Preparation For The Bowl Judgements
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና የራዕይ 14 ጥናታችንን በራሱ ላይ የወርቅ አክሊልን እና በእጁ ስለታም ማጭድን በመያዝ በደመና ላይ በሚመጣዉ በሰዉ ልጅ መልክ አጠቃለናል ፡፡ ማጭዱን በምድር ላይ በመጠቀም ሰበሰባት ፤ ከዚያም አንድ መለዓክ ከአንድ ማጭድ ጋር በመገለጥ የምድርን ወይን ለመሰብሰብ ማጭዱን በመጠቀም ወደ እግዚአብሔር የወይን መጥመቂያ ዉስጥ ወረወራቸው ፡፡ ደምም ከወይን መጥመቂያዉ ዉስጥ እስከ ፈረሶች ልጓም ድረስ 180 ማይል ያክል ፈሰሰ (ቁጥር 14-20) ፡፡ ከምዕራፍ 14 ምዕራፍ 15 ሰባቱን ጽዋዎች እና እያንዳንዳቸዉ የተቀበሉትን ተፅዕኖ ስናጠና ወደ ሌላ አስፈሪ ዝምታ እንሄዳለን ፡፡ ፍሰቱን ለመረዳት ከምዕራፍ (6-11) በአንድ አቀማመጥ/ማዕቀፍ ዉስጥ ማጥናት የተሻለ ነው ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (15፡ 1-4)፡ ከዚያም ዮሐንስ የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚፈጽሙ ሰባት መለዓክትን ከሰባት መቅሰፍቶች ጋር አዬ ፡፡ “ ይፈፀማል “ (ቁጥር 1) የእግዚአብሔር እቅድ የተፈፀመ መሆኑን ያመለክታል ፡፡ ስለ መከራዉ ብዙ አመለካከቶች/እይታዎች አሉ፡ አንዳንዶች የክርስቶስ ተከታዮች ከመከራዉ በፊት ወደ ሰማይ እንደሚነጠቁ ያምናሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ የክርስቶስ ተከታዮች ከሰባቱ አመት መከራ በኋላ እንደሚነጠቁ ያምናሉ ፡፡ ያም ሆነ ይህ መከራው በስድስት በተለዩ ማህተሞች በኩል ይፈፀማል(ራዕይ 6)፡
- በነጭ/በአምባላይ ፈረስ ላይ አንድ ፈረሰኛ ተገለጠ ሐሰተኛዉም ክርስቶስ ነው ፤ ይህ ማቴዎስ 24 ከራዕይ 6 ጋር የሚያመሳስል እና የሰባቱ አመት ጊዜ መከራ መጀመሪያም ነው ፡፡ ታላቁ መከራ በዚያ ሰባት አመት ጊዜ ዉስጥ በግማሹ ላይ ይጀምራል ፡፡
በቀይ/ዳማ ፈረስ ላይ የሰዎችን ሰላም ለመዉሰድ አንድ ፈረሰኛ ይገለጣል - ጦርነት እና የጦርነት ወሬ ይኖራል (ማቴዎስ 26) ፡፡
በጥቁር/ጉራቻ ፈረስ ላይ አንድ ፈረሰኛ እጥረትን፣ አለመብቃትን እና ርሀብን በሚወክል የመስፈሪያ ሚዛን ይገለጣል (6፡ 5-6) ፡፡
በሐመር ፈረስ ላይ ሞትን እና ሲዖልን የሚወክል አንድ ፈረሰኛ ይገለጣል ፡፡
አስታዉሉ፡ ብዙ ምሁራን እነዚህ የመጀመሪያዎቹ አራት ማህተሞችበመከራዉ የመጀመሪያዉ ሰዎስት አመት ከግማሽ ቀደም ብለዉ እንደሚመጡ ያመለክታሉ ነገር ግን በእርግጠኝነት አናዉቅም፡
በሰማይ በስሩ የታመኑ ሰማዕታት ያሉት አንድ መሰዊያ ይገለጣል (ማቴ 24፡ 9, ራዕ 6፡ 9-11) ፤ የዚህን ሁሉ የመሆኛ ጊዜን እርግጠኞች መሆን አንችልም ነገር ግን በአምስተኛዉ እና በስድስተኛዉ ማህተም ጊዜ አማኞች ንዴት እንደሚሰማቸዉ እርግጠኛ መሆን እንችላለን ፡፡
የመሬት መናወጥ ክስተት፣ የፀሐይ ወደ ጥቁር/ጨለማ መቀየር፣ የጨረቃ ደምን የመሰለች መሆን እና የፍጥረት ስርዓት የተዘበራረቀ/የፈራረሰ መሆን የአለም ፍጻሜ በእጁ ላይ እንደሆነ ይናገራል ፡፡
አስታዉሉ፡ አንዳንድ ምሁራን ማህተሞቹ፣ መለከቶቹ እና ጽዋዎቹ ሁሉም በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚሆኑ ያመለክታሉ ፤ መለከቶቹ ፡- 1) የምድርን ሳር ሊያቃጥል የሚመጣዉን ኃይለኛን እሳትን፣ 2) የባህሮችን መበከልን፣ 3) የንጹህ ዉኃን መበላሸትን እና 4) የፀሐይ ሲሶ፣ የጨረቃ ሲሶ እና የከዋክብት ሲሶ መጨለምን መምጣትን አወጁ ፡፡ አንድ መለዓክ ቀጣዮቹ ሰዎስቱ መለከቶች ብዙ አስከፊ ነገሮችን ወደ ተግባር እንደሚጠሩ ተናገረ ፡- 5) የሰይጣን ወረራ፣ 6) ሰይጣን በሰዎች ላይ ጦርነትን ያውጃል/ያደርጋል በተጨማሪም 7) የሰባቱ ጽዋ መሰጠት ፡፡ በመሰረቱ እነዚህ ሰባተኛዉን ማህተም ይጀምራሉ ፤ ሁሉም አማኞች ከዚህ በፊት እንደሚነጠቁ በኃይለኛዉ አምናለሁ ፡፡ የሰባት አመቱ የመጀመሪያዉ ግማሽ አመት መጨረሻ ላይ ታላቁ መከራ ይጀምራል ፤ ምዕራፍ 15 በዚያ ክስተት ይጀምራል፡፡
ዋይርስቤ ቁጥር (1-4) “ እንደ ድል አድራጊነት ድምጽ “ ይገልፃቸዋል ፡፡ ቁጥር 2 በአዉሬዉ ላይ ድል አድራጊዎች የሚሆኑትን ይገልፃል ፤ ያ ድል አድራጊነት የሚታይ ነዉ ምክንያትም ምናልባትም በሰመዓትነት በሰማይ እያመለኩ ስለሆነ ፡፡ ቅዱሳኖች በአምልኮ የእግዚአብሔርን በገና በመጫወት በብርጭቆ ባህር ላይ ቆመዋል ፤ በራዕ (5፡ 8) ሽማግሌዎቹም በገናን ሲጫወቱ ታይተዋል ፡፡ ማክአርቱር “ በሰማይ ላይ ባህር እንደሌለ (21፡ 1) ነገር ግን ልክ እንደ ታላቅ የሚያንፀባርቅ ባህር የእግዚአብሔር የዙፋን ወለል በመሆን የሚያገለግል የብርሌ ንጣፍ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ “ እስራኤል ጨምሮ ከሁሉም ሕዝብ የሆኑት እነዚህ ቅዱሳኖች በኢየሱስ ክርስቶስ ካላቸዉ እምነት የተነሳ በመጨረሻም በሰይጣን እና በሐሰተኛዉ ክርስቶስ እና በስርዓቱ ላይ ድልን ያደርጋሉ “ ፡፡ ቅዱሳኖቹም የአምልኮ ዜማንም ይዘምራሉ (ቁጥር 3-4) ፤ መዝሙራቸዉ ያገኙትን የሚገልፁ ናቸው - በእርግጥ ሁሉም ሕዝብ በአንድ ላይ ጌታን በማመስገን ነበሩ ፡፡
ይህ ቅዱሳን በአምልኮ በሚዘምሩ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቁጣ ከመቀመሳቸዉ በፊት እረፍት እንደሆነ እናስታዉሳለን፡፡ ማክአርቱር የሙሴ መዝሙር “ በቀይ ባህር ዉስጥ ካለፉና ከግብጡያን ሰራዊት ከነፃመዉጣታቸዉ በኋላ ወዲያዉኑ በእስራኤላዊያን የተዘመረ እንደ ነበር (ዘጸ 15፡ 1-18)…. ሐሰተኛዉን ክርስቶስ እና ስርዓቱን የሚቋቋሙ ቤዛነታቸዉን ያገኙት ድል አድራጊዎች እና ነፃ ወጪዎች በፈቃደኝነት እንደሚለዩ “ አመልክቷል ፡፡ በተጨማሪም የሙሴን መዝሙር እና የበጉን መዝሙር መዘመር “ ሁለት የቤዛነት/የመቤዠት ክስተቶች ያስምራል ፡- 1) በሙሴ በኩል ከግብጽ በእግዚአብሔር የእስራኤል ነፃ መዉጣት እና 2) በክርስቶስ በኩል ከኃጢዓት በእግዚአብሔር የኃጢዓተኞች ነፃ መዉጣት “ ፡፡
ራዕይ (15፡ 5-8)፡ ዋይርስቤ (15፡ 5 -16፡ 21) “ የመፈፀም ድምጽ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ዮሐንስ የሰማይ መቅደስ እና የምስክሩም ኪዳን በእርሱ ፊት ሲከፈት ተመለከተ (ቁጥር 5) ፤ ከዚያም ጥሩ የጌጥ ልብስን እና የወርቅ መታጠቂያን የለበሱ ሰባት መለዓክ እና ሰባት መቅሰፍቶች ከመቅደሱ ወጡ (ቁጥር 6) ፡፡ ማክአርቱር “ የወርቅ መታጠቂያዎቹ ብልፅግናን፣ ንጉሳዊነትን እና የማይጠፋ /የማይደበዝዝ ክብር እንደሚያሳይ “ ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሔር ማን እንደ ሆነ ይገለጣል !
በቁጥር 7 ላይ የተጠቀሱት ፍጥረቶች በራዕይ (4፡ 6-8) ላይ የተዋወቁት ነበሩ - አንበሳዉ፣ ጥጃ፣ የሰዉ ፊት እና ንስር ነበሩ ፡፡ ከእነዚህ ፍጥረቶች ዉስጥ አንዱ በእግዚአብሔር ቁጣ የተሞሉትን ሰባት የወርቅ ጽዎች ሰባቱን መለዓክት ሰጣቸው ፡፡ ማክአርቱር የወርቅ ጽዋዎቹን “ ብዙ ጊዜ በቤተ መቅደስ ስራዎች ላይ ለምሳሌም ከወይን እና ከደም ጋር የተገናኙ የተለመዱ የሆነ ቅርብ ጥልቀት ያላቸዉ ማስቀመጫዎች እንደሆኑ ፤ ዝርግ የሆነዉ ጥልቀታቸው የድነትን ጽዋ መጠጣትን እምቢ ያሉትን በዝግታ ከማፍሰስ ከማስመጥ ይልቅ የመለኮት ፍርድ እንዴት በፍጥነት ባዶ እንደሚያደርገዉ የሚያሳይ እንደ ሆነ “ ይገልፃል (1ነገ 7፡ 50, 2ነገ 12፡ 13, 25፡ 15) ፡፡ እነዚህ ጽዋዎች በቀጥታ ከቤተ መቅደሱ መጡ ፡፡
መቅደሱ በእግዚአብሔር ክብር ጭስ የተሞላ ስለ ነበር (ዘጸ 19፡ 16-18, 40፡ 34-35, 1ነገ 8፡ 10, ኢሳ 6፡ 4, ሕዝ 10፡ 4)ሰባቱ መቅሰፍቶች እስኪፈጸሙ ድረስ ማንም መግባት አይችልም (ቁጥር 8) ፡፡
መደምደሚያ
የእግዚአብሔር መገኘት እና ቁጣ በሰባቱ የወርቅ ጽዋዎች ይለቀቃል ፡፡ ኢየሱስን ካወቃችሁ ከእግዚአብሔር ቁጣ የሚያስፈራችሁ ምንም ነገር አይኖርም ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians—Revelation, v. 11 (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 608.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 2003.
MacArthur, p. 2023.
MacArthur, p. 2023.
MacArthur, p. 2023.
Wiersbe, p. 609.
MacArthur, p. 2023.
MacArthur, p. 2024.
ጥያቄዎች
-
በራዕ (15፡ 2-4) መሰረት በመጨረሻ ለክርስቶስ የታመኑት በምድር ላይ ስለ ሚፈስሰው ቁጣ ምስክሮች ይሆናሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
የሙሴ መዝሙር በምን ተከበ/ተዘመረ (ዘጸዓት 15) ? የበጉ መዝሙር በምን ይከበራል ? (ኤር 10፡ 7, ራዕ 5፡ 9, 14፡ 7)
-
በመጽኃፍ ሌላ ስፍራ ላይ እግዚአብሔር ራሱን በጢስ የገለፀበትን ሌሎች አንዳንድ ስፍራ ጥቀሱ (ዘጸ 13፡ 21, 19፡ 18, 33፡ 9, 1ነገ 8፡ 10, ኢሳ 6፡ 4) ? በዚህ ማጣቀሻ/ማሳያ ዝርዝር ዉስጥ ምን እየሆነ ነበር ? በመጽኃፍ ላይ የእግዚአብሔር ክብር በጢስ የተገለጠበትን ስፍራ ማሰብ ትችላላችሁ ?
-
በራዕይ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 15:2–3
“I also saw something like a sea of glass mixed with fire, and those who had won the victory over the beast, his image, and the number of his name, were standing on the sea of glass with harps from God. They sang the song of God’s servant Moses and the song of the Lamb: Great and awe-inspiring are Your works, Lord God, the Almighty; righteous and true are Your ways, King of the Nations.”
የእግዚአብሔር ቁጣ ወደ ፍጻሜው ቀረበ፣ ቅዱሳኑም ሰባት መህተሞችንና ሰባት መለከቶችን ይይዛሉ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ሰባት መላእክትም ሰባቱን ቁጣ የሞላባቸው ጽዋዎች ይዘው ይወጣሉ፡፡ ነገር ግን መጀመሪያ ቅዱሳን በብርጭቆ ውሃ ላይ ቆመው በበገናና በዝማሬ ሁሉን ቻይ የሆነውን ጌታ እግዚአብሔርን እያመለኩ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ የተቀዳጁትን ድል ያወሳሉ፡፡
ዮሐንስ ከመከራ፣ ከፈተናና ከነውጥ ጊዜ በኋላ የድል ዝማሬን ሰማ፡፡ ይህ መዝሙር ጌታን ለማመስገን እና ቀኑን ሙሉ ስሙን ለማወደስ እንደ ማንቂያ ማስታወሻ ይሁንላችሁ፡፡ ምናልባት መዝሙሩን እንደማትችሉት ወይም ሪትሙን መጠበቅ እንደማትችሉ ታስቡ ይሆናል ሆኖም ግን ይህ እግዚአብሔርን በልባችሁ ከማምለክ እንድያግዳችሁ አትፍቀዱ፡፡ ለእርሱ አዲስ የምስጋናን መዝሙር ዘምሩለት፡፡ በእጆቹም ስራ ደስ ይበላችሁ፡፡ ስለመንገዱም ስለ አሰራሩም አመስግኑት፡፡ ታማኝ ስለሆኑ ተስፋዎቹ ደግሞም በህይወታችሁ እያደረገ ስላለው እርዳታ እውቅናን ስጡ፡፡ ይህም እግዚአብሔር የማይቻለውን ነገር ሲያደርግ ማየት ወይም ሁልጊዜም በእርሱ ሰላም ማረፍ ሊሆን ይችላል፤ እርሱን ስለተቀዳጃችሁት ድል አመስግኑት፡፡ አሁን በሉ ተነሱና ለእግዚአብሔር በግ፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ ዘምሩ! ለነበረው፣ ላለውና ለሚመጣው!
“በእሳትም የተቀላቀለውን የብርጭቆ ባሕር የሚመስለውን አየሁ፥ በአውሬውና በምስሉም በስሙም ቍጥር ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤ እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።”
- ራዕይ 15፡2-3
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘጸአት 15:1 — “በዚያም ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።”
መዝሙር 98:1 — “ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፥ እግዚአብሔር ተኣምራትን አድርጎአልና፤ ቀኙ የተቀደሰም ክንዱ ለእርሱ ማዳን አደረገ።”
ራዕይ 15:1 — “ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።