Revelation Revelation

The Fifth And Sixth Trumpets

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 717 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የራዕይ ጥናታችንን በምዕራፍ 9 እንቀጥላለን ፡፡ የመጽኃፉ ርዕስ ራዕይ እንጂ መገለጥ አይደለምምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋሪያዉ ለዮሐንስ የተሰጠ የማያቋርጥ ራዕይ ስለሆነ ፡፡ ምዕራፍ 1 ስለ ራዕይ ይገልፃል፣ ምዕራፍ (2-3) ስለ ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ይሸፍናሉ ፤ ምዕራፍ (4-5) ለበጉ ስለ ተዘጋጀዉ የእግዚአብሔር ዙፋን ክፍል ይሸፍናል ፡፡ ምዕራፍ (6-8) ክርስቶስ እንዴት ለሕዝቡ - ለአይሁዶች፣ ለአሕዛቦች እና ለማያምኑት እንደሚገለጥ ምስልን ይሰጣሉ ፡፡ በሁሉም ጥናታችን መሰረት የዚህ የጊዜ ቅደም ተከተል መረዳታችን ይህ ነው፡

  • ኢየሱስ ሰባቱን ማህተም በሚገልጥበት ሰባት አመት ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ይለቀቃል ከዚያም ጦርነት፣ ርኃብ፣ ሞት፣ የተሰዉት መስዋዕት መጠበቅ፣ አስፈሪ የተፈጥሮ ክስተቶች እና ዝምታ ይሆናል ፡፡
  • የዚህ የሰባቱ የመጨረሻው ሰዎስት አመት ከግማሽ አመት የታላቁ መከራ ጊዜ ነው ፤ መከራው ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ወደ ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ (የክፋት ጥፋት) በመሄድ አምላክ እንደሆነ በሚያዉጅ ጊዜ ይጀምራል ፡፡
  • ከዝምታ በኋላም ስለሚመጣዉ ጥፋት/አደጋ የሚያስጠነቅቁ ሰባት መለከቶች (መለዓክቶች) የተገለጡ ናቸው ፡፡ በመጀመሪያዎቹ በአራቱ ላይ ተመልክተናል፡ 1) እሳት፣ 2) ባህሮች በደም ተበክለው፣ 3) የመጠጥ ዉኃ መበላሸት እና 4) ፀሐይ፣ ጨረቃ እና ከዋክብት እንደ ተፈጥሮ እንደተቀየረ ይጠፋሉ/ይጉዳሉ ፡፡

በምዕራፍ 9 በአምስተኛዉ እና በስድስተኛዉ መለከትን ድምጽ እናነሳለን ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (9፡ 1-2)፡ አምስተኛዉ መለከት ከተነፋ በኋላ አንድ ኮኮብ ከሰማይ ይወድቃል የትልቁም ጉድጓድ መክፈቻ የተሰጠዉ ይሆናል (ቁጥር 1) ፤ በቁጥር 11 መሰረት ኮኮቡ ክፉዉ ወይም ሰይጣን ራሱ ወይም ደግሞ ሰዎስተኛው ግምት መለዓክ ሊሆን ይችላል ፡፡ ኬይሊ ሰይጣን ወደሚለዉ ያዘነብላል ፤ ሌሎች መጽኃፍ ቅዱሳዊ ፅሁፎች ይህን ይደግፋሉ፡

ሉቃ (10፡ 18) የኢየሱስን ቃል ለ70ዎቹ መዝግቧል፡ “ ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ “ ፡፡

ኢሳ (14፡ 12-14)፡ “ አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቆረጥህ “ በማለት ይናገራል (ኢሳ 14፡ 12) ፡፡

ሕዝ (28፡ 12-15)፡ “ ከተፈጠህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ “ (ሕዝ 28፡ 15) ፡፡

ይህ ማለት ሰይጣን ቁልፍን በመቀበል የጥልቁን ጉድጓድ ከፈተው ጢሱም ከታላቁ እቶን መጣ ማለት ነው (ቁጥር 2) ፤ ብዙ ሙህራን ሰይጣን ሲዖልን ወደ ምድር ለማምጣት በጥልቁ ጉድጓድ ዉስጥ የካፋትን ሰራዊት እንደሚለቅ ማለት እንደ ሆነ ያስባሉ ፡፡ ከዚህም የተነሳ አንዳንዶች አምስተኛዉን መለከት እንደ ሰይጣን ወረራ ያመለክቱታል /ይጠቅሱታል ፡፡ ታላቁን ጉድጓድ ሰይጣንም፣ አጋንንትም ወይም መለዓክት ይክፈተው የክፉዉ ሰራዊት ክፋታቸዉን እንዲያደርጉ አንድ የመጨረሻ እድል ተሰጣቸው ፡፡

ራዕይ (9፡ 3-6)፡ ቀጥሎም አንበጦች ከጭሱ ዉስጥ ወጡ ጊንጥ እንዳላት ተመሳሳይ ኃይል ተሰጥቷቸዉ ነበር (ቁጥር 3) ፡፡ ማክአርቱር “ ይሁን እንጂ እነዚህ የተለመዱ አንበጣዎች አይደሉም ነገር ግን አንበጣ የሚመስሉ የመንጋን ጥፋት የሚያመጡ ሆን ተብሎ ዉጫዊ የአጋንንት መገለጫ የሆኑ አንዴ በተለዬ የተዘጋጁ እንደ ሆኑ “ ይናገራል ፡፡ አንበጣዎቹ ሳርን እንዳይጎዱ ተነገራቸዉ ምክንያቱም ቀድሞ ጠፍቶ ስለ ነበር ነገር ግን በግንባራቸዉ ላይ የእግዚአብሔር ማህተም የሌላቸዉን ብቻ እንዲጎዱ ተነገራቸው (ቁጥር 4) ፤ ይህ የእግዚአብሔር ማህተም በግንባራቸዉ ላይ ካላቸው ከ144,000 ዉጪ በሁሉም ላይ ይሆናል ፡፡ እንዲገድሉ አልተፈቀደላቸዉም ለአምስት ወራት ተጠቂዎቹን እንዲያሰቃዩአቸዉ እንጂ (ቁጥር 5) ፤ ማክአርቱር የአንበጣ የህይወት የተለመደዉ የህይወት ኡደት አምስት ወር እንደ ሆነ እና አብዛኛዉን ጊዜ ከግንቦት እስከ መስከረም እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡ ስቃዩ ሰዎች ለማምለጥ ያልተሳካ ራስን መጥፋት እስኪሞክሩ በጣም አስከፊ ይሆናል (ቁጥር 6) ፡፡

ራዕይ (9፡ 7-12)፡ አንበጦቹ በወርቅ አክሊል እና የሰዉ ፊት ያላቸዉ ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶችን ይመስላሉ፣ ፀጉራቸዉ የሴት ፀጉር ይመስላል፣ ጥርሳቸዉ የአንበሳን ይመስላል በተጨማሪም ደረታቸዉ የብረት ጥሩር ይመስላል፡፡ ክንፎቻቸው ልክ ወደ ጦርነት እንደሚጋልቡ ሰረገላዎች ድምጽ ድምፃቸዉ ይመስላል (ቁጥር 7-9)፣ ጅራታቸዉም ልክ እንደ ጊንጥ መዉጊያ ነበረው (ቁጥር 10) ፡፡ አንዳንድ ምሁራን እነዚህ አንበጣዎች ከሰይጣን እንደ ነበሩና ልክ በመለዓክት ዉስጥ ደረጃ እንዳለ በሰይጣን/በክፉው ዉስጥ ደረጃ/ቅደም ተከተል እንደ ነበራቸው ያመለክታሉ ፡፡ ማክአርቱር ሰይጣናዊ/የክፉዉ ፍጥረት ስሙ “ በግሪክ እና በዕብራዊ በሁለቱም ስሙ አጥፊ የሚል የሆነ ንጉስ እንዳላቸው ፤ በግልፅ የጥልቁ ጉድጓድ መለዓክ ከሰይጣን አንዱ በጣም የታመነዉ መሪ ወይም ምናልባትም ራሱ ሰይጣን እንደ ሆነ “ ይናገራል ፡፡ ይህ የሁሉም የሰይጣናዉ ሰራዊት ዉጊያ መልክ ነው ፡፡

ኢየሱስ አሁንም ሁሉም በቁጥጥሩ ስር እንደ ሆነ እና ለዚህም እንደ ፈቀደ እንዳትረሱ (ኤፌ 6፡ 12) ፡፡ ዛሬ በዚህ ላይ የምናወራ ይመስለኛል ፤ ዮሐ (10፡ 10) ሰይጣን “ ሊሰርቅ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል “ ይላል ፡፡ ቁጥር 12 የሚመጡ ሌላ ሁለት “ ዋይታ/ኃዘኖች “ (መለከቶች) እንዳሉ ያስጠነቅቃል ፡፡

ራዕይ (9፡ 13-21)፡ ስድስተኛዉ መለዓክ መለከቱን ነፋው ዮሐንስም በእግዚአብሔር ፊት ካለዉ አራት ቀንድ የወርቅ መሰዊያ ድምጽ ሲወጣ ሰማ (ቁጥር 13) ፤ ይህ ቋንቋ ከስርየቱ መቀመጫ የወጣ ነው ፡፡ ድምጹም ስድስተኛዉን መለዓክ በኤፍራጠስ ወንዝ ላይ የታሰሩትን አራት መለዓክቶች እንዲለቃቸዉ አዘዘው (ቁጥር 14) ፡፡ እነዚህ የሰዉን ልጅ አንድ ሰዎስተኞዉን ለመግደል ሰራዊት እንዲመሩ የተለቀቁ ለሚሆኑበት ትክክለኛ ክስተት የተዘጋጁ የወደቁ መለዓክት ናቸው (ቁጥር 15) ፡፡ ሁለት መቶ ሚሊዮን አጋንንታዊ/ሰይጣናዊ ወታደሮች ይሳተፋሉ (ቁጥር 16) ፡፡ ፈረሰኞቹ ሰራዊቶች ቀይ፣ ሰማያዊ እና ቢጫ የብረት ጥሩ ለብሰዉ ነበር የፈረሶቹም ራስ እሳትን፣ ጭስን እና ዲንም ይተፋ ነበር (ቁጥር 17) ፡፡

ከሰዉ ልጆች ሲሶው በእነዚህ በሰዎስቱ መቅሰፍቶች - በእሳት፣ በጭስ እና በድን ይገደላሉ (ቁጥር 18) ፡፡ ራዕ (6፡ 8) አንድ አራተኛዉ የሰዉ ልጅ የጠፋ እንዲሆን ይገልፃል ስለዚህም ይህን እሲሶዉ ላይ ሲጨመር እዚህ ስፍራ ላይ ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ የሰዉ ልጅ ይጠፋል ፡፡ ፈረሶቹ ጉዳት የሚያደርስ እባብ የሚመስል ጅራት አላቸው (ቁጥር 19) ፡፡ ተገድለዉ ያልነበሩት እስካሁን ንስኃ ባለመግባት ሰይጣንን እና ጣዖትን ማምለክ ቀጠሉ (ቁጥር 20) ፡፡ “ ስለ መግደላቸዉም ቢሆንም ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም “ (ቁጥር 21) ፡፡

መደምደሚያ

የዚህ ሁሉ ምክንያት ሰዎችን ወደ ንስኃ ለመጥራት ነው ፡፡ ከአለም ሕዝብ ግማሽ ያክሉ ተገድሎ እንኳን አሁንም ሰዎች ወደ እግዚአብሔር አይመለሱም ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 2010.

  2. MacArthur, p. 2010.

  3. MacArthur, p. 2010.

  4. MacArthur, p. 2010.

  5. MacArthur, p. 2010.

ጥያቄዎች

  1. በራዕ (9፡ 1) ከሰማይ ወድቆ የነበረዉ ኮኮብ ማን እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ (ኢሳ 14፡ 12, ሉቃ 10፡ 18, ራዕ 8፡ 10, 20፡ 1) ? ለምን ያን አሰባችሁ ?
  2. በራዕ (9፡ 3) አንበጦቹ ማን ወይስ ምንን ይወክላሉ ? በመጽኃፍ ላይ በምን ትንቢት ላይ ስለዚህ ቀን ቀድሞ ተነግሯል ? (ዘጸ 10፡ 4-5, ኢዩ 2፡ 2, 3, ራዕ 9፡ 10)
  3. በራዕይ (9፡ 2-3) መሰረት እግዚአብሔር አጋንንቶችን ለምን ሰዎችን እንዲያሰቃዩ ወደ ምድር ይለቅቃቸዋል (ዘጸ 12፡ 23, ራዕ 7፡ 2-3) ? ምን ያክል አስከፊ እንደሚሆን እንዴት ታስቡታላችሁ ? (ኢዮ 3፡ 21, ራዕ 6፡ 16)
  4. በራዕይ (9፡ 14-15) መሰረት በምድር ላይ ምን ያክል ሰዉ ይገደላል ? በዚህን ጊዜ ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍርድ የተነሳ በጠቅላላ ምን ያክል ሰዉ ተገደለ ? (ራዕ 6፡ 7-8)
  5. የቀሩት ሰዎች ብዙ ሞትን ካዩ በኋላ ንስኃ ገቡ ? ይህ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ ስለ ክፋት አደገኝነት እናጥመት ምን ይላል ? አሁን በዚህ ጊዜ ዉስጥ እየኖርን እንደ ሆነ ታስባላችሁ ? ልክ በኖህ ዘመን ከኖሩት ከጥንት ሰዎች ይበልጥ ክፋትን የምናደርግ ነን (ዘፍ 6፡ 5, 13፡ 13) ? እግዚአብሔር የዚህን ያክል ቁጣዉን ለምን እንዳዘገየዉ ምን ታስባላችሁ ? (2ጴጥ 3፡ 3-10)
  6. በራዕይ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 9:4–6

“They were told not to harm the grass of the earth, or any green plant, or any tree, but only people who do not have God’s seal on their foreheads. They were not permitted to kill them but were to torment them for five months; their torment is like the torment caused by a scorpion when it strikes a man. In those days people will seek death and will not find it; they will long to die, but death will flee from them.”

አምስተኛውም መለከት ሲሰማ፣ ምድር በጢስ ተሞላች ጨለማም ዋጣት፡፡ አንበጦችም የጊንጦች ስልጣን ተሰጥቷቸው የለመለመን ነገር ሁሉ እንዳይጎዱ ነገር ግን በግንባራቸው የእግዚአብሔር ማህተም የሌላቸውን ብቻ እንድጎዱ ተነገራቸው፡፡ የተፈቀደላቸው እንድገድሉ አልነበረም ይልቁንም ለአምስት ወራት እንድያሰቃዩ እንጂ፡፡ ሰዎች መሞትን ይፈልጋሉ ነገር ግን ሞት ከእነርሱ ይሸሻል፡፡ ስድስተኛውም መለከት ሲነፋ ሲሶ በሚሆነው የሰው ዘር ላይ ሞትን አመጣ፤ ይህም የሚሆነው ሰይጣናዊ በሆነ ወረራ 200ሚሊዮን በሚሆኑ እሳትን፣ ጭስንና ድንን በሚተፉ ፈረሰኞች ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ስላለመታዘዛቸው ንስሀ በማይገቡ ሰዎች ላይ ስቃይና ሞት ይመጣል፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻዎቹ ቀናትም ጭምር ሰዎች የመመለስና ንስሃ የመግባት እድል ይኖራቸዋል፡፡ ለምን እዚያ ድረስ ትጠብቃላችሁ? ዛሬውኑ ወደ ጌታ ለመመለስ ወስኑ፡፡ ምናልባት ህይወታቸውን ለኢየሱስ ያልሰጡ ሰዎችን ታውቁ ይሆናል፡፡ ለእነርሱ በጾም ጸልዩ፤ በእናንተ ውስጥ ያለውን ኢየሱስንም ለማወቅ ይሹ ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ንገሩዋቸው ደግሞም በተግባር አሳዩዋቸው፡፡ ሀዘኑ ይመጣል፤ ስቃዩ መከራው ይመጣል በጣምም መራራ ይሆናል፡፡ ዛሬ በዙሪያችሁ ያለው አስቸጋሪ ሁኔታ ሳያግዳችሁ ለሆነ ሰው በኢየሱስ ላይ ስላላችሁ ተስፋ ተናገሩ፡፡ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉና ከክፉ ስራቸው ለሚመለሱ ሁሉ ለእነርሱ ኢየሱስ ተስፋን ሰላምንና ዘላለማዊ ህይወት እንደሚሰጥ ተናግሯል፡፡

“የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተባለላቸው።አምስትም ወር ሊሣቅዩአቸው ተሰጣቸው እንጂ ሊገድሉአቸው አይደለም፤ እነርሱም የሚሣቅዩት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሣቅይ ነው።በዚያም ወራት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ አያገኙትምም፥ ሊሞቱም ይመኛሉ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።”

  • ራዕይ 9፡4-6

ተጨማሪ ጥቅስ

ሉቃስ 24:47 — “በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።”

ሐዋርያት ሥራ 26:20 — “ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሐ ይገቡ ዘንድና ለንስሐ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ዘወር ይሉ ዘንድ ተናገርሁ።”

ራዕይ 9:20–21 — “በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም፤ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም።”