Revelation Revelation

A Multitude From The Great Tribulation

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 715 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለዚህ ሳምንት ክፍል/ትምህርት ስዘጋጅ ምናልባትም ይህ እስካሁን በሪቫይቭ ት/ቤት ዉስጥ ለማላመጥ በጣም ስጋ የነበረዉ ይህ እንደ ሆነ አምናለሁ ፡፡

በመጨሻው ዘመን ላይ ከተለያዩ ተቋማት እና ስነመለኮታዊያን በአንድ ላይ 30 ያክል ቻርቶችን ተመልክቻለሁ ፤ እነዚህን በማስቀመጥ ማወዳደር ስጀምር በራዕይ ላይ የቀረበዉን የተከተለ እንዳልሆነ አስተዉሌአለሁ ፡፡ ሁሉንም ለእኛ እንደማስታወስ የሆነ ነገር ምንም ስሜት የማይሰጥ ከሆነ ትንሽ ወደኋላ በመሳብ ያነበባችሁትን እና የሰማችሁትን ለማሰብ ትንሽ ጊዜን ዉሰዱ ፡፡ የማንኛዉ የጊዜ ገደብ/ቅደም ተከተል ከራዕይ ጋር የማይጣጣሙበት ምክንያት የእግዚአብሔርን ጊዜ ማንም ስለማያዉቀዉ እንደ ሆነ አስባለሁ ፡፡ ወደ መጨረሻዉ ዘመን በይበልጥ እና በይበልጥ እየቀረብን ስንመጣ በደንብ ግልፅ እንደሚሆን አምናለሁ ፤ ይህ ሁሉም እየጀመረ እንደሆነ አስባለሁ ፡፡

ኢየሱስን በራዕይ ዉስጥ የምናይበት ሐረግ እኔ የሚል ነው (ራዕ 1፡ 7-8) ፡፡ በምዕራፍ 6 እና ከዚያ ባለፈዉ ኢየሱስ ራሱን እንዴት የገለጠበት መልክ ነው ፡፡ ክርስቶስ “ እኔ ፊተኛና ኃለኛ ነኝ “ አለ ፡፡

ቶም ቼይፈር ከሰባቱ ማህተም በስድስቱ ዉስጥ ይመራናል ፡፡ ምዕራፍ 7 ስለ ማህተሞቹ መስጠት ላይ እረፍትን ይሰጣል ፡፡ ማህተሞቹን ለመፍታት ኢየሱስ ብቻ የተገባዉ ነው ፤ እያንዳንዳቸዉ መጽኃፍት/ጥቅሎች በዉስጣቸዉ ያለዉን ለመግለጥ ሙሉ ለሙሉ ተከፈቱ ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ማህተሞች፡

  1. የመጀመሪያዉ ፈረሰኛ በአምባላይ/በነጭ ፈረስ ላይ የተገለጠው ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ነው ፡፡ ይህ ማቴዎስ 24 ከራዕይ 6 ጋር የሚያመሳስል እና የሰባት አመቱ ታላቅ መከራ መጀመሪያ ነው ፤ ታላቁ መከራ ከሰባቱ አመት ጊዜ ከግማሽ በኋላ ይጀምራል ፡፡
  2. ሁለተኛዉ ፈረሰኛ በዳማ/በቀይ ፈረስ ላይ የተገለጠው ከሕዝቦች ላይ ሰላምን ይወስዳል - ጦርነት እና የጦርነት ወሬዎች ይኖራሉ (ማቴዎስ 26) ፡፡
  3. ሰዎስተኛዉ ፈረሰኛ በጉራቻ/በጥቁር ፈረስ ላይ ዕጥረትን፣ ትክክለኛ ያልሆነ እና ርኃብን ከሚወክል ሚዛን ጋር ተገለጠ (6፡ 5-6) ፡፡
  4. አራተኛው ፈረሰኛው በሐመር ፈረስ ላይ የተገለጠው ሞትን ይወክላል ፡፡
  5. በሰማይ ላይ በስሩ የታመኑ ሰመዓታት ያሉት መሰዊያ ተገለጠ (ማቴዎስ 24፡ 9, ራዕ 6፡ 9-11) ፡፡ ስለዚህ ሁሉ ነገር ጊዜ እርግጠኞች መሆን አንችልም ነገር ግን አማኞች በአምስተኛዉ እና በስድስተኛዉ ማህተም ጊዜ ቁጣዉን/መዓቱን መረዳት እንደሚችሉ እርግጠኞች መሆን እንችላለን ፡፡
  6. የመሬት መንቀጥቀጥ ይከሰታል፣ ፀሐይ ወደ ጨለማ/ጥቁር ትቀየራለች፣ ጨረቃ ልክ እንደ ደም ትሆናለች እንዲሁም የፍጥረት ሁሉ ስርዓት መፈራረስ ይጀምራል የአለም መጨረሻ በእጅ ላይ እንዳለ ይታወጃል ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (7፡ 1-8)፡ በራዕይ 7 ሁለት ዋና ዋና ቡድኖች አሉ - 144,000 አይሁዳዊያን ወንጌላዊያን እና እምነታቸዉን በኢየሱስ ላይ ያደረጉት እጅግ ታላቅና ብዙ ሕዝብ ፡፡ ይህ ሰባተኛዉ ማህተም ከመፈታቱ እና የእግዚአብሔር ቁጣ ከመለቀቁ በፊት ይሆናል ፡፡ ዮሐንስ ንፋሱን እየከለከሉ የነበሩ በምድር በአራቱም መዓዘናት ላይ የቆሙ አራት መለዓክትን አዬ (ራዕ 14፡ 18) ፡፡ ምድርን እና ባህርን የመጉዳት ኃይል የነበራቸዉን አራቱን መለዓክት ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች በ144,000 ዎች ግንባር ላይ በእግዚአብሔር ምልክት/ማህተም እስኪቀመጥባቸዉ ድረስ ምንም ነገር እንዳይጎዱ የሚናገር ከፀኃይ መዉጫ ምልክትን/ማህተምን የያዘ አምስተኛ መለዓክ ተነሳ ፡፡

ምሁራን 144,000 በሚረዱበት መንገድ አይስማሙም ፤ አንዳንዶች ይህ በቀጥታ 144,000 ሰዎችን ነዉ ሲሉ ሌሎች ደግሞ ይህ የሚወክል ቁጥር ነዉ ይላሉ ፡፡ በቀጥታ 144,000 እዲሆን እፈልጋለሁ ምክንያቱም ያ ትክክል እንደ ሆነ ስለተሰማኝ ፤ በዘፍጥረት 12 እና 49 እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚያድናቸው ቃል ገብቷል ፡፡ እግዚአብሔር ከእያንዳንዱ 12 ነገዶች አንዳንድ ቅሬታዎችን ማስነሳቱ ለምን ትርጉም አይሰጥም ?

ራዕይ (7፡ 9-10)፡ ቁጥር 9 በለዉጥ ይጀምራል ፤ ከሚሆኑት ሁሉም ነገሮች ጋር እንኳን ሁልጊዜ የሚተርፉ ቅሬታዎች ይኖራሉ ፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ ራሱ ለማምጣት ትንሽ ቡድኖችን ይጠቀማል ፡፡ ማህተሞቹ/ምልክቶቹ ስለሚመጣው አዲስ ዘመን የዉልደት ህመምን ያንፀባርቃሉ ፡፡ ከዚያም ዮሐንስ ከሁሉም ሕዝቦች፣ ነገድ፣ ሕዝብ እና ቋንቋ ብዙ ቁጥር ሕዝብን አዬ - በዙፋኑ ፊት እና በበጉ ፊት ቆመዉ የነበሩት ከመብዛታቸዉም የተነሳ ማንም ሊቆጥረዉ አይችልም ፡፡ ነጭ ልብስ ለብሰዉ እና የዘንባባ ቅርንጫፍ ይዘዉ ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ በአሁኑ ስዓት 200 ሕዝቦች እና በምድር ላይ በሽ የሚቆጠሩ ቋንቋዎች አሉ ፡፡

ብዙዉ ሕዝብም በታላቅ ድምጽ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠዉ ለበጉ ለእግዚአብሔር ማዳን ነዉ እያሉ ጮኹ (ቁጥር 10) ፤ ከሚባለዉ በላይ በስትክክል እነዚህ ክርስቶስን ለማወቅ የመጡና ምናልባት የተሰዉት ሰዎች ናቸው ፡፡

ራዕይ (7፡ 11-14)፡ መለዓክት ከሽማግሌዎቹ እና ከአራቱ እንስሳቶች ጋር በዙፋኑ ዙሪያ በመክበብ በግንባራቸዉ በመደፋት እግዚአብሔርን አመለኩ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ከሽማግሌዎቹም አንዱ እነዚህ ነጭ የለበሱት ሁሉም እነማን እንደ ነበሩ ጠየቀ (ቁጥር 13) ፡፡ ዮሐንስ ለሽማግሌዉ “ ጌታ ሆይ አንተ ታዉቃለህ “ በማለት መለሰለት ፤ ሽማግሌዉም እነዚህ ከታላቁ መከራ የወጡ እንደ ነበሩ መለሰለት ፡፡ ልብሳቸው በበጉ ደም የታጠበ ነበር (ቁጥር 14)፡፡

ራዕይ (7፡ 16-18)፡ ከድነታቸዉ/ከመዳናቸዉ የተነሳ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ቀን እና ሌሊት እርሱን ያገለግላሉ ፤ ይጠብቃቸዋልም/በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል (ቁጥር 15) ፡፡ ርሀብ እና ጥማት አይኖርም ፀሐይም አያጠቃቸዉም /አያቃጥላቸዉም (ቁጥር 16) ፤ ይህ በመከራዉ ገጥመዋቸዉ የነበሩት ነገሮች መግለጫ ነው ፡፡ በጉም ለእነርሱ ይጠነቀቅላቸዋል ወደ የህይወት ዉኃ ምንጭም ይመራቸዋል ፡፡ እግዚአብሔር ከአይኖቻቸዉ ሁሉንም እንባ ያስወግዳል (ቁጥር 17) ፡፡

መደምደሚያ

ስለዚህ እዚህ ጋር የሁለት አይነት ሰዎች ቡድንን አይተናል፡ ከ 12 ነገዶች 144,000 ወንጌላዊያንን እና ብዙዉ ሕዝብ፡፡ ነገ ምዕራፍ 8 ሰባተኛዉን ማህተም ይገልጣል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. የህያዉ እግዚአብሔርን ማህተም የያዘዉ መለዓክ ምድርን እና ባህርን እንዲጎዱ ኃይል ተሰጥቷቸዉ የነበሩትን አራት መለዓክቶች ምን ነገራቸው ? (ራዕ7፡ 20
  2. ከእያንዳንዱ 12 ነገድ አስራ ሁለት ሺህ በግንባራቸዉ ላይ የታተሙ ይሆናሉ ፤ ስለ እነዚህ ማህተሞች ምን እናዉቃለን (ራዕ 14፡ 1) ? ሕዝ (9፡ 4) ላይ ተመልከቱ ፤ በዮሐ (6፡ 27), በ 2ቆሮ (1፡ 21-22) እና ኤፌ (1፡ 13) መሰረት ሌላ ማነዉ የታተመው ?
  3. እነዚህ 144,000 በትክክል እስራኤላዊያን ወይስ የቤተ ክርስቲያን ወይም የሌላ ቡድን መወከያ እንደ ሆኑ ታምናላችሁ ? በራዕ (7፡ 3-8 እና 14፡ 1-5) ስለእነዚህ የተሰጡት የተለዬ መገለጫዎች ምንድን ናቸው ?
  4. በራዕ (7፡ 9-10) ብዙ ሕዝብ የተገለፀ ነው ፤ ምን ዝርዝር ነገር ተሰጥቷል ? በራዕ (7፡ 14-15) ስለዚህ ብዙ ሕዝብ ዮሐንስ ምን ነበር የተነገረው ?
  5. በራዕይ (7፡ 14) መሰረት ምንም እንኳን እነዚህ ከታላቁ መከራ ቢወጡም የድነታቸዉን መግለጫ ለምን ወይም ለማን አደረጉ ? (ራዕ 7፡ 10)
  6. በራዕይ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 7:9–10

“After this I looked, and before me was a great multitude that no one could count, from every nation, tribe, people and language, standing before the throne and before the Lamb. They were wearing white robes and were holding palm branches in their hands! And they cried out in a loud voice: ‘Salvation belongs to our God, who sits on the throne, and to the Lamb.’”

ስድስተኛውም ማህተም ከተፈታ በኋላ፣ ዮሐንስ ከጸሐይ መውጫ የወጣ መልአክ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የሆኑ 144000 ሰዎችን እንዳተመ ተናገረ፡፡ ከዚያም ቀጥሎ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ሰዎች፣ ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ የሆኑ በዙፋኑና በበጉ ፊት እንደቆሙ ገለጸ፡፡ በጉ የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆነው መስዋዕት ኢየሱስ ነው ፡፡ ነጭ ልብስ ለብሰው፣ ሊቆጠሩ የማይቻሉ ብዙ ሰዎች በታላቅ ድምጽ ፡- “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው “ በማለት ጮኹ፡፡

“ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች” እንዴት ስለ በጉ ሊያውቁ ይችላሉ ? ይህ ምስል ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠውን ታላቅ ተልዕኮ ማለትም ከሁሉም ወገን ደቀ መዛሙርትን ለማድረግ የተሰጠውን ስልጣን ለማሟላት ይመስላል፡፡ ዛሬም ቢሆን ኢየሱስ አማኞች ወደ ዓለም ሁሉ እንድሄዱና የእግዚአብሔርን ፍቅር እንድያካፍሉ ያዛል፡፡ ማነው በህይወታችሁ ውስጥ ስለ ኢየሱስ፣ ስለ መስዋዕቱ በግ፣ ስለ ሁሉም ሰው ወገን ህዝብና ቋንቋ ኃጢአት ስለሞተው፣ ቤዛነትንና ዘላለማዊ ህይወትን ስላሰጠው ስለ እርሱ መስማት ያለበት? ልክ ሄዳችሁ ስትናገሩ ጌታ በሚመራችሁ ቦታ ሁሉ ትመሰክሩ ዘንድ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይልን ትቀበላላችሁ፡፡ ለመናገር ትሄዱ ዘንድ ጊዜው አሁን ነው፡፡

“ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤ በታላቅም ድምፅ እየጮሁ፦ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ። “

  • ራዕይ 7፡9-10

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 28:19–20 — “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

ሐዋርያት ሥራ 1:8 — “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”

ራዕይ 7:3–4 — “የአምላካችንን ባሪያዎች ግምባራቸውን እስክናትማቸው ድረስ ምድርን ቢሆን ወይም ባሕርን ወይም ዛፎችን አትጕዱ አላቸው።የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።”