Revelation Revelation

Reaping The Earth's Harvest

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 722 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ አዲስ ብራንድ ሳምንት ሲሆን አሁንም በራዕይ መጽኃፍ ዉስጥ ነን ፡፡ ራዕይ ልክ እንደተገለጠ እንደ አንድ ረጅም ትምህርት ወይም ታሪክ ይመስላል ፡፡ ምዕራፍ 13 መጨረሻ ላይ ታላቁ መከራ ተገልጦ አይተናል ፡፡ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር በምድር ላይ የነፃ ገዢነት ተሰጥቶት ነበር ፤ ዘንዶዉን (ሰይጣንን)፣ የባህሩን አዉሬ (ሐሰተኛዉን ክርስቶስን) እና የምድር አዉሬዉን (ሐሰተኛ ነቢዩን ) ሁሉንም በአንድ ላይ አይተናል ፡፡ በተጨማሪም በአስቸጋሪ ጊዜ ዉስጥ የሚያልፉትን የቅዱሳንን መልክ አይተናል ፡፡ ምዕራፍ 14 የታላቁን መከራ መጨረሻ በማሳየት ይጀምራል ፤ ዮሐንስ የዕይታዉን አመለካከት ከአዉሬዉ ወደ አዲሱ ዘር በአጠቃላይ ቀየረ ፡፡ የሚያስፈሩ ጭራቆች አይኖሩም ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (14፡ 1)፡ በዚህ ቁጥር ላይ የተጠቀሰው “ በጉ “ ኢየሱስ ነው ፡፡ ብዙ መጽኃፍ ቅዱሳዊያን ምሁራን እዚህ ጋር የፂዎን ተራራ ምን እንደሚወክል ተወያይተዋል/ተናግረዋል ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ የፂዎን ተራራ ቤተ መቅደሱ ተገንብቶባቸዉ በነበሩት ኮረብቶች ላይ በማተኮር የምድራዊቱ ኢየሩሳሌም ተመሳሳይ እንደ ሆነ ፤ ይህ የምድራዊዉን ወይም የሰማዩን የፂዎን ተራራ እንደሚወክል በመወሰን ዉስጥ አስቸጋሪነት እንዳለ “ ይገልፃል ፡፡

ራዕይ (14፡ 2-3)፡ ዮሐንስ “ በጉን “ አዬ በተጨማሪም ደግሞ ከሰማይ ድምጽን ሰማ ፡፡ ይህ የሰማያዊ ድምጽ አዲስ ዜማ ነበር ፤ ድምጹም ከምድር የተዋጁት 144,000 በሰማይ እንዳሉ ይመስላል ፤ እነዚህ የተቤዡት የሚዘምሩ ብቸኞቹ ነበሩ ፡፡

ራዕይ (14፡ 4)፡ በሰማይ ላይ የጌታ 144,000 አምላኪዎች እና ሽማግሌዎቹ በምድር ላይ ከሚኖሩት ከሐሰተኛዉ ክርስቶስ አምላኪዎች በኃይለኛው የተለዩ ናቸው ፡፡ 144,000 ለእግዚአብሔር እና ለበጉ በኩራቶች ነበሩ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በኩራቶች በኋላ ብዙ ምርት እንደሚመጣ የሚያመለክት መጀመሪያ የሚሰበሰብ የምርት ክፍሎች እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ ይህን ኃሳብ ከማንም በተሻለ መስሎታል/ገልጾታል (1ቆሮ 15፡ 23-26) ፤ ይህ ለብዙ ምርኮ የክርስቶስን ተመልሶ መምጣት መልክ ነው ፤ የእርሱ ለሆኑት ተመልሶ ይመጣል ፡፡

ራዕይ (14፡ 5)፡ ብዙ ምሁራን ይህ ጥቅስ 144,000 ያለኃጢዓት ነበሩ ማለት እንደ ሆኑ ያምናሉ ፤ ያ እዉነት ነዉ ብዬ አላምንም ፡፡ ሁላችንም ኃጢዓተኞች ነን የሚለዉን ሮሜ (3፡ 23) እናምናለን ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ 144,000 በምድራዊ ኑሮአቸዉ ኃጢዓት አልባ ያልነበሩ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ ከምስክርነታቸዉ አንፃር ዉሸት እና እንከን የሌለባቸው እንደ ነበሩ “ ይናገራል ፡፡ ማክአርቱር “ 144,000 የእግዚአብሔርን እዉነት ያለ ምንም ግነት እና ያለ ምንም መቀነስ በትክክልና በሚገባ እንደሚናገሩ “ ፅፏል ፡፡ ይህ የ144,000 ዳራ ነው ፤ በጥናታችን እዚህ ስፍራ ላይ ስለሚመጣዉ ታላቅ መከር መወኪያ/ወኪል ናቸው ፤ እዚህ ስፍራ ላይ ታላቁ መከራ ላይ መጨረሻ ላይ እንደ ሆነ አምናለሁ ፡፡

ራዕይ (14፡ 6-7)፡ ወንጌልን ለአሕዛቦች የሞያዉጅ አንድ መለዓክ አለ ፤ እንደምንም ሁሉም ሰው የእግዚአብሔር አዋጅ ይሰማል (ማቴ 24፡ 14) ፡፡ ጌታ ሁሉም ሰው የእርሱን መልካም ዜና የመስማት እድል እንዳላቸው እርግጠኛ ይሆናል ፡፡ እግዚአብሔር ተስፋዉን እንደሚፈጽም እርግጠኞች መሆን እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ወንጌል የሚለዉ ቃል መልካም ዜና ማለት ነው ፡፡ ማክአርቱር በዚህ በመጨረሻ ደረጃ ላይም እንኳን እግዚአብሔር “ የአለምን ሕዝብ ጥምረታቸዉን ከአዉሬዉ ወደ በጉ እንዲቀይሩ “ ማሳሰቡን እንደሚቀጥል ይፅፋል ፡፡ የመለዓኩ መልዕክት የእግዚአብሔርን ክብር መስጠት እና ፍርድ እየመጣ እንደ ነበር ማስጠንቀቅ ነበር ፡፡

ራዕይ (14፡ 8)፡ በመቀጠልም ዮሐንስ የመጀመሪያዉን የተከተለዉን ሁለተኛዉን መለዓክ ገለፀው ፡፡ የመጀመሪያዉ መለዓክ ሰባት የቁጣን መለከቶች ወደፊት አመጣ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ባቢሎን እዚህ በራዕይ ላይ መጀመሪያ በመጠቀስ በራዕይ 16-18 የእግዚአብሔር ፍርድ ትኩረት እንደሆነች “ ይገልፃል ፡፡ ከአንድ ከተማ በላይ በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ መላዉ አለምን ትወክላለች ፡፡

ራዕይ (14፡ 9-12)፡ በቁጥር 9 ምንም የተሻለ ዜና አይገኝም ፤ ሰዎስተኛዉ መለዓክ ከሁለት ከሚያዉጁ ከሁለት መለዓክቶች ኋላ በመገለጥ “ ለአዉሬዉና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ደግሞ በቁጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል “ (ቁጥር 9-10) ፡፡ እዚህ ጋር ያለዉ መዓት የሰይጣንም ቁጣ ነው ፤ ይህ በሰይጣን ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ነው ፡፡ ይህ ቋንቋ የእሳት እና የድን ነው ፤ ስቃዩም ለዘላለም የሚቆይ ነው ፡፡ የእግዚአብሔርን በግ ካልያዛችሁ በሲዖል ለዘላለም ስቃይ ይደርስባችኋል ፡፡ ስለ ጌታ ለሌሎች ለማዉራት በመፍራት መያዝ አልችልም ፤ ዉጤቶቹ በጣም ታላቅ ስለሆነ፡፡

ራዕይ (14፡ 13)፡ በቁጥር 13 ከሰማይ ዮሐንስ ሌላ “ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸዉ “ ብለህ ፃፍ የሚል ድምፅ ሰማ ፡፡ ስለ ብፁዕነት “ ስለ መባረክ “ እንዴት እንዳወራን እናስታዉለን ? ከእነርሱ ዉስጥ ይህ አንዱ ይሆናል ፡፡

በመሰረቱ የኔልሰን ማብራሪያ “ በዚያ በመንጠላጠል/በመጣበቅ በመጨረሻ የተባረካችሁ ትሆናላችሁ “ ይላል ፡፡ በዚህ ሁኔታ አማኞች በሚሞቱ ጊዜበጌታ እረፍትን ያገኛሉ ፤ እነዚህ ቃሎች ጊዜዉ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳን ለማትጋት እንደ ማበረታቻነት ያገለግላሉ ፡፡ እስከ መጨረሻው ታገሱ ፤ በዚህ ፅሁፍ መሰረት በመከራዉ መጨረሻ ላይም ያለን ይመስላል ፡፡ ወንጌል ለሁሉም ሰው የታወጀ ስለ ነበር እና የአለመቀበል ዉጤትም ስለ ተነገረ ፡፡

ራዕይ (14፡ 14)፡ በዚህ ቁጥር ላይ የሚያስደንቅ የክርስቶስን መልክ እናያለን ፡፡ በእጁ ያለዉ ማጭድ እህል ለመሰብሰቢያ መሳሪያ ነው ፤ ይህ እንደ ንጉስ የክርስቶስ መልክ ነው ፡፡ መዝ (48፡ 1-2)፣ ኢሳ (24፡ 23) እና ራዕ (19፡ 16) ፡፡ እንደ ንጉስ ተመልሶ በሚመጣዉ በዚህ ምስል መጣበቅ እፈልጋለሁ ፡፡

ራዕይ (14፡ 15-16)፡ አራተኛዉ መለዓክ መከር መድረሱን ሁሉም ሰዉ መልካሙን ዜና መስማቱን በመናገር ተገለጠ ፤ አሁን ይህ ለሁሉም የተሰበሰቡ ለመሆን የተሻለዉ ጊዜ ነበር ፤ በክርስቶስ ማጭድ በአንድ ጊዜ መጣል ምድር ተሰበሰበች/ታጨደች ፡፡

ራዕይ (14፡ 17-19)፡ በተጨማሪም በእጁ አንድ ማጭድን የያዘ አምስተኛ መለዓክ ተገለጠ ፤ ከዚያም “ በእሳት ላይ ስልጣን የነበረው “ ስድስተኛ መለዓክ በመገለጥ (ቁጥር 18) አምስተኛዉን መለዓክ ከምድር ላይ የደረሰዉን ወይን ለመሰብሰብ ማጭዱን እንዲጠቀም ነገረው ፤ ይህ በእዉነት በፍጥነት በኃይል ተገኘ/ሆነ ፡፡ ይህ ማጭድ እና ወይኑ/የወይኑ ዘለላ የፍርድ መወከያ ናቸው ፡፡ ክርስቶስ መከሩን እየሰበሰበ ፍርድ በአምስተኛዉ መለዓክ የተከፋፈለ እየሆነ ነበር ፡፡

ራዕይ (14፡ 20)፡ ብዙዎች ይህ የአርማጌድዮን ጦርነት መጀመሪያ የሚካሄድበት ነው ይላሉ ፤ ይህ በራዕ (19፡ 11-21) በይበልጥ የተገለፀ ክስተት ሊሆን ይችላል ፡፡ “ ከከተማ ዉጪ “ ከኢየሩሳሌም ዉጪ ያለዉን የኢዮሳፍጥን ሸለቆ ሊያመለክት ይችላል (ኢዩ 3፡ 12-13) ፡፡

መደምደሚያ

ወንጌልን መያዝ ፤ የሐሰት አምልኮን አለመያዝ ፤ ክርስቶስን መያዝ ፡፡ የማታምኑ ከሆነ ፍርድ እየመጣ እንደሆነና ደም መፍሰስ እንደሚጀምር ታዉቃላችሁ ፡፡ የአርማጌድዮን ጦርነት ይካሄዳል ክርስቶስም ያሸንፋል ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1753.

  2. Nelson’s Commentary, p. 1753.

  3. Nelson’s Commentary, p. 1754.

  4. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 2021.

  5. MacArthur, p. 2021.

  6. Nelson’s Commentary, p. 1754.

  7. Nelson’s Commentary, p. 1755.

ጥያቄዎች

  1. በራዕ (14፡ 1) ከበጉ ጋር በፂዎን ተራራ ላይ የቆሙት 144,000 እነማን ናቸው ? (ማቴ 19፡ 12, ራዕ 3፡ 12, 7፡ 4, 13-17)
  2. በራዕ (14፡ 6) ላይ መለዓኩ በምድር በሕዝቡ ላይ የሚመጣዉን ፍርድ እያወጀ እንደሆነ ወይስ ወደ ኢየሱስ እንዲመጡ አንድ የመጨረሻ የልመና እድል እየሰጣቸዉ እንደሆነ ታምናላችሁ (ዳን 8፡ 19, ሐዋ 14፡ 15) ? ያን ለምን አሰባችሁ ?
  3. በራዕ (14፡ 9-11) መሰረት የአዉሬዉን ምልክት በተቀበሉት ላይ ምን ይሆንባቸዋል ?
  4. ራዕ (14፡ 14-16) ስለ ምንድን ነዉ የሚያወራው (ማቴ 13፡ 39-41) ? የክርስቶስ ታማኝ ተከታዮች ይህን ይፈራሉ ?
  5. በራዕ (14፡ 18-20) የተጠቀሰዉ አስፈሪ ክስተት በምን ትንቢት ላይ ተተንብዮአል ? (ሕዝ 39፡ 17-21)
  6. በራዕይ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 14:13

“Then I heard a voice from heaven saying, ‘Write: The dead who die in the Lord from now on are blessed.’ ‘Yes,’ says the Spirit, ‘let them rest from their labors, for their works follow them!’”

የዮሐንስ ራዕይ ከክርስቶስ ተቃዋሚ ወደ በጉ ተሸጋገረ፤ ዮሐንስም ከአምስት መላእክት ተከታታይ የሆኑ ኃይል ያላቸውን መልዕክቶች አየ አደመጠም፡፡ የመከራው ማብቂያ ሲቃረብ፣ ስለ ድነትና ቁጣ የሚያወሱ መልእክቶች በግልጽ ተነገሩ፡፡ አንድ መልእክት፣ ከሰማይ የሆነ ድምጽ ዮሐንስን “ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው” ብልህ ጻፍ ብሎ አዘዘው፡፡ መንፈስም “አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል!” ብሎ መለሰ፡፡

ጓደኞቼ በዚያ ውስጥ ቆዩ፡፡ በጌታ በርቱ፡፡ ከምታደርጉት ምንም የሚከስር የሚባክን ነገር የለም፣ በመጨረሻ ትባረካላችሁ፡፡ በእርግጥ መከራ ይጎዳል ቁስልም ህመምን ያስከትላል፡፡ አዎን የዚህ አለም ነገሮች በጊዜያዊ ደስታ ነው እርካታን ሊሰጡዋችሁ የሚሞክሩት ደግሞም ክርስቶስን በፍጹም ልባችሁ ከመከተል የሚያንሸራትቱዋችሁ፡፡ በእርግጥ ፈተናዎች ሁልጊዜ በመንገዳችሁ ይጋረጣሉ ልባችሁንም ያርዳሉ፡፡ ሆኖም ግን አንድ ነገር አስታውሱ፣ ኢየሱስ አሸናፊ ነው፡፡ ኢየሱስ በቂ ነው፡፡ በጉ፣ የአለም አዳኝ የሆነው ኢየሱስ ከጥፋት፣ ከፍርድ እና ከዘላለማዊ እሳት ሊታደጋችሁ መጥቷል፡፡ ስለዚህ አሁን፣ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ በርቱ በተጨማሪም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጠበቅና በኢየሱስ ዘንድ ባለ እምነት በመጽናታችሁ፣ ትባረካላችሁ፡፡

“ከሰማይም፦ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ፦ አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ።”

  • ራዕይ 14፡13

ተጨማሪ ጥቅስ

1ኛ ጴጥሮስ 4:12–14 — “ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።”

1ኛ ጴጥሮስ 4:19 — “ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።”

ራዕይ 14:6–7 — “በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤በታላቅ ድምፅም፦ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ።”