Revelation Revelation

The Women And The Scarlet Beast

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 725 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ምዕራፍ 17 በቀይ አዉሬ ላይ በተቀመጠች ሴት ምስል ጀመረ ፡፡ ሰባት የመከራ አመታቶች ነበሩ ፤ በእነዚህ ሰባት አመታቶች ሰባት ማህተሞች፣ ሰባት መለከቶች እና ሰባት የእግዚአብሔር ቁጣ ጽዋዎች ነበሩ ፡፡ በእነዚህ ሁሉ መካከል ላይ እንኳን እግዚአብሔር ሰዎች ንስኃ እንዲገቡ ፈለገ ፤ በራዕይ እዚህ ስፍራ ላይ የአርማጌድዮን ጦርነት እስካሁን አልሆነም ፡፡ ሁልጊዜ የራዕይ መጽኃፍ የጊዜ ቅደም ተከተልን አይደለም ፤ አሁንም ክርስቶስ እዚህ ስፍራ ላይ ተመልሶ አልመጣም ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (17፡ 1-18)፡ ከሰባቱ ጽዋዎች አንድ የነበረዉ ከሰባቱ መለዓክት አንዱ ከዮሐንስ ጋር ቃለ ምልልስ ነበረው ፡፡ ራዕይ 17 ስለ ባቢሎን ስርዓት ነበር - ከገለሞታይቱ ከመንፈሳዊነት አመለካከት ስርዓት አንፃር እና ሀሰተኛዉን ክርስቶስ/አዉሬዉን እና ሰይጣንን ከሚይዘዉ ከባቢሎን ስርዓት በሁለቱም ላይ ነበር ፡፡ ምዕራፍ 18 የባቢሎንን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስርዓትን ይሸፍናል ፤ በምዕራፍ 19 ክርስቶስ በመምጣት ሁሉንም ነገር ያነፃል ፡፡

ይህ ምዕራፍ የባቢሎን ስርዓት የእግዚአብሔር ከተማ እንዳደረገች በደረጃ እንዴት እንዳልነበር ይገልፃል ፤ ሁልጊዜ በባቢሎን እና በእግዚአብሔር መካከል ዉጥረት ነበር ፡፡ መለዓኩ ዮሐንስ ያሳየዉ ምስል በብዙ ዉኃዎች ላይ የተቀመጠችን የጋለሞታይቱን ስርዓት ነበር ፡፡

ቁጥር 2 የአለም ነገስታቶች ከጋለሞታይቱ ጋር ያልተገባ ወሲብን ፈጽመዉ እንደ ነበር ይናገራል ፤ የምድር ነገስታቶች በጋለሞታዋ ጋብዣ ላይ እየተሳተፉ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ ገለሞታዋ ከአለም ፖለቲካ መሪዎች ጋራ ራሷን እንዳስተባበረች ፤ እዚህ ጋር ዝሙት ጣዖት አምላኪነትን እንጂ የወሲብ ኃጢዓትን እንደማያመለክት ፤ የአለም መሪዎች ሁሉ ወደ የሰይጣን ሐሰተኛ ክርስቶስ አገዛዝ/ኢምፓየር የተሳቡ እንደሚሆኑ “ ይገልፃል ፡፡

በራዕይ መለዓኩ ዮሐንስ በመንፈስ ከአንድ ደሴት ወደ አንድ በርሃ ወሰደው (ቁጥር 3) ፡፡ ዮሐንስ በስድብ ስሞች በተሞላ እና ሰባት ራሶች እና አስር ቀንዶች በነበሩት ቀይ አዉሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አዬ ፤ ይቺ ሴት እንደ ገለሞታ እና እንደ ባቢሎን በሁለቱም የምትታወቅ ነበረች ፡፡ ባቢሎን በእግዚአብሔር ላይ የተነሳ ስርዓት ምሳሌ እና በሐሰተኛዉ ክርስቶስ ምትዘወር ስርዓት ነበረች ፡፡

ቀጥሎም ዮሐንስ ሐምራዊ እና ቀይ ልብስን የለበሰችዉን ሴት መልክ ገለፀ ፤ ወርቅ፣ የከበሩ ድናጋዮችን እና ዕንቁዎችን ለብሳለች ፡፡ በከንቱ ነገር የተሞላ የወርቅ ጽዋን በእጇ ይዛ ነበር ፤ ሁሉም በቁጥጥሯ ስር እንደ ነበርና ከአለም ሕዝቦች እና መሪዎች ጋር ራሳን እያሳተፈች እንደ ነበር አሰበች ፤ በሂደቱም ባለጸጋ ሆነች ፡፡ ኃይማኖታዊ ጋለሞታዋ ሰዎችን ወደራሷ ለመሳብ እየሞከረች ነበር ፡፡

የኔልሰን ምብራሪያ “ ሴቲቱ ባቢሎን ልክ እንደ ንግስት ለብሳለች (18፡ 7) ሐምራዊ፣ ቀይ እንቁ፣ ወርቅ እና እንቁዎችን እንደ ለበሰች ፤ የታላቋ ጋለሞታ መልክ (ቁጥር 1, 5) የሚያምር/ሞገስ ያለዉ ቢሆንም የንጉሳዊ የወርቅ ጽዋዋ በክፋት የተሞላ ነው….. እግዚአብሔርን ያስቆጣ/ያስከፋ ቆሻሻነት፣ የጣዖት ንግግሮች እና የርኩሰት ድርጊቶች እንዳሉት “ ይናገራል ፡፡ ይህ በዘፍጥረት ላይ ካለዉ ኤደን ገነት ተቃራኒ መልክ ነበር ፡፡ በግንባርዋም ላይ ታላቂቱ ባቢሎን የጋለሞቶች እና የምድር ርኩሰት እናት የሚል የሚስጥር ስም ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ ይህ በሮማዉያን አመንዝሮች በራሳቸዉ ሁሉም እንዲያየው መጥፎነታቸዉ የሚያሰልፍ በላዉ ላይ ስማቸዉ ያለበትን የራስ ጥምጣም/መታጠቂያ መልበስ (ኤር 3፡ 3) የተለመደ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ የወርቅ ጽዋዉ ሕዝቦችን ወደ መንፈሳዊነት ዝሙት ለመምራት የሚጠቅም ነበር ፤ አላማው እርሷን የሚከተሉ ሕዝቦችን ማግኘት ነበር ፡፡ ይቺ ታላቂቱ ባቢሎን ከመልከዓ ምድር አቀማመጥ ከታሪካዊቱ ባቢሎን ከተማ የተለየች ነበር ፡፡

በዘፍጥረት 11 ከባቢሎን ግንብ እስከ ራዕይ (14፡ 8) ባቢሎኖች እና የባቢሎን መወከያዎች ነበሩ ፡፡ የባቢሎን ግንብ ሐሳብ ሰዎች ራሳቸዉን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ለማድረግ ነበር ፡፡ በመጽኃፍ ላይ ሌላዉ ሁሉም ነገር ከዚያ ካባቢሎን ግን መልክ ተዘረጋ ፡፡

በመጨረሻ ላይ ምናየው በከተሞች ላይ የጋለሞቶች እና የሁሉም ስርዓት ኃይል ማዕከል እናትን ነበር ፡፡ እነዚህ ከተሞች ከግዜ በኋላ ሲወድቁ የዶሚኖ ተጽዕኖ ነበር ፡፡ የዮሐንስ መግለጫ ስለነዚህ ስርዓት መጨረሻ ነበር ፡፡

በቁጥር 6 ስርዓቱም የተሳካለት ሆኖ ይታሰብ ነበር ምክንያቱም ክርስቶስን የሚከተሉትን ገድሎ ስለ ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ የቅዱሳን ደም… የክርስቶስ ሰማዕታት/ምስክር “ የሚለዉን ሐረግ፡ “ አንዳንዶች የመጀመሪያዉን ቡድን እንደ ብሉይ ኪዳን ቅዱሳን እና ሁለተኛዉን ደግሞ እንደ አዲስ ኪዳን ቅዱሳን እንደሚያዩ - ይህ የመከራዉ ሰመዓታት ምስል ጥቃቅን የሆነ ልዩነት እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡

ኮንስታብል “ ይህ ስርዓት እዉነተኛ አማኞችን አጥፍቶ እንደ ነበርና በሞታቸዉ እንደተደሰተ ፤ ይህ ራዕይ ዮሐንስን እንዳስገረመው (በኃይለኛዉ እድነቃለሁ) ፤ አንድ ስርዓት እግዚአብሔርን የሚያከብረው የታመኑ ተከታዮቹን በመግደል የሚል ፍች እንደነበረው ! “ የሚል አመለካከት ነበረው ፡፡

በቁጥር 7 መለዓኩ የአዉሬዉን ምስል የተደበቀ ትርጓሜ እና ሰባቱን ራሶች እና አስሩን ቀንዶች ገልጾአል ፡፡ ቁጥር 8 አዉሬዉን እንደ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ እና ስርዓቱም በሐሰተኛዉ ክርስቶስ ላይ የተቀመጠችዉ ሴቲቱ እንደ ነበረች ይለያል ፡፡ ስርዓቱ በሐሰተኛዉ ክርስቶስ በኩል የሚፈስስ እና የፈሰሰ ነበር ፤ ሴቲቱ በክርስቶስ ላይ የተነሳች ነበረች ፡፡

ሐሰተኛዉ ክርስቶስ የነበረ፣ ያለ እና እንደ ገና ተመልሶ የሚመጣ ነው ፡፡ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ የሐሰት ትንሳኤ ይኖረዋል ፤ በታላቁ መከራ መካከል ላይ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ የሞተ በመምስል ተመልሶ ወደ ህይወት ይመጣል ፤ በክርስቶስ ላይ እምነት የሌላቸዉም ይደነቃሉ ፡፡ በራዕ (13፡ 3-4) ከሐሰተኛዉ ክርስቶስ/ከአዉሬዉ ራሶች አንዱ በሰይፍ የሚገድል ቁስል ነበረው ነገር ግን ዳነ/ተፈወሰ ፤ በራዕ (13፡ 12-13) ሐሰተኛዉ ነቢይ ሰዎች የሞት ስላልነበር ሐሰተኛዉን ክርስቶስን እንዲያመልኩ አበረታታቸው ፡፡

በቁጥር 9 ሰባቱ ራሶች ሰባት ተራሮች እንደሆኑ የተገለጹ ናቸው ፡፡ ሴቲቱም በተራሮቹ ላይ ተቀምጣ ነበር ፡፡ ሰባት ነገስታቶች ነበሩ አምስቱም ቀድመዉ ወድቀዉ ነበር ፡፡ ስለ ሰባቱ ተራሮች ብዙ ቴዎሪዎች አሉ ፤ አንዱ ቴዎሪይ ሰባቱ ተራሮች ሮም ተገንብታባቸዉ የነበሩትን ሰባት ኮረብታዎች የሚወክሉ እንደ ሆኑ ሲሆን ፤ ሌለኛዉ ቴዎሪይ ሰባት መንግስታት እና ሰባት ነገስታት እንደ ነበሩ የሚያመለክት ነው ፡፡ ከሰባቱ ነገስታቶች ዉስጥ የተወከሉት፡ የግብፅ፣ የአሶር፣ የባቢሎን፣ የሜዶንና ፋርስ፣ የግሪክ፣ የሮም እና የመጨረሻው ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ይሆናል ፡፡ ዮሐንስ እነዚህ ስርዓቶች የእግዚአብሔር እንዳልነበሩ አንድ ጉዳይን/ነገርን አድርጓል ፡፡

ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ከሞቱና ከትንሳኤዉ የተነሳ ሰባተኛዉን እና ስምንተኛዉን መንግስት ይወክላል ፡፡ በቁጥር 12 አስሩ ቀንዶች በሐሰተኛዉ ክርስቶስ ስር ያሉትን መንግስታት ይወክላሉ ፤ ለተወሰነዉ ጊዜ ብቻ ከሐሰተኛዉ ክርስቶስ የሆነ ስልጣን ነበራቸው ፡፡ የተጠቀሰዉ አንድ ስዓት ኃይላቸዉን እና ስልጣናቸዉን ለአዉሬዉ የሚሰጡበትን የሰወስት አመት ጊዜ ሊወክል ይችላል ፡፡ እነዚህ አስሮቹ ከጌቶች ጌታ እና ከነገስታት ንጉስ ጋር ጦርነት ያደርጋሉ ፤ ቁጥር 14 ስለ አርማጌድዮን ጦርነት ነው ፡፡

ቁጥር 15 ሴቲቱ በሕዝቦች፣ በብዙ ነገዶች፣ በአሕዛቦች እና በቋንቋዎች ላይ ስልጣን እንደ ነበራት ይናገራል ፡፡ አንድ አለማቀፋዊ የኃይማኖት ስርዓት ይኖራል ፡፡ በመጨረሻም አዉሬዉ እና ሁሉም አስሩ ሕዝቦች ስርዓቱን ይጠሉታል ፤ ሴቲቱንም በእሳት ያቃጥሏታል ፡፡ አዉሬዉ እና አስሩ ሕዝቦች የጌታን ፍቃድ ያደርጋሉ ፤ የሰይጣን የራሱ መንግስት በራሱ ተከፋፈለ ፡፡

መደምደሚያ

በራሱ የሚከፋፈል መንግስት መቆም አይችልም ፤ ማር (3፡ 23-26) በራሱ ስፍራ ላይ ስለ መንግስት መከፋፈል አዉርቷል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 2026.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1758.

  3. MacArthur, p. 2027.

  4. MacArthur, p. 2027.

  5. Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): Revelation, p. 273; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/revelation.pdf.

ጥያቄዎች

  1. በራዕ (17፡ 1) እግዚአብሔር ዮሐንስን ስለ ታላቂቱ ገለሞታ ስለሚገልጥለት ነገር ምን ታስተዉላላችሁ ? ስለ ሴቲቱ ዮሐንስ ምን እንድናዉቅ ይፈልጋል ? (ራዕ 18፡ 10, 18, 21)
  2. ታላቂቱ ገለሞታ ማነች (ራዕ 17፡ 18) ? በራዕ (17፡ 2) ታላቂቱ ገለሞታ ራሷን ከማን ጋር ታወዳጃለች / ታጣምራለች ?
  3. ዘፍጥረት 2 ከራዕይ (17፡ 2-6) ጋር አወዳድሩ ፤ ኃጢዓት ለዓለም ጥፋት ምክንያት እንደሆነ አስታዉሉ ፡፡
  4. አስሩ ቀንዶች ስልጣን መቼ ይቀበላሉ (ራዕ 17፡ 22) ? አንድ አላማቸዉ ምንድን ነው ከማን ጋርስ ጦርነትን ያደርጋሉ ?
  5. ገለሞታዋን ማን ይጠላታል (ራዕ 17፡ 16) ? የማን እቅድስ ነበር ? ለምን ያክል ጊዜ መንግስት ይኖራቸዋል ? (ዘፍ 50፡ 20, ምሳ 19፡ 21)
  6. በራዕይ 17 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 17:14

“These will make war against the Lamb, but the Lamb will conquer them because He is Lord of lords and King of kings. Those with Him are called, chosen, and faithful.”

የዮሐንስ ራዕይ ሲቀጥል፣ የክርስቶስ ዳግም መጽዓት ሲሆን ለሚጀመረው ጦርነት ዝግጅት ተደረገ፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህልም ስልጣንን የተቀበሉት የምድር ነገሥታት ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ፡፡ ነገሥታቱም ከአውሬው ጋር ሆነው በበጉ ላይ ጦርነትን ያውጃሉ፡፡ ነገር ግን በጉ ኢየሱስ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፡፡ የእርሱም ደቀ መዛሙርት፣ አማኞች ከበጉ ጋር ሆነው ይዋጋሉ፡፡ እርሱም የተመረጣችሁ እና የታመናችሁ ብሎ ይጠራቸዋል፡፡

ኢየሱስ የዓለም ሁሉ አዳኝ በመንግስታት ሁሉ ላይ በአሸናፊነት ይነግሳል፤ አውሬውም ይሁን የምድር ንጉሥ በእርሱ ላይ ድልን አይቀናጅም፡፡ እርሱ ምርጦች ብሎ ለጠራቸው ደግሞም ለታመኑት ለእነርሱ ነገርን ሁሉ ለበጎ ያደርገዋል፡፡ በህይወታችሁ ውጊያ፣ መከራ ወይም የማታውቁት ነገር ሲገጥማችሁ አትፍሩ፡፡ በእርሱ የታመኑና ምርጦች ተብላችሁ ስለተጠራችሁ፣ በኃያሉ አምላክ ጥላ ስር ስትኖሩ እግዚአብሔርን እንዲህ ማለት ትችላላችሁ ፡- “አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።” ወደ እርሱ ተጣሩ እርሱም ይመልስላችኋል፡፡ እርሱ ይታደጋችኋል፤ ያረካችኋል እንድሁም ደህንነትን ይሰጣችኋል፡፡ ዛሬ አትፍሩ አትደንግጡም፡፡ ጌታ በእርሱ ዘንድ ተስፋ እንዳለ ተናግሯል፡፡ እርሱ መኖሪያችሁ ነው፡፡ በደንብ ትንፋሽ ውሰዱና በእርሱ ኃያል ክንፎች ስር እረፉ፡፡ እርሱ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይሆናል፡፡

“እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”

  • ራዕይ 17፡14

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 91:1–2 — “በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።”

ዮሐንስ 15:16 — “እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።”

ያዕቆብ 2:5 — “የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን?”