Revelation Revelation

The Millennial Reign Of Christ

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 728 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ራዕይ 19 ቤቱን ለማንፃት በነጭ/በአምባላይ ፈረስ በመቀመጥ ተመልሶ እንደሚመጣ መዝግቧል ፡፡ አሕዛቦች/ሕዝቦች ይጠፋሉ፣ አዉሬዉ እና ሐሰተኛዉ ነቢይ ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ ፡፡ እያጠናን ያለነዉ ሁሉም ነገር ኤደን ገነት ወደፊት ስለሚመጣ ነው (ዘፍጥረት 3) ፡፡ ለዘፍጥረት መጽኃፍ የተጠቀምነዉ ቃል ዘር የሚል ነበር ለራዕይ መጽኃፍ የተጠቀምነዉ ቃል ደግሞ እኔ የሚል ነው ፡፡ ከመጀመሪያዉ ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ክርስቶስ ነበር አሁንም አለ ፡፡ ምዕራፍ 20 ስንጀምር ቀደሞ/ቀደም ብሎ የአርማጌድዮን ጦርነት ተጀምሯል ፤ ምዕራፍ 20 የመታደስ ሂደትን ማሳየት ይጀምራል ፡፡

ትምህርት

ራዕይ (20፡ 1-2)፡ የጥልቁ ጉድጓድ መክፈቻን የያዘዉ መለዓክ ሰይጣንን በመያዝ ለ1,000 አመታት አሰረው ፡፡ በተጨማሪም መለዓኩም ሰንሰለትን ተሸክሞ/ይዞ ነበር ፡፡ እዚህ ጋር የሆነ ፈተና እንደ ነበር ማመን አለባችሁ ለ1,000 አመታት ሰይጣን በፍቃደኝነት ወደ ሰንሰለቱ/ማሰሪያው ስለማይገባ/ስለማይሄድ ፤ ይህ ከአርማጌድዮን ጦርነት በኋላ ሲሆን ኢየሱስም በምድር ላይ ይሆናል ፡፡ እዚህ ላይ ታላቅ የሆነ የስነ መለኮታዊ ክርክር አለ ፤ ሰዎች ሰይጣን የምር ለ1,000 አመታት የታሰረ እንደሚሆን ወይም ምሳሌያዊ እንደ ነበር መወያየትን ይወዳሉ ፡፡ እኔ ለ1,000 አመታት የተሳረ እንደነበር አምናለሁ ፡፡

ራዕይ (20፡ 3)፡ አዉሬዉ (ሐሰተኛዉ ክርስቶስ) እና ሐሰተኛዉ ነቢይ በታላቁ ጉድጓድ ወይም በእሳት ባህር ዉስጥ ቀድመዉ ተጥለው እንደ ነበሩ እናስታዉሳለን ፤ አሁን ሰይጣን ይቀላቀላቸዋል ፡፡ ሰዎች ይህን ጊዜ የሺዉ አመት ብለዉ ይጠሩታል ፤ ማክአርቱር በዚህ 1,000 አመት የሰዎስት ዋና ት/ቤቶችን አስተምሮ ያሳያል፡

  1. “ ቅድመ ሚሊኒየም አሳቢዎች/አማኞች ይህን በቀጥታ እንደ 1,000 አመት ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ የሆነዉን የብሉይ ኪዳንን ትንቢት ለመፈጸም በምድር ላይ የሚገዛበት እንደሆነ ይተረጉሙታል (2ሳሙ 7፡ 12-16, መዝሙር 2, ኢሳ 11፡ 6-12, 24፡ 23, ሆሴ 3፡ 4, 5፣ ኢዩ 3፡ 9-21, አሞ 9፡ 8-15, ሚክ 4፡ 1-8, ሶፎ 3፡ 14-20, ዘካ 14፡ 1-11, ማቴ 24፡ 29-31, 36-44) “ ፡፡
  2. “ ድህረ ሚሊኒየም አሳቢዎች/አማኞች ለ 1,000 አመት ጊዜን እንደ የወርቃማ የጽድቅ እና የመንፈሳዊነት ብልጽግና እንደ ምልክት በመሆን እንደሚያመለክት ይረዳሉ ፤ በአሁኑ ቤተ ክርስቲያን ዘመንበወንጌል መሰራጨት የሚደረስ እና በክርስቶስ መመለስ ወደ ፍፃሜ የሚመጣ እንደሆነ ያስባሉ ፤ በዚህ አመለካከት መሰረት በምድር ላይ የክርስቶስን አገዛዝ በቀዳሚነት በቤተ ክርስቲያን በአማኞች ልብ መንፈሳዊ አገዛዙን ይገልፃል “ ፡፡
  3. “ የሚሊኒየሙ አሳቢዎች/አማኞች 1,000 አመትን ዝም ብሎ የረጅም ዘመን ጊዜ መወከያ እንደሆነ ይረዳሉ ፤ ይህ አመለካከት የሺዉን አመት የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች አሁን በመንፈሳዊነት በቤተ ክርስቲያን (በምድር ላይ ወይም በሰማይ ላይ) የተፈፀመ እንደሚሆን ወይም ለዘላለማዊ መንግስት እንደ ማሳያ ይተረጉሙታል “ ፡፡

በፍጹም አንድም አስተያየት አልወሰድኩም ነገር ግን የሚመጣዉን ነገር መቼ እንደምታዩት አስቸጋሪ ነው ፡፡ ዮሐንስ በመጨረሻም ሰይጣን የተለቀቀ እንደሚሆን እና ከዚያም እንደሚታሰር ፅፏል ፡፡ በቀጥታ 1,000 አመት ካልወሰዳችሁ ራዕይ (20-22) ለመተርጎም አስቸጋሪ እንደሚያደርገው አስባለሁ ፡፡ በቀጥታ 1,000 የሚያመለክተዉን ሀሳብ እንጠቀማለን ፤ ከእነዚህ አመታት በኋላ ሰይጣን ይፈታል ፡፡ ማክአርቱር “ ሰይጣን ስለሚለቀቅ እግዚአብሔር አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር ከመመስረቱ በፊት የኃጢዓትን ዘላቂ መጨረሻ ማድረግ እንደሚችል “ ይናገራል ፡፡ ሰይጣን ክርስቶስን ካልተቀበሉት ጋር የመጨረሻን አቋም በማድረግ የተጨፈለቁ ይሆናሉ ፡፡

ራዕይ (20፡ 4)፡ የአዉሬዉን ምልክት ባለመቀበላቸው ተሰዉተዉ የነበሩት በመነሳት ከክርስቶስ ጋር ይገዛሉ ለእነዚህ 1,000 አመታቶችም እንዲፈርዱ ስልጣን የተሰጣቸዉ ይሆናል ፡፡ ዮሐንስ አካላዉ ትንሳኤን አዬ ፡፡ ቶም ኮንስታብል እግዚአብሔር ያስነሳበትን ወይም የሚያስነሳባቸዉን ጊዜያት አስቀምጧቸዋል፡

መጀመሪያ ያንቀላፉት በኩራት የሆነዉን ኢየሱስ ክርስቶስን አስነሳው (1ቆሮ 15፡ 23) ፡፡

ሁለተኛ ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ በአጭሩ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ አንዳንድ ቅዱሳንን አስነሳ (ማቴ 27፡ 52-53) ፡፡

ሰዎስተኛ በምጽዓቱ ጊዜ ክርስቲያኖችን ያስነሳል (1ተሰ 4፡ 13-18) ፡፡

አራተኛ በታላቁ መከራ ጊዜ ሁለቱን ምስክሮች ያስነሳቸዋል (ራዕ 11፡ 3, 11) ፡፡

አምስተኛ በሺዉ አመት መጀመሪያ ላይ የመከራዉ ሰመዓቶችን ያስነሳቸዋል (ራዕ 20፡ 4-5) ፡፡

ስድስተኛ በተመሳሳይ ጊዜ የብሉይ ኪዳንን ቅዱሳን ያስነሳቸዋል (ኢሳ 26፡ 19-21, ሕዝ 37፡ 12-14, ዳን 12፡ 2-4) ፡፡

ሰባተኛበሺዉ አመት ጊዜ የሚሞቱትን ቅዱሳን በግልጽ ያስነሳል (ራዕይ 12-13) ፡፡

ይህ የእግዚአብሔር ሂደት የሚሆን ይመስላል ፡፡ ሰዎችን መልሶ ወደ ሕይወት የማምጣት ችግር የለበትም ፤ በዚህ አገላለጽ የመከራዉ ሰማዕቶች ተመልሰዉ ወደ ሕይወት ተመልሰዉ ሲመጡ እናያለን ፡፡ እነዚህን ጥቅሶች በጽናት ስትተረጉሙ 1,000 አመታት እንደ መወከያ/ምሳሌ የምትናገሩት/የምትሉት ከሆነ በቁጥር 4 ምን ታደርጋላችሁ ?

ራዕይ (20፡ 5)፡ ብዙ ምሁራኖች ከ1,000 አመት በኋላ የሚነሱት የማያምኑት አካል እንደ ሆነ ያመለክታሉ ፡፡ እነዚህ አላማኞች እስካሁን አልተፈረደባቸውም ፡፡

ራዕይ (20፡ 6)፡ የመጀመሪያዉ ትንሳኤ የህይወት ትንሳኤ ነው ፡፡ ማክአርቱር የህይወት ትንሳኤ “ የጻድቃን ትንሳኤ እንደ ሆነ (ሉቃ 14፡ 14)፣ በእርሱ መምጣት የክርስቶስ የሆኑ ትንሳኤ እንደ ሆነ (1ቆሮ 15፡ 23) እና የተሻለ ትንሳኤ እንደ ሆነ (ዕብ 11፡ 35) ፤ የተቤዠዉን የቤተ ክርስቲያንን ዘመን፣ ብሉይ ኪዳንን እና የመከራዉን ዘመን ብቻ እንደሚያካትት ፤ ከመከራው ከተረፉት አማኞች ጋር በትንሳኤ ሰዉነታቸው ወደ መንግስቲቱ እንደሚገቡ “ ፅፏል ፡፡ አማኞች ከክርስቶስ ጋር ለእነዚህ 1,000 አመታቶች ይገዛሉም ያስተዳድራሉም ፤ ሁለተኛዉ ሞት በእነርሱ ላይ ስልጣን የለዉም ፡፡ “ የመጀመሪያዉ ሞት አካላዊ ብቻ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ በእሳት ባህር ዉስጥ የመጨረሻ እና የዘላለም የሲዖል መንፈሳዊ ሞት ነው “ ፡፡ በራዕይ ዉስጥ ሰባት “ ብፁዕ/የተባረከ “ የሚል ንግግሮች አሉ ፡፡ እዚህ ጋር ዮሐንስ “ በፊተኛው ትንሳኤ ዕድል ያለዉ ብፁዕና ቅዱስ ነው ! “ በማለት ፅፏል ፡፡ በጌታ የሞቱ ወደ መንግስቱ በመግባት ዕድል የተባረኩ ናቸው ፡፡

ራዕይ (20፡ 7)፡ ከ1,000 አመታት በኋላ አሁንም ክርስቶስ በምድር ላይ ንጉስ ነው ፡፡ ክርስቶስ ሁሉም አማኞቹ ከእርሱ ጋር አሉ ነገር ግን አሁንም የማያምኑ ይኖራሉ ፤ ያ 1,000 አመት እዚህ በምድር ላይ የክብር/የመክበር ጊዜ አይደለም ፤ አሁንም ኃጢዓት ይኖራል ፡፡ ሰይጣል አንድ የመጨረሻ ተኩስ/ምት እንዲኖረዉ ይለቀቃል፤ እንደሚወድቅ እናዉቃለን ፡፡

ራዕይ (20፡ 8-9)፡ በትክክል ሁለት ጦርነቶች አሉ - የአርማጌድዮን ጦርነት እና ሰይጣን ከተለቀቀ በኋላ ያለዉ ጦርነት ፡፡ ሰይጣን “ የቅዱሳንን ሰፈር “ የሚከብብ ታላቅ ሰራዊትን ይሰበስባል ፤ አንድም እሳት ከሰማይ በመዉረድ ትበላቸዋለች (ሁሉንም ) ፡፡

ራዕይ (20፡ 10)፡ እንደ ገና እዚህ ስፍራ/ጊዜ ላይ አዉሬው እና ሐሰተኛዉ ነቢይ አሁንም በእሳት ባህር ዉስጥ መሆናችንን እናስታዉሳለን ፡፡ አሁን ሰይጣን ከእነርሱ ጋር በመጣመር ቀን እና ማታ ለዘላለም ይሰቃያሉ ፡፡ ሲዖል የለም በማለት የሚያሳስቱ አስገራሚ የመጽኃፍ ቅዱስ አስተማሪዎች አሉ ፤ ይህ እዉነት ከሆነ ለምን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞተ ? ህይወትን ለእኛ ሊሰጠን ከመስቀል ላይ የተነሳ ነበር ፡፡ ይህን የቀን እና የማታ የዘላለም ስቃይ እንዲደርስብን አይፈልግም ፡፡ “ የሚያሰቃዩ ቀን እና ሌሊቶችን “ በምትወስዱ ጊዜ የመስቀሉንም ኃይል ትወስዱታላችሁ ፤ ሰዎች መልዕክቱን ማለዘብ/ማለስለስ ይፈልጋሉ ፡፡

ራዕይ (20፡ 11-15)፡ ይህ የሰይጣን የመጨረሻው ፍርድ ይሆናል ፤ ይሆናል በግልፅም ያልቃል ፡፡ አሁን ታላቁን ነጭ ዙፋን ማየት እንጀምራለን ፤ ከ 1,000 አመት በኋላ የተነሱት የማያምኑት በምድር ላይ በነበራቸዉ ድርጊት እና ሀሳብ የተፈረደባቸዉ ይሆናሉ ፡፡ ክርስቶስን ያልተቀበሉ ሁሉም ፍርድ ይገጥማቸዋል ፤ ማንም አያመልጥም ፡፡ ከዚያን በኋላ ሞት ስፍራ የለዉም ፡፡

መደምደሚያ

አንዳንዶች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ለመለወጥ ሲሞከር ስለ ሲዖል አይሰበክም ይላሉ ፡፡ እኔ ግን አድርጉት እላለሁ ! ኢየሱስ ለማቅረብ ብዙ አለው ፡፡ ሲዖል እዉነት/አለ ነው ፡፡ ራዕይ ወደ እዉነት፣ ወደ ፍቅር እና ወደ ርህራሄ/ቸርነት ይወስደናል ፡፡ ስማችሁ በህይወት መጽሃፍ ዉስጥ ካልተፃፈ አትገቡም ፤ ማንም ያንን አይቋቋምም ፤ ክርስቶስን ለማጋራት ይህንን እንደ ማነሳሻነት መጠቀም እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ ፍርድ በማዕዘናቱ ዙሪያ ነው ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 2034.

  2. MacArthur, p. 2034.

  3. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Revelation, p. 324; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/revelation.pdf.

  4. MacArthur, p. 2035.

  5. MacArthur, p. 2035.

ጥያቄዎች

  1. በራዕ (20፡ 1) የተጠቀሰዉ ጥልቁ ጉድጓድ በራዕ (9፡ 1) ካለዉ ጉድጓድ ጋር ይመሳሰላል ? ለምን ወይስ ለምን አይመሳሰልም ?
  2. ጥቂት ደቂቃ ዉሰዱና በመካከላችን ያለዉ ክፉ ሁሉ በእነዚህ 1,000 አመታት በታሰረ ጊዜ አለም ከሰይጣን እና ከክፋቱ ዉጪ ምን እንደምትመስል አስቡ ፤ ምን እንደምትመስል ምን አያችሁ ?
  3. ራዕ (20፡ 4-6) ስለ ተነሱ ሙታኖች ይናገራል ፤ ሁለተኛዉ ሞት ምንድን ነው፣ ለምንስ ከክርስቶስ ጋር ለመግዛት ወደ ሕይወት ተነስተዉ በነበሩት ላይ ለምን ኃይል የለዉም ? (ራዕ 2፡ 11, 20፡ 14, 21፡ 8)
  4. በራዕ (20፡ 11-15) ስለ ታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ አስቸጋሪ ወይም አስፈሪ ሀሳቦችን አግኝታችኋል ? ስማችሁ በበጉ የሕይወት መጽኃፍ ላይ ስለመሆኑ እንዴት እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ (ሮሜ 10፡ 9-10) ? የክርስቶስን የሚያድን እዉቀት ልታጋሩት የምትችሉት ሰዉ ታዉቃላችሁ ? ከእነርሱ ጋር ስትጋሩ በተመሳሳይ የሕይወት መፅኃፍ ላይ ስማቸው እንዳለ ማወቅ ይችላሉ ፡፡
  5. በራዕይ 20 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Revelation 20:15

“And anyone not found written in the book of life was thrown into the lake of fire.”

ሰይጣንም ከተሸነፈ በኋላ ከዘላለም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃይ ዘንድ ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፡፡ ዮሐንስም ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን ኢየሱስን አየ፣ መጽሐፍትም ተከፍተው ነበር፡፡ ኢየሱስን የተቀበሉትንና እርሱን አዳኝ አድርገው ካልተቀበሉትና ንስሀ ካልገቡት የሚለየው፣ የመጨረሻው ፍርድ ደረሰ፡፡ ጊዜው የፍርድ ጊዜ ነበር፡፡ ስሙም በህይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ሁሉ ከሰይጣን፣ ከክርስቶስ ተቃዋሚውና ከሐሰተኛው ነቢይ ጋር ቀንና ለሊት ከዘላለም እስከ ለዘላለም ይሰቃይ ዘንድ ወደ እሳት ባህር ተጣለ፡፡

ኢየሱስ በሰይጣን ላይ የተቀዳጀውን ድል ስትመለከቱ ከዚህ ጋር ስላልዳኑትም ሰዎች ከባዱን እውነት ታያላችሁ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ኢየሱስን ጌታና አዳኝ አድርገው ያልተቀበሉ፤ ስማቸው በህይወት መጽሐፍ ያልተጻፉት እነርሱ ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ፡፡ በመጨረሻ ሊመጣ ስላለው ነገር ዮሐንስ ያየው ራዕይ እንድትዘጋጁ ያድርጋችሁ፡፡ ዛሬ ጌታን አዳኛችሁና ለደህንነታችሁ የሚሆን ዘላለማዊ ተስፋ አድርጋችሁ ፈልጉት፡፡ የክርስቶስን ፍቅር ከሌሎች ጋር ትካፈሉ ዘንድ እርሱ በውስጣችሁ ርኅራኄን ይዝራባችሁ፡፡ እርሱ እንድትጸልዩ ደግሞም ጊዜ ሳያልቅ የምታውቋቸውንና የምትወዷቸውን ሰዎች ያድን ዘንድ እግዚአብሔርን እንድትለምኑ ያበርታችሁ፡፡ መቼም በመጨረሻ የምትወዱት ሰው እንዲህ ብሎ ሲጠይቅ መስማት አትፈልጉም ፡- “ ለምንድን ነው ስለዚህ ስለ ኢየሱስ አንድም ሰው ነግሮኝ የማያውቀው?” በሉ አሁን ሂዱና ወንጌልን ስበኩ፡፡ ምን ትጠብቃላችሁ?

“በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።”

  • ራዕይ 20፡15

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 33:4–5 — “የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። ጽድቅንና ፍርድን ይወድዳል፤ የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች።”

ፊልጵስዩስ 4:3 — “አንተም ደግሞ በሥራዬ አብረህ የተጠመድህ እውነተኛ ሆይ፥ እንድታግዛቸው እለምንሃለሁ፤ ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከቀሌምንጦስና ደግሞ ከእኔ ጋር አብረው ከሠሩት ከሌሎቹ ጋር በወንጌል ከእኔ ጋር አብረው ተጋድለዋልና።”

ራዕይ 20:10 — “ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ።”