Feasts Of Judgements
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ራዕይ 19 የታወቀ እና በራዕይ ዉስጥ ብዙ ጊዜ የሚጠና ምዕራፍ ነው ፡፡ ይህ ምዕራፍ በነጭ ፈረስ ላይ የኢየሱስን ተመልሶ መምጣት እና የአርማጌድዮን ጦርነትን መልክ ይይዛል ፡፡ ማህተሞቹ፣ መለከቶች እና ጽዋዎቹ ሁሉ ስለ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ እና ስለ ባቢሎን የተመለከትነዉ ሁሉም ነገር ወደዚህ ምሕራፍ ይመራል ፡፡ ራዕይ 19 ከታላቁ መከራ ወደ ሺዉ አመት መንግስት እንደ ድልድይ ያገለግላል - ከሰባት የመከራ አመታት ወደ 1,000 የኢየሱስ አገዛዝ አመት ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (19፡ 1-6)፡ “ ከዚህ በኋላ “ የባቢሎንን ዉድቀት ያመለክታል (ቁጥር 1) ፡፡ የከተማዋ መዉደቅ በምዕራፉ ዉስጥ የመጀመሪያዎቹን አራት ጊዜ እንዲናገሩ በሰማይ ብዙ ድምጽን አከማቸው ፤ ብዙዉን ድምጽ ማን ያደርገዋል?(ቁጥር 1) ፡፡ ከራዕይ 7 ቅዱሳን ወይም መለዓክት ወይም የሁለቱም ድብልቅ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህ ምስጋና ማክአርቱር አምስት ምክንያቶችን አጉልቶ አሳይቷል፡ “ 1) ሕዝቡን ከጠላቶቻቸዉ ስለ እግዚአብሔር ማዳን (ቁጥር 1)፣ 2) የእግዚአብሔር ፍርድ ፍትኂ ስለሆነ (ቁጥር 2)፣ 3) የሰዉን አመጽ የእግዚአብሔር በቋሚነት ስለ ማጥፋቱ/መስበሩ (ቁጥር 3)፣ 4) ስለ እግዚአብሔር ሉዓላዊነት (ቁጥር 6) እና 5) ከሕዝቡ ጋር ስለ እግዚአብሔር ሰርግ/መተሳሰር (ቁጥር 7) “ ፡፡
በቁጥር 4 24 ሽማግሌዎች የእስራኤል ቤተ ክርስቲያን ወይም የ12 ሐዋሪያት እና የ12 ነገዶች መወከያ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ “ አራቱ ሕይዋን ፍጥረቶች “ አንበሳ፣ ጥጃ፣ ንስር እና የሰዉ ፊት ያለዉ እንስሳ ናቸው ፡፡
ራዕይ (19፡ 7-10)፡ በዚህን ጊዜ በመንግስቱ ላይ ለመቀመጥ ስለሚደርስ ብዙ ሕዝብ አመሰገነው ፡፡ አዲስ መንግስት ይፈጠራል ኢየሱስም ይገዛል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ መንግስት “ ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን ቲኦክራሲይ እንደሆነ - ሁሉን ቻኝ የሆነዉ እግዚአብሔር አምላክ በጽድቅ ስለሚገዛ በእግዚአብሔር የሚተዳደር መንግስት እንደ ሆነ (ኢሳይያስ 11) “ ያመለክታል ፡፡
ብዙ ሕዝብ እግዚአብሔርን አመሰገኑ ምክንያቱም “ የበጉ ሰርግ ስለደረሰ እና ሚስቱም ራሷን ስላዘጋጀች “ (ቁጥር 7)፡፡ በብሉይ ኪዳን እስራኤል እንደ እግዚአብሔር ሚስት ተገልፃለች ፤ በአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ እንደ ሆነች ተገልፃለች ፡፡ ኤፌ (5፡ 23 እና 32)፡ “ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና….. ይህ ምስጢር ታላቅ ነዉና እኔ ግን ይህ ስለ ክርስቶስ እና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ “ ፡፡ በቁጥር 7 ኢየሱስ “ እንደ በግ “ የተገለፀ/የተመላከተ ነው ፡፡
2ቆሮ (7፡ 1)፡ “ እንግዲህ ወዳጆቼ ሆይ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን በእግዚአብሔር ፍርኃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ስጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ “ ይላል ፡፡ ምናልባትም እስካሁን ክርስቶስ ያልመጣበት አንዱ ምክንያት ሙሽራዉ ቤተ ክርስቲያን ራሷን ስላላዘጋጀች ይሆናል ፡፡ ይሁዳ 21፡ “ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደዉን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ “ ይላል ፡፡ ማክአርቱር በቁጥር 10 ላይ የተገለፀው የጋብቻ ድግስ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ብዙዉ ሕዝብ እግዚአብሔርን ባመሰገነበት አምስት ምክንያቶች የምናከብርበትን የጋብቻዉን ፍፃሜ በዓልን እንደሚወክል ይፅፋል ፡፡
በበጉ የጋብቻ ድግስ ላይ በተጋበዙት ሁሉ ላይ በረከት የታወጀ/የተነገረ ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ ኢየሱስ ሙሽራው ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሙሽሪት ከሆነች ወደ ድግሱ ላይ የተጋበዙ የሚሆኑት እነማን ናቸው ? በግልጽ አንዳንድ ቡድኖች እዚህ ጋር ተገልፀዋል ግን እነማን ናቸው ? ከበዓለ ሀምሳ ቀን በፊት በእምነት በኩል በፀጋዉ የዳኑ እና በሺዉ አመት ጊዜ ከክርስቶስ ጋር የሚገዙ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ወይም የመከራዉ ጊዜ ቅዱሳን ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡
ይህንን ካዬ በኋላ ዮሐንስ እነዚህን ነገሮች የገለጠለትን/ያሳየዉን መለዓክ “ ለማምለክ ዕግሩ ስር ተደፋ “ ፤ መለዓኩም ዮሐንስን በማስቆም “ ለእግዚአብሔር ስገድ ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነዉና በማለት “ አሳሰበው (ቁጥር 10) ፡፡ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ትንቢት ጭብጥ ነበር ፤ ይህ ሁሉ በአንድ ላይ የያዘ ማሰሪያ/ገመድ ነበር ፡፡
ራዕይ (19፡ 11-16)፡ ዮሐንስ “ እንደ ታማኝ እና እዉነተኛ “ ተጠቅሶ የነበረዉን ኢየሱስን በነጭ/በአምባላይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አየው ፡፡ አሁን ኢየሱስ “ ፍርድናን ጦርነትን በጽድቅ ያደርጋል “ (ቁጥር 11) ፤ በዚህ ማሳያ ኢየሱስ “ ከእርሱም በቀር አንድ ስንኳ የማያዉቀው የተፃፈ ስም አለው “ (ቁጥር 12) በተመሳሳይ ራዕይ (3፡ 12)፡ “ ድል የነሳው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም የአምላኬን ስማና የአምላኬን ከተማ ሰም ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደዉን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ “ ፡፡ ልብሱ በደም የተረጨ ሲሆን “ “ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሏል “ (ቁጥር 13) ፡፡ በልብሱ ላይ ያለዉ ደም ከአርማጌድዮን ዉጊያ/ጦርነት የሆነ ደም አይደለም ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ደሙ ከተበተዠበት ሞቱ ወይም ከእግዚአብሔር የቁጣ መጥመቂያ ማረጋገጫ ወይም ከሁለቱም ሊሆን እንደ ሚችል ያመለክታል ፡፡
“ በሰማይ የነበሩት ሰራዊቶች “ ኢየሱስን የተከተሉ (ቁጥር 14) ቤተ ክርስቲያን፣ የብሉይ ኪዳን አማኞች፣ የመከራዉ ቅዱሳኖች እንዲሁም መለዓክቶች ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ ማክአርቱር የሰማይ ሰራዊቶቹን “ በጦርነቱ ላይ ኢየሱስን ለማገዝ እንደማይመለሱ ነገር ግን ጠላቶቹን ካሸነፈ በኋላ ከእርሱ ጋር ለመግዛት እንደሚመለሱ “ ተመልክቷል/አስተዉሏል ፡፡ ከአፉ የሚወጣዉ የተሳለዉ ሰይፍ የኢየሱስ ኃይል ጠላቶቹን እንደሚገድላቸዉ ያሳያል ፡፡
ራዕይ (19፡ 17-21)፡ የአርማጌድዮን ጦርነት እዚህ ጋር ይሆናል ፤ አንድ መለዓክ አዕዋፋትን/ወፎችን “ ወደ እግዚአብሔር ታላቅ የራት ግባዣ “ እንዲሰበሰቡ በመጥራት ይጀምራል ፡፡ ይህ ቀደም ብሎ በራዕይ 19 ተገልፆ እንደ ነበረው የበጉ የሰርግ/የጋብቻ ድግስ አይደለም ፤ ይልቁንም ወፎች “ የነገስታትን ስጋና የሻለቆችን ስጋ የብርቱዎችንም ስጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ስጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችን ሁሉ ስጋ “ (ቁጥር 18) ሲበሉ የሚታዩበት የሚመጣዉ የእግዚአብሔር የመጨረሻው ፍርድ ነው ፡፡
በቁጥር 19 አዉሬዉ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ሲሆን የምድር ነገስታቶች ደግሞ አስሩ ሀገራት ናቸው ፡፡ ከኢየሱስ እና ከሰራዊቱ ጋር ለመዋጋት በአንድ ላይ ይሰበሰባሉ ፤ በጦርነቱ ጊዜ አዉሬዉ እና ሐሰተኛዉ ነቢይ ወደ እስራት በመወሰድ “ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ “ (ቁጥር 20) ፡፡ ራዕይ (20፡ 10)፡ “ ያሳታቸዉም ዲያብሎስ አዉሬዉና ሐሰተኛዉ ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ “ ይላል ፡፡ ዳን (7፡ 11)፡ “ የዚያን ጊዜም ቀንዱ ይናገረው ከነበረው ከታላቁ ቃል ድምጽ የተነሳ አየሁ ፤ አዉሬይቱም እስክትገደል አካልዋም እስኪጠፋ ድረስ በእሳትም ለመቃጠል እስክትሰጥ ድረስ አየሁ “ በማለት ትንቢት ተናግሯል ፡፡
ዘላለማዊ ቅጣት ሰይጣንን፣ አዉሬዉን እና ሐሰተኛዉን ነቢይ ይጠብቃቸዋል ፡፡ የአዉሬዉም ሰራዊት “ በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ “ (ቁጥር 21) ፡፡
መደምደሚያ
ኢየሱስ በድል አድራጊነት እና በእርሱ ላይ የቆሙትን ሁሉ በማሸነፍ ይገዛል የሰማይም ሰራዊት ከእርሱ ጋር ይጣመራሉ ፡፡ ስለ ሕዝቡ ሁሉንም ጦርነት ያደርጋል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 2030.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1761.
MacArthur, p. 2031.
MacArthur, p. 2031.
Nelson’s Commentary, p. 1762.
MacArthur, p. 2032.
MacArthur, p. 1023.
ጥያቄዎች
-
24 ሽማግሌዎች በራዕይ ዉስጥ በተለያዩ ብዙ ስፍራዎች ላይ ተጠቅሰዋል (ራዕ 4፡ 4, 5፡ 8, 11፡ 16, 19፡ 4) ፤ 24 ሽማግሌዎች ማን ሊሆኑ እንደሚችሉ ታስባላችሁ ? መልሳችሁን በምን መጽኃፍ ተጠቅማችሁ አስደገፋችሁ ?
-
የብዙ ዉኃዎች ድምጽ ተጠቅሷል (ራዕ 19፡ 6) ፤ በመጽኃፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ የብዙ ዉኃዎች ድምፅ ተጠቅሷል ? (ሕዝ 1፡ 24, 43፡ 2, ራዕ 1፡ 15, 14፡ 2)
-
በራዕ (19፡ 15) ተጠቅሶ የነበረዉ ሰይፍ በዕብ (4፡ 12) ተጠቅሶ ከነበረው ሰይፍ ጋር ተመሳሳይ አይነት ነበር (ራዕ 1፡ 16, 2፡ 12) ? ለምን ያን አሰባችሁ ?
-
ሕዝ (39፡ 18-20) አንብቡ ፤ ይህ ከራዕ (19፡ 17-18) እንዴት ይወዳደራል ? ሁለቱም ተመሳሳይ ክስተትን ያመለክታሉ ? ጌታ በአዕዋፍ የተበሉ በመሆን እንደ ባሪያዎች በተመሳሳይ ደረጃ እንዲጨርሱ ነገስታቶችን ያልተሸሉ እንዲሆኑ ጌታ አደረጋቸው ? ለምን ወይስ ለምን አላደረጋቸዉም ?
-
በራዕይ 19 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 19:20
“But the beast was taken prisoner, and along with him the false prophet, who had performed the signs in his presence. He deceived those who accepted the mark of the beast and those who worshiped his image with these signs. Both of them were thrown alive into the lake of fire that burns with sulfur.”
ባቢሎን ፈጽማ ከጠፋች በኋላ እጅግ በጣም ብዙ ድምጽ ሃሌ ሉያ ብለው ዘመሩ ደግሞም እግዚአብሔርን ስለ ማዳኑ፣ ፍርዱና ሉዓላዊነቱ አመሰገኑ፡፡ ከዚያም በዮሐንስ ራዕይ ውስጥ ሰማይ ተከፈተ፣ ፈረስ የጋለበም ስሙም የታመነና እውነት የተባለ፣ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ በአምባላይ ፈረስ ሆኖ ተገለጠ፡፡ የአማኞችም ጦር ተከተለው፤ እርሱም ውጊያውን ከአውሬውና ከሐሰተኛው ነቢይ ጋር ተዋጋ፡፡ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይም በተያዙ ጊዜ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ፡፡ ከአፉም በሚወጣ ሰይፍ የአውሬውን ጠቅላላ ጦር ገደለ፡፡
ኢየሱስ በአውሬው፣ በሐሰተኛው ነቢይና እነርሱን በተከተሉት ላይ የተቀዳጀው ድል እናንተም ዛሬ የራሳችሁን ውጊያ ማለትም ከስጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ስትዋጉ ብርታት ይሁናችሁ፡፡ በእኔ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ጠላትንም እቀጣ ዘንድ ተመልሼ በምመጣው በእኔ፣ ድልን ትቀዳጃላችሁ፡፡ ነገር ግን እስከዚያው የመንፈስን ሰይፍ የእምነትንም ጋሻ ያዙ፡፡ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ የመዳንንም ራስ ቁር አድርጋችሁ ተራመዱ ፡፡ በሰላም እግሮች ወገባችሁንም በእውነት ታጥቃችሁ፥ ያለማቋረጥ ተራመዱ፡፡ ጸንታችሁ ቁሙ፡፡ ንቁ፡፡ ሳታቋርጡ ጸልዩ፡፡ የኢየሱስን ስም ስትጠሩ፣ ጠላት ይሸሻል! ሃሌ ሉያ! ደግማችሁ በሉት፣ ሃሌ ሉያ፡፡ ማዳን፣ ክብርና ኃይል የአምላካችን ነው!
“አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።”
- ራዕይ 19፡20
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ 15:57 — “ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።”
ኤፌሶን 6:14–18 — “እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፡፡”
ራዕይ 19:1 — “ከዚህ በኋላ በሰማይ፦ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።”
ራዕይ 19:11–13 — “ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም።ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።