተገብቶላቸዋል ( “ የሕይወትን ዛፍ እንዲበሉ “ ) (ቁጥር 7) ፡፡
ራዕይ (2፡ 8-11)፡ በቁጥር 8 ዮሐንስ በሰምርኔስ ላለች ቤተ ክርስቲያን ፃፈ ፡፡ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያንን ስራ እና መከራዋን ያውቃል ፤ እንዲሁም ሰይጣን የነበሩ ነገር ግን አይሁድ እንደ ሆኑ የሚናገሩትንም ስድብ ያውቃል (ቁጥር 9) ፡፡ በግልፅ በሰምርኔስ ከአይሁዳዊያን መናፍቅ የመጣዉ ኃይለኛ ተቃዉሞ በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ብዙ መከራዎችን አምጥቶባት ነበር ፡፡ ዮሐንስ ክርስቲያኖች መከራ እንደሚደርስባቸዉ ነገር ግን እንደማይፈሩ አስጠነቀቃቸው ፤ ወደ እስር ቤት ይጣላሉ፣ ይደክማሉ ከአስር ቀንም በኋላ ይገደላሉ ፤ ይሁን እንጂ ለሞትም እንኳን የታመኑ ይሆናሉ ከዚያም የሕይወትን የክብር ዘዉድ/አክሊል ይቀበላሉ (ቁጥር 10) ፡፡
ራዕይ (2፡ 12-17)፡ በቁጥር 12 ዮሐንስ በጴርጋሞን ላለች ቤተ ክርስቲያን በመፃፍ የኢየሱስ መልዕክት ከሁለቱም በኩል እንደተሳለ ሰይፍ እንደ ነበር ገለፀላቸው ፡፡ ኢየሱስ የቤተ ክርስቲያኗን ስራ እና ሕዝቡ የሰይጣን ዙፋን በነበረበት ስፍራ (ምናልባትም የባቢሎናዊያን ባህል ማዕከል) እንደሚኖሩ ያውቃል ፡፡ ዮሐንስ ስለ ስራቸዉ ቤተ ክርስቲያንን በማመስገን ወደ ማዉገዝ ሄደ ፤ የበለዓም እና የባለቅ መጠቀስ በቤተ ክርስቲያኗ ዉስጥ ጥንካሬን ስለማምጣት ነው ፤ ቤተ ክርስቲያኗ በጥንኳሬዋ የተጠቃች ልትሆን አትችልም ነገር ግን በድክመቷ ግን የተጠቃች ልትሆን ትችላለች (ቁጥር 14) ፡፡ ለቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን ድክመቶቿ የወሲብ ኃጢዓት፣ ራስን ማሞላቀቅ እና ለጣዖት ስጋን መሰዋት ነበሩ (ቁጥር 14) ፡፡
በእዉነታዉ እነዚህ ነገሮች አሁንም በቤተ ክርስቲያናችን ዛሬም የሚገጥሙን ነገሮች ናቸው ፡፡ የቤተ ክርስቲያናችሁ ጥንቃሬዎች ምንድን ናቸው ድክመቶቿስ ምንድን ናቸው ? በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን የገጠማት ሁኔታ ዛሬም አልተቀየረም ፡፡
በጴርጋሞን ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን በኤፊሶን እንደ ነበረችዉ በኒቆላዉያን ጉዳይ የተያዙ አልነበሩም ነገር ግን አስተምሯቸዉን በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ፈቅደው ነበር (ቁጥር 15) ፡፡ ዮሐንስ ወዲያዉኑ ወደ ንስኃ ጠራቸው (ቁጥር 16) ፡፡ “ ነጭ ድንጋይ “ የሚለዉ ሐረግ ምን ማለት እንደሆነ አናዉቅም በነገሩም ዉስጥ መቆየት/መኖር አያስፈልገንም ፡፡ ልናዉቃቸዉ የማንችላዉ ትንቢታዊ ነገሮች አሉ ፡፡
ራዕይ (2፡ 18-29)፡ በቁጥር 18 ዮሐንስ በትያጥሮን ላለች ቤተ ክርስቲያን ፃፈ ፡፡ ዮሐንስ ስርዓቱን/ሂደቱን በመከተል መልካም ስራቸዉን፣ ልግስናቸዉን፣ አገልግሎታቸዉን፣ እምነታቸዉን እና ትዕግስታቸዉን እዉቅና ሰጠ (ቁጥር 19) ፡፡ በጊዜ ብዛትም የተሻለ አግኝተዉ ነበር ፤ ከዚያም ዉግዘቱን/ግሳፄዉን ሰጣቸው ፡፡ ሕዝቡ በወሲባዊ ኃጢዓት የተሳቡ እና ያለምንም ፀጸት እና ንስኃ ለጣዖት ተሰዉቶ የነበረን ስጋ ይበሉ ነበር (ቁጥር 20-21) ፡፡ ዮሐንስ ያለ ንስኃ መከራ እና ሞት ስለሚገጥማቸው ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ኢየሱስ እኔ የሚለዉ እንደሆነ እና በእነርሱም ላይ ኃላፊነት እንዳለዉ እንዲያዉቁ ይገልፃል (ቁጥር 23) ፡፡ በመቀጠልም ዮሐንስ ተስፋን አቀረበ - በእነዚህ ኃጢዓቶች ጥፋተኞች ያልነበሩ ተመሳሳይ የሆነ መከራ እንደማይገጥማቸው (ቁጥር 24) ፡፡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቁ በአሕዛብ ላይ ሁሉ ስልጣንን በመሰጠት የተባረኩ ይሆናሉ “ የንጋትም ኮኮብ “ የተሰጣቸው ይሆናሉ (ቁጥር 28) ፡፡
መደምደሚያ
በዚህ ምዕራፍ ላይ እግዚአብሔር ምን እንደሚላችሁ ማየታችሁን እንድትቀጥሉ እፀልያለሁ ፡፡
ጥያቄዎች
-
ኢየሱስ በኤፌሶን ያለችዉን ቤተ ክርስቲያን ስለ ምን አስጠነቀቀ ? በእነርሱ ላይ ምን ተፈጥሮ ነበር (ራዕ 2፡ 4-5) ? ምን እንዲያደርጉ ነገራቸው ?
-
በሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን ምን እየሆነ ነበር ኢየሱስስ እንዴት አጽናናቸው ? ስለ እምነታችሁ እንደ ተሳደዳችሀሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በሰምርኔስ ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን እየደረሰባት ከነበረዉ ጋር ወይም በአሁኑ ስዓት በአንዳንድ በአለም ክፍሎች ክርስቲያኖች ከሚደርስባቸዉ ጋር እንዴት ታወዳድሩታላችሁ (ራዕ 2፡ 9-10) ?
-
በጴርጋሞን ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን ከእነርሱ መካከል በሰማዕትነት ቢያልፉም እንኳን የኢየሱስን ስም ባለመካድ የታመኑ ነበሩ ፤ በአሁኑ ጊዜ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት የሚያደርጉት እያደረጉት የነበረዉ ስህተት ምን ነበር (ራዕ 2፡ 14-15) ?
-
የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን በትክክል እያደረጓቸዉ ከነበሩት ጥቂት ነገሮችን ጥቀሱ (ራዕ 2፡ 19) ? እነዚህ ነገሮች እያሉ ዉድቀታቸዉ ምን ነበር (ራዕ 2፡ 20-21) ?
-
ከክፉ ስራቸዉ የማይመለሱ ከሆነ በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ ምን እንደሚሆን ዮሐንስ ባለዉ ላይ ተመልሳችሁ ተመልከቱ ፤ መሆን ያለባቸዉን እግዚአብሔርን መዉደድን እና ሰዉን መዉደድን በጣሉ አብያተ ክርስቲያናት ልትገኙ/ልትታደሙ ትችላላችሁ፣ እዉነትን የሚያመቻምቸው ወይስ በትምህርታቸው የተበከለው ማነው ?
-
በራዕይ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 2:29
“Anyone who has an ear should listen to what the Spirit says to the churches.”
ዮሐንስ ደብዳቤውን ለመጻፍና ለሰባቱ ቤተ ክርስቲያናት ለማድረስ፣ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ትዕዛዝ ተከተለ፡፡ እግዚአብሔርም ለኤፌሶን፣ ለሰምርኔስ፣ ለጴርጋሞን እና ለትያጥሮን ሲናገር ራሱ ይህንን ሀረግ ደጋግሞ ይል ነበር ፡- “ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህን…….አውቃለሁ” አዎን በርግጥም እግዚአብሔር ጥንካሬቸውን፣ ስራቸውን ደግሞም በመከራና በፈተና ውስጥ እንዴት ጸንተው እንደቆሙ በተጨማሪም እንዴት እንደወደቁ ያውቅ ነበር፡፡ እያንዳንዷ ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር የተለያያ ነቀፌታን ተቀብላለች፡፡ አንዳንዶቹን ንስሀ እንድገቡ ይነግራቸዋል፡፡ ሌሎቹን ደግሞ አሸናፊዎች ስለሚሆኑና የህይወትን አክሊል ስለሚቀበሉ እንድጸኑና እስከሞት እንድታመኑ ይመክራቸዋል፡፡ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያናቱን በዚህ ቃል ያሳስባቸዋል ፡- “መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ፡፡”
ከጌታ ወይም ደግሞ በጓደኛ ምክር ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባያችሁት ፓስት ኃጢአትን እየሰራችሁ እንደሆነ የሚናገር መልዕክት ቢደርሳችሁ ቸል በማለት ወደ ሌላኛው መንገድ አትሂዱ፡፡ ለመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ታዘዙ፡፡ ምናልባት እናንተም እንደ ኤፌሶን፣ ጴርጋሞንና ትያጥሮን ቤተክርስቲያን ንስሀ ልትገቡና ወደ ቀድሞ ፍቅራችሁ ወደ ኢየሱስ ልትመለሱ ያስፈልጋችኋል ይሆናል፡፡ አስታውሱ እግዚአብሔር ያውቃችኋል፡፡ እግዚአብሔር ስራችሁን፣ ፍቅራችሁን፣ እምነታችሁንና ትዕግስታችሁን ያውቃል፡፡ እርሱ መከራችሁንና ችግራችሁን ያውቃል፡፡
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።”
- ራዕይ 2፡29
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 26:2 — “ አቤቱ፥ ፍተነኝ መርምረኝም፤ ኵላሊቴንና ልቤን ፍተን።”
ሐዋርያት ሥራ 3:19 — “እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ፣ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።”
ራዕይ 2:4 — “ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።