Worship In Heaven
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በራዕይ ዉስጥ አብዛኛዉ መልዕክት ስላልመጣዉ ነገር ግን ሊመጣ ስላለዉ ነገር ነው ፡፡ በታሪክ ዉስጥ የሙሴ መዝገብ /መግለጫ አለን በተራራዉ ላይ መቼ እንደ ወጣ እና ከእርሱ ጊዜ በፊት ከቀድሞ ከመጀመሪያ ምን እንደ ነበር እግዚአብሔር መዝገብን እንደሰጠው ፤ ያም በዘፍጥረት ላይ የሚገኝ ነው ፡፡
በአዲስ ኪዳን ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ የሩቅ ጥንትን/ያለፈን እና የቤተ ክርስቲያን መልዕክትን መዝገብ ሰጥቷል ፤ ጳዉሎስ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ላይ ትዕዛዝን ሰጥቷል በተጨማሪም በቤተ ክርስቲያን ዘመን ስርዓትን አካትቷል፡፡
አሁን በራዕይ ላይ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ይመጣ ስለ ነበረዉ ነገር መግለጫን ሰጥቷል ፤ ከእነዚህ ከሰዎስቱ የመጽኃፍት ፀኃፊዎች እግዚአብሔር ማን እንደ ነበር፣ እግዚአብሔር ማን እንደ ሆነ እና የሚመጣዉስ እግዚአብሔር ማን እንደ ሆነ ማብራሪያ መጥቷል ፡፡
በራዕይ በመጀመሪያዎቹ አራት ምዕራፎች ዉስጥ ዮሐንስ ኢየሱስ ማን እንደ ሆነ እና ምን እንደሚመስል ገልፆአል ፡፡ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቃል ነው ፡፡ ምዕራፍ 4 በዙፋኑ ላይ የእግዚአብሔርን መልክ መግለጫ እና ማብራሪያን ይሰጣል ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (5፡ 1-14)፡ ምዕራፍ 5 ከክርስቶስ መልክ ማብራሪያ በኋላ የሚከተለዉ እቅድ ነዉ የሚሆነው ፡፡ ዮሐንስ ወደ ዙፋኑ የትዕይንት ክፍል መጣ ከዚያም ትዕይንቱ በአራቱ አዉሬዎች እና በ24 ሽማግሌዎች ወደ ድርጊት ሄደ ፡፡ ዮሐንስ በዙፋኑ ፊት ከአድማጮቹ ጋር ተቀላቀለ ፡፡
ዮሐንስ እግዚአብሔርን በዙፋኑ ላይ አየዉ በቀኝ እጁም ላይ አንድ መጽኃፍ ነበር ፡፡ ይህ መጽኃፍ በሁለቱም በኩል የተፃፈበት እና በሰባት ማህተም የታተመ ጥቅል ነበር ፡፡
በቁጥር 2 መልዓኩ “ መጽኃፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹን ይፈታ ዘንድ የሚገባዉ ማነው ? “ በማለት ጮኸ ፤ ማህተሞቹን ለመፍታት ለየብቻ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች አሉ ፡፡ ንፅፅሩ በንጉስ ፊርማ የታተመን ጥቅል ለመክፈት ስልጣን ከነበረዉ ሰዉ ጋር ይመሳሰላል ፡፡
የሁሉም ፍላጉት በጥቅሉ ዉስጥ ምን እንደ ነበር ለማወቅ ነበር ነገር ግን ማንም ስልጣን አልነበረዉም ወይም ጥቅሉን ለመክፈት የተገባዉ አልነበረም ፡፡ ከሽማግሌዎቹ ዉጪ ሁሉም ተመልካቾች እያለቀሱ ነበር ፤ መልሱ ከሽማግሌዎቹ ከአንዱ መጣ - ክርስቶስ እንደ ነበርና የሚችለዉና ሊፈታዉ የተገባዉ እንደሆነ ፡፡
ቁጥር 6 የእግዚአብሔርን በግ እንደ ታረደ ሆኖ ከሰባት ቀንዶችና ሰባት አይኖች በአድማጮቹ በአዉሬዎቹና በሽማግሌዎቹ መካከል በዙፋኑ ላይ ይገልፀዋል ፤ ከስቅለቱ ላይ የተገለፀዉ የማርቆስ ገለፃ መልክ የታረደ ሆኑ ለመታየቱ መልክን ይሰጣል ፡፡ ሰባቱ ቀንዶችና አይኖች የእግዚአብሔርን ሰባቱን መናፍስት ይወክላሉ ፤ ኢሳይያስ 11 የሰባቱን መናፍስት ዝርዝር ይይዛል ፡፡
የእግዚአብሔር ሰባቱ መናፍስት በዘኁልቁ 5፣ በኢሳይያስ 4, 29 እና 61፣ ሆሴዕ 5፣ ሉቃስ 13፣ ሐዋሪያት ስራ 16፣ ሮሜ 11፣ 2ጢሞቴዎስ 1 እና 1ዮሐንስ ላይ ከሚገኙት የክፋት መናፍስት ጋር የተለያዬ ሊሆን ይችላል ፡፡ የእግዚአብሔር ሰባቱ መናፍስት የሚያካትቷቸው፡ የጌታ መንፈስ፣ የጥበብ መንፈስ፣ የማስተዋል መንፈስ፣ የመምከር መንፈስ፣ የእዉቀት መንፈስ እና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ፡፡ የክፉ መናፍስት የሚያካትታቸው፡ የቅናት መንፈስ፣ የፍርድ መንፈስ፣ የሚያናድድ መንፈስ፣ የመጨነቅ/የመክበድ መንፈስ፣ የደካማነት መንፈስ፣ የሟርት መንፈስ፣ የእንቅልፍ መንፈስ፣ የፍርኃት መንፈስ እና የሐሰተኛዉ ክርስቶስ መንፈስ ፡፡
እግዚአብሔር ተፅዕኖዉን በምድር ላይ በመናፍስቱ በኩል ላከ በተለይም ቀድመዉ ከእግዚአብሔር መንፈስ ለተወለዱት እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቤቱ በሚሆኑት ወይም ማደሪያ ስራ በሆኑት በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ላሉት ላከላቸው ፤ የመንፈስ ተፅዕኖ ወዲያዉኑ በእነርሱ ዉስጥ ይሆናል ፡፡ ፀላይ በሚመላለስ ጊዜ እግዚአብሔርን እነዚህን ስፍራዎች በሰባቱ መናፍሰቱ እንዲሞላቸዉ መጠየቅ ትችላላችሁ ፡፡
ማቴ (12፡ 44) የክፉ መናፍስት መጣልን ያሳያል ፤ ስልጣን እንዲኖር በመናፍስት ላይ እቅድ አለ ፤ ምክንያታዊ አተገባበሩ የእግዚአብሔርን መናፍስቶች ዝርዝር ከአማኞች ህይወት ጋር ማወዳደርን ያካትታል ፡፡ ጥያቄዉ የሚሆነው በአማኞች እና በመሪዎች ህይወት የእግዚአብሔር መንፈስ ስለ መኖሩ ማስረጃዉ ምንድን ነው ? የሰባቱ መናፍስት አስፈላጊነት አማኞች በኑሮአቸዉ የእግዚአብሔርን ስራ በመስራት ማስረጃን እንዲያቀርቡ ነው ፡፡
በራዕይ በጉ ክርስቶስን ይወክላል ፡፡ በራዕይ ላይ 24 ሽማግሌዎቹ የእስራኤልን 12 ነገዶች እና 12 ሐዋሪያት ሊወክሉ ይችላሉ ፤ 24 ምስክሮች ይሆናሉ ፡፡ ክርስቶስ በመሰቀል የከፈለዉ ዋጋ መፅኃፉን እንዲከፍት እና ማህተሙን እንዲፈታ ስልጣንን ሰጠው ፡፡
በቁጥር 8 ክርስቶስ መጽኃፉን/ጥቅሉን ወሰደ 24 ሽማግሌዎች እና አራቱ አዉሬዎች በበጉ ፊት ተደፉ/ወደቁ ፤ በበገናዎችም የክርስቶስን ስልጣን በማወጅ አዲስ መዝሙር ዘመሩ ፡፡ የነበሯቸዉን የዕጣን እቃን ከእጣኑ ጋር ለክርስቶስ መስዋዕት አቀረቧቸው ፡፡ የክርስቶስ ድል አድራጊነት አማኞችን በእግዚአብሔር ፊት መንግስት እና ካህናት አደረጋቸው ፡፡
በቁጥር 11 ላይ ያለዉ ፅኁፍ “ ለበጉ ይገባዋልና “ የመሉ ከ100 ሚሊዮን በላይ ዜማ ዘማሪዎች ይናገራል ፡፡ ሰባት ባህሪያት በዝማሬዉ ዉስጥ የተጠቀሱ ናቸው ፤ የባህሪያቱ ዝርዝሮች የሚያካትታቸው፡ ኃይል፣ ባለ ጠግነት፣ ጥበብ፣ ብርታት፣ ክብር፣ ምስጋና እና በረከት ፡፡
በአንድ ላይ እየመጣ የነበረ ነገር ነበር ፤ በዙፉኑ ላይ ያለዉ መጽሃፉን አልያዘዉም ፡፡ አራቱ አዉሬዎች እና 24 ሽማግሌዎች በጉን ሲያመልኩ በፊት ለፊትም በጉም መጽኃፉን/ጥቅሉን ያዘ ፡፡
መደምደሚያ
ስለ እምነታቸዉ መከራ የደረሰባቸው የምስጋናን መዝሙር ይሰማሉ ይደሰታሉም ፡፡ ያሉት ሁሉም በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ያመልካሉ ፡፡ ምዕራፍ 5 በዚህ ስፍራ ላይ የሚጀምር እግዚአብሔርን የማምለክ መልክን ይሰጣሉ ፤ በመቀጠልም ስለሚመጡት ጥልቅ ነገሮች ደረጃዉ የተቀመጠ ነው ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዙፋኑ ላይ በተቀመጠዉ እጅ መጀመሪያ የተገኘዉ መጽኃፍ ሊከፈት/ሊፈታ አልቻለም ፤ በራዕ (5፡ 4) መሰረት የተፈታ/የተከፈተ ሊሆን ለምን አልቻለም ?
-
መጽሃፉን እና ማህተሙን መፍታት የሚችለዉ ማነው ? (ራዕ 5፡ 5)
-
ለበጉ የ24 ሽማግሌዎች እና የአራቱ ህያዉ ፍጥረቶች ምላሽ ምን ነበር ? (ራዕ 5፡ 8)
-
በጉ ለእግዚአብሔር ምን ገዛ ምንን በመክፈል ? (ራዕ 5፡ 9)
-
በራዕ (5፡ 12) ለበጉ የተባለዉ በራዕ (4፡ 11) ለእግዚአብሔር ከተባለዉ ጋር አወዳድሩ ፤ በእነዚህ በሁለቱም አባባል “ የተገባው “ የሚለዉ ቃል አስፈላጊነት ምን እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
በራዕ (5፡ 13) በሰማይ፣ በምድር ወይም ከምድር በታች እና በባህር ላይ የነበሩ ሁሉም ፍጥረቶች ሁሉንም ነገር ምን አሉ ለማን ? “ ሁሉም የተፈጠረ ነገር “ ምን ማለት እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
በራዕይ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 5:5
“Then one of the elders said to me, ‘Stop crying. Look! The Lion from the tribe of Judah, the Root of David, has been victorious so that He may open the scroll and its seven seals.’”
የዮሐንስ ራዕይ ሲቀጥል አንዱ ሽማግሌ መጽሀፉን ይከፍት መህተሙንም ይፈታ ዘንድ የተቻለው ማን እንደሆነ ተናገረ ፡- “ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል ።” ኢየሱስ በጉ መጽሀፉን ይከፍት ዘንድ ይቻለዋል፡፡ እርሱ ታርዷልና ደሙም ሰዎችን ሁሉ ለእግዚአብሔር ከነገድ፣ ከቋንቋ፣ ከወገን እና ከህዝብ ሁሉ ይዋጃል፡፡ አዎን በእርግጥም ኢየሱስ ብቻውን ይቻለዋል፡፡ ዮሐንስም በታላቅ ድምፅ እንድህ የሚል የመላዕክትን ዝማሬ ሰማ ፦ “ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ!”
ምናልባት መከራ፣ ችግር፣ ስደት ይገጥማችሁ ይሆናል ወይም ያልተሟላ ፍላጎት ይኖራችሁ ይሆናል፡፡ እስኪ ለደቂቃ በሰማያዊው ተስፋ እረፉ፡፡ አንድ ቀን አለ ምድር ሁሉ የተገባውን የእግዚአብሔርን በግ የሚያመልክበት ቀን፡፡ እስኪ ይህንን በሰማይ የሚደረግ አምልኮ አስቡት፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ እርሱ ባደረገው ቤዛነት ላይ አትኩሩ፡፡ ኢየሱስ ባለ ጠግነትን ጥበብን ብርታትን ክብርን ምስጋናንና በረከትን ይቀበል ዘንድ ይገባዋል፡፡ እርሱን ቆመህ ለማምለክ ወይም በፊቱ ወድቀህ እርሱን ለማምለክ ፍቃደኛ ነህን? ዛሬ እርሱን ስታመልኩ ለኢየሱስ ሙሉ ልባችሁን ስጡት፡፡ እርሱ ይህ ሁሉ ይገባዋል፡፡
“ከሽማግሌዎቹም አንዱ፦ አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።”
- ራዕይ 5፡5
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘፍጥረት 49:9–10 — “ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፤ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፤ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።”
ዮሐንስ 1:29 — “በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።”
ራዕይ 5:11–12 — “አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።