The Might Angel And The Small Scroll
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አሁን ከዮሐንስ ራዕይ ከሰባቱ መለከት የነፉትን ስድስት መለዓክቶች ሸፍነናል ፡፡ ወዲያዉኑ ከተነፉት መለከቶች በፊት በሚመጣዉ በማንኛዉም ነገር የተጎዱ የማይሆኑ አይሁዳዊ ወንጌላዊያን የነበሩ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ 12,000 በአጠቃላይ 144,000 ሰዎች በእግዚአብሔር የታተሙ ነበሩ ፡፡ ምዕራፍ 10 በስድስተኛዉ እና በሰባተኛው መለከት መካከል እረፍትን ያቀርባል ፤ በስድስተኛዉ እና በሰባተኛዉ ማህተም መካከልም እረፍት እንደ ነበር እናስታዉሳለን ፡፡
እስካሁን ስድስት መለከቶች (መለዓክቶች) ስለሚመጣው አደጋ ማስጠንቀቂያዎችን ገልጠዋል፡ 1) እሳት፣ 2) በደም የተበከሉት ባህሮች፣ 3) የተበከለ የመጠጥ ዉኃ፣ 4) ፀሐይ፣ ጨረቃ እና ከዋክብት ተፈጥሮ እንደተቀየረ ተጎዱ፣ 5) ማህተም የሌላቸዉን ለአምስት ወራት የሚያሰቃይ የሰይጣን ወረራን እና 6) 200,000,000 አጋንንቶች/የሰይጣን ጭፍሮች ለጦርነት እንደሚዘምት አንበጣ መንጋ ቅርፅ ፡፡ ከስድስተኛዉ መለከት በኋላ በአለም ከሚኖረዉ ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ይጠፋሉ ፤ በራዕ (6፡ 8) መሰረት አንድ ሰዎስተኛ የሚሆነዉ ሕዝብ ቀድመዉ ጠፍተዉ ስለ ነበር እዚህ ስፍራ/ጊዜ ላይ ደግሞ ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ የአለም ሕዝብ ሞተዋል ፤ ይህ ወደ ምዕራፍ 10 ዝምታ/እረፍት ይመራል ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (10፡ 1)፡ በቁጥር 1 ዮሐንስ ሌላ ብርቱ መለዓክ በራሱ ላይ ቀስተ ደመና ያለዉ ከሰማይ በደመና ሲወርድ አዬ፡፡ ማክአርቱር “ ሌላ “ ብርቱ መለዓክ ኢየሱስን ሳይሆን ሌላ ፍጥረትን የሚያመለክት እና መለዓኩን “ በዉበበት፣ በታላቅነት እና በኃይል እንደ ተሞላ “ እንደተገለፀ ያመለክታል ፡፡
በራዕይ ላይ የቀረቡት መለዓክቶች ላይ ተመልከቱ፡
- ራዕይ (5፡ 2) ማህተሞቹን ሊፈታቸዉ የተገባ ማን እንደ ነበር ሲጠይቅ “ የብርቱ መለዓክ “ መገኘትን ይናገራል ፤ መልሱ ኢየሱስ ነበር ፡፡
- በራዕ (18፡ 1) አንድ መለዓክ “ ታላቅ ስልጣን እንደተሰጠው “ ይገልፃል ፡፡
- በራዕይ (12፡ 7) በዚያ መለዓኩን ሚካኤል እንደ ሆነ ለይቶታል ፡፡
በራዕይ (10፡ 1) ስለ መለዓኩ የኔልሰን ማብራሪያ “ ሌላ ስፍራ ላይ በስሙ የተጠቀሰዉ ሚካኤል እንዳልሆነ (ራዕ 12፡ 7, ዳን 12፡ 1) ወይም በአዲስ ኪዳን በፍጹም እንደ አንድ መለዓክት ስላልተጠራ ኢየሱስም እንዳልሆነ “ ይገልፃል ፡፡ በዘጽ (16፡ 10) የእግዚአብሔርን ክብር በመግለጥ ደመናዉ ተገለጠ ፤ የራዕይ (10፡ 1) ቋንቋ ተመሳሳይ ነው ፡፡
ራዕይ (10፡ 2-3)፡ ጭብጡ/ፍሬ ነገሩ ይህ መለዓክ ማን እንደሚሆን ማንም አለማወቁ ነው ፡፡ መለዓኩ በእጁ የተከፈተች ትንሽ መፀኃፍ አለው የቀኝ እግሩንም በባህር ላይ አስቀመጠዉ ግራ እግሩን ደግሞ በመሬት ላይ አስቀመጠው (ቁጥር 2) ፡፡ ይህ ተፈተዉ/ተከፍተዉ ከነበሩት ማህተሞች ጋር ተመሳሳይ ከሆነ እደነቃለሁ ፤ ያ መፅኃፍ ከነበር ይህ መለዓክ ክርስቶስ ነው ፡፡ መለዓኩ ልክ እንደሚያገሳ አንበሳ ጮኸ ሰባት ነጎድጓድም በድምፃቸዉ ተናገሩ (ቁጥር 3) ፡፡
ራዕይ (10፡ 4)፡ ዮሐንስ ሰባቱ ነጎድጓዶች ያሉትን ለመፃፍ ዝግጁ ነበር ነገር ግን ከሰማይ የሆነ ድምጽ እንዳይጽፍ ነገረው (ቁጥር 4) ፡፡ ራዕ (1፡ 4) ስለ ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ተናግሯል ነገር ግን እነዚህ ሰባት ነጎድጓዶች ተመሳሳይ መናፍስት እንደሆኑ መናገር አንችልም ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ከሰማይ የመጣዉ ድምጽ ከብርቱዉ መለዓክ የተለዬ እንደ ሆነ እና ምናልባት ክርስቶስ እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡
ራዕይ (10፡ 5-7)፡ በአንድ እግሩ ባህር ላይ በሌለኛዉ እግሩ ደግሞ መሬት ላይ የቆመዉ መለዓክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ በማንሳት በዘላለም አምላክ እና በሁሉም ነገር ፈጣሪ መኃላን ማለ ፤ መለዓኩ “ ወደ ፊት አይዘገይ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልዓክ ሊነፋ ባለዉ ጊዜ ድምጹም በሚሰማበት ዘመን ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምስጥር ይፈፀማል “ (ቁጥር 7) በማለት ማለ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ሰባተኛዉ መለከት ከተነፋ በኋላ ወደ ክርስቶስ መመለስ የሚመሩ ክስተቶች መገለጥ ላይ ምንም መዘግየት እንደማይኖር “ ይናገራል ፡፡
ቁጥር 7 ሳነብ በሪቫይቭ ት/ቤት ዉስጥ በትክክል ለማድረግ ያስቀመጥነዉ እንደ ሆነ አስባለሁ ፡፡ ማክአርቱር ቁጥር 7 “ ሚስጡሩ (የተሰወረዉ እቅድ) እግዚአብሔር ኃጢዓተኞችን በማጥፋት በምድር ላይ የጽድቅ መንግስቱን ሲመሰረት የሁሉም ነገር የመጨረሻ ፍፃሜ እንደሆነ እንደሚገልፅ ፤ ይህ ሚስጥር በእግዚአብሔር ነቢያት የታወጀ ሙሉ ለሙሉ ያልተገለጠ እንደ ነበር (አሞ 3፡ 7) እንደሚገልፃ “ ይናገራል ፡፡
ከዚያም የእግዚአብሔር እቅድ የተፈፀመ ይሆናል ፡፡ ማክአርቱር ሚስጥር ወይም የተሰወረ ለሚለው ቃል “ የታሸገ “ ወይም “ የተዘጋ “ የሚል የግሪክ ቃል እንደ ሆነ ያመለክታል ፤ ያ ማለት የታሸገ ወይም የተዘጋ ማንኛዉም ነገር የተከፈተ አይሆንም ማለት ነው (ኤፌ 3፡ 4-5) ፡፡
ሁሉም ነገር ወደ ፍሬአማነት እንደሚመጣ ተስፋን ስለሚሰጥ የመሀላ ዋጋዉ ትልቅ ነው ፡፡ ለሁሉም ለሪቫይቭ ት/ቤት ቁልፍ ጥቅሳችን ማቴ (5፡ 17) ነው፡ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ ፤ ይህ ሁሉም ሚስጥር - ሁሉም እቅድ ወደ ፍሬአማነት ይመጣል ፡፡
ራዕይ (10፡ 8-11)፡ ከሰማይ የሆነዉ ድምጽ እንደ ገና በመናገር ዮሐንስን መጽሃፉን ከመለዓኩ እጅ ላይ እንዲወስደዉ ነገረው ፡፡ ዮሐንስም እንደታዘዘው አደረገ መለዓኩም ዮሐንስን በሆዱ መራራ ነገር ግን በአፉ ላይ እንደ ማር የምትጣፍጠዉን መፅኃፏን እንዲበላ ነገረው (ቁጥር 8-9) ፡፡
መጽኃፉ ስለሚመጣዉ ነገር ልዩነት ያሳያል ፤ የሚመጣዉ ነገር ሰዎች በሂደቱ ስለሚጎዱ ጥሩ አይሆንም ነገር ግን የእግዚአብሔር እቅድ መፈፀም ስለሆነ መልካም ይሆናል ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደ እንጀራ (ማቴ 4፡ 4)፣ እንደ ወተት (1ጴጥ 2፡ 2)፣ እንደ ደስታ (ኤር 15፡ 16)፣ በሐዋሪያዉ ጳዉሎስ እንደ ስጋ እና በመዝሙር ላይ እንደ ማር ተገልፆአል ፡፡ በሕዝ (2፡ 9) መጽኃፉን ሕዝቅኤል እንዲበላዉ ተደረገ ፡፡
ዮሐንስ መጽኃፉን በመዉሰድ በላው ፤ በአፉ ዉስጥ እንደ ማር ጣፋጭ ነገር ግን በሆዱ መራራ ነበር (ቁጥር 10) ፤ ከዚያም “ በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገስታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት እንዲናገር “ ተነገረው (ቁጥር 11) ፡፡
መደምደሚያ
አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር በሚለቀቅ/በሚነገር ጊዜ ሰዎች አይወዱትም ምክንያቱም ጣዕሙ መራር ስለሆነ ፡፡ ኢየሱስ ስለ ኃጢዓታችሁ በመስቀል ላይ እንደ ሞተና ተመልሶ እንደሚመጣ ካላመናችሁ ወደ ሲዖል ትሄዳላችሁ ፤ ይሄ ለማያምኑት መራር መልዕክት ነው ፤ የማያምኑ የዘላለም ጥፋት ይገጥማቸዋል ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንደ ሞተ አምላካችሁ እና አዳኛችሁ ለመሆን ተመልሶ ወደ ህይወት እንደ መጣ ካመናችሁ በዚህ አጠቃላይ ሂደት የዘላለም ተስፋ ይኖራችኋል ፡፡
መሀላው በአጠቃላይ በመጽኃፍ ቅዱስ ጥናት ያወራናቸዉ ሁሉም ነገሮች ወደ ፍሬአማነት/ወደ እዉነት እንደሚመጡ ነው ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን/ሲደረግ እስካሁን ሰባተኛዉን መለከት አላገኘነውም/አልተነፋም ፡፡ ዮሐንስ ለሁሉም እንዲናገር የማስጠንቀቂያ መልዕክት ተሰጠው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 2010.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1748.
Nelson’s Commentary, p. 1748.
Nelson’s Commentary, p. 1748-1749.
MacArthur, p. 2012.
ጥያቄዎች
-
በራዕ (10፡ 1) በመለዓኩ ራስ ላይ ያለዉ ቀስተ ደመና ምን እንደሚወክል ምን ታስባላችሁ ?
-
በራዕ (10፡ 4) እግዚአብሔር ዮሐንስን ከሰባቱ ነጎድጓድ ደዉሎች/ድምጾች የሚሰማዉን እንዳይጽፍ ነገረው ፤ ይህ ለዮሐንስ ከራሱ እንኳን መጠበቅ ምን ያክል አስቸጋሪ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? በአሁኑ ጊዜ ከእግዚአብሔር የሆነን ቃል የሚያዉቁ ለመናገር ግን ያልታደሉ ሰዎች እንዳሉ ታምናላችሁ ?
-
ራዕይ (10፡ 7) አንብቡ ፤ ይህ ምን ማለት እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ? የእግዚአብሔር ሚስጥር ምንድን ነው ? በዚህ ጊዜ ላይ ሁሉም የመፅኃፍ ቅዱስ ትንቢት የተፈፀመ ይሆናል ?
-
መለዓኩ ዮሐንስን “ ትሻን መፅኃፍ “ እንዲበላ አዘዘው ፤ በመጽኃፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ይህን ታዩታላችሁ (ሕዝ 2፡ 8-9, 3፡ 1-3) ? ራዕይ (10፡ 9) ምን ማለት እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ? ይቺ ትንሽ መጽኃፍ ለምን በአፉ ላይ ጣፋጭ በሆዱ ግን መራራ ጣዕም ኖራት ?
-
በራዕይ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 10:6b–7
“There will no longer be an interval of time, but in the days of the sound of the seventh angel, when he will blow his trumpet, then God’s hidden plan will be completed, as He announced to His servants the prophets.”
ሰባተኛው መለከት ከመነፋቱ በፊት ዮሐንስ ኃይለኛ መልአክ ደመናን ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየ፡፡ መልአኩም ሲጮኽ ሰባቱ ነጎድጓዶች ተናገሩ፣ ነገር ግን ዮሐንስን ይህንን እንዳይጽፈው የሆነ ድምጽ ተናገረው፡፡ ከዚያም በኋላ መልአኩ ምንም የቀረ ጊዜ እንደሌለ፣ ከዚህ በኋላ እንደማይዘገይ መጠበቁ እንዳበቃ ተናገረ፡፡ ሰባተኛውም መልአክ ሰባተኛውን መለከት ሲነፋ፣ የእግዚአብሔር የተደበቀ አሳብ የእርሱ ምስጢር ይፈጸማል፡፡
ይህንን ቃልና የዮሐንስን ራዕይ ስታነቡ፣ የወንጌልና የክርስቶስ ምስጢር በፍጹም የሚገለጥበት ጊዜ እንደሚመጣ እመኑ፡፡ መታገሱ መጠበቁ የሚያበቃበትና አሳቡ የሚፈጸምበት ጊዜ ይመጣል፡፡ እስከዚያም እውነቱን መግለጥ ትችሉ ዘንድ ጌታ ኃይልና ብርታት ይሰጣችኋል፡፡ ስለ ክርስቶስ ሚስጥር፣ ስለ እርሱ ሙላት እና ስለ ክብሩ ባለጠግነት ትናገሩ ዘንድ እግዚአብሔር ጸጋን ይሰጣችኋል፡፡ ከክፉ መንገድ ለመመለስ፣ ንስሀ ለመግባትና ጌታን ለመፈለግ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣና አሳቡም ሲፈጸም፣ ዝግጁ ሆናችሁ እንድያገኛችሁ ዛሬ ኢየሱስን ወደ ህይወታችሁ ከመቀበል የሚከለክል የትኛውም ማቅማማትም ሆነ ማመንታት ይቁም!
“ ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።” - ራዕይ 10፡7
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኤፌሶን 3:8–9 —“ ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፥ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ፡፡”
- 1ኛ ቆሮንቶስ 2:7 — “ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።”
- ራዕይ 10:10–11 — “ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ።በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል ተባለልኝ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።