The Fall Of Babylon The Great
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ራዕይ (1፡ 4) የጠቅላላ የራዕይ መጽኃፍን ፍሬ ሀሳብ ይሰጣል፡ “ ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስትያናት ፤ ካለዉና ከነበረው ከሚመጣው በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት ከታመነዉም ምስክር ከሙታንም በኩር የምድርም ነገስታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን “ ፡፡ ምዕራፍ (1-3) ኢየሱስ ማን እንደሆነና እንደ ነበር ሲመዘግብ ምዕራፍ (4-5) ኢየሱስ እንዴት ወደፊት እንደሚመለስ ያዉጃል ፡፡ ዛሬም የራዕ (1፡ 4) ምስልን አሁንም እየሸፈንን ነው ፡፡ በራዕይ 16 በሰባቱ መለከቶች ላይ ከዚያም የቁጣዎቹን ሰባት ጽዋዎች ለሰባቱ መለዓክት አሳልፈዉ የሰጡትን አራት ፍጥረቶች ተመልክተናል ፡፡ እነዚህ ሰባት ቁጣዎች ለማያምኑት የተካተቱ ናቸው፡ 1) በፍጹም የማይጠፋ ቁስል፣ 2) የደም ባህሮች፣ 3) በም የተበከለ የሚጠጣ ዉኃ፣ 4) እስካሁን ካለዉ ሙቀት በኃይል የሚያቃጥል ፀሐይ፣ 5) በሐሰተኛዉ ክርስቶስ እና በሕዝቦቹ ላይ የሚመጣ ጨለማ፣ 6) የኤፍራጠስ ወንዝ (1800 ማይል የሚረዝመው) መድረቅ እና 7) እያንዳንዳቸዉ 100 ፓዉንድ የሚመዝኑ ግዙፍ በረዶዎች በከተሞቹ ላይ ይወድቃሉ ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ቁጣ ነው ፤ የሰይጣን ቁጣ ምናልባትም በራዕይ በሰባተኛዉ ማህተም ላይ የሚታይ ነው ፡፡
በራዕይ 17 የባቢሎን መዉደቅ የኃይማኖት ስርዓቷ እና ከሰይጣን ጋር ያለዉ ዉጊያ ተቀምጧል ፡፡ በመጨረሻም ሰይጣን በእግዚአብሔር በግ በኢየሱስ ላይ በአርማጌድዮን ላይ ጦርነትን ያዉጃል ፤ ራዕይ 18 የገበያ እና የኢኮኖሚ አካልን እና የባቢሎን ዉድቀት የፖለቲካ ክፍልን ያቀርባል ፡፡ ራዕይ 19 የኢየሱስን መመለስ ያሳያል ፡፡ የቁጣዉን ጽዋዎች የዳሰስንበት ምክንያት እዚህ ስፍራ ላይ አሁንም ሕዝቡ በጨለማ ስለ ነበሩ ነው (በ 5 ቁጣ ) ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (18፡ 1-3)፡ ዮሐንስ በታላቅ ስልጣን ሌላ መለዓክ ከሰማይ ሲወርድ እና አጠቃላይ ምድርም በእርሱ ብርኃን/ክብር አብርታ እንደ ነበር አዬ (ቁጥር 1) ፡፡ ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ቁጣ ቢቀጥልም ሰዎች የእግዚአብሔርን ክብር እንዲመሰክሩ ተፈቅዶላቸዉ ነበር ፡፡ ኮንስታብል ቁጥር (1-3) እንደ “ የፍርድ የመጀመሪያ መለዓካዊ ማሳወቅ “ ያጠቃልላቸዋል ፤ ዋይርስቤ እነዚህን ተመሳሳይ ጥቅሶች “ እንደ ኩነኔ ድምፅ “ ያጠቃልላቸዋል፡፡ የዌብስተር መዝገበ ቃላት “ ኩነኔ/ፍርድ “ የሚለዉን እንደ “ የተሳሳተ ስለሆነ የመፍረድ ወይም የመናገር፣ የመዉቀስ እና ግሳጼ “ ይገልፀዋል ፡፡ መለዓክ በእግዚአብሔር ክብር በባቢሎን አለመደሰቱን ለመናገር ይወርዳል ፤ መለዓኩም የባቢሎናዊያን ስርዓት ወድቆ እንደ ነበርና የአጋንንት፣ የርኩሳን መናፍስት፣ ንጹህ ያልሆኑ የወፎች እና እንስሳቶች ማደሪያ ስፍራ እንደሆነች ተናገረ (ቁጥር 2) ፡፡ ስርዓቱ አጋንንቶች ከታላቁ ጉድጓድ ይልቅ በዚያ በማደር አበላሽተዉት ነበር ፤ እዉነታዉ አጋንንቶች በአሁኑም ጊዜ መኖራቸዉ ነው (ኤፌ 6፡ 12) ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህን ለምን አንደርስም ? መለዓክት ስለ እኛ አጋንንቶችን የሚዋጉባቸዉ ጊዜያት አሉ ፡፡ የባቢሎን ጥፋተኝነት ብቻ አልነበረም ሌሎች ሕዝቦች ወደ ባቢሎን ስርዓት መሳባቸዉም ነበር ፡፡ ነገስታቶች ወደ ወሲባዊ ብልሽት ተሰቡ ነጋዲዎችም በኃይለኛ ስህተት ባለጠጎች ሆኑ (ቁጥር 3) ፡፡
ራዕይ (18፡ 4-8)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (4-8) “ እንደ መለየት ድምጽ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ከሰማይም ሌላ ድምጽ አማኞችን ከባቢሎን እንዲለዩ/እንዲወጡ ጠራቸው በኃጢዓታቸዉ እና በመቅሰፍታቸዉም አይያዙም (ቁጥር 4) ፡፡ ማክአርቱር “ እግዚአብሔር የራሱን ከዚህ ክፉ ስርዓ እንዲለዩ እንደሚጣራ ፤ ምናልባት ይህ የተመረጡት የአለምን ስርዓት በመተው በአዳኙ ወደ ማመን እንዲመጡ የእግዚአብሔር ጥሪ እንደሚሆን “ ያመለክታል ፡፡ ድምጹ የባቢሎን ኃጢዓት እጅግ ታላቅ ስለ ነበር እስከ ሰማይ እንደደረሰ እና እግዚአብሔርም በኃጢዓታቸዉ ላይ እንደተመለከተ ገለፀ (ቁጥር 5) ፡፡ ዋይርስቤ “ ዮሐንስ ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ከሰይጣናዊ ስርዓት ራሳቸዉን እንዲለዩ ሁለት ምክንያቶችን እንዳቀረበ ፤ የመጀመሪያው የእርሷ ኃጢዓት ተካፋይ በመሆን መበከልን ማስወገድ እንደ ሆነ (1ጢሞ 5፡ 22, ራዕ 18፡ 4) “ ፤ “ ሁለተኛዉ ምክንያት የእግዚአብሔር ሕዝብ በባቢሎን ላይ ከሚልከዉ አስከፊ መቅሰፍት እንዲድኑ “ እንደሆነ ያመለክታል ፡፡
በቁጥር 6 ዮሐንስ ሴቱቱ በኃጢዓቷ መሰረት ሁለት ዕጥፍ ምላሽ እንዲከፈላት የሚል ድምጽን ሰማ (ኢሳ 51፡ 19-22) ፤ ማክአርቱር “ መለዓኩ እግዚአብሔርን እንደ ስራ በራሷ ጽዋ ቁጣዋን እንዲኪፍላት/እንዲክሳት እንደተጣራ ፤ ይህ በእግዚአብሔር የሚተገበር የብሉይ ኪዳን የበቀል አስተጋቢ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ፍርድን እጥፍ ማድረግ እየመጣ ነበር ፤ መበለቲቱም ራሷን በማክበር እንደ ንግስት እያዮች ነበር (ቁጥር 7) ፡፡ የሚመጣዉ ፍርድ ይገባት ነበር ፤ ስለዚህም ሴቲቱን የሚገጥማት ፍርድ በአንድ ጊዜ በአንድ ምሽት ይመጣል - ሞትን፣ ሐዘንን እና ርኃብ ይገጥማታል (ቁጥር 8) ፡፡
ራዕይ (18፡ 9-19)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶች “ እንደ ኃዘን ድምጽ “ ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ሴቲቱ ብቻ አትቃጠልም ነገር ግን እርሷን ይደግፏት የነበሩና በኃማኖታዊ እና በኢኮኖሚያዊ ስርዓቷ ላይም የተሳተፉ የምድር ነገስታቶችም አይተርፉም (ቁጥር 9) ፡፡ ባቢሎን በአንድ ቀን ትወድቃለች (ዳን 5፡ 30-31) ፡፡ ማክአርቱር ለሀዘን ወይም ለለቅሶ ከተመሳሳይ የግሪክ ቃል እንደ መጣ “ በክርስቶስ ተመልሶ መምጣት ላይ የማያምነዉ አለም ተስፋ መቁረጥን የሚገልጽ “ ማለት እንደ ሆነ ያመለክታል ፡፡ ነገስታቶች ያዝናሉ ምክንያቱም የሚፈልጉትን ማግኘት ስለማይችሉ - የነበራቸዉን ሁሉም ነገር እና የሚፈልጉት ነገር ያልፋል ፡፡ በፍርኃት ነገስታቶች የሚችለትን ሁሉ ከሴቲቱ ፍርድ ርቀዉ ይቆማሉ (ቁጥር 10) ፡፡
ነጋዴዎች የሚሸጡትን የሚገዛቸዉ ስለሌለ ያዝናሉ (ቁጥር 11-13) ፤ ነጋዴዎቹ ቢዝነሳቸዉን ያጣሉ ፡፡ ማክአርቱር “ በሰለጠነዉ አለም ሕዝቦች ለረጅም ጊዜ የታገደዉ የባሪያ ንግድ በሐሰተኛዉ ክርስቶስ የተዋረደ የንግድ ስርዓት ላይ እንደ ገና እንደሚከሰት “ ያመለክታል ፡፡ ይፈልጓቸዉ ለእነርሱም ዋጋ የነበራቸው ነገሮች ከእነርሱ እንደሚለይ እና መልሶም እንደ ገና አያገኙትም (ቁጥር 14) ፡፡ ነጋዴዎቹ በፍርኃት እንደሚቆሙና በአንድ ሰዓት ዉስጥ ሁሉም ነገር ስለሚጠፋ ያዝናሉ (ቁጥር 15-17) ፡፡
የመርከብ መሪዎችም፣ መርከበኞች እና የመርከብ ተሳፋሪዎችም በራስ ወዳድነት በባህሩ አጠገብ ከዚህ በኋላ ስለማይኖሩ ከሩቅ አዘኑ (ቁጥር 17-19) ፡፡ በቁጥር 18 ጥያቄዉ ያጡትን ተስፋቸዉን በማወጅ ላይ ይደገፋል ፤ ባቢሎን መዉደቅ ከቻለች ለእነርሱ ሌላ እኩል የሚሆን አማራጭ አልነበረም ፡፡ የምታዉቁት እና ዋጋ ያለዉ ነገር በጠፋ ጊዜ ወዴት ትመለሳላችሁ ? የባህሩ ሰዎች እንደ መልሳቸዉ ባቢሎንን ብቻ ማየት ይችላሉ ፡፡ በተስፋ ማጣት ዉስጥ በራሳቸዉ ላይ ትቢያን በመነስነስ ስለማጣታቸዉ ማዘናቸዉን ቀጠሉ ፡፡ በተስፋ ማጣታቸዉ ወደ ጌታ/እግዚአብሔር ብቻ የመጮኽ ፍቃደኝነት ነበራቸው (ኢያ 7፡ 6, 1ሳሙ 4፡ 12, ኢዮ 2፡ 12) ፡፡
ራዕይ (18፡ 20-24)፡ ዋይርስቤ እነዚህን የመጨረሻ ጥቅሶች “ የማክበር/የደስታ ድምጽ “ በማለት ያጠቃልላቸዋል፡፡ በቁጥር 20 የእግዚአብሔር ሰዎች እንዲደሰቱና እንዲያከብሩ ተነገራቸዉ ምክንያቱም እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ፍርድን ስላደረገ ፡፡ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ የተደረጉትን ሁሉንም የሰይጣን እና የሐሰተኛዉ ክርስቶስ ስራዎችን ተበቀለ ፡፡ ከዚያም አንድ ብርቱ መለዓክ እንዴት ባቢሎን ወደታች የተወረወረች እንደምትሆንና እንደምትጠፋ ለማሳየት አንድ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይን ወደ ባህሩ ዉስጥ ወረወረው (ቁጥር 21) ፡፡ የባቢሎን ሕዝቦች በፍጹም አይደሰቱም፣ በፍጹም አይሰሩም በፍጹምም እንደ ገና አይነግዱም (ቁጥር 22) ፡፡ በባቢሎን ምንም ሕይወት አይቀጥልም - ትዳር/ጋብቻ አይቀጥልም፣ እደገና ለእነርሱ ምንም ብርኃን አልታዬም (ቁጥር 23) ፡፡
መደምደሚያ
ኮንስታብል ለምን ባቢሎበን እንዲህ አይነት ጥፋትን እንደሚደርስባት መለዓኩ ሰዎስት ምክንያቶችን እንደ ሰጠ ያመለክታል፡ “ ከባቢሎን ተፅዕኖ የተነሳ ሰው አለምን እንደ ታላቅ በማድረግ ራሳቸዉን ስላበለጸጉ እና በትዕቢት ከፍ ከፍ ስላደረጉ (ኢሳ 23፡ 8) ፤ ሁለተኛው ከመጀመሪያዉ ምክንያት የተነሳ ባቢሎን ሕዝቦችን ሁሉ ሳበች/አማለለች/ተዳራች “ ፤ ሰዎስተኛው ባቢሎን የእግዚአብሔርን ቅዱሳን ተመለከተች /ገደለች ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Revelation, p. 283; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/revelation.pdf.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians–Revelation, v. 11 (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 614.
Wiersbe, p. 614.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 2029.
Wiersbe, p. 614.
Wiersbe, p. 615..
MacArthur, p. 2029.
Wiersbe, p. 615.
MacArthur, p. 2029.
MacArthur, p. 2030.
MacArthur, p. 1982.
Wiersbe, p. 616.
Constable, p. 293.
Constable, p. 293.
ጥያቄዎች
-
በራዕ (18፡ 2) የወደቀችዉ ባቢሎን “ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች “ በሚል ጊዜ ምን ማለቱ እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ኢሳ13፡ 21)
-
ራዕ (18፡ 4) በምታነቡ ጊዜ ሰዶምን ታስባላችሁ ? በመጽኃፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከሰዎች እና ከስፍራ የተለዩ እንዲሆኑ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ? (ዘፍ 19፡ 12-13, 17, ኢሳ 48፡ 20, 52፡ 11, ኤር 51፡ 6, 45, 2ቆሮ 6፡ 17)
-
በመጽሃፍ ላይ መጀሪያ ስለ ባቢሎን የምንሰማዉ የት ላይ ነው ? ዘፍ (11፡ 4) አንብቡ ፤ የሰዎቹ መነሳሳት ምን ነበር ? ራዕ (18፡ 5) አንብቡ ፤ እነዚህ ሁለት ጥቅሶች እንዴት ይገናኛሉ ?
-
ራዕ (18፡ 7) እና ኢሳ (47፡ 7-8) ባቢሎን መበለት ሳትሆን ንግስት እንደ ሆነች እንደጠራች ፅፈዋል ፤ በእርግጥ በኢሳይያስ 47 ሁለት ጊዜ ባቢሎን በልቧ “ እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም “ (ኢሳ 47፡ 8, 10) እንዳለች ተጠቅሳለች ፤ በኢሳ (46፡ 9) ከጌታ ቃል ጋር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተመሳሳይ ነው ፡፡ ባቢሎን ለምን ከተልባ እግር የተሰራ በፍታ፣ ሐምራዊ እና ቀይ እንቁ እና በወርቅ እና በከበረ ድንጋይ ያጌጡ ዕንቁዎችን እንደለበሰች ተደርጋ ስለመገለፃ ምን ታስባላችሁ ? (ዘጸዓት 39, 40፣ ራዕ 17፡ 4, 18፡ 16, 21፡ 18-21)
-
በታላቋ ባቢሎን መዉደቅ እና በአዲሱ ሰማይ እና ምድር መካከል ሆን ተብሎ የተሰራ ልዮነት አለ ( ለቅሶ እና ሐዘን፡ ራዕ 18፡ 15, 19, 21፡ 4፣ መብራት ወይም ብርኃን፡ ራዕ 18፡ 23, 21፡ 23፣ የምድር ነገስታቶች፡ ራዕ 18፡ 3, 21፡ 24፣ ሕዝቦች መስተጋብር፡ ራዕ 18፡ 3, 21፡ 25-26፣ አለመቀደስ ከመቀደስ ጋር፡ ራዕ 18፡ 2-3, 21፡ 27) ? እዚህ ጋር ያልተዘረዘሩ ሌላ መዘርዘር ትችላላችሁ ?
-
ራዕ (18፡ 22) በተለዬ ከዚህ በኋላ በባቢሎን ምን ሙዚቀኛ እና መሳሪያ እንደማይሰማ መዝግቧል ፤ ይህ ከዳን 3፡ 5, 7 እና 15 ጋር ግንኙነት አለዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? በዳን (3፡ 15) ለምስሉ ያለመስገድ ዉጤት ወደ ሚነድደዉ እሳት ዉስጥ መጣል ነበር ፡፡ ራዕ (18፡ 8 እና 18) አንብቡ ፤ የባቢሎን መጥፋት/መፈራረስ መለኮታዊ ፍትሕ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በራዕይ 18 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 18:2
“He cried in a mighty voice: It has fallen, Babylon the Great has fallen! She has become a dwelling for demons, a haunt for every unclean spirit, a haunt for every unclean bird, and a haunt for every unclean and despicable beast.”
የዮሐንስ ራዕይ ሲቀጥል ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን ለዘላለም ወደቀች፡፡ የፓለቲካ መሪዎች ወደቁ፣ ነጋዴዎች ወደቁ በተጨማሪም ንግድን በባህር ላይ የሚከውኑት ሁሉ ወደቁ፡፡ ሁሉም ጠፍተው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ገንብተውት የነበረውን ደግሞም ተስፋ ጥለውበት የነበረውን ሁሉ ጠራርጎ አጠፋ፡፡ ይህ ሌሎች መንግስታትንም አስደነገጠ፤ ህዝቦችም ሁሉ አዝነው አለቀሱ፡፡ ትዕቢትና መዳራት ባቢሎንን ሞልቷት ነበር፡፡ እናም አሁን በመጨረሻ ይህን የመጨረሻ ፍርድ ተቀበሉ፡፡
በማንና በምንድን ነው ተስፋችሁን የምትጥሉት ? የአክስዮን ገበያው ቀንሶ ቢሆን ኖሮ፣ መኪናችሁ ተጋጭቶ ቢሆን ኖሮ፣ በቢሮ ውስጥ ካላችሁ የመሪነት ቦታ ስልጣን ወርዳችሁ ቢሆን ኖሮ ወይም ደግሞ በየቀኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት ቢሳናችሁ ኖሮ ይህ ነገር እንድታዝኑ እና እንድታለቅሱ ያደርጋችኋልን? ወይስ ተስፋችሁ በእርሱ ላይ ስለሆነ በጌታ ብርቱ ጽኑ ሆናችሁ ትቀጥላላችሁ? ህይወት ሲከብድ ሲሞሰቋቆል እናንተ ለዚህ የምትሰጡት ምላሽ በግልጽ ተስፋችሁን በምንድን ወይም በማን ላይ እንደጣላችሁ ያሳያል፡፡ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ ለበጎ እንደሚያደርገው በተናገረው በዚህ ተስፋ እረፉ፡፡ እርሱ እቅድ አለው ደግሞም እርሱ በምድር ሁሉ ላይ ገዥ ነው፡፡ እርሱ ሸክማችሁን ይሸከማል፡፡ የሚያስፈልጋችሁ የእርሱን እውነት ማመን ብቻ አይደለም ይልቁንም ይህ ህይወት ከሚሰጣችሁ ጊዜያዊ ደስታ ይልቅ እግዚአብሔር እንደሚበልጥ ያላችሁን እምነት በተግባር መኖርም እንጂ፡፡ ተስፋችሁን በእርሱ ላይ ስታደርጉ፣ ህይወታችሁ የእርሱን ታማኝነት ያንጻባርቅ፡፡
“በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፡፡ “
- ራዕይ 18፡2
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ቆሮንቶስ 4:16–18 — “ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።”
ራዕይ 18:16–17a — “በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና!”
ራዕይ 18:23b–24 — “ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፥ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና። በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።