The Two Witnesses
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በራዕይ ዉስጥ ስናጠና ተስፋችን ለራሳችሁ በመጽኃፍ ዉስጥ ጠልቆ በመግባት እንዲያስተምራችሁ ለጌታ መፍቀድ ነው ፡፡ ሰባተኛዉ መለዓክ መለከቱን በነፋ ጊዜ መለዓኩ “ ምንም የሚዘገይ ጊዜ እንደማይኖር “ በመናገር መሀላን ወሰደ ነገር ግን “ የእግዚአብሔር የተደበቀው እቅድ ይፈፀማል “ (ራዕ 10፡ 6-7) ፡፡ የክርስቶስ ሙሽራ ተመልሶ ለመምጣቱ የተዘጋጀች መሆን ያስፈልጋታል ፡፡
እስከዚህ ስፍራ/ጊዜ ድረስ ስድስቱ መለከቶች ተነፍተዋል ፡፡ ራዕይ 10 በስድስተኛዉ እና በሰባተኛዉ መለከት መካከል እረፍትን ያሳያል፤ ይህ እግዚአብሔር ለመጨረሻው ድርጊት በገበታ ላይ እንደ ተቀመጠ ነበር ፡፡ ራዕይ 11 በመጽኃፉ የጊዜ ስርዓት ይጀምራል ፡፡ ለ1260 ቀናት ትንቢት የሚናገሩ ሁለት ምስክሮች የተገለፁ ይሆናሉ ፤ አንዳንዶች የምስክሮቹ ትንቢት በሰባቱ አመት የመከራ ጊዜ መጀመሪያ ላይ እንደሚጀምር ይከራከራሉ ፤ የኛ አቋም ምስክሮቹ በታላቁ መከራ በሰባት አመቱ በሁለተኛዉ አጋማሽ ላይ እንደሚተነብዩ ነው ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (11፡ 1-3)፡ ዮሐንስ እንዲለካዉ ተነግሮት የነበረዉ መቅደስ እና መሰዊያ ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ ሊሆን ይችላል ፡፡ ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ በዚህ ዘመን ይቆማል ምክንያቱም መስዋዕት በሚደረግበት በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ራሱን ስለሚገልጥበት ፡፡ ዮሐንስ የቤተ መቅደሱን መግቢያ አደባባይ (እድሞ) እንዳይለካ ታዘዘ ምክንያቱም “ ለአሕዛቦች ተሰጥቷልና እነርሱም 42 ወር የተቀደሰችዉን ከተማ ይረግጡአታል “ (ቁጥር 2) ፤ አራባ ሁለት ወር ሰዎስት አመት ከግማሽ የሚለዉ ሌለኛዉ መንገድ ፡፡
በታላቁ መከራ ዉስጥ ኢየሩሳሌም ለአሕዛቦች የተሰጠች ትሆናለች ፡፡ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ በመጀመሪያዉ ሰዎስት ከግማሽ አመት ጊዜ የሰላም ስምምነትን ስለሚያደርግ ነገሮች በሚያምር ፀጥታ/ዝምታ ውስጥ ነበሩ ፤ ዳንኤል ስለዚህ ጊዜ ትንቢትን ተናግሯል፡ “ እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባኤ ያደርጋል ፤ በሱባኤዉም እኩሌታ መስዋዕቱንና ቁርባኑን ያስቀራል ፤ በርኩሰትም ጫፍ ላይ አጥፊዉ ይመጣል ፤ እስከ ተቆረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሰፍት በአጥፊዉ ላይ ይፈስሳል “ (ዳን 9፡ 27) ፡፡ በዳንኤል አንድ ሳምንንት ሰባት አመትን ያሳያል ፡፡
ራዕይ (11፡ 4)፡ በዚህ በሚቀየር ተመሳሳይ ጊዜ እግዚአብሔር ትንቢት እንዲናገሩ ሁለት ምስክሮችን ያቆማል፡ “ እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው “ (ቁጥር 4) ፤ ይህ ለዘካርያስ (3-4) ማጣቀሻ ነበር ፡፡ ማክአርቱር በመቅረዞቹ ላይ ያለዉ ዘይት ከወይራ ዛፎቹ የመጣ እንደ ሆነ ፅፏል ፡፡ የወይራ ዛፎቹና የመቅረዞቹ የመነቃቃት/የመነሳሳት መልኮች ናቸው ፤ የማጠቃለያ ብልጭታቸዉ የንስኃ መልዕክትንም ያካትታል ፡፡
በዘካርያስ ኢያሱና ዘሩባቤል ቤተ መቅደሱን መልሰዉ ስለ ገነቡ እንደ ወይራ ዛፍ እና መቅረዝ የተገለፁ ነበሩ ፤ አሁን እነዚህ ሁለቱ አዲሶቹ ምስክሮች የእግዚአብሔር ፍርድ እየመጣ እንደ ሆነ በማስጠንቀቅ ሰዎችን ወደ ጌታ በማመልከት በታላቁ መከራ በሁለተኛዉ ግማሽ ጊዜ ተመሳሳይ ነገርን ያደርጋሉ ፡፡
ራዕይ (11፡ 5-6)፡ እግዚአብሔር ምስክሮቹን በተዓምራታዊ መንገድ ይጠብቃቸዋል ፡፡ ሊጎዳቸዉ የሚሞክረዉን የሚበላ እሳት ከአፋቸዉ ዉስጥ ይወጣል (ቁጥር 5) ፤ በተጨማሪም እንዳይዘንብ የማድረግ፣ ደምን ወደ ዉኃ የመቀየር እና “ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሰፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ “ (ቁጥር 6) ስልጣን የተሰጣቸዉ ናቸው፡፡
ምስክሮቹ እነማን ናቸው ? ማክአርቱር ለምን ሙሴና ኤልያስ ሊሆኑ እንደሚችሉ ስድስት ምክንያቶችን ዘርዝሯል፡
- “ ልክ እንደ ሙሴ ምድርን በመቅሰፍት ይመታሉ እንዲሁም ደግሞ ልክ እንደ ኤልያስ እንዳይዘንብ የማድረግ ኃይል አላቸው “ ፡፡
- “ የአይሁድ ታሪኮች/ባህሎች ሙሴ እና ኤልያስ ሁለቱም እንደሚመለሱ ይጠብቃሉ “ ፡፡
- በዘዳ (18፡ 16) መሰረት “ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህም እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል ፤ እርሱንም ታደምጣለህ “ ፡፡
- ሚል (4፡ 5) “ እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ “ በማለት ይናገራል ፡፡
- ዮሐ (1፡ 21) “ እንኪያስ ማን ነህ ? ኤልያስ ነህን ? ብለዉ ጠየቁት ፡፡ አይደለሁም አለ ፡፡ ነቢዩ ነህን ? አይደለሁም ብሎ መለሰ “ ፡፡
- የአይሁድ ሰዎች ያለማቋረጥ የሙሴን እና የኤልያስን መመለስ እየጠበቁ ነበር ፡፡
- “ ኤልያስ እና ሙሴ ሁለቱም በኢየሱስ በመለዉጡ ጊዜ ቀርበዉ ነበር “ ፡፡
- “ ሙሴ እና ኤልያስ ሁለቱም ለንስኃ ለማነሳሳት መለኮታዊ ኃይልን ተጠቅመዋል “ ፡፡
- “ ኤልያስ በህይወት እያለ ወደ ሰማይ ሲወሰድ እግዚአብሔር የሙሴን አካል በፍፁም ባማይገኝ ስፍራ ቀበረው “ ፡፡
- “ ሁለቱ ምስክሮች የሚያመጡት ድርቅ ርዝማኔ ኤልያስ ካመጣዉ ጋር ተመሳሳይ ነው “ ፡፡
ምስክሮቹ የፍርድን መልዕክት ያመጣሉ እንዲሁም ደግሞ የከበረ የምህረትንም እድል ያመጣል ፡፡
ራዕይ (11፡ 7-10)፡ በቁጥር 7 “ ምስክርነታቸዉን ከፈፀሙ በኋላ “ የሚለዉ ሐረግ የሰዎስት አመት ከግማሽ መጨረሻውን ያመለክታል ፡፡ የሰይጣንን መገኘት የሚወክለዉ አዉሬዉ “ ከጥልቁ ጉድጓድ ይወጣል “ ከዚያም “ ይዋጋቸዋል፣ ያሸንፋቸዉማል ከዚያም ይገድላቸዉማል “ (ቁጥር 7) ፡፡ አንዳንዶች ይህ በመጀመሪያዉ ሰዎስት አመት ከግማሽ መጨረሻ አካባቢ እንደሚከሰት ሲያምኑ ሌሎች ደግሞ ቆይቶ እንደሚከሰት ያምናሉ ፡፡ መሰረታዊዉ/ዋና ዝርዝር ከጥልቁ ጉድጓድ አዉሬዉ የሚወጣበት ጊዜ ነው ፤ በጊዜ አቀማመጡ ላይ ይህ ክስተት ትክክለኛ መሆኛዉን ጊዜ በእርግጠኝነት መወሰን አስቸጋሪ ነው ፡፡
አዉሬዉ ምስክሮቹን ከገደላቸዉ በኋላ በድናቸዉን “ በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸዉ የተሰቀለባት ናት “ (ቁጥር 8) ፤ ያቺ ከተማ ኢየሩሳሌም ነበረች ፡፡ ሰዎችም ለሰዎስት አመት ከግማሽ በድናቸዉን ለማየት በአጠገባቸዉ ይመጣሉ ፤ በዚህን ጊዜ ማን እንዲቀብራቸዉ የተፈቀደለት አይሆንም ፡፡ አለም በምስክሮቹ መሞት በመደሰት “ እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስለ ሳቀዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል በደስታም ይኖራሉ እርስ በእርሳቸዉም ስጦታ ይሰጣጣሉ “ (ቁጥር 10) ፡፡
ራዕይ (11፡ 11-14)፡ ከሰዎስት አመት ከግማሽ በኋላ እግዚአብሔር ከሞት ያስነሳቸዋል (ቁጥር 11) ፡፡ እግዚአብሔር ምስክሮቹን “ ጠላቶቻቸዉም እየተመለከቷቸው “ (ቁጥር 12) በደመና ከሰማይ ጠራቸው ፤ ይህ እንደ ሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከተማዋን መታት “ ከከተማይቱም አስረኛዉ እጅ ወደቀ በመናወጥም 7,000 ሰዎች ተገደሉ “ (ቁጥር 13) ፤ የቀሩትም “ ፍርሃት ያዛቸው ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ “ (ቁጥር 13) ፡፡ አሁን “ ሁለተኛዉ ወዮ አልፏል “ (ቁጥር 14) ፤ እስካሁን በስድስተኛዉ እና በሰባተኛዉ መለከት መካከልበዝምታ/በእረፍት ጊዜ ላይ ነን ፡፡
ራዕይ (11፡ 15-19)፡ አሁን ሰባተኛዉ መለከት ተነፋ ድምጾችም በሰማይ የመሲሁን ድል ማድረግ እና የዘላለም መንግስትን አወጁ (ቁጥር 15) ፡፡ 24 ሽማግሌዎችም እግዚአብሔርን አመሰገኑ/አከበሩ (ቁጥር 17-18) ፡፡
መደምደሚያ
የእግዚአብሔር ታማንነት፣ ኃይል እና ቁጣ ይገለጣል ፡፡ የእግዚአብሔር ምህረትና ታማኝነት ሰባተኛዉ መለከት ወደ ሰባጠናዉ የእግዚአብሔር ቁጣ መለከት መነፋት ሲመራ ይገለጣል ፤ ይህ ሁሉ በሁለቱ ምስክሮች ስራ ተጀመረ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 2013.
MacArthur, p. 2013.
MacArthur, p. 2013.
ጥያቄዎች
-
በራዕይ 11 መጀመሪያ ላይ እግዚአብሔር ዮሐንስ ምን እንዲያደርግ አዘዘው ? ከቤተ መቅደሱ ዉጪ ያለዉን/መግቢያ አደባባይ ወይም እድሞ ለምን አላካተተዉም ነበር ? መለዓኩ ለማንኛዉ ቤተ መቅደስ አመለከተ /ገለፀ ? (ዳን 9፡ 27, ሉቃ 21፡ 24, 2ተሰ 2፡ 4)
-
ሁለቱ ምስክሮች ለምን ያክል ጊዜ ትንቢት ይናገራሉ ? እንዴት የተገለጹ ነበሩ ? ምን አይነት ስልጣን አላቸው ?
-
ሁለቱ ምስክሮች ከሙሴ እና ከኤልያስ ጋር እንዴት ነበር የሚመሳሰሉት ? (ዘጸዓት 7-11, 1ነገስት 17, ሚልክያስ 4፡ 5, ያዕ (5፡ 16-18), ራዕ 11፡ 5-6)
-
ሁለቱ ምስክሮች እንዴት ይገደላሉ ? ለምን ያክል ጊዜ የሞቱ ይሆናሉ ? በሞቱ ጊዜ የሕዝቡ ምላሽ ምን ይሆናል ? ምስክሮቹ ከተነሱ በኋላ ምላሻቸዉ ምን ይሆናል ?
-
በራዕይ (11፡ 17) በጣም አስተማማኙ የግሪክ ፅኁፍ “ የሚመጣዉ “ የሚለዉን ሐረግ ትቶታል ፤ ያ ሐረግ ያላስፈለገዉ ለምንድን ነው ? (ራዕይ 1፡ 4, 8፣ 4፡ 8)
-
በራዕይ 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 11:16-17
The 24 elders, who were seated before God on their thrones, fell facedown and worshiped God, saying: We thank You, Lord God, the Almighty, who is and who was, because You have taken Your great power and have begun to reign.”
በስድስቱ መለከቶች ምክንያት በተፈጠረው መከራ ወቅት፣ እግዚአብሔር ለ1260 ቀናት ወይም ለሶስት ዓመት ከመንፈቅ ትንቢትን ይናገሩ ዘንድ ሁለት ምስክሮችን ይሾማል፡፡ ሁለቱ ምስክሮችም ምስክርነታቸውን በቋጩ ጊዜ፣ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ፣ ሰይጣን ይገድላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ከሶስት ቀን ከግማሽ በኋላ የእግዚአብሔር የህይወት መንፈስ መልሶ ያቆማቸዋል ወደ ሰማይም ያርጋሉ፡፡ ከዚያም ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ይነፋል፤ ታላላቅ ድምጾችም በሰማይ ፡- “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል!” ይላሉ፡፡ ሰዎችም ይደነግጣሉ ሆኖም ለእግዚአብሔር ክብርን ይሰጣሉ፡፡
ሁለቱ ምስክሮች በመከራው ወቅት ስላለው መነቃቃት ያመለክታሉ፡፡ በውስጣቸውም ከሞት የተነሳው አዳኝ ኃይል ነበራቸው፡፡ እናንተም ይህ ከሞት የተነሳው አዳኝ ኃይል አላችሁ፡፡ እናንተ ለክብሩ መጠቀሚያ ትሆኑ ዘንድ ውድ እቃዎች ናችሁ፡፡ እግዚአብሔር በእናንተ ውስጥ ባለው ኃይሉ አማካኝነት በጨለማ ላይ፣ በአጋንንት ላይ ደግሞም በበሽታ ላይ ስልጣንን ሰጥቷችኋል፡፡ ጌታ ሰዎች ከዘላለማዊ ፍርድ ይድኑ ዘንድ እናንተ ምስክሮች ለመሆን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እንደሚሰጣችሁ ተናግሯል፡፡ ዛሬ በጌታ ኃይልና ስልጣን ሂዱና መልካሙን ዜና ተናገሩ፡፡
“በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ፦ ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን ፡፡”
- ራዕይ 11፡16-17
ተጨማሪ ጥቅስ
ሉቃስ 9:1 — “አሥራ ሁለቱንም ሐዋርያት በአንድነት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይ ደዌንም ይፈውሱ ዘንድ ኃይልና ሥልጣን ሰጣቸው፡፡”
ሮሜ 8:11 — “ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።”
ራዕይ 11:6 — “እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።