Revelation Revelation

The Word For Revelation: I AM

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 714 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሽግግሩ በምዕራፍ 4 እና 5 ጀምሯል ፡፡ ምዕራፍ 6 የአዲስ መጽኃፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ አይደለም ነገር ግን የአዲስ ክፍል እና የለዉጥ ምዕራፍ ነው ፡፡ የራዕይ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ምዕራፎች የክርስቶስን መልክ እና ለአብያተ ክርስቲያናት የእርሱን ሀሳብ አቅርበዋል ፡፡ ምዕራፍ 4 እና 5 ከሁሉም እይታዎች እና ድምጾች ጋር የተለየዉን የዙፋኑን መልክ አካትተዋል ፡፡

ምዕራፍ 6 በዮሐንስ የራዕይ አፃፃፍ ይጀምራል ፤ ስሚዝ እና ካርድ የዚህ ክፍል ጥናት አስቸጋሪነትን ይፅፏሉ፡

“ ምዕራፍ 4 እና 5 ስታነቡ አብዛኛዉ ምስል ከተለመደዉ በላይ ቢሆንም እንኳን ራዕይ ቅርጽ የሚሰጠዉ አይነት እና ያልተለመደ የመጽኃፍ ቅዱስ አካል ስሜት አለው ፤ በእርግጥ ልባችሁ የዙፋኑን ክፍል ራዕይ ድምጽ እና የቀረቡትን እይታዎች ስታብሰለስሉት ይበረታታል ይነሳሳልም…. ከዚያም ረጅም ከማንበብ በፊት በምዕራፍ 6 ላይ ጥናታችሁን ስትቀጥሉ ግን የራዕይን ግንብ ትመቱታላችሁ ፤ በማህተም፣ በመለከት እና በለቅሶ ረግረግ/አርንቋ ዉስጥ መጥፋት ወደ ደህና እና ወደ ዮሐንስ ወንጌል እና መዝሙር የሚገመት ወደብ ለመሮጥ ትጓጓላችሁ “ ፡፡

ምዕራፍ 6 ግጥሞችን፣ ምስሎችን እና አብዛኛዉ ግለሰብ የለመደዉ ሊሆን የሚችሉ የተያዩ የፅሁፍ አይነቶችን ይይዟል ፤ በትንቢታዊ ፅሁፍ ከተለመደ መንገድ ምንም ነገር አይመጣም ፡፡

በምዕራፍ 6 የተፃፈበት ፍሰት ከብዙ አመለካከት አንፃር ሊታይ ይችላል ፡፡ የዘመንን ጊዜ ቅደም ተከተልን የሚል ዝንባኤል/ሀሳብ አለ ፤ ሌለኛዉ አማራጭ “ ማህተሞቹን “፣ “ መለከቱን “ እና “ የዕጣኑን ዕቃዎች “ አራቱ ወንጌላት በተለያዬ አራት መንገድ ስለ ተመሳሳይ ታሪክ እንደሚያወሩት ስለ ተመሳሳይ ነገር እንደሚያመለክቱ ይተረጎማሉ ፡፡ ሰዎስተኛዉ አማራጭ ምዕራፍ 6 እንደ ሚጠመጠም የአፃፃፍ ስታይል ያያል ፡፡ ሊዞርኪን ዋይዘንበርግ፡ “ በአይሁዶች አስተሳሰብ ታሪክ የሚጠመጠም/የሚሽከረከር እንጂ ቀጥተኛም ዙርም እንዳይደለ ያስታዉሳል ፤ አንድ ትንቢት ስለ አለፈዉ፣ ስለ አሁኑ እና ስለ ወደፊቱ ሊናገር ይችላል “ በማለት ፅፏል ፡፡

ራዕይ በቀጥታ የመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖችን ደርሷል ፡፡ ለመኖር በክፉ እና በመልካም መካከል ያለዉን ጊዜ የማይገድበዉን እዉነት አቅርቧል ፡፡ ስላልመጣዉ ነገር ግን ይመጣ ስለ ነበረዉ ብዙ ነገር ይል ነበር ፤ አንዱ በራይ ላይ የተመለከተበት መንገድ እንዴት እንደተቀበለዉ ተፅዕኖ ነበረው ፡፡ ፍሰቱን ለመረዳት በአንድ ማዕከል/ቁጭታ ዉስጥ ምዕራፍ 6-11 ማንበብ የተሸለ ነው ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (6፡ 1-17)፡ የማህተሞቹ ራዕይ ከዙፋኑ ክፍል ዉስጥ እየመጣ ነበር ፤ መጽኃፉ በሰባት ማህተም ታትሞ ነበር ፤ የመጀመሪያዉ ማህተም በበጉ ተከፈተ ፤ ማህተሙ እንደ ተከፈተ ከፍጥረቶቹ አንዱ “ መጥተህ እይ “ በማለት በነጎድጓድ ድምጽ ተጠራ ፡፡ የመጀመሪያዉ ማህተም መከፈት በአምላይ/ነጭ ፈረስ ላይ አክሊል ደፍቶ የተቀመጠን ቀስት ያለዉ ፈረሰኛን አመጣ ፤ ይህ ከራዕዩ ከአራቱ ፈረሰኞች የመጀመሪያዉ ነበር ፡፡

በቁጥር (1-8) ያለዉ የፈረሶች መልክ በዘካ (1፡ 8-17) ላይ ከሚገኘው የፈረሶች መልክ ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ ዘካርያስ የተለያዬ መልክ ቀይ/መጋላ፣ አምባላይ/ነጭ፣ ቡናማ/ሐመር፣ ዥንጉርጉር ግራጫ እና ጥቁር መልኮችን አዬ ፡፡ በራዕይ የፈረሶቹ መልክ ከጋላቢያቸዉ ባህሪ/ተግባር ጋር ይገጣጠማል - ድል አድራጊነት ነጭ/አምባላይ ነበር፣ ደም ማፍሰስ ቀይ/ዳማ ነበር፣ እጥረት ጥቁር/ጉራቻ ነበር እንዲሁም የሞት ሐመር ነበር (ቁጥር 8) ፡፡

ሞንሴ በዘካርያስ ፈረሰኞቹ ምድርን እንዲፈትሹ/እንዲሰልሉ እንደ ነበር እና በራዕይ ደግሞ ፈረሰኞቹ በምድር ላይ ጥፋትን ሊያመጡ/ሊለቁ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ የዮሐንስ ራዕይ ቅርጽ ከዘካርያስ ጋር ይመሳሰላል ነገር ግን የራዕይ ርዕስ ስለ መጨረሻው ዘመን ከወንጌላት የኢየሱስ አስተምሮ ነበር ፡፡

ፈረሰኛው በአክሊል እና በሰይፍ ወጣ ፤ ይህ ለራዕይ 19አስፈላጊነት አለው ፤ እኔ ያለዉ በነጩ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ነበር ፡፡ በምዕራፍ 6 ጋላቢዉ ነጭ ፈረስን ጋልቧል ሐሰተኛዉን ክርስቶስንም ይወክላል ፤ በነጩ ፈረስ ላይ ያለው ይህ ጋላቢ ጥፋትን አመጣ ፡፡

ምናልባትም በራዕይ በአራተኛዉ ፈረሰኛ እና በዳንኤል በሰባኛዉ ሳምንት መካከል ግንኙነት ይኖራል ፤ በነጩ/በአምባላይ ፈረስ ላይ ያለዉ ፈረሰኛ በሰዉ ላይ የመጨረሻዉ ሰይጣናዊ አምባገነን ይሆናል ፡፡

ሁለተኛዉ ማህተም ተከፈተ ፍጥረቱም “ ናና እይ “ በማለት ጮኸ አንድ ፈረሰኛም በዳማ/በቀይ ፈረስ ላይ ተገለጠ ፤ ተግባሩም ሰላምን ከሕዝቦች ላይ መዉሰድ ነበር ፡፡ ቀለሙ/መልኩ ደም መፍሰስን እና መታረድን ያመለክታል ፤ ይህ እሳታማ ቀይ ፈረስ ጦርነትን ይወክላል ፡፡ በ 2 ተሰ (2፡ 6-12) ጳዉሎስ ስለ ሰላም መወገድ አስጠንቅቋል ፡፡ የመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ሕዝቦች በዚህ አዉድ/ንግግር ለምደዋል/አድሳቸዉ አይደለም ፡፡

ሰዎስተኛዉ ማህተም ተከፈተ/ተፈታ ፤ አንድ ፍጥረትም “ ናና እይ “ በማለት ጮኸ አንድ ፈረሰኛ በጉራቻ/በጥቁር ፈረስ ላይ ወደፊት መጣ ፤ ጉራቻ/ጥቁር ፈረስ እጥረትን፣ አለመብቃትን እና ድርቅን ይወክላል ፡፡ ፈረሰኛው የመለኪያ ሚዛን ነበረው ፤ ገለፃው/አገላለፁ በሕዝ (4፡ 6-11) እንጀራ በክብደት እንደሚበላ እና የሚጠጣ ዉኃ እንደሚለካ ከሚያወራዉ ፅሁፍ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡

ሞንሴ ከሲሰሮ ማጣቀሻው መሆን ካለበት ዋጋው ከአስር እስከ 12 እጥፍ እንደ ነበር ይገልፃል ፤ የወይራ ዘይት እና ወይን የቅንጦት ሳይሆኑ መሰረታዊ ፍጆታዎች ነበሩ ፤ በቁጠባ ጥቅም ላይ ይዉሉ ነበር ፡፡

አራተኛዉ ማህተም ተፈታ አራተኛዉም ፍጥረት “ ናና እይ “ በማለት ጮኸ ፡፡ አንድ ፈረሰኛም ሞትን በሚወክለዉ በሐመር ፈረስ ላይ ተከለጠ/ተከሰተ ፤ በሰይፍ፣ በርኃብ፣ በመቅሰፍት እና በዱር እንስሳት እንዲገድል ስልጣን ነበረው ፤ ይህ ፈረሰኛ ከምድር በአራተኛዉ እጅ ላይ ስልጣን የተሰጠው ነበር ፡፡ ይህ በመጽኃፍ ላይ በአራተኛው ፈረሰኛ ላይ መረጃዉን ይሞላል ፡፡

አምስተኛው ማህተም ተከፈተ/ተፈታ ፤ በሰማይ ላይ መሰዊያ ታዬ በስሩም የታመኑ ሰምዓታት ነበሩ ፤ ነጭ ካባ/ልብስ ተሰጥቷቸው ነበር ለጥቂት ጊዜም እንዲጠብቁ ተነገራቸው ፡፡ ነጩ ልብስ ንጽህናቸዉን እና መባረካቸዉን ይወክላል ፡፡

ሰባተኛዉ ማህተም ወደ ሁለት ቡድን የተከፈለ ነበር የመጀመሪያዎቹ አራቱ እና የመጨረሻዎቹ ሰዎስቱ ፡፡ አራቱ ፈረሰኞች የመጀመሪያዎቹ አራት ማህተሞች ነበሩ ፡፡ የተለያዩ ትዕይንቶች በቀሩት በሰዎስቱ በእያንዳንዳቸዉ ማህተሞች መክፈቻ ላይ ታይቷል ፡፡

ስድስተኛው ማህተም ተከፈተ/ተፈታ የመሬት መንቀጥቀጥም ሆነ ፡፡ ፀሐይ ወደ ጥቁር/ወደ ጨለማ ተቀየረች ጨረቃም ልክ እደ ደም ሆነች ፡፡ የአለም መጨረሻ በእጁ ላይ እንደ ነበር በማሳወቅ የፍጥረት ሁሉም ስርዓት መፈራረስ ጀመረ ፡፡ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ቁጣ/መዓት ለመጋፈጥ ፈሩ ፤ የእግዚአብሔርን ቁጣ/መዓት ከመጋፈጥ ይልቅ በማንኛዉም መንገድ ሞትን ናፈቁ ፡፡

መደምደሚያ

አማኞች ብቻ በእግዚአብሔር ታላቅ ፍርድ ላይ መቆም ይችላሉ ፤ ይህ በኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት በኩል በጸጋ መጽደቅን ይፈልጋል ፡፡

እግዚአብሔር ነገሮች እንዴትም ቢመስሉ ችግር የለዉም ሁሉንም ይቆጣጠራል ፤ በእምነት ጽድቅን ያወጁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ይኖራቸዋል ፡፡

2 Dr. Eli Lizorkin-Eyzenber at https://israelbiblecenter.com.

  1. Scotty Smith and Michael Card, Unveiled Hope (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1997), p. 106.

  2. Robert Mounce, The New International Commentary of the New Testament: The Book of Revelation (Grand Rapids, MI: Wm. B. Eerdesman Publishers, 1997), p. 152.

  3. Mounce, p. 155.

ጥያቄዎች

  1. መጽኃፍቱን ለመክፈት የተገባዉ ሆኖ የተገኘዉ ኢየሱስ ብቻ ነበር ፤ በምዕራፍ 6 እንደተገለፀው ከእያንዳንዳቸዉ ከመጀመሪያዎቹ መጽኃፍት የእግዚአብሔር የወደፊቱ ፍርዶች ምን ነበሩ ?
  2. በመጀመሪያዉ ማህተም የተገለፀው የፍጥረቱ ድምጽ እንዴት ነበር ? በሰማይ ድምጾቹን ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋሉት መግለጫዎች ምን ነበሩ ? (ራዕ 1፡ 10, 4፡ 1)
  3. በራዕይ 6 በፈረሶቹ ላይ የነበሩት ፈረሰኞች እንዴት ነበር የተገለፁት ? እያንዳንዳቸዉ እንዴት ነዉ የሚለዩት?
  4. በራዕ (6፡ 11) ነጩ ካባ/ልብስ ምንን ይወክላል ? (ራዕ 3፡ 4, 7፡ 9, 13-14, 19፡ 8, 14)
  5. በራዕ (6፡ 16) የተጠቀሱት በስህተት ወደ ምን ጮኹ ? ወደ ጌታ ለምን እንዳልጮሁ ምን ታስባላችሁ ? (ሮሜ 1፡ 18-25)
  6. በራዕይ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 6:16–17

“And they said to the mountains and to the rocks, ‘Fall on us and hide us from the face of the One seated on the throne and from the wrath of the Lamb, because the great day of Their wrath has come! And who is able to stand?’”

እንደተጠበቀው በጉ የመጽሀፉን ስድስት ማህተሞች ፈታ፡፡ እያንዳንዱ ማህተም የሆነ ነገር ሊመጣ እንደሆነ ይገልጣል ፡- የመንግስታትን መያዝ እና መለወጥ፣ ጦርነት፣ ርሃብ፣ ድርቅ፣ ሞት፣ ሰማዕትነትንና ቁጣ፡፡ ከማህተሞቹ አንድ እንኳ የሆነ ደስ የሚልን የሚመችን ነገር ያሳየ የለም፡፡ እያንዳንዱ ፍርሀትንና ስቃይን ያመጣል፡፡ ምናልባት በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ማን መቆም እንደሚችል ትጠይቁ ይሆናል፡፡ ሊመጣ ያለውን ስቃይ ማን ሊቋቋመው ይችላል?

እናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባላችሁ እምነት ጸንታችሁ መቆም ትችላላችሁ፡፡ ጳውሎስ አማኞች በፈተና በጌታና በኃይሉ እንዲበረቱ ይመክራቸዋል፡፡ ጌታ እጆቻችሁን ለውጊያ ያስታጥቃል፡፡ የጌታ ስም የጸና ግምብ ነው እናንተም ወደ እርሱ ሮጣችሁ በእርሱ መሸሸግ ትችላላችሁ፡፡ እርሱ ይጠብቃችኋል፡፡ እግዚአብሔር በመከራ ቀን መሸሸጊያ ነው ምክንያቱም በእርሱ ለሚታመኑት ለሚደገፉት ሁሉ ያስባልና፡፡ በእምነት ጸድቃችኋል፡፡ በእምነታችሁ ጸድቃችኋል በኢየሱስ ክርስቶስም በኩል ከአብ ጋር ታርቃችኋል፡፡ ህይወት ምንም ያህል የሚስጠላ ቢሆንባችሁ በክብር ተስፋችሁ ደስ ይበላችሁ፡፡ አስታውሱ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው ስለዚህም በእርሱና በሰጠው ተስፋ ላይ መቆም መታመን ትችላላችሁ፡፡ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው ፈጽሞም አይተዋችሁም፡፡

“ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው።”

  • ራዕይ 6፡16-17

ተጨማሪ ጥቅስ

ናሆም 1:6–7 — “በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ።እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል።”

ምሳሌ 18:10 — “የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።”

ኤፌሶን 6:10 — “በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።”