Revelation Revelation

The Beast From The Earth And The Sea

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 721 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ ሙሉ ሳምንት ነው ፤ አንድ የሚቀጥል ትምህርት ይመስላል ፡፡ ሙሉ ራዕይ እኔ ስላለዉ የዮሐንስ ራዕይ ነው ፡፡ ራዕይ የኤደን ገነት መታደስ ነው ፤ የሚያምር መልክ ነው ፡፡ የትናትናዉ ፅሁፍ/ትምህርት በሰይጣን እና ደግመን ደግመን ባየነዉ በዘሩ መካከል ስላለዉ ዉጊያ ነበር ፡፡ ቀድመን በምዕራፍ 12 የነበረዉ ዘንዶ ሰይጣን እንደ ነበር እናዉቃለን ፤ አሁን ለዉጊያ በመዘጋጀት በባህር ላይ የቆመን ሰይጣን እናያለን ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (13፡ 1)፡ የዚህ ምዕራፍ መጀመሪያ በባህር ላይ ከቆመዉ ሰይጣን ወደ የክርስቶስ ተቃዋሚን ወደ ሚወክለው የተለያዩ አዉሬዎችን ወደሚገናኘዉ ሰይጣን በመሸጋገር ይጀምራል ፡፡ ሐሰተኛዉን ክርስቶስን በመጠቀም የሰይጣንን እቅድ እየገለጥን ነው ፡፡ አዉሬ የሚለዉ ቃል ጭራቅ ማለት ነው ፡፡

ራዕይ (13፡ 2)፡ ሰይጣን የሐሰተኛዉ ክርስቶስ ኃይል እና ስልጣን ተሰጠው ፡፡ ይህ ፊልም ይመስላል ፡፡ እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ስጋ ሲሆን ሰይጣን ደግሞ ለስጋ ስልጣን በመስጠት ኃሰተኛዉ ክርስቶስ/አዉሬው በማለት ጠራው ፡፡ በሐሰተኛዉ ክርስቶስ/በአዉሬው መግለጫ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም እንስሳቶች እንከፋፍላቸዋለን ፤ ማክአርቱር “ ነብሩ የጥናታዊቷ ግሪክ ዘይቤአዊ መገለጫ እንደሆነ…. ድብ የቀድሞ ሜዶንና ፋርስ ዘይቤአዊ መገለጫ እንደሆነ እና አንበሳ ደግሞ ባቢሎንን እንደሚወክል “ ፅፏል ፡፡ የአዉሬዉ/የሐሰተኛዉ ክርስቶስ መንፈስ ዘሩን ለመያዝ በመኮሩት በእነዚህ ሁሉ ሕዝቦች ላይ ሊገኝ ችሏል ፡፡ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ በመሆን የሚገኝ ትክክለኛ ሰዉ እንዳለ አምናለሁ ፡፡

ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚዉ/ስለ አዉሬዉ መንፈስ ስናወራ በመጽኃፍ ዉስጥ ተገልፆ እናየዋለን ፡፡ በመጽኃፍ ላይ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ/አዉሬው የኃጢዓት እና የክፋት ሰው በመባል (2ተሰ 2፡ 3-4) እና የሚመጣዉ አለቃ በመባል ተገልፆአል (ዳን 9፡ 26) ፡፡ በተጨማሪም ሐሰተኛዉ ክርስቶስ እንደ ትንሽ ቀንድ (ዳን 7፡ 8)፣ እንደ አዉሬ (ራዕ 13፡ 2-10, 18) እና የጥፋት ልጅ (ዮሐ 17፡ 12) በመባል ተገልፆአል ፡፡ በታላቁ መከራ ጊዜ ይገዛል (ዳን 7፡ 25) ፡፡

ማክአርቱር የክርስቶስን እና የሐሰተኛዉ ክርስቶስን ትይዩነትን/መመሳልን ያወዳድራል፡

ክርስቶስ

ሐሰተኛዉ ክርስቶስ

1. መገለጥ

2 ተሰ 1:7

2 ተሰ 2:3, 6, 8

2. መምጣት

2 ተሰ 2:1,8

2 ተሰ 2:9

3. መልዕክት

2 ተሰ 2:10 (እዉነት)

2 ተሰ 2:11 (ዉሸት)

4. አምላክነት

ዮሐ 1:1 (እዉነት)

2 ተሰ 2:4 (በይገባኛልነት የተጠየቀ)

5. ማረጋገጫ ምልክቶች

ሐዋ 2:22

2 ተሰ 2:9

6. ስልጣን አሰጣጥ

ሐዋ 2:22 (አምላክ)

2 ተሰ 2:9 (ሰይጣን)

7. ሞት

ማር 15:37

ራዕ 13:3,12,14

8. ትንሳኤ

ማር 16:6

ራዕ 13:3,12,14”2

ሐሰተኛዉ ክርስቶስ በመጽኃፍ ላይ እንዳለ ላሳያችሁ እፈልጋለሁ ፡፡ በመጽኃፍ ዉስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ የተለያዩ ርዕሶችን እና መገለጫዎችን እናያለን ፤ ስለዚህም ዘንዶዉንና አዉሬዉን በምታዩ ጊዜ ከሴቱቱ እና ከክርስቶስ ተከታዮች ጋር ዉጊያ ሲጀመር እናያለን ፡፡

ራዕይ (13፡ 3-4)፡ ከአዉሬዉ ራሶች አንዱ ሞቶ ታዬ ከዚያም ተፈወሰ ፤ ብዙዎች ይህ ትክክለኛ ሞት እንዳልነበር ይናገራሉ ፤ አጠቃላይ የሐሰተኛዉ ክርስቶስ ግብ/አላማ ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ ለመሸወደ እንደ ብርኃን በዙሪያ መሰለፍ/መታየት ነው ፡፡ ከባድ/ቁጣ ከሆነዉ ቁስል ለመፈወሰን አዉሬዉ በታዬ ጊዜ ምድር ሁሉ የተደነቁ በመሆን እርሱን መከተል ይጀምራሉ ፡፡ አዉሬዉን በሚከተሉ ጊዜ ሰይጣን የሆነዉን ዘንዶዉን ያመልካሉ ፡፡ አለም ሰይጣንን እና አዉሬዉን ያመልካሉ ፤ በአዉሬዉ እና በዘንዶዉ የተጠበቁ እንደሚሆኑ ያምናሉ ፡፡

ራዕይ (13፡ 5-6)፡ ማክአርቱር “ እግዚአብሔር በምድር ላይ ለሰዎስት አመት ከግማሽ የሰይጠንን ዘመን ወደ ድምዳሜዉ ላይ ለማምጣት የመጨረሻውን ክፋት/ነቀፋ እንዲያመጣ እንደፈቀደለት “ ፅፏል ፡፡

ራዕይ (13፡ 7)፡ ዮሐንስ “ በቅዱሳን ላይ የጦርነት ዘመቻ “ ብሎ ሲፅፍ “ ቅዱሳኖቹ “ እነማን እንደ ሆኑ ብዙ የግል አስተያየቶች አሉ ፤ ከመራዉ በፊት የሚለዉን አስተሳሰብ የሚወስዱት/የሚቀበሉት ቅዱሳኖቹ በመከራዊ ጊዜ ክርስቶስን ወደ ማወቅ የሚመጡ ሰዎች እንደሆነ ይከራከራሉ ፡፡ የትኛዉም እይታ/አመለካከት የተወሰደ ቢሆንም ከሰይጣን ጋር ለመዋጋት የሚዋጉ አማኞች በዙሪያ እንዳሉ ግልፅ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑትን እንዲገድላቸዉ የተፈቀደለት እንደሆነ “ ጽፏል ፡፡ ከሕመም ነፃ እንደምንሆንና ከዚህ እንደምንወጣ እነግራችኋለሁ ፤ እነዚያ ቅዱሳኖች እኛ ብንሆንስ ? አሁንም የተዘጋጀን እንድንሆን እፈልጋለሁ ፡፡ ሰመዓት እንድንሆንስ ተጠርተን እንደሆን ?

ራዕይ (13፡ 8-9)፡ ስማቸዉ በሕይወት መዝገብ ላይ ያልተፃፉት ሁሉ የታረዱ/የተገደሉ ይሆናሉ ፡፡ ማክአርቱር የሕይወት መጽኃፍን “ እንዲድኑ እግዚአብሔር የመረጣቸዉን እና ከዚያም የዘላለም ሕይወትን የሚያገኙትን ሁሉ ስም የመዘገበ መለኮታዊ መጽሄት/መጽኃፍ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ሐሰተኛዉን ክርስቶስ የሚያመልኩ ሁሉ ስማቸዉን በሕይወት መዝገብ መጽኃፍ ላይ አያገኙትም ፡፡

ራዕይ (13፡ 10)፡ እዚህ ጋር ትልቅ መልክ ይኖራችኋል ፤ ይህ የቅዱሳን ቋንቋ ነው ፡፡ እነዚህ በመከራዊ ጊዜ የሚኖሩ አማኞች ናቸው ? ያልተነጠቁት ናቸው ? ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም ፡፡ ቅዱሳኖቹ እኛ ብንሆንስ ? ይህ የእግዚአብሔር እቅድ ሊሆን ይችላል ፤ በክርስቶስ ስም ምክንያት መከራ የደረሰባቸው በሰማይ የሚሸለሙ ናቸው (ማቴ 5፡ 8) ፡፡ ሀሳቡ ስደት/መከራ ሊመጣ እንደሚችል ነው ፤ ስንዘጋጅ እና ስንጠብቅ ማየት እፈልጋለሁ ፡፡

ራዕይ (13፡ 11-14)፡ ሰይጣኑ ዘንዶዉ እና አዉሬዉ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ አሉ ፤ እዚህ ጋርም ሐሰተኛ ነቢያትን የሚወክል ከሌላ አዉሬ እርዳታ ሲያስፈልጋቸው እናያለን ፤ ስልጣኑ ከሐሰተኛዉ ክርስቶስ የሚያንስ ይሆናል ፤ በመሰረታዊነት ሰዎች ሐሰተኛዉ ክርስቶስን እንዲያመልኩ የሚያስት አሸንጉላሊት ማለት ነው ፡፡ የመሲሁን እና የሌሎች ታላቅ ነቢያት ተዓምራትና ምልክቶችን ለመድገም ይሞክራል ፡፡

ራዕይ (13፡ 15-18)፡ አንድ ሰዉ ሐሰተኛዉን ክርስቶስን የማያመልክ ከሆነ ይሞታል ፤ ሰዉዬዉ ለመትረፍ የአዉሬዉ ምልክት ይኖረዋል ፤ ቁጥሩም 666 ይሆናል ፡፡ ሰዎች ለምን 666 እንደ ሆነ ለመገመት ሞክረዋል ፤ መደምደም የምችለዉ ብቸኛዉ ነገር ስድስት ቁጥር የተሟል እንዳልሆነ ነው ፡፡ ቁጥር ስድስት ከእግዚአብሔር ፍጹም ቁጥር ሰባት አንድ የሚያንስ ፍጹምነት የሚያንሰዉ እንደሆነ ይሰማል ፤ ያ ፍጹም እንደ ሆነ እርግጠኛ መሆን አንችልም ፡፡ ልናዉቅ የምንችለዉ ሁሉም ነገር ቁጥር 6 ፍጹም አለመሆንን እንደሚያመለክት ነው ፡፡

መደምደሚያ

ጠላት የራሱ ምልክት ቢኖረዉም ግን የራሳችን ስላለን እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ በእኛ ላይ በአካል ላይታይ ይችላል ነገር ግን በክርስቶስ መሰቀል ላይ በአካል የሚታይ ነው ፡፡ በዚህን ጊዜ ሁሉም ነገሮች የሆኑትን ነገር ቢሆንም ወዴት እንደምንሄድ እና ተስፋ እንዳለን እናዉቃለን ፡፡ ያለን ህይወት የሆነዉን የመጨረሻዉን ምልክት በሞቱና በትንሳኤዉ በኩል ነው ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005) p. 2017.

  2. MacArthur, p. 1769.

  3. MacArthur, p. 2018.

  4. MacArthur, p. 2018.

  5. MacArthur, p. 1999.

ጥያቄዎች

  1. በራዕ (13፡ 1) ላይ ያለዉ የባር አሸዋ በቀጥታ ነዉ ወይስ መመሰያ ነው ? (ራዕ 17፡ 15)
  2. በራዕ (13፡ 1) “ ሰባቱ ራሶች “፣ “ አስሩ ቀንዶች “ እና “ አስሩ ዘዉዶች “ ምንን ይወክላሉ ? (ዳን 7፡ 23-25, ራዕ 17፡ 10-16)
  3. በግል አስተያየታችሁ ራዕይ (13፡ 7) ከመከራዉ በፊት ያሉትን ቅዱሳኖች ወይስ ከመከራዉ መጀመር በኋላ ወደ ክርስቶስ በመምጣት ቅዱሳን ሊሆኑ ስለቻሉት ይናገራል ? ያላችሁትን ለምን አሰባችሁ ?
  4. መጽኃፍ ቅዱስ ስለ ክስተቱ በግልጽ ተናግሮ ሳለ በመጨረሻው ጊዜ በምድር ላይ ብዙዎች እንዴት ሙሉ ለሙሉ የተሸዱ ይሆናሉ ? የተሸዱ የሚሆኑ የኢየሱስ አማኞች እንደሚኖሩ ወይም ደግሞ በዚህን ጊዜ በእርሱ ላይ ጀርባቸዉን የሚያዞሩ ይኖራሉ ብላችሁ ታስባላችሁ (ማቴ 24፡ 24) ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
  5. በራዕ (13፡ 16-18) ምልክቱ ተገልፆአል ፡፡ በአሁኑ በእኛ ዘመን በሰዎች ዉስጥ ችፕን እያስቀመጡ ያሉ ድርጅቶች አሉ ፡፡ በግል አስተያየታችሁ ይህ የምልክቱ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይሆንም ?
  6. በራዕይ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 13:8

“All those who live on the earth will worship him, everyone whose name was not written from the foundation of the world in the book of life of the Lamb who was slaughtered.”

የዮሐንስ ራዕይ ሲቀጥል ሌላ ተጨማሪ ሁለት አውሬዎች መጡ፣ እነዚህም የክርስቶስ ተቃዋሚው ከባህር እና ሐሰተኛው ክርስቶስ ከምድር ናቸው፡፡ ሰይጣንም ለክርስቶስ ተቃዋሚው ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው። ሐሰተኛውም ነቢይ በሚያደርጋቸው ምልክቶች በምድር ላይ ያሉትን ሁሉ ያስታል፡፡ ምድርም ሁሉ ይደነቃል፡፡ ስማቸው በህይወት መጽሐፍ ከተጻፉትና ስለደህንነታቸው በታረደው በበጉ በኢየሱስ ከተለዩት በቀር፣ ብዙዎች ሐሰተኛውን ክርስቶስ ይከተሉታል ይሰግዱለታልም፡፡ አዎን ቅዱሳን ግን ጌታን ማምለካቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ሆኖም ግን በግዞት ሊወሰዱ ወይም በሰይፍ ሊገደሉ ይችላሉ፡፡ ጌታም ለቅዱሳኑ ጽናትንና እምነትን ይሰጣቸዋል፡፡

በመከራው እንደ ክርስቶስ አማኝ እናንተም ልትማረኩ ወይም በሰይፍ ልትገደሉ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ሊደርስባችሁ ስለሚችለው ስቃይና መከራ ስታስቡ፣ ከእናንተ በፊት የነበሩት ቅዱሳን ስለ እምነታቸው መከራን ስደትን እንደተቀበሉ ይህንን አስታውሱ፡፡ በእነርሱም መከራ፣ አሁን ሌሎች በክርስቶስ ይኖራሉ፡፡ በመጨረሻዎቹ ቀናት ጌታ ጽናትንና እምነትን ይሰጣችኋል፡፡ አስታውሱ ጌታ “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው ምክንያቱም መንግስተ ሰማይ የእነርሱ ናትና” እንዳለ ፡፡ ስለዚህ ደስ ሊላችሁና ሀሴት ልታደርጉ ይገባል ምክንይቱም ዋጋችን በሰማይ ታላቅ ነውና፡፡ ዛሬ በኢየሱስ ዘንድ በሆነው ተስፋ እረፉ፡፡ በፍርሀት ሳይሆን በእምነት ተራመዱ፡፡ ትባረካላችሁ፡፡

“ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል።”

  • ራዕይ 13፡8

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 5:10-12 — “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”

ቆላስያስ 1:11-12 — “በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን።”

ራዕይ 13:9-10 — “ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።”