The Throne Room of Heaven
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘፍጥረት የነበረዉ ገነት ወደ መሲሁ በማመልከት ወደ ራዕይ ይቀርባል ፡፡ በራዕይ 4 ዮሐንስ የክርስቶስ ራዕይ ነበረው ፤ ክርስቶስ ዮሐንስን ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያኖቹ እንዲያወራ ነገረው ፡፡ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ከእግዚአብሔር ፊታቸዉን ማዞራቸዉን የቀጠሉትን እስራኤላዊያንን የሚመስሉ ነበሩ ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗቱ በክርስቶስ አምነዋል ነገር ግን የሆነ ስፍራ/ጊዜ ላይ ከእርሱ ዞር ብለዋል ፡፡
ራዕይ (1፡ 19) አጠቃላይ መፅኃፉን ሲያሳይ ምዕራፍ 4 በእያንዳንዳቸዉ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚከናወነዉን ሰዎስተኛዉን ክፍል ይሰጣል ፡፡ በመሰረታዊነት ራዕይ (1፡ 19) “ ቀጥሎ ምን ይከናወናል ? “ የሚለዉን ጥያቄ ይጠይቃል ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ስለሚመጣዉ ነገር ናቸው - ወደ ፍሬአማነት ስለሚመጣዉ የወደፊት ቃል ናቸው ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (4፡ 1-11)፡ ራዕይ 4 በሰማይ ማምለክ ምን እንደሚመስል ራዕይን ይዟል ፡፡ ዮሐንስ ክርስቶስ ከዚህ በኋላ ስለማያንኳኳ የተከፈተ በርን አዬ ፤ የተከፈተዉ በር ወደ እግዚአብሔር መገኘት የተዋጁትን የሚቀበል ራዕይ ነበር ፡፡ የእግዚአብሔር ድምጽ እንደ መለከት ተናገረ ፡፡ እንደ ዋረን ዋይርስቤ ገለፃ ግብዣው በዙፋኑ ላይ የእግዚአብሔር መልክ ነው ፡፡
ቁጥር 2 ዮሐንስ አሁን በመንፈስ ነበር ፡፡ እንደ ማክአርቱር ገለፃ ዮሐንስ ሁሉም ስሜቱ/ህዋሱ በእግዚአብሔር የተወሰደ እንዲሆን ፈቅዷል፡ “ ይህ ህልም አልነበረም ፤ ዮሐንስ ከተለመደ ስሜት ያለፈ/የሚበልጥን ነገር ለመልመድ በመለኮታዊ ኃይል ከቁሳዊዉ አለም ማንቀላፋት ተወስዶ ነበር - እንቅልፍ አልነበረም ፤ መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ራዕይን እንዲቀበል የስሜት አካሉኑ አበረታው (ሐዋ 10፡ 11) “ ፡፡ ሁሉም የዮሐንስ የስሜት ህዋስ /ስሜት የጠነቀሩ ነበሩ ፡፡ ለሁሉም ትንቢታዊ ቃል አንዳንድ ተግባራዊ ስራዎች ይኖራሉ ፤ ይህ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀመጦበት በነበረዉ በሰዎስተኛዉ ሰማይ ላይ ተካሄደ ፡፡
ቁጥር 3 ዙፋኑን ስለ ከበበዉ ነገር ይገልፃል ፤ በዚያ ተቀምጦ የነበረው የከበረ ድንጋይ፣ ኢያስጲድን እና ሰርዲኖንን ይመስል ነበር ፡፡ ኢያስጲድን ልክ እንደ አልማዝ ንፁህ እንደሆነ ብርሌ የተገለፀ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ዮሐንስ ይህን ንፁኅ ማዕድን/ብርሌ (21፡ 11) ምናልባትም በሚያስደንቅ መናፀባረቅ ሁሉንም ቀለም ስፔክትረም የሚያንፀባርቀዉን አልማዝን እያመለከተ እንደ ሆን “ ይናገራል ፡፡ የሰርዲኖን ድንጋይ እሳታማ ቀይ ቀለም ስላለዉ እንደ እሳት ተገልጧል/ተከስቷል ፡፡
በተጨማሪም ማክአርቱር “ ንፁህ አረንጓዴ ቀለም ኢመራልድ የእግዚአብሔርን ዙፋን የከበበዉን ብዙ ቀለም ያለዉን ቀስተ ዳመና እንደዋጠው (ሕዝ 1፡ 28) ፤ ከኖህ ዘመን ቀስተ ዳመና ለቃሉ፣ ለኪዳኑ እና ለኖህ ኪዳን የእግዚአብሔር ታማኝነት ምልክት እንደ ሆነ (ዘፍ 9፡ 12-17) “ ይገልፃል ፡፡ እንደ ሰው በዙፉኑ ላይ የእግዚአብሔርን መልክ መረዳት አስቸጋሪ ነው ፡፡
በኃይል ወንጌልን እየሰበከ ስለ ነበር በአንድ ደሴት ላይ ብቻዉን ተጥሎ እንደ ነበር ዮሐንስ ከአንድ መለዓክ ራዕይን ተቀበለ ፡፡ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነበር፣ ንፁህ የአልማዝ ድንጋይን ይመስላ፣ በአረንጓዴ ቀስተ ዳመና ኢመራልድ ተከቦ ነበር ፤ ዮሐንስ ያየዉ እዉነተኛ መልክ የማይገለፅ ነበር ፡፡
በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ ተጨማሪ 24 ዙፋኖች ነበሩ ፤ ነጭ ካባ የለበሱ እና የወርቅ አክሊል የጫኑ ሽማግሌዎች በእያንዳንዳቸዉ ዙፋኖች ላይ ተቀምጠው ነበር ፤ ምናልባት እነዚህ አንዳንድ ንጽህናን እና ጽድቅን ይወክላሉ ፤ ምናልባት እነዚህ የተቤዡትን ይወክላሉ ፡፡ ማክአርቱር “የእስራኤል ሕዝቦች እስካሁን ስላልዳኑ፣ ስላልከበሩ እና የንግስና በዓላቸዉን ስላልፈፀሙ ጥያቄዉ የትኛዉ መቤዠት/ቤዛነት የሚል እንደ ሆነ ? “ ያመለክታል ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ “ የሽማግሌዎቹ ማንነት በእርግጠኝነት የታወቀ እንዳልሆነ ፤ አንዳንዶች በሰማይ ቤተ ክርስቲያንን ወይም አማኞችን እንደሚወክሉ ያስባሉ ነገር ግን ሽማግሌዎቹን ሰማያዉ የማስተዳደር መማክርት መለዓክትን የሚይዙ እንደሆኑ ማየት የተሻለ እንደሚመስል (ኤር 23፡ 18, 22) “ ይገልፃል ፡፡ ምሁራን የተለያዬ አመለካከት አላቸው ፤ ትርጓሜአቸዉ ምንም ይሁን ምን እግዚአብሔር ዙፉኑን እንዲከቡት እነዚህን 24 እንደመረጠ ይስማማሉ ፡፡
በቁጥር 5 የመብረቅ ብርኃን ተከሰተ ፤ ከዚያም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ተገለጡ/ተከሰቱ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት በሰባቱ መቅረዞች እንደተወከሉትየመንፈስ ቅዱሱን ሰባቱን የስጦታ ባህሪያትን መፈፀምን እንደሚያቀርቡ (ኢሳ 11፡ 2, 3) “ ይገልፃል ፡፡ ማንም በእርግጠኝነት ሰባቱ መናፍስት ምን እንደሚወክሉ አያውቅም ፡፡
በቁጥር 6 ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባህር በዙፋኑ ፊት ነበር ፤ ራዕይ (21፡ 1) ባህሩ ከዚያ በኋላ እንዳማይኖር ይገልፃል ፡፡ ስለዚህ በዙፉኑ ፊት የነበረዉ የብርሌ ምስል ዉኃ አልነበረም ፡፡
አይን የሞላባቸው አራት ፍጥረቶች እና የሚከሰትን ሁሉንም ነገር ማየት የሚችሉ ናቸው ፤ ፍጥረቶቹ እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች ነበሯቸው ፤ በኔልሰን ማብራሪያ መሰረት “ አንበሳ፣ ጥጃ፣ ሰዉ እና ንስር በተለዬ ክርስቶስን መሳላቸው ለአራቱ ወንጌላት እንደ ማሳያነት ተረድቷቸዋል “ ፡፡ ፍጥረቶቹ መዝሙርን ይዘምራሉ ፡፡
ቁጥር 10 ሽማግሌዎቹ አክሊላቸዉን በዙፋኑ ፊት እንደሚያስቀምጡ ይናገራል ፤ ሁሉም ነገር ከእግዚአብሔር የመጣ እንደ ነበር እዉቅናን ሰጡ ፤ ከዚያም ሽማግሌዎቹከአራቱ ፍጥረቶች ጋር መዘመር ጀመሩ ፡፡
መደምደሚያ
ዜማዉ/መዝሙሩ በእግዚአብሔር አምላክ ፊት በማምለክ ክብርን ሁሉ ማምጣት ነበር ፤ ይህ አምልኮ ቀን እና ማታ ይሆናል በፍጹምም አያቆምም ፡፡ ዮሐንስ እነዚህን ምስሎች ሁሉንም እንዲጽፈዉ የሚነግረዉ በሌለበት አየ ፡፡ የነበሩት ሁሉም የህያዉ እግዚአብሔርን መገኘት አይተዋል/ቀምሰዋል ፡፡ እግዚአብሔር ብቻዉ ክብር፣ ኃይል እና አክብሮት መቀበል የተገባዉ ነበር ፡፡
ራዕይ 1 ዮሐንስ ከክርስቶስ ራዕይ የተቀበለበት ነው ፤ ራዕይ (2-3) አይኖቻቸዉን በክርስቶስ ላይ እንዲያደርጉ ስለ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው ፡፡
ራዕይ 4 ቀርበዉ/ይታዩ የነበሩትን እና እየተካሄደ የነበረዉን የዙፋኑን የዮሐንስን እይታ ይገልፃል ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament: Ephesians-Revelation (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 528.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 2002.
MacArthur, p. 2002.
MacArthur, p. 2002.
MacArthur, p. 2002.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1742.
Nelson’s Commentary, p. 1742.
Nelson’s Commentary, p. 1742.
ጥያቄዎች
-
ዮሐንስ በሰማይ ላይ በቀስተ ደመና የተከበበ ዙፋን ተገልጦለት ነበር ፤ ካለዉ ይህ ቀስተ ደመና እግዚአብሔር ለኖህ እና ለሰዉ ልጅ ሁሉ ካደረገዉ ኪዳን ጋር ምን አይነት ግንኙነት እንዳለዉ ምን ታስባላችሁ (ዘፍ 9፡ 11-17) ? በራዕ (4፡ 3) በዙፉኑ ላይ የተቀመጠዉን ለመግለፅ ጥቅም ላይ ወደ ዋለዉ የቀስተ ደመናን (የኢመራልድን) መልክ እና የድንጋዮችን መልክ አስፈላጊነት እንመልከት፡
-
አስተዉሉ፡ በዙፉኑ ዙሪያ ያለዉ ቀስተ ዳመና የአረንጓዴ ጥላ ነው ፤ አረንጓዴ ፀጋን/ምህረትን ይወክላል ፡፡ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠዉ የሚመነጩት መልኮች/ቀለሞች ሰዉ ሊቀርበዉ የማይፈልገዉ የእግዚአብሔርን ቁጣ/ፍትህ የሚያሳይ ደማቅ ቀይ እና ሰዉ ሊቀርበዉ የማይችለዉ የእግዚአብሔርን ንጽኅና እና ፅድቅን የሚያሳይ ኢያስጲድን (አልማዝ፣ ንፁህ እና ነጭ ቀለም) ናቸው ፡፡ ይሁን እንጂ በዕብራዉያ በድፍረት የፀጋዉን ዙፋን መቅረብ እንደምንችል ተነግሮናል (ዕብ 4፡ 16) ፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ፀጋ የኢመራልድ ቀስተ ደመና ቀላል የማድረግ መልክ ነው ፡፡
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 4:10–11
“The 24 elders fall down before the One seated on the throne, worship the One who lives forever and ever, cast their crowns before the throne, and say: Our Lord and God, You are worthy to receive glory and honor and power, because You havecreated all things, and because of Your will they exist and were created.’”
አስቡት እስኪ ዮሐንስ ብቻውን በደሴት ላይ ሆኖ ሊመጣ ስላለው ዘመን ከጌታ ራዕይን ሲቀበልና ያየውንም ራዕይ ለሰባቱ የኢስያ ቤተ ክርስቲያናት እንድልክ ከጌታ ትዕዛዝን ሲቀበል፡፡ ዮሐንስም በመንፈስ ሆኖ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውንና በእርሱ ዙሪያ ያሉትን 24 ዙፋኖችና በእነርሱ ላይ የተቀመጡትን 24 ሽማግሌዎች አየ፡፡ ዮሐንስም ሳያቋርጡ ቀንና ሌሊት “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እያሉ የሚጮኹትን አራት እንሰሶች ገለጸ፡፡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው ፡- “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል “
ምናልባት እናንተ በአካል በሰማዩ ዙፋን ስር መሰብሰብ ላትችሉ ትችላላችሁ ነገር ግን እግዚአብሔርን ለማምለክ ጊዜ መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ እርሱን ለማምለክ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ ያለውን “ አክሊል” ስጡት፡፡ ስላላችሁ ነገር የሚሰማችሁ ምንም አይነት ስሜት ይሁን ነገር ግን ያላችሁን ሁሉ ለእርሱ ስጡት፡፡ ጌታን አመስግኑ፡፡ እግዚአብሔር የሁልም ነገር ፈጣሪና ባለቤት ነውና እርሱ ውዳሴ፣ ኃይልና ክብር ሁሉ እንደሚገባው አድርጋችሁ ለእርሱ እውቅናን ስጡ፡፡ እርሱ ሁሉም ነገር ይገባዋልና አመስግኑት አምልኩት፡፡ ይህ በምድር ላይ ስላላችሁ ህይወት አይደለም ይልቁንም ስለ ጌታ እና ሊመጣ ስላለው በሰማይ ስለሆነው መንግስቱ እንጂ፡፡ በቀንና በማታ ሁሉም ነገር ለሚገባው ለእርሱ ምስጋናችሁ ይድረስ፡፡
“ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።”
- ራዕይ 4፡10-11
ተጨማሪ ጥቅስ
ኤርምያስ 10:7 — “የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?”
ቆላስያስ 1:16 — “የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና፣ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል ፡፡”
ራዕይ 4:8 — “አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።