The Great Dragon
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሪቫይቭ ት/ቤት አስረኛዉ እና የመጨረሻው ክፍል በሆነዉ በራዕይ መጽኃፍ ዉስጥ እየቆፈርን/እየተማርን ነው ፡፡ ይህን ለሁለት አመታት ማድረግ ተዓምር/ዕብደት ነው ! የራዕይ መጽኃፍ የክርስቶስ መገለጥ ነው ፡፡ ክርስቶስ ተመልሶ ስለሚመጣ እኔና እናንተ ተስፋ ሊኖረን ይችላል ፡፡ በተለይም ስለ ራዕይ መጽኃፍ በሚታሰብ ጊዜ የመጨረሻው ዘመን ማስፈራት መፍራት ነው ፤ ይሁን እንጂ የራዕይ መጽኃፍ በእዉነት ተስፋን፣ የሰላምን ስሜት እና ድል ማድረግን ያመጣላችኋል ፡፡ ለዚህ መጽኃፍ ቃላችን እኔ የሚል ነው ፡፡ ክርስቶስ መጀመሪያና መጨረሻ ነው ፤ ሁሉም በክርስቶስ ቁጥጥር ስር ስለሆነ የሚያስፈራን ምንም ነገር የለም ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ዛሬ ወደ ሰባቱ ምልክቶች ሽግግርን እንመለከታለን ፡፡ ምዕራፍ 12 ከሰባቱ መለከቶች በኋላ ይካሄዳል ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (12፡ 1-2)፡ እዚህ ጋር የተገለፀው ሰማይ ሰዎስተኛዉ ሰማይ ነው - የእግዚአብሔር መገኘት ያለበት ሰማይ ፡፡ በራዕይ መጽኃፍ ትምህርት ዉስጥ ሰባት ምልክቶች አሉ ፡፡ እነዚህ ምልክቶች መለኮታዊ እና ሰይጣናዊ ሁለቱንም ናቸው ፡፡ እዚህ ጋር ስለ ተገለፀችዉ ሴት ብዙ የተለያዩ ቲዎሪዎች አሉ ፤ አንዳንዶች ቤተ ክርስቲያንን እንደምትወክል ያምናሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ የሚያምኑትን አይሁዶች ትወክላለች ይላሉ እንዲሁም ሌሎች ደግሞ የአይሁድን ዘር/ጎሳ እንደምትወክል ይናገራሉ ፡፡ እኔ የእስራኤል መወከሊያ እንደሆነች አማናለሁ ፡፡ በብሉይ ኪዳን ዉስጥ እስራኤል እንደ አንድ ሴት እና እንደ እግዚአብሔር ሚስት ተጠቅሳለች ፡፡
በራዕይ ዉስጥ የተጠቀሱ ሌሎች ሴቶች አሉ፡ ኤልዛቤል (2፡ 20)፣ የተዋበች/በእንቁ ያጌጠች ሴት (17፡ 3-6) እና የበጉ ሚስት (19፡ 7) ፡፡ በራዕይ ላይ ጥቅም ላይ ከዋለዉ መልካቸዉ የተነሳ አንስቻቸዉ/አምጥቻቸዋለሁ ፡፡ በዚህ መጽኃፍ ዉስጥ ስታነቡ መጽኃፉ ምን ወይም ስለ ማን እንደሚያወራ ለመለየት መጽኃፉን መጠቀም አለባችሁ ፡፡ መጽኃፉን ከተጠቀሱት ከሌሎች ሴቶች ጋር ሳወዳድረው የተገለፀችዉ እርጉዟ ሴት የእስራኤል ሕዝብ እንደሆነች እንዳምን ይመራኛል/ያደርገኛል ፡፡ የመጀመሪያዉ ምልክት አንድ እርጉዝ ሴት ናት ፡፡
ራዕይ (12፡ 3-4)፡ አንዲት ሴት ምጥ ተይዛ ሳለ ከዚያም አንድ ዘንዶ መግባቱን ሳሉት እሰኪ ፡፡ ይህ ሁለተኛዉ ምልክት ነው ፡፡ ዘንዶዉ ሰባት ራሶች እና አስር ቀንዶች አሉት ፤ ይህ ዘንዶ የሴቲቱ የሞት ጠላት ነው ፡፡ አጠቃላይ የዘንዶዉ አላማ ልጁን መብላት ነው ፡፡ ዘንዶዉ የሰይጣን ማሳያ/መወከያ ነው ፡፡ የዘንዶዉ ጅራት አንድ ሰዎስተኛ የሚሆኑትን ከዋክት ወደ ምድር ጣላቸው ፤ ብዙዎች ወደ ምድር የተጣሉት ከዋክብቶች የሰይጣንን አመጽ በመቀላቀል አጋንንት የሆኑ መለዓክቶችን እንደሚወክሉ ያምናሉ ፡፡ ከመለዓክት ቁጥር አንድ ሰዎስተኛ የሚሆኑት ከሰይጣን ጋር ተጣምረዋል/ተባብረዋል ፡፡ አጠቃላይ የሰይጣን እና የመለዓክቱ/የጭፍሮቹ አላማ እርጉዛን ሴት ማጥፋት ያ ካልሆነ ደግሞ ልጇና ማጥፋት ነው ፡፡
ሊመረመሩ፣ ሊለዩ እና ሊያከራክሩ የሚችሉ ብዙ ቋንቋዎች እና አወካከሎች አሉ ፤ ሰባቱ ራሶች ሰባቱ ሕዝቦች፣ ሰባቱ ተራሮች ወይም ሰባቱ ነገስታቶችን ሊወክሉ ይችላሉ ፡፡ ሰባቱ ምንም ይሁኑ ምንም ሐሰተኛዉ ክርስቶስ በእነርሱ ላይ እንደሚሳተፍባቸዉ መናገር ትክክል ይመስለኛል ፤ የሐሰተኛዉ ክርስቶስ/የአዉሬዉ አጠቃላይ ግቡ ልጁን ማሳደደ ነው ፡፡
ራዕይ (12፡ 5-6)፡ ሴቲቱ (እስራኤል) አንድ ወንድ ልጅ ወለደች ፤ ልጁም ኢየሱስ ነው ፡፡ ኢየሱስም ከዘንዶዉ በመዳን በሰማይ ዙፋን ላይ ተቀመጠ ፤ ይህ የእርገቱ የሚያምር መልክ ነው ፡፡ በተጨማሪም ይህን መልክ በምድር ላይ ከኢየሱስ ዉልደት ጋር አወዳድሩት ፤ ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ ማርያም እና ዮሴፍ ወንድ ሕፃናትን እየገደለ ከነበረዉ ከሄሮድስ ለማምለጥ ወደ ግብፅ እንዲሸሹ ተገደዱ ፡፡
ሴቲቱ ወደ ምድረበዳ ሸሸች ፤ ይህን ቋንቋ ቀድመን በዘጸዓት መጽኃፍ ላይ አይተነዋል ፡፡ ይህን መልክ እወደዋለሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕዝቡን ያለማቋረጥ በምድርበዳ የሚጠብቅበት ስለሆነ ፡፡ እዚህ ጋር ትልልቅ ጥያቄዎቹ፡ እነዚህ ክስተቶች የሚገጣጠሙት የት ጋር ነው ? ከታላቁ መከራ በፊት ነው ? ወይስ የታላቁ መከራ አካል ነው ? እነዚህ ጥያቄዎች ላይ ተመልሰን እንመጣባቸዋለን ፡፡
ራዕይ (12፡ 7-9)፡ ጦርነት በሰማይ ሆነ ፤ የመለዓክት አለቃ ሚካኤል እና መለዓክቱ ከዘንዶዉ እና ከመለዓክቱ/ከአጋንንቶቹ ጋር ተዋጉ ፡፡ ዘንዶዉ እና መለዓክቶቹ/አጋንንቶቹ ከሰማይ ተጣለ ፡፡ ታላቁ ዘንዶ ማን እንደ ሆነ ጥያቄ የሚፈጥር አይደለም ፤ ዮሐንስ ሰይጣን እና ዲያቢሎስ ተብሎ እንደሚጠራ ፅፏል ፡፡ የአለም ሁሉ አሳች ነው ፡፡
ሰይጣን ከሰማይ ወደ ምድር ተጣለ ፤ ይህ የሰይጣን መልክ ተገልጦ/ተንጠልጥሎ እና በምድር ዙሪያ ተበትኖ እናገኘዋለን ፡፡ የዚህ አለም አምላክ በመባል የታወቀ ነው ፤ ምንም እንኳን ሰይጣን እና አጋንንቶች ከሰማይ የተጣሉ ቢሆኑም አሁንም ወደ ሰማይ የማግኘት/የመሄድ መንገድ አለው (ኢዮ 1፡ 6) ፡፡ ሰይጣን ከሰማይ ወደ መሬት ወደፊት እና ወደኋላ እንደሚሄድ/እንደሚመላለስ ምስሉ/ሀሳቡ አለን ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የሰይጣን ከሰማይ ወደ ምድርመባረር ማለት ይህ አለም የስራዉ የሚሰራበት መሰረቱ ትሆናለች ማለት እንደ ሆነ “ ይናገራል ፡፡
ራዕይ (12፡ 10-12)፡ የኔልሰን ማብራሪያ ሰይጣን ሰዎስት ጊዜ ድል እንደተነሳ ይገልፃል፡ “ በበጉ ደም፣ በምስክርነቱ ቃል እና በወንድሞች ሰመዓትነት “ ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ሰይጣን በመግደል፣ በመስረቅ እና በማጥፋት ማንኛዉንም ነገርያደርጋል ፡፡ በብድር ጊዜ ላይ እንዳለ ያውቃል ፤ ሰይጣን በፍጹም ክርስቶስን ሊያሸንፈዉ አይችልም ፡፡
ራዕይ (12፡ 13-14)፡ እስራኤል ያለማቋረጥ በቋሚነት የመሲሁ ዘር ከእስራኤል ስለ መጣ በሰይጣን የተጠቃች ትሆናለች ፤ እዚህ ስፍራ ላይ የዘንዶዉ ግብ ኢየሱስ ተመልሶ እንዳይመጣ በማድረግ በምድር ላይ ጊዜዉን ማራዘም ነው ፡፡
በዚህ ፅሁፍ ላይ ያለን ስዕል በመጀመሪያዉ ሰዎስት አመት ከግማሽ በእርጉዟ ሴት ላይ ያለዉ ጥቃት ነው ፡፡ በሁለተኛዉ ሰዎስት አመት ከግማሽ ጊዜሴቲቱ ከዘንዶዉ የተጠበቀች ትሆናለች ፡፡
ራዕይ (12፡ 15-17)፡ ሰይጣን እስራኤላዊያንን ለማስወሰድ እየሞከረ ነው ፤ ምንም እንኳን ጠላት ሊያጠቃቸዉ ቢሞክርም እግዚአብሔር እስራኤላዊያንን አዳናቸው ፡፡ በሆነ ጊዜ ላይ የእስራኤላዊያን ሕዝቦች ቡድን የሚሞቱበትን ጊዜ አናዉቅም ፤ እግዚአብሔር ቢያንስ የሕዝቡን አንድ ሰዎስተኛ ያድናል ፡፡
ሰይጣን ከሴቲቱ ጋር ያለዉን ጦርነት ስለፈራሌሎቹን የክርስቶስ ተከታዮች ያሳድዳል - የእግዚአብሔርን ቃል የሚጠብቁትን እና ትዕዛዙን የሚፈፅሙትን ፡፡ ዘንዶዉ ሰይጣን ለጦርነቱ የተዘጋጀ ነው ፡፡
መደምደሚያ
ለሰዎስት አመት ከግማሽ እግዚአብሔር እስራኤላዊያንን ስለሚጠብቅሌላዉ ሁሉም ነገር ግን የማጣት ረፍት ስለሚቀጥል ደህና ነዉ የሚባለዉ ለዛ ነው ፡፡ እንደ ገና ነገ ወደ ራዕይ 13 መጽኃፍ ላይ ስንገባ ተቀላቀሉን ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1752.
ጥያቄዎች
-
ሴቲቱ የምትወልደዉ ወንድ ልጅ ማነው (መዝ 2፡ 9, ራዕ 12፡ 5) ? ከዚያስ የትኛዉ ሕዝብ የሴቲቱ ምልክት ነው ? (ሮሜ 1፡ 3, 9፡ 4-5)
-
እንደ እሳታማ ቀይ ዘንዶ የታየዉ ማነው (ራዕ 12፡ 9, 20፡ 2) ? የሰይጣን ዘመን የማብቃቱ ምልክት ምን ይሆናል ? (ራዕ 11፡ 15)
-
በመከራዉ መካከል ላይ ምን ይሆናል (ዳን 9፡ 27, ማቴ 24፡ 15, ራዕ 11፡ 2) ? በዚህን ጊዜ እግዚአብሔርን እንዴት ይጠብቃል ያድናልስ ? (ዳን 11፡ 41, ራዕ 12፡ 6)
-
ሰይጣን ስለ ራሱ ምን ያውቃል ? ይህን ስለ ራሱ ሲያዉቅ በተለዬ ማንን ትኩረት ያደርጋል ? (ራዕ 12፡ 13, 17)
-
የሚመጣዉ መከራ/ስደት ቢሆን ምን ማድረጋችሁን መቀጠል አለባችሁ ? (ዮሐ 8፡ 31-32)
-
በራዕ (12፡ 17) ዘንዶዉ ከቀሩት ከሴቲቱ ልጆች ጋር ጦርነት ለማድረግ በሚወጣ ጊዜ እነዚህ አይሁዶች ወይስ ክርስቲያኖች እንደ ሆኑ ታስባላችሁ ? (ገላ 4፡ 26, 31, ራዕ 13፡ 7)
-
በራዕይ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 12:4b–5
“And the dragon stood in front of the woman who was about to give birth, so that when she did give birth he might devour her child. But she gave birth to a Son—a male who is going to shepherd all nations with an iron scepter—and her child was caught up to God and to His throne.”
ሁለት ምልክቶች ለዮሐንስ ተገለጡለት፡፡ የመጀመሪያው እርጉዝ ሴት በምጥ ተይዛ ስትጮኽ ነበር፡፡ ይህ በይበልጥ የሚያሳየው የመሲሁን በኢየሩሳሌም መወለድ ነው፡፡ ሁለተኛው ታላቅ ቀይ ዘንዶ የሰይጣን ምልክት የሆነ፣ የሴቲቱን ልጅ ይበላ ዘንድ በእርጉዟ ሴት ፊት ቆሞ ነበር፡፡ ሴቲቱም አህዛብን ሁሉ የሚገዛ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ በራዕዩ ልጁ በሰይጣን አልተበላም ነበር ይልቁንም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተወሰደ እንጂ፡፡ በመጨረሻም ዘንዶው ከሴቱዋ ጋር የነበረውን ጦርነት አላሸነፈም ህጻኑን ወንድ ልጅዋንም አልወሰደም፡፡ ይህ ራዕይ በይበልጥ የሚያሳየው ኢየሱስ በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠና ሰይጣንም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ከጠበቁትና የኢየሱስ ምስክርነት ባላቸው ላይ ጦርነትን ለማወጅ እንደሄደ ነው፡፡
በመጀመሪያ ሰይጣን የእግዚአብሔርን እቅድ ለማሸነፍ አልሞ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን ድል የኢየሱስና ትዕዛዙን ለሚጠብቁ ህዝቦቹ እና በኢየሱስ ምስክርነት ላይ ለተጣበቁት ነው፡፡ ሰይጣን ይሰርቅ፣ ይገድልና ያጠፋ ዘንድ ይሻል፡፡ ተዘጋጁ፡፡ በውጊያው ውስጥ ጸንታችሁ ቁሙ፡፡ ታጥቃችኋል፡፡ ጠላት በኢየሱስ ስም ኃይል ተሸንፏል፡፡ ኢየሱስ ለአህዛብ መልካሙ እረኛ ጠባቂ ነው፡፡ ስለዚህም ድምጹን ተከተሉ በኢየሱስም ላይ ተጣበቁ፡፡
“ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።”
ራዕይ 12:4b–5
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዘፍጥረት 3:15 — “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።”
- ዮሐንስ 10:10–11 — “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
- ራዕይ 12:17 — “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፡፡”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።