Letters To Three More Churches
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ በቀጣዮቹ ሰዎስት አብያተ ክርስቲያናት ላይ በመመልከት እንቀጥላለን ፡፡ በዳሰሳ በኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ላይ ፍቅር የሌላት ቤተ ክርስቲያንን፣ በሰምርኔስ ሚዛናዊነት የሌላትን ቤተ ክርስቲያን፣ በጴርጋሞን የምታመቻምች ቤተ ክርስቲያንን እና በትያጥሮን በስነ-ምግባር የምታመቻምች ቤተ ክርስቲያንን ተመልክተናል ፡፡ ዮሐንስ በቴኒይ ያደገዉንወጥ የሆነዉን መመሪያን ተጠቅሟል፡ 1) ተልዕኮን፣ 2) ባህሪን፣ 3) ምስጋና፣ 4) ማዉገዝ፣ 5) ማስተካከል፣ 6) ጥሪ እና 7) መሞገት ፡፡ በአሁኑ ጊዜ መሞገት እና ጥሪ የተገለበጡ/የተቀያየሩ ናቸው ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (3፡ 1-6)፡ በመቀጠልም ዮሐንስ በሰርዴስም ያለችን ቤተ ክርስቲያን ደረሰ ፡፡ በቁጥር 1 ኢየሱስ ራሱን ለዮሐንስ “ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስትና ሰባቱ ከዋክብት ያሉት “ በማለት ይገልፃል ፡፡ በሙት/በጨዉ ባህር ጥቅል የተገኘዉ ከዕብራዉያን ፅሁፎች አንዱ 1ሄኖክ (20፡ 1-8) መጽኃፍ ሰባቱን መለዓክት ይጠቅሳቸዋል፡ ኡራኤል፣ ራፋኤል፣ ራጉኤል፣ ሚካኤል፣ ሳርኤል፣ ገብርኤል እና ራሚኤል ፡፡ በራዕ (8፡ 2) እነዚህ መለከቱን የነፉት መለዓክቶች ናቸው ፡፡ በራዕይ መጽኃፍት ዉስጥ ሰባት ቁጥር ጥቅም ላይ የዋለ ነው ፤ እስካሁን ሰባቱን መናፍስት/ሰባቱን ከዋክብት፣ የመንፈስ ሰባቱን የስራ ጥቅሎችን(ኢሳ 11፡ 2) እና የአይሁዶች ልምድ ሰባት ሊቀ መላዓክትን አይተናል ፡፡ በራዕይ (4-5) ሌላ ብዙ ሰባቶች ይመጣሉ ፡፡
ኢየሱስ ሰርዴስን ስለ ስራቸዉ እና እየኖረ ስላለዉ ዝናቸው አመሰገናቸው ፡፡ ስለ እያንዳንዳቸዉ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠው ሁሉም ነገር ስለ ከተማዎቹ እና ስለ ሁኔታው መረጃን ይሰጣል ፡፡ በኤፌሶን እና በሰርዴስን ቤተ ክርስቲያናት መካከል አንዳንድ ተመሳሳይነትን ትፅፉ ይሆናል ፤ ሰርዴስ ከኤፌሶን ሰሜን ምስራቅ 50 ማይል የምትገኝ ሲሆን መልከዓ ምድራዊያ ዳራዋ ሰዎስት ዋና ዋና ምልክቶችን ይዟል፡ 1) ከከተማዋ 800 ጫማ ከፍ ያለዉ እና የተፈጥሮ ምሽግ የሚሰራ በሰዎስቱ ጎኑ/በኩል ቀጥ ብሎ የቆመ አለት የነበረው የተጠናከረዉ ምሽግ፣ 2) አልቆ ያልነበረዉ እና ለካቤል( የሞቱትን ወደ ሕይወት የመመለስ ኃይል እንዳለዉ ይታመንበት ለነበረዉ አማልዕክት) በቀድሞዉ ቤተ መቅደስ ላይ የተገነባዉ ቤተ መቅደስ እና 3) የ1,000 ኮረብታዎች የሙታን መገናኛ ስፍራዎች - ከከተማዋ ሰባት ማይል በሰማይ ላይ ሊታይ የሚችል የመቃብር ድንጋይ ፡፡ በመቀጠልም ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ህያዉ እንደምትሆን ብታምንም እንኳን እንደ ሞተች ተግሳፅን ሰጣቸው ፡፡ ቤተ ክርስቲያን በዉስጧ በመሞት በህይወት በዉጫዊ መልክ ተቀምጣ ነበር ፤ አንዳንዶች ይህ ከሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ከፋ ዉግዘት ያዩታል (ቁጥር 3) ፡፡ ሰርዴስ የትዕቢት፣ የመኩራራት እና በኃይለኛው በቀድሞዉ አፈፃጸማቸዉ እና ዝናቸዉ የሚደገፉበት የብልፅግና ከተማ ነበረች ፡፡ አደጋው አሁን ቤተ ክርስቲያኗ ክርስቶስን ከማናፀባረቅ በላይ ከተማዋን ማንፀባረቋ ነበር፡፡
ከሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ዉስጥ አምስቱ መታደስ አሰፈለጋቸው ያም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከ60 አመታት በኋላ ብቻ ነበር ፤ የቤተ ክርስቲያን ማደስ ችግሩ ምንም አዲስ ነገር አለመኖሩ ነው ፡፡ ስለዚህ በስም ብቻ ሙሽራ የነበረዉን ጉባኤ በሚያስብ ጊዜ የእግዚአብሔር ልብ አዘነ ፡፡ ኢየሱስ በጥቃት ስር ስለ ነበሩ በአስቸኳይ መንቃት እንዲያስፈልጋቸዉ ነገራቸው ፤ ነቅተዉ መጠበቅ/መቀመጥ አስፈለጋቸው (ቁጥር 3) ፡፡ ኢየሱስ ቀድሞ ገጥማቸዉ የነበረዉ ጥቃት በከተማዋ ላይ እንደሚሆን አሳሰባቸው ፡፡ አንድ ታሪክ ቂሮስ ለመዉጣት በጣም ከፍ ያለ/የሚያስፈራ ትልቅ ምሽግ ቀጥ ብለዉ ከቆሙት ግንቦች ዉስጥ በአንዱ ስንጥቅ የሚወጣን እንዴት እንደላከ ይነግረናል ፤ ቆይቶም ተመሳሳይ ነገር በሮም ሆኗል ፡፡ ማስጠንቀቂያው ራስን ደህና እንደሆኑ በመመልከት ተጠንቅቆ መቀመጥ ጥፋትን ያመጣ እንደ ነበር ነው ፡፡ ከክርስቶስ ሞት 17አመት በኋላ ሰርዴስ አደገኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ገጥሟታል ፤ በኃላም ከተማዋ በአጼ ጠበሪያስ በሚታይ ድጋፍ/ርዳታ መልሳ ተገንብታ ነበር ነገር ግን በፍጹም ሙሉ በሙሉ አልታደሰችም ፡፡ በእርግጥም ከተማዋ ያልተሟላ ሆኗ ተቀመጠች በፍጹምም ሙሉ በሙሉ መልሳ አልተከነባችም ነበር ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ የነቃች/የተጠነቀቀች ካልሆነች ኢየሱስ ሊፈርድ በማይታይ ክስተት ይመጣባቸዋል ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በግዴለሽነት ትፈተናለች ፡፡ ለመቀጠል ምን አይነት መልክ አለን ? ከማንመለከተዉ ስፍራ የሚመጣ የእባብ ጥቃት አለ ? በዉስጣችን የሞትን ነን ? የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን በመታመን የተመላለሱ እና የተገባቸዉ ስለሆኑ ከክርስቶስ ጋር በነጩ የሚመላለሱ ጥቂት ሰዎች (ቅሬታዎች) ነበሯት (ቁጥር 4) ፡፡ በእስያ ግዛት አፈር የነካዉ/የቆሸሸ ልብስ አምላኪዉን የሚያስባርር እና አማልዕክቱን የማያከበር ነበር ፤ ነጭ ልብሶች የንፅህና እና የድል አድራጊነት ተምሳሌት ነበሩ (ራዕ 19፡ 8) ፡፡ ነጭ ልብስ በራዕይ ዉስጥ ሰባት ጊዜ የተጠቀሰ ነው (3፡ 4-5, 4፡ 4, 6፡ 11, 7፡ 9 እና 19፡ 14) ፡፡ ትግሉ/ፈተናው ታማኝ ሆኖ በመቀጠል/በመገኘት ድል አድራጊ መሆን ነበር ፡፡ ስለ መታመናቸዉም ስማቸዉ በሕይወት መጽኃፍ ላይ ይመዘገባል (ይጨመራል) (ቁጥር 5) ፡፡ መልዕክቱ እንድንሰማዉ ለሁላችንም አስፈላጊ/ጠቃሚ ነው ፡፡ የመጀመሪያው ማጣቀሻ ስለ ሕይወት መጽኃፍ በዘጸ (32፡ 32-33) ነው ፡፡
ራዕይ (3፡ 7-13)፡ ከዚያም ዮሐንስ በሰርዴስ ከተማ ተመሳሳይ ሸለቆ በምስራቅ መጨረሻ ላይ የምትገኘዉን በፊልድልፍያ ያለችዉን ቤተ ክርስቲያን ደረሰ ፡፡ ፊልድልፍያ የንግድ መስመሮች መገናኛ ላይ የምትገኝ ነበረች - ከሮም የነገስታት ቋሚ መንገድ በከተማ ዉስጥ ማለፉ “ ወደ ምስራቅ መግቢያ በር “ የሚልን ስያሜ አስገኝቶላታል፡፡ ከተማዋ የንግድ ጠቃሚነት ነበራት ፤ ከከተማዋ በስተ ሰሜን ወይን ይበቅልበት የነበረ ለም ሜዳ ነበር ፤ ይህም የወንድሙን መሰጠት እና የታማኝነት መስዋዕትነቱን ለማስታወስ በንጉስ ጴርጋሙም የተመሰረተ ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ ስፍራው የመሬት መንቀጥቀጥ የሚደርስበት እና ከክርስቶስ ሞት 17 በኋላ አስከፊ የመሬት መንቀጥቀጥ የደረሰበት ነበር ፡፡ በተጨማሪም በአምስተኛዉ ክፍለ ዘመን ብዙ ቤተ መቅደሶች ስለ ነበሩት “ ትንሺቱ አቴን “ በመባል ትታወቅ ነበር ፡፡ በዚያ ወይን ይበቅል ስለ ነበር አለቃዉ አማልዕክት ይመለክ ነበር፣ ዳይንሱስ የወይን እና የምርታማለት/የለምነት አማልዕክት ነበር ?
እንደ ገና እኔ የሚለዉ ኢየሱስ ቤተ ክርስታኗን ደረሰ ፡፡ ይህ መግለጫ ኢየሱስን የዳዊት ቁልፍ የያዘ እንደሆን ያካትታል ፡፡ ቁልፍ የሚለዉ ቃልቁልፍን/መፍቻዉን እና ጋኑንም አካትቷል (ቁጥር 7) ፤ ያም መሲሁ የዘላለም መንግስትን ማግኛን እንደሚቆጣጠር ስለሚያወራዉ እዉነት ይስባል ፡፡ ኢየሱስ ከአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ማንኛዉንም ሰዉ ያለማስገባት ወይም የማስገባት የማይሻር ስልጣን አለው ፤ ይህ ለሕዝቅኤልን ዳኝነት ፀኃፊ ለኤልያቄም ተደርጎ የነበረዉ ተስፋ ቀጥተኛ ማጣቀሻ/ማሳያ ነው ፡፡ ኢየሱስታማኝነታቸዉን ወደ ተከፈተዉ በር መግባትን በመስጠት እዉቅና ሰጣቸው ፤ ምንም እንኳን የደከመ ጥንካሬ/ኃይል ቢኖርም ቤተ ክርስቲያኗ የክርስቶስ ስም ክህደትን ተቃዉማ እና የተወገደም እንዲሆን የምትፈቅድ አልነበረችም (ቁጥር 8) ፡፡ በመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በበር መዋቅር ላይ መሆን ደህንነት ያለበት ስፍራ እንደሆነ አስታዉሱ ፡፡
እግዚአብሔር ከሰይጣን የመጡትን በክርስቲያኖች እግር ስር እንዲደፉ ያደርጋቸዋል ፡፡ ቁጥር (9-10) በቤተ ክርስቲያን እና “ በሰይጣን ማህበር “ መካከል የሚደረገዉን ኃይለኛ ግጭትን ያመለክታሉ ፤ ይሁን እንጂ አማኞች በመከራ ጊዜያት ጠንክረዉ ነበር ፡፡ የኃይማኖት ስርዓት ጣሽዎስ ይህንን ፅሁፍ ከመከራዊ በፊት ምጽዓት እንደሚሆን እንደ ማረጋገጫነት ይጠቀሙበታል ነገር ግን የግሪኩ ወደዚያ ትርጓሜ አይመራም ፤ ያም ሀሳባቸዉንም ስህተት መሆኑን አያረጋግጥም ነገር ግን በቁጥር 10 የተረጋገጠ ሊሆን አይችልም ፡፡ ኢየሱስ በፍጥነት ይመጣ እንደ ነበርና ጥንካሬዉም በድክመታቸዉ ላይ እንደሚጨመር ቃል ገባ ፡፡ ይህ በመካከለኛዉ ዘመን እና በዘመናዊዉ ጊዜ ዉስጥ የሙስሊም ወረራ እና በቤተ ክርስቲያን ላይ ጫና ግፊት እያለ በጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያን ምስክሮች መቅረታቸዉ/መኖራቸውን ማስተዋል አስደናቂ ነው ፡፡ ኢየሱስ በሕይወት አክሊል አሸናፊዎች እንደሚያደርጋቸዉ ቃል ገባ፡፡ የተሰጠ ዉግዘት ወይም ማስተካከያ እንዳልነበር አስታዉሉ ፤ ለድል አድራጊ የተሰጡ ሰዎስት ዕጥፍ ፅኁፎች ነበሩ፡ ስለታማኝነታቸዉ የአምላኩን ስም፣ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከዜግነታቸዉ የተነሳ የእግዚአብሔር ከተማ ስም እና ከክርስቶስ ጋር በተለዬ መንገድ ይገናኙ ስለ ነበር የራሱን አዲስ ስም (ራዕ 7፡ 3, 14፡ 1) ፡፡ በፊልድልፍያ ያለችዉ ቤተ ክርስቲያንየታመነች፣ ጀግና እና ትሁት ነበረች ፤ ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ በታላቅ መንገድ እንደሚጠቀምባቸው ቃል ገባ ፡፡ ለማንኛዉም ቤተ ክርስቲያን ለዉጤታማነት ቁልፉ በእኛ ዉስጥ ኃይሉን ከሚያሳየዉ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዉጪ ኃይል የሌለ/አቅመ ቢስ እንደምንሆን ማስተዋል ነው ፡፡
ራዕይ (3፡ 3፡ 14-22)፡ የዮሐንስ ሰባተኛዉ እና የመጨረሻው መልዕክት በሎዶቅያ ላለች ቤተ ክርስቲያን ነበር ፡፡ ይቺ ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ የብልፅግናን ኃይል ይዛ በነበረው በሮም ከተማ ዉስጥ ነበረች ፡፡ ኢየሱስ እንደ ገና እኔ አሜን የሆንኩት በማለት ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ ስራቸዉን ስለሚያውቅ በራድ ወይም ሞቃት እንዳልነበሩ ተናገረ ፤ በአጠቃላይ መታመናቸዉ ለብ ያለ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ከአፉ እንደሚተፋቸዉ ተናገረ ፤ እዚህ ጋር መትፋት የሚለዉ ቃል በኃይል መጥፋት/ማዉጣት ማለት ነው ፡፡ ኃብታቸው ምን ለማድረግ ፍቃደኞች ለነበሩት ነገሮች የገደብ መንስኤ ሆነ (ቁጥር 17) ፡፡ በአካባቢያዊ መልክዓ ምድር ላይ ለብ ያለ የተሻለ ትርጓሜ ነው ፤ በፖል አካባቢ ላይ ለሰሜኑ ሙቅ የምንጭ ዉኃ ጤና ሲሆን ለደቡብ ቀዝቃዛ ንፁህ እና ለመጠጥ የሚሆን የምንጭ ዉኃ ነበር ፡፡ ሎዶቅያ ከደቡብ በስድስት ማይ በመጣዉ የዉኃ ቦይ የማያቋርጥ ችግር ነበረባት ፤ ዉኃው ለብ ያለ፣ ንፁኅ ያልሆነ፣ የማይጠጣ እና ሰዎችን የታመሙ ማድረግ የሚችል ነበር ፡፡ በጣም የበለፀጉ እና ኃያላን ስለ ነበሩ መንፈሳዊ ስኬታማ እንደ ነበሩ ያስባሉ ፤ ስለ ብልፅግናቸዉ የእግዚአብሔርን እይታ ችላ ያሉ ነበሩ ፤ በኃብታቸዉ የታወሩ ስለ ነበሩ በመንፈሳዊነት ድሀ፣ እዉር እና ባዶ/ራቁታቸዉን ነበሩ ፡፡
መደምደሚያ
ዉግዘቶቹ እና ጥሪዎቹ ከእርሱ ጋር መልሰዉ ወደ ትስስር/ግንኙነት የሚያመጡ የእግዚአብሔር የፍቅር ቋንቋዎች ናቸው ፡፡ ንስኃ ግቡ ! ኢየሱስ በበር ቆሞ ያንኳኳል ፤ ድምፁን በመስማት ለእርሱ በሩን የሚከፍትለት ይድናል ፡፡ የምንቋቋም እና ድል አድራጊዎች እንድንሆን የተጠራን እና በእርሱ የዘላለም ህይወት ተስፋ የተገባልን ነን !
Merrill C. Tenney, Interpreting Revelation (Grand Rapids, MI: Wm. B. Erdmans Publishing House, 1951), n.p.
ጥያቄዎች
-
በሰርዴስ ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን ንቁ እና ህያዉ የሆነች ብትመስልም እንኳን በዉስጧ በመንፈሳዊ ነገር ሞታ ነበር ፤ በአሁኑ ጊዜ እንደዚች አይነት ቤተ ክርስቲያን ታውቃላችሁ ? ዮሐንስ በእነርሱ ላይ ምን ይሆናል አለ (ራዕ 3፡ 3) ?
-
በፊልድልፍያ ቤተ ክርስቲያን ጌታ የተደሰተዉ ለምን ነበር ? ምን ተስፋ ሰጣቸዉ/ገባላቸው (ራዕ 3፡ 10) ?
-
ለብ ስላለ ቤተ ክርስቲያን ጌታ ምን አለ (ራዕ 3፡ 15-17) ? የቤተ ክርስቲያናችሁ የሚቀት መጠን ምንድን ነው ?
-
ኢየሱስ እስከ መጨረሻ ለሚታገሱ እና ለሚችሉ ምንን ተስፋ ይሰጣል ? (ራዕ 2፡ 7, 11, 17, 26፣ 3፡ 5, 12, 21)
-
ከእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት የትኛዉ መልዕክት በይበልጥ በቀጥታ ስለ ቤተ ክርስቲያናችሁ ሁኔታ እና ስለ ራሳችሁ መንፈሳዊ ነገር ሁኔታ ይናገራችኋል ? ለመቀየር ምን ታደርጋላችሁ ?
-
በራዕይ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 3:19–20
“As many as I love, I rebuke and discipline. So be committed and repent. Listen! I stand at the door and knock. If anyone hears My voice and opens the door, I will come in to him and have dinner with him, and he with Me.”
ቀጥሎም ዮሐንስ ስለተቀሩት ስለ ሶስቱ ቤተ ክርስቲያኖች ማለትም፡- ስለ ሰርዴስ፣ ስለ ፊልድልፍያና ሎዶቅያ ከጌታ የተቀበለውን ራዕይ በመናገር መልዕክቱን ቀጠለ፡፡ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያንም የተለያየ ሀላፊነትን ሊያስተካክለው የሚገባ ነገር ነበራው ይህም ፡- ለአንዱ እንድነቀና የቀሩትን ሊሞቱ ያሉትን ነገሮች እንድያጸና፤ ለሌላው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በታማኝነት እየጠበቀ በነገር ሁሉ እንድታገስ፣ እንድበረታና በፍቅር ቀና እንድሆን እንድሁም ደግሞ ለሌላኛው ለብ ካለ ህይወት ንስሀ እንድገባ እና ለክርስቶስ እንድቆርጥ፡፡
በተለይም ጌታ ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ አለ ፡- “እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።” ይህ መልዕክት ለእናንተም ነው፡፡ የእረኛውን ድምጽ ታውቁታላችሁን ? ኢየሱስ እንዲህ አለ ፡- “ በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ፣ እኔም አውቃቸዋለሁ እነርሱም ይከተሉኛል፡፡” ዛሬ እናንተ የጌታን ድምጽ ትሰማላችሁን? ጌታ በራችሁን ሲያንኳኳ ትሰማላችሁን? ከስራ ብዛት ትንስ አረፍ በሉና ጊዜ ወስዳችሁ በጸጥታ ተቀመጡ፡፡ ጌታን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፡- ኢየሱስ እኔ ስለ አንተ እንዳውቅ የምትፈልገው ምንድን ነው? እራት አብረን ብንበላ ኖሮ፣ ምን ነበር ምትለኝ? እነዚህን ጥያቄዎች ስትጠይቁ፣ ልክ ከጓደኛችሁ ጋር እንደምታወሩ ቁጭ ብላችሁ አዳምጡ፡፡ ዛሬ የሚመራችሁን፣ የሚያውቃችሁንና የሚወዳችሁን እርሱን አዳምጡት፡፡ ንቁ ደግሞም ተዘጋጁ፡፡
“እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ።እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።”
- ራዕይ 3፡19-20
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ 10:3–4 —ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል “
ራዕይ 3:2–3 — “ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና። እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ፥ ጠብቀውም ንስሐም ግባ። እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸውም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታውቅም።”
ራዕይ 3:15–16 — “በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።