Revelation Revelation

The Trumpet Judgements Begin

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 716 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

አንዳንድ ጊዜ ራዕይ ልክ ከእሳት ቧንቧ እንደመጠጣት ሊሰማ ይችላል ፤ በዉስጡ ያሉትን ሁሉንም ነገር ለመዉሰድ አስቸጋሪ ነው ! የራዕይ (1፡ 3) ተስፋ ለማስታወስ የሚያበረታታ ነው፡ “ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በዉስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው “ ፡፡ ራዕይን በማንበብ ብቻ የተባረከ እንደሚኮን የሚናገረዉ ተስፋ በመጽኃፉ ዉስጥ ሰባት ጊዜ ይደገማል ፡፡

ለራዕይ መጽኃፍ ሐረጋችን/ቃላችን እኔ የሚል ነው ፡፡ ኢየሱስ ፊተኛና ኋለኛ እንደ ሆነ ከተረዳችሁ ትባረካላችሁ ፡፡ ራዕይ እንዳታስወግዱ ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን ስለ ስፍራችሁ እርግጠኞች ስላልሆናችሁ ፡፡ ለክርስቶስ ተመልሶ መምጣት የተዘጋጀን በመሆን አስቸጋሪ/ጠንካራ ነገሮችን መያዝ አለብን ፡፡ በዚህ በራዕይ ጥናት ዉስጥ ተስፋችን ልክ ከሺዉ አመት በፊት እና ከነገድ በፊት የሚሉትን ትልቅ/ሰፊ ቃሎች በመግለፅ ለመርዳት ነው ፡፡

ባለፉት ጥቂት ቀናቶች በሰባት አመት ጊዚያት ዉስጥ የተለቀቁ ስለሚሆኑት ስድስት ማህተሞች አጥንተናል ፡፡ በራዕይ 1,260 ቀናት ብዙ ጊዜ ተጠቅሶ እናያለን ፤ ይህ 3.5 አመት ወይም የመከራ ጊዜ ተብሎ የሚታወቀዉ የሰባት አመቱ ግማሽ አመት ስለሆነ አስፈላጊ ነው ፡፡ በዮሐንስ ራዕይ በዚህን ጊዜ አዉሬዉ/ሐሰተኛዉ ክርስቶስ በምድር ላይ ነው ፡፡ ብዙ ነገር እየሆነ ነው ፤ ድርቅ/ርሀብ፣ ጦርነት እና ሞት አለ ፤ በተፈጥሮ አስፈሪ ነገሮች ሆነዋል ፡፡ አንዴ የመጀመሪያው 1,260 ቀናት ካለፈ የመከራዉ ሁለተኛዉ ግማሽ ታላቁ መከራ በመባል ይታወቃል ፤ በታላቁ መከራ ታላቅ ቁጥር ያለዉ ሕዝብ ከነገድ፣ ከቋንቋ እና ከሕዝብ ወደ ክርስቶስ ይመጣሉ ፡፡ ይህም በራዕይ 7 ታላቅ ሕዝብ እግዚአብሔርን በዙፋኑ ፊት ሲያመልኩት ስለሚያሳይ በብዛት ሰማዓታት እንደሚሆኑ የሚያሳይ የሚመስል ነው ፡፡

ኢየሱስ ሁሉንም ማህተም የፈታ ነበር ፤ ከእነርሱ ስድስቱ በዚህ ስፍራ ላይ ድረስ ተፈተዋል ፡፡ ስድስተኛዉ ማህተም ከተከፈተ/ከተፋታ በኋላ አንድ መለዓክ ከእያንዳንዳቸዉ የእስራኤል 12 ነገዶች 12,000 በአጠቃላይ 144,000 ሰዎችን እንዲያትም ስልጣን ተሰጥቶት ስለ ነበር ማህተም በመፍታት ታሪኩ ዉስጥ መቆም ነበር ፡፡ የታተሙ ሆኑ ማለት ማንም ሊነካቸዉ አይችልም ማለት ነው ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (8፡ 1-6)፡ ዋይርስቤ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ቁጥሮች የዝግጅት ጊዜን እንደሚያሳዩ ጽፏል ፡፡ ኢየሱስ ሰባተኛዉን ማህተም ፈታ ሰማይም “ ለግማሽ ስዓት “ (ቁጥር 1) ፀጥ አለ ፤ የሰማይ ዝምታ/ፀጥታ ከማዕበል በፊት እንዳለ እርጋታ ተመሳሳይ ነው ፡፡ ከዚህ የሚሆነዉ ሁሉም ነገር ለምድር ሕዝብ ታላቅ ነገር አይደለም ፡፡

ሰባት መለዓክት ሰባት መለከት ተሰጥቷቸዉ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ የሰማይም ዝምታ በመሰዊያዉ ፊት “ ከቅዱሳን ሁሉ ፀሎት ጋር “ (ቁጥር 3) ይሰዋበት የነበረዉን የወርቅ ጥና ይዞ በመቆመዉ መለዓክ ተሰበረ ፤ መለዓኩም “ በእግዚአብሔር ፊት “ (ቁጥር 4) ጥናዉን በእሳት ከመሙላቱ በፊትና ወደ ምድር ከመወርወሩ በፊት ፀሎቶቹን አቀረበ (ቁጥር 5) ፡፡ ከዚህም የተነሳ “ ነጎድጓድና ድምጽም፣ መብረቅ እና የመሬት መናወጥም “ ነበር (ቁጥር 5) ፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት 144,000 ታትመዉ እንደ ነበር አስታዉሱ ፡፡

ራዕይ (8፡ 7)፡ በቀረዉ በምዕራፍ 8 ዉስጥ አራት መለከቶች ተነፉ ፡፡ በተለምዶ መለከት እንደ ማስጠንቀቂያ፣ የሚመጣ ሰራዊትን እንደ ማሳወቂያነት፣ አዲስ ንጉስን እንደ ማሳወቂያነት እንዲሁም ደግሞ የኢዩቤልዩ አመት መምጣትን እንደ ማሳወቂያነት ያገለግላል ፡፡

በመጀመሪያዉ መለከት ሲነፋ “ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆኖ ወደ ምድር ተጣለ “ (ቁጥር 7) ፤ ከዚህም የተነሳ “ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ የለመለመም ሳር ሁሉ ተቃጠለ “ (ቁጥር 7) ፡፡ ዋይርስቤ ይህንን በምድር ላይ እንደሆነ ፍርድ ይመስለዋል ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ በዘጸዓት የመጀመሪያዉ እና የሰባተኛዉ መቅሰፍት ጥምረት እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡

ራዕይ (8፡ 8-11)፡ በሁለተኛዉ መለከት ሲነፋ “ በእሳት የሚቃጠል ታላቅ ተራራን የሚመስል ነገር በባህር ተጣለ “ (ቁጥር 8) ፤ ከዚህም የተነሳ “ የባሕርም ሲሶው ደም ሆነ በባህርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ የመርከቦችም ሲሶዉ ጠፋ “ (ቁጥር 8-9) ፡፡ ዋይርስቤ ይህን በባህር ላይ እንደሆነ ፍርድ ይመስለዋል ፡፡ ሰዎስተኛዉ መለከት ሲነፋ “ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ በወንዞችና በዉኃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ “ (ቁጥር 10) ፤ ይህም ኮኮብ ስሙ “ እሬቶ “ ይባል ነበር ፤ ከዚህም የተነሳ “ የዉኃዉም ሲሶ መራራ ሆነ መራራም ስለ ተደረገ በዉኃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ “ (ቁጥር 11) ፡፡ ማክአርቱር “ እሬቶ “ “ ለስካር መንስኤ የሚሆን እና በመጨረሻም የሚገድል መራራ የተመረዘ የስር ንጥረ ነገር “ እንደ ነበር ያሳስባል ፡፡ ዋይርስቤ ይህን በመጠጥ ዉኃ ላይ እንደሆነ ፍርድ ይመስለዋል ፡፡

ራዕይ (8፡ 12-13)፡ አራተኛዉ መለከት ሲነፋ “ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ የእነዚህም ሲሶ ጨለመ “ (ቁጥር 12) ፤ ከዚህም የተነሳ “ የቀንም ሲሶዉ እንዳያበራ እንዲሁም የሌሊቱ “ (ቁጥር 12) ፡፡ በቁጥር 13 ከአራተኛዉ መለከት በኋላ የሚያወራ እንድ ንስር በሰማይ እየበረረ “ የሰዎስቱ መለዓክት መለከት ስለሚቀረው ድምጽ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው ! “ በማለት አወጀ ፡፡

መደምደሚያ

አሁን ሰባተኛዉ ማህተም ተፈቷል ፤ በዚህ ሂደት ዉስጥ የቅዱሳን ፀሎት፣ ሰማያዊ መስዋዕት በምድር ላይ ተጣሉ ፤ መለዓክት በምድር ላይ በሚወድቀዉ በእግዚአብሔር ፍርድ ማስጠንቀቂያ መለከታቸዉን ይነፋሉ ፡፡

በምላሹ ምናልባት ሰዎች ንስኃ በመግባት የሚመጣዉን ፍርድ እንዲያስወግዱ በአስቸኳይ የኢየሱስን መልካም ዜና ማጋራት/መናገር አለብን ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Ephesians–Revelation, v. 11 (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 592.

  2. Wiersbe, p. 593.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1746.

  4. Wiersbe, p. 593.

  5. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 2009–2010.

  6. Wiersbe, p. 593.

ጥያቄዎች

  1. የሰባተኛዉ ማህተም መፈታታ ወዲያዉኑ በምን የተከተለ ነበር (ራዕ 8፡ 1) ? በዚህን በዝምታ/በጸጥታ ጊዜ ቁርባን እና የቅዱሳን ሁሉ ፀሎት በእግዚአብሔር ፊት የሚሄድ እንደ ነበር ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ ሰባተኛዉ ማህተም ከተፈታ በኋላ ማንኛዉም ነገር ከመሆኑ በፊት መሆኑ ለምን አስፈለገ ?
  2. መለዓኩ ጥናዉን በእሳት በመሙላት ወደ ምድር ለምን እንደጣለዉ ምን ታስባላችሁ?ስለ ነጎድጓድ ድምጽ፣ ስለ መብረቅ ብልጭታ እና ስለ መሬት መናወጥ የእናንተ ሀሳብ ምንድን ነው ? (ራዕ 8፡ 5, 11፡ 19, 16፡ 18)
  3. የመጀመሪያዉ መለከት ወደ ምድር የምን ፍርድን ያመጣል ?
  4. በሁለተኛዉ መለከት የሚነድድ የሚመስል ተራራ ወደ ባህር ተወረወረ ፤ ይህ ዮሐንስ ስለሚያዉቀዉ የሜዴትራሊያ ባህር ማሳያ እንደ ሆነ ታስባላችሁ “ ዉቅያኖስ “ የሚመስል እንደሆነ ? በዚህ አገባብ/አገላለጽ “ እሬቶ “ ምን ማለት እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ራዕ 8፡ 11)
  5. በመጀመሪያዎቹ በእያንዳንዳቸዉ መለከቶች የምድር የትኛዉ ክፍል ተጎዳ ? እስከዚህ ስፍራ ድረስ ዮሐንስ በሕዝቡ የተደረገን ንስኃ መግባትን መዝግቧል ?
  6. በራዕይ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 8:13

“I looked again and heard an eagle flying high overhead, crying out in a loud voice, ‘Woe! Woe! Woe to those who live on the earth, because of the remaining trumpet blasts that the three angels are about to sound!’”

ሰባተኛውም ማህተም ሲፈታ በሰማይ ዙፋኑ ባለበት ክፍል ለግማሽ ሰዓት ያክል ጸጥታ ሆነ መልአክም በእግዚአብሔር ፊት ዕጣንና የቅዱሳን ጸሎትን አቀረበ፡፡ ከዚያም ዮሐንስ ቀጥሎ አራት መላዕክት የመጀመሪያዎቹን አራት መለከቶች ሲነፉ አየ፡፡ መለከቶቹም በምድር ላይ ጥፋትን አመጡ ፡- ሲሶውን የምድር አካል እሳት አጠፋ፤ ሲሶውም የባህር ክፍል በደም ተሞላ፤ ሲሶውም የውሃ ክፍል መራራ ይሆናል ከዚያም በኋላም የጸሀይ፣ የጨረቃ እና የክዋክብት ሲሶውም በጨለማ ይሞላል፡፡ በመጨረሻም ገና የቀሩት ሶስት መለከቶች ሲነፉ የበለጠ አስከፊ ሊሆን ነበርና፣ አንድ ንስር በማስጠንቀቅ እንዲህ በማለት ጮኸ “ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው!”

በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ባለው ነገር ውስጥ ለመኖር ማሰብ ከባድ ሆኖ አገኛችሁት አይደል? አዎን እውነቱ እናንተም የክርስቶስ ተከታይ ሆናችሁ ይህንን ብጥብጥ አመጽ ልታዩ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን በጨለማው ፊት፣ በብጥብጡ ፊት፣ በጥፋቱ ፊት ጌታ ከእናንተ ጋር እንደሚሆን ይናገራል፡፡ እርሱ ጠባቂያችሁ ነው፣ እርሱ ተስፋችሁ ነው፡፡ የሚገጥማችሁ ነገር ምንም ይሁን ጨለማ፣ መራራ ውኃ ወይም አሳት ሊሆን ይችላል፣ ጌታ ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ ፈጽሞ እንደማይተዋችሁ ይናገራል፡፡ እርሱ በመካከላችሁ ነው፡፡ ስትደክሙ እርሱ ብርታታችሁ ይሆናል፡፡ ዛሬ ሌሎችም እንደ እናንተ በነውጥ ውስጥ ሰላምን ያገኙ ዘንድ የእግዚአብሔርን ተስፋ ንገሩዋቸው፡፡ በሉ ሂዱ ተናገሩ!

“አየሁም፥ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ፦ ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው ሲል ሰማሁ።”

  • ራዕይ 8፡13

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘዳግም 31:6 — “ጽኑ፥ አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፥ ከፊታቸውም አትደንግጡ፤ አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ አይጥልህም፥ አይተውህም።”

ምሳሌ 8:10 — “የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።”

ራዕይ 8:1–2 — “ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው።”