The Seven Bowls
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ከሰባቱ ማህተሞች እና ከሰባቱ መለከቶች በኋላ ዮሐንስ በሰባቱ መለዓክት ተይዘዉ የነበሩትን ሰባቱን ጽዋዎች አዬ ፡፡ ይህ ክፍለ ጊዜ በአጠቃላይ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ነበር ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ በማያምኑት ላይ በተለይም ሐሰተኛዉን ክርስቶስን በሚከተሉት ላይ ነበር ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (16፡ 1-21)፡ ዮሐንስ ከመቅደሱ የሚወጣ የሚጮኽ ድምጽ ሰማ ፡፡ መቅደሱ በሰማይ በዙፋኑ ክፍል ነበር ፤ ዮሐንስ ያየዉን መልክ እና ድርጊት በአጠቃላይ ለመረዳት እና ለመያዝ ብዙ መረዳቶችን/ስሜቶችን ተጠቅሟል ፡፡ ሰባት መለዓክቶች የእግዚአብሔር ሰባት ጽዋ ቁጣን በምድር ላይ እንዲያፈሱት ታዘዙ ፡፡
በቁጥር 2 የመጀመሪያዉ መለዓክ የአዉሬዉን ምስል በሚያመልኩት እና ምልክቱን በለበሱት/ባደረጉት ሁሉ ላይ በመጀመር ለሚያም የቁስል ምክንያት የሆነዉን አንዱን ጽዋ አፈሰሰው ፡፡ ቀደም ሲል የአዉሬዉ ምልክት የነበራቸው አማኞች ማግኘት ያልቻሉዓቸዉን ነገሮች የመግዛት እና የመሸጥ መብት ተሰጥቷቸዉ እንደ ነበር አይተናል ፤ አሁን በራሳቸዉ ላይ እና በእጃቸዉ ላይ ምልክት አለ ማለት የእግዚአብሔርን ቁጣ ይቀበላሉ ማለት ነው ፡፡
ማክአርቱር የእነዚህን የተለዩ የጽዋዎች አስፈላጊነትን ይገልፃል፡ “ ትልልቅ ሰው ግብፃዊያንን የቀሰፈዉን (ዘጸ 9፡ 9-11) እና ኢዮብን ያጠቃዉን (ኢዮ 2፡ 7) ቁስል/ሽፍታ ለመግለጽ ተመሳሳይ የግሪክ ቃል እንደሚጠቀም ፤ በአዲስ ኪዳን ምጽዋተኛዉን አልዓዛርን በመሸፈን የሚታየዉን ቁስል እንደሚገልጽ (ሉቃ 16፡ 21) ፤ በመላዉ አለም ላይ ሰዎች በማይድን፣ በሚታይ እና የማይለቅ ቁስል እንደሚያጠቃቸው “ ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር “ የሐሰተኛዉ ክርስቶስ አምላኪዎች ብቻ የተጠቁ እንደሚሆኑ (13፡ 16, 14፡ 9-11) ተመልከቱ “ ይጨምራል ፡፡ የመጀመሪያዉ የቁጣ ጽዋ ክርስቶስ ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት ፈሰሰ/ወረደ ፡፡
ሌለኛዉ መለዓክ ሁለተኛዉን ጽዋ በባህር ላይ አፈሰሰዉ ፤ ባህሩም ወደ ደም ተቀየረ በባህር ዉስጥ ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ሞቱ ፡፡ ይህ ጽዋ ከሁለተኛዉ መለከት ጋር የሚመሳሰል ነበር ፡፡ በማህተሞቹ፣ በመለከቶቹ እና አሁን በጽዋዎቹ ቅደም ተከተል የእግዚአብሔር ቁጣ በሂደት እየከፋ የሄደ ይመስላል ፡፡ ማክአርቱር “ ይህ የሁለተኛዉ መለከት (8፡ 8, 9) እና በግብጽ ላይ የመጀመሪያዉ መቅሰፍት (ዘጸ 7፡ 20-25) የሚመስል/የሚያስታዉስ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡
በቁጥር 4 ሰዎስተኛዉ መለዓክ ሰዎስተኛዉን ጽዋ አፈሰሰው ፡፡ የሰዎስተኛዉ ጽዋ የመፍሰስ ዉጤት የመጠጥ፣ የወንዝ እና የምንጭ ዉኃ ወደ ደም መቀየር ነበር ፤ ሁሉም የመጠጥ/ንጹህ ዉኃ ወደ ደም ተቀየረ ፡፡ የሚጠጣ ምንም ነገር አልነበረም ፡፡ የዉሆች መለዓክ ሰዎስተኛዉን ጽዋ ካፈሰሰዉ መለዓክ ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል ፡፡
እግዚአብሔር ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ “ ማን እንደ ሆነ እና ማን እንደ ነበር “ የተገለጸ ነበር ፡፡ ቁጥር 6 ለመጠጣት ያለዉ ብቸኛዉ ነገር ደም እንደ ነበር ይናገራል ፤ ምክንያቱም በሰማዕቶቹ ላይ ሞትን እና ጥፋትን አምጥተዉ ስለ ነበር ፡፡
ማክአርቱር “ ቁጥር 6 ዘላለማዊዉ አምላክ በፍትሐዊነት/በሚገባ ይፈርዳል ምክንያቱም አማኞችን እና ወንጌል ሰባኪዎችን ገድለዋል (6፡ 9-11, 7፡ 9-17, 11፡ 18, 17፡ 6, 18፡ 20) ፤ ይህ መታረድ በታሪክ ተመሳሳይ አይኖረውም (ማቴ 24፡ 21) እና ምንም የእግዚአብሔር በቀልም እንደማይሆን (ሮሜ 12፡ 19-21 “ ይገልፃል ፡፡ አማኞች ራሳቸዉን ለማንፃት ዉኃ አልነበራቸዉም ፡፡ የእግዚአብሔር ፍርድ ፍትሐዊ እና ተገቢ እንደሆነ የተገለፀ ነበር ፡፡
በቁጥር 7 አንድ ድምጽ ከመሰዊያዉ በመምጣት እግዚአብሔር ያፍ ፍርድ እንደሚመጣ በተደጋጋሚ አስጠንቅቆ ስለ ነበር የጽዋዎቹ ቁጣዎች ተገቢ እንደ ነበሩ ተናገረ ፤ ሁሉም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲቀበሉ እድል ተሰጥቷቸዉ ነበር፡፡
በቁጥር 8 አራተኛዉ መለዓክ አራተኛዉን ጽዋ አፈሰሰው ፡፡ ጽዋዉ በጽሐይ ላይ የፈሰሰ ነበር ፤ ሰዎችም ተቃጠሉ/ነደዱ ፤ ስጋቸዉም በእሳትና በሙቀት የተቃጠለ እና የነደደ ነበር ፡፡ በቁጥር 9 መጨረሻ ላይ ዮሐንስ ሰዎቹ ንስሐ እንደማይገቡ ተናገረ ፤ እነዚህ መግለጫዎች እና ንስኃ ለመግባት የሕዝቡ/የሰዎች እምቢ ማለት ከፈረዖን ምላሽ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ ሰዎች/ሕዝቡም ለእግዚአብሔር ክብሩን ለመስጠት እምቢ አሉ ፤ ሕዝቡም በእግዚአብሔር ላይ ስድብን ተናገሩ ፤ እግዚአብሄር ሁሉም ነገር በቁጥጥሩ ስር እንደ ነበር እዉቅና መስጠትን እምቢ አሉ ፡፡
ቁጥር 10 የአምስተኛዉን ጽዋ መግለጫ ይሰጣል ፡፡ ይህ ጽዋ በአዉሬዉ ዙፋን ላይ ይፈስሳል መንግስቱም በጨለማ ተቀመጠ ፡፡ አሁንም ሰዎች እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ እንደ ነበር ባስተዋሉም ጊዜ እንኳን እግዚአብሔርን ተሳደቡ ፡፡ ዉጤቱም አለማቀፋዊ ጨለማ ነበር ፡፡
ስድስተኛዉ ጽዋ በቁጥር 12 የተገለፀ ነው ፡፡ በኤፍራጠስ ወንዝ ላይ ፈሰሰ ወንዙም ነገስታቶችም መሻገር/ማቋረጥ እንዲችሉ ደረቀ ፡፡ ማክአርቱር “ በመጽሐፍ ላይ ታላቁ ወንዝ በመባል አምስት ጊዜ የተጠራው ከምንጩ በአራራት ተራራ ዳገት ላይ ወደ ፋርስ ባህር 1,800 ማይል እንደሚፈስ ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ተስፋ የገባትን ምድር የምስራቅን ድንበር እንደሚያበጅላት (ዘፍ 15፡ 18, ዘዳ 1፡ 7, 11፡ 24, ኢያ 1፡ 4), ራዕ 9፡ 14) “ ይገልፃል ፡፡
ማክአርቱር በመቀጠልም “ ቀድሞ በፍሰቱ በረጅም ድርቅ እና በከፍተኛ ሙቀት ፈሰቱ እንደቀነሰ እግዚአብሔርም በመለኮታዊ ኃይል ወደ እስራኤል እንዲደርሱ ለምስራቅ የጥምረት ሰራዊት መንገድን ለማዘጋጀት እንደሚያደርቀዉ (ኢሳ 11፡ 15) “ ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ሰራዊት በዚህ ስፍራ እንዲሆኑ መንገዱን ይጠርግላቸዋል ለአርማጌድዮን ዉጊያና ለራሳቸዉ ጥፋትም በዚያ ይሆናሉ ፡፡ “ ምናልባትም ለመምጣታቸዉ ምክንያቱ የአለምን መከራ ለመቀነስ ባለመቻሉ ያለ ጥርጥር ዝናዉን ለማጥፋት በሐሰተኛዉ ክርስቶስ ላይ ለማመጽ ፤ ወይም ደግሞ ምናልባትም ይህ እስራኤልን ለማጥፋት የመፈለግ የፀረ ሴማዊያን የመጨረሻ የእብደት ተግባር ምናልባት በአምላኳ በእግዚአብሔር ለተላከዉ መቅሰፍት በቀል “ ፡፡
በቁጥር 13 ሰዎስት ርኩሳን መናፍስት ከዘንዶዉ አፍ መጡ ፡፡ ሰዎስቱ ምስሎች ሐሰተኛዉ ክርስቶስ/አዉሬዉ፣ ሰይጣን እና ሐሰተኛ ነብዩ ነበሩ ፤ የክፉዉንም መናፍስት ይወክላሉ ፡፡ ማክአርቱር “ ቅዱስ ያልሆነ ሶስትነት “ የሚለዉን ቋንቋ ሰዎችን በአንድ ላይ ለአርማጌድዮን ጦርነት የሚሰበስብ እንደ ነበር ይናገራል ፡፡
አሁንም የጽዋዎቹ ቁጣ በመምጣት ሂደት ዉስጥ ነበሩ ፤ ነገር ግን በቁጥር 15 እግዚአብሔር ለክርስቶስ ተመልሶ መምጣት የተዘጋጄ መሆን እንደሚያስፈልግ አብራርቷል ፤ ስዕሉም ለጦርነት የተዘጋጀ የአንድ ወታደር ምስል ነበር ፡፡
ሰባተኛዉም መለዓክ ጽዋዉን ወደ አየር ዉስጥ አፈሰሰው ፡፡ እንደ ማክአርቱር አገላለጽ “ በሰማይ ከቤተ መቅደስ የሚወጣዉ ድምጽ ያለምንም ጥርጥር የራሱ የእግዚአብሔር ነው ፤ ተፈጸ የሚለዉ የተሸለ ትርጓሜ ነው የሆነና የሚፈፀም ነው (ዮሐ 19፡ 30) ፡፡ እግዚአብሔር በምድር ታሪክ ታላቅ/ኃይለኛ በሆነ በሚያጠፋ የምድር መናወጥ የቁጣዉን መፈጸም ይጠብቃል (ቁጥር 18-21) “ ፤ ይህ በኢየሩሳሌም እና በባቢሎን መካከል ንጽጽርን አንፀባርቋል ፡፡
መደምደሚያ
እስካሁን ክርስቶስ ተመልሶ አልመጣም ፤ በዚህ በመጨረሻ ዘመን ክስተት ላይ የተገኘን ላለመሆን ማስወገጃዉ መንገድ ክርስቶስን እንደ አዳኝ እና እንደ ጌታ መቀበል ነው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 2024.
MacArthur, p. 2024.
MacArthur, p. 2024.
MacArthur, p. 2024.
MacArthur, p. 2025.
MacArthur, p. 2025.
MacArthur, p. 2025.
MacArthur, p. 2025.
MacArthur, p. 2026.
ጥያቄዎች
-
የሰባቱን መለከቶች መቅሰፍት በደንብ አብራሩ ፡፡
-
ስለ እነዚህ መቅሰፍቶች የሕዝቡ ምላሽ ምን ይሆናል ? በዚያ መንገድ ለምን ምላሽ እንደሚሰጡ ምን ታስባላችሁ ? (ያዕ 4፡ 6, 2ጴጥ 3፡ 9)
-
እነዚህን ሰባት ጽዋዎች በምድር ላይ የሚያፈሱት እነማን ናቸው ? የፈሰሱ የሆኑት ጽዋዎችስ እነማን ናቸው?
-
እንዲደረጉ የታቀዱት በራዕይ (16፡ 14) የተጠቀሱት ምልክቶች ምንድን ናቸው ? (1ነገ 22፡ 20-23, ማር 13፡ 22, ራዕ 19፡ 20)
-
ከክርስቶስ መመለስ በፊት በምድር ላይ የሚሆነዉ የእግዚአብሔር የመጨረሻ የፍርድን ምን ያደርጋል ?
-
በራዕይ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 16:9
“And people were burned by the intense heat. So they blasphemed the name of God, who had the power over these plagues, and they did not repent and give Him glory.”
ሰባቱ መላእክት ሰባቱን ቁጣ የሞላባቸው ጥዋዎች በምድር፣ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ላይ የሚያፈሱበት ጊዜ ደረሰ፡፡ በእርግጥም እነዚህ ሰዎች ንስሀ አልገቡም፤ ወደ እግዚአብሔርም አልተመለሱም፤ ለእግዚአብሔርም ክብርን አልሰጡም ስሙንም ተሳድበዋል፡፡ አሁን በእግዚአብሔር የተነገረውን ቁጣና ፍርድ ይቀበላሉ፡- የሚነዘንዝ ቍስል፣ ባህሩ የሰው ደም መሆን፣ ወንዞችና የውኃ ምንጮች ደም መሆን፣ የሚያቃጥል እሳትና ሙቀት፣ ጨለማ፣ መብረቅ፣ ነጎድጓድ፣ መሬት መንቀጥቀጥና አንድ ታላንት ሦስት ፈረሱላ የሚያህል የበረዶ ድንጋይ ከሰማይ መውደቅ፡፡ አሁንም እንኳ በዚህ ሁሉ ስቃይ መሀል ሀያሉን አምላክ እግዚአብሔርን መሳደባቸውን ቀጠሉ ንስሀ ለመግባትም እምቢ አሉ፡፡
ንስሀ ከመግባትና ህይወታችሁን ለኢየሱስ ከመስጠት አትዘግዩ፡፡ የተደበቀ ነገርም ካላችሁ አሁኑኑ አቁሙ፡፡ ተውት፡፡ ንስሀ ግቡና እንዲህ በሉ፡-“ ጌታ ሆይ ኃጢአቴን ይቅር በል፣ ህይወቴን እሰጥሀላሁ፡፡” እግዚአብሔር ለእናንተ ካለው ፍቅር የራቀ ምንም አይነት ኃጢአት፣ ቆሻሻ ወይም የሚያስጠላ ሁኔታ የለም፡፡ ኩራታችሁን ትምክህታችሁን ተውት፡፡ አስኪ አንዴ በህይወታችሁ ራሳችሁን ትሁት በማድረግ ንስሀ ግቡ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ መከልከላችሁን መገደባችሁን እስካልተዋችሁ ድረስ፣ ፍቅሩ ወደ ህይወታችሁ እንድገባ እስካልፈቀዳችሁ ድረስ እርሱ ለእናንተ ያለውን ፍቅር ፈጽማችሁ ልትረዱ አትችሉም፡፡ ተው፣ ከእግዚአብሔር ማምለጥ አቁሙ፡፡ መልካምነቱና ምህረቱ በህይወት ዘመናችሁ ሁሉ ከእናንተ ጋር ይሆናሉ፡፡
“ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፥ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፥ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሐ አልገቡም።”
- ራዕይ 16፡9
ተጨማሪ ጥቅስ
ሐዋርያት ሥራ 3:19–20 — “እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።”
2ኛ ቆሮንቶስ 6:2 — “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”
ራዕይ 16:1–2 — “ለሰባቱም መላእክት፦ ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።