The New Jerusalem
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የራዕይን መጽኃፍ እና ሁሉንም 66 የመጽኃፍ ቅዱስ መጽኃፎችን ለመጨረሰ ሁለት ቀን አለን ፡፡ ሪቫይቭ ት/ቤት ከምንጠብቀዉ በላይ ብዙ ነገር ያለዉ ሆኗል ! ከማናስባቸዉ ነገሮች አንዱ ቃሉ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያመጣብን ነበር ! ቡድናችን በብዙ አድጓል ፡፡ ስለ አዲስ ሰማይ እና ስለ አዲስ ምድር እናወራለን ይህም ትርጉም ይሰጣል ፡፡ ሁሉንም ነገር መሳል አልችልም ፤ ነገር ግን ወደኋላ ተመልሳችሁ ወደ ዘፍጥረት ጥናት በምትሄዱ ጊዜ ሁሉም ወደ እነዚህ የመጨረሻ ምዕራፎች ያደርሳል/ይሰራል ፤ ትክክልም እንደ ሆነ ይሰማል ፡፡ በምዕራፍ 20 መጨረሻ ላይ ክርስቶስን የማያዉቁት ሁሉ ወደ እሳት ባህር ይወረወራሉ ፤ ሰይጣንን፣ አዉሬዉን እና ሐሰተኛዉን ነቢይ ጨምሮ ሁሉም ለዘላለም ቀን እና ሌሊት ይሰቃያሉ ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (21፡ 1-2)፡ ዮሐንስ የአደስ ጅማሬ ራዕይን አዬ ፡፡ አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር ይሆናል ፤ ባህርም ዉኃም አይኖርም ፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን በማንኛዉም ጊዜ በራዕይ ላይ ዉኃን ጥቅም ላይ አዋዋሉን ሳስብ ሁልጊዜ በፍርድ እና በማሰቃየት ጥቅም ላይ ስለሚዉል ፡፡ ይህ አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር የብሉይ ኪዳን እና የአዲስ ኪዳን ትንቢት መፈጸም ናቸው (መዝ 102፡ 25-26, ኢሳ 65፡ 17, 66፡ 22, ሉቃ 21፡ 33, ዕብ 1፡ 10-12) ፡፡ ይህ አዲስ ራዕይ እንዳልሆነ ላሳያችሁ እፈልጋለሁ ፤ ዮሐንስ ቀድማ በተመሰረተችወ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም በተለዬ መልክ አቅርቦናል ፤ ይህ በግልፅ የጽድቅ ስፍራ እና ዋና ከተማ ከሰማይ እንደምትወርድ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ከሰማይ ወጥቶ ሲወርድ የታዬ ከሆነ ቀድሞዉኑም እንዳለ ነገር ግን ከፍ ካለዉ ስፍራው ወደ አዲሱ ሰማይ እና አዲሱ ምድር እንደሚወርድ ፤ ይህም ቅዱሳን የሚኖሩበት ከተማ እንደ ሆነ (ዮሐ 14፡ 1-3) “ ፅፏል ፡፡
ራዕይ (21፡ 3-5)፡ በመስቀል ላይ ለመሞት የክርስቶስ ወደ ምድር መምጣት የአዲሱ ሰማይ እና የአዲሲቱ ምድር ጥላ ነው ፡፡ ራዕ (7፡ 15) የቁጥር ሰዎስት መፈፀም ነው ፡፡ የሰማያዊዉን ዙፋን እንድናይ/እንድንመለከት እንጋበዛለን ፤ መዝሙር 132 ደግሞ ደግሞ የእግዚአብሔርን መኖሪያ ማደሪያ ስፍራ ያመለክታል/ይጠቅሳል ፤ ይህ ስዕል/መልክ ከ 1,000 የሺዉ አመት በኋላ ይሆናል ፤ ይህ እያወራን ስላለነዉ ሰማይ መልክ ነው - ኃዘን የለም፣ ህመም የለም፣ ለቅሶም የለም (ኢሳ 25፡ 8, 1ቆሮ 15፡ 54-58, 2ቆሮ 5፡ 17) ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ሙሉ መፈፀም ይሆናል ፤ ለእኔ ይህ ከዘፍጥረት እና ከራዕይ የንፅፅር መልክ ነው ፡፡ ቶም ኮንስታብል እንድንመለከተዉ የሚከተለዉን ሰንጠረዥ ሰጥቶናል ፡፡
ዘፍጥረት | ራዕይ | ||
ሰማይና ምድር ተፈጠሩ | (1:1) | አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር | (21:1) |
ፀሐይ ተፈጠረች | (1:16) | ፀሐይ አያስፈልግም | (21:23) |
ምሽት ተመሰረተ/ተቋቋመ | (1:5) | ምሽት/ጨለማ የለም | (21:25/22:5) |
ባህሮች ተፈጠሩ | (1:10) | ባህሮች የሉም | (21:1) |
እርግማን ተጀመረ | (3:14–17) | እርግማን የለም | (22:3) |
ሞት ገባ | (3:19) | ሞት የለም | (21:4) |
ሰዉ ከገነት ተባረረ | (3:24) | ሰዉ ወደ ገነት ተመለሰ | (22:14) |
ሐዘን እና ስቃይ/ሕመም ጀመረ | (3:17) | ሐዘን፣ ስቃይ እና ለቅሶ አይኖርም/የለም | (21:4) |
የቀደሞዉን ተፈጥሮ እንዴት እግዚአብሔር እንዳደሰዉ ማየት እንድንችል እፈልጋለሁ ፤ ይህ የሚያምር ኃይለኛ የሆነ ምስል ነው ፡፡ ቁጥር 5 ኢየሱስ በነጭ/በአምባ ላይ ፈረስ ተቀምጦ ተመልሶ ሲመጣ እና ለቃሉ ታማኝ እና እዉነተኛ እንደሆነ የምናይበትን ራዕ (19፡ 11) ያስታዉሰናል ፡፡
ራዕይ (21፡ 6-8)፡ ተፈጽማል ! ምን አይነት የሚያስደንቅ መልክ ነው! ምንድነዉ የተፈፀመው ? የእግዚአብሔር የቁጣ ተግባር/ስራ ነው ፡፡ ኢየሱስ መጀመሪያም መጨረሻም ነው ፤ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ኢየሱስ አለ ፡፡ ኢየሱስ የሚሰጠዉ ዉኃ የሕይወት ዉኃ ነው ፤ ዉኃዉ በፍፁም ስለማይደርቅ ባህር አያስፈልግም ፡፡ መከራን የተቋቋሙ እና በክርስቶስ የሚያምኑ ድል አድራጊዎች ናቸው (1ዮሐ 5፡ 4-5) ፤ ድል አድራጊዎቹ መንፈሳዊ ዉርስ ያላቸዉ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ ፡፡ የማያምኑት ርስታቸዉን በእሳት ባህር ዉስጥ ያገኛሉ - ሁለተኛዉን ሞት ፡፡ የመጀመሪያዉ ሞት አካላዊ ሞት ሲሆን ሁለተኛዉ ሞት ደግሞ ዘላለማቸዉን በእሳት ባህር ዉስጥ ለሚያሳልፉት ለማያምኑት ነው ፡፡
ቁጥር 8 የሚፈሩትን፣ የማያምኑ፣ ርኩሳኖችን፣ ነፍሰ ገዳዮችን፣ ሴሰኛዎችን፣ አስማተኞችን፣ ጣዖት አምላኪዎችን እና ዉሸጻሞችን ይዘረዝራል ፡፡ እነዚህ ሁሉ የአኗኗር ስርዓቶች ወደ ሲዖል ይልኳችኋል ፡፡ ምናልባትም ሁሉም ሰዉ ዉሸት እንደሚናገር እርግጠኛ ነኝ ፡፡ የሆነ ጊዜ/ስፍራ ላይ ብዙዎች ከሴሰኝነት አንፃር ፍራት ይይዛቸዋል/ይፈራሉ ፡፡ ፍርድ በአኗኗር ላይ እንጂ በኃጢዓት ላይ አይደለም ፤ ይህ ወደነዚህ አይነቶቹ መርዛማ የአኗኗር ዘዴ እንዳንገባ እንደ ማስጠንቀቂያነት ያገለግላል ፡፡ ጳዉሎስም በ 1ቆሮ (6፡ 9-10) ከእነዚህ ነገሮች እንድንጠነቀቅ አስጠንቅቆናል ፡፡ መልዕክቱ በሚገባ ግልፅ ነው - እነዚህ አኗኗሮች ተቀባይነት የሌላቸዉ ናቸው ፡፡ መልካሙ ነገር እምነታችሁን በክርስቶስ ላይ በምታስቀምጡ ጊዜ ሁሉንም ነገሮች ይቀይራቸዋልን ?
ራዕይ (21፡ 9-14)፡ በእነዚህ ጥቅሶች የአዲሲቱን ኢየሩሳሌም መገለጫ/ባህሪይ ማየት እንጀምራለን ፡፡ ማክአርቱር “ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በተቡዡት በነዋሪዎቿ ባህሪ እንደምትወሰድ “ ፅፏል (ራዕ 19፡ 7-9, 21፡ 2) ፤ ኮንስታብል “ ቁጥር (11-22) የከተማይቱን አካላዊ መልክ እንደሚገልፁ “ ይገልፃል ፡፡ ከተማዋ በ12 መለዓክት የሚጠበቅ 12 ረጃጅም ቅጥሮች ነበሯት ፤ በሮቹ በ12 የእስራኤል ነገድ ልጆች ስም ተሰይመዋል (ሕዝ 48፡ 30-35) ፡፡ በከተማዋ በእያንዳንዱ አቅጣጫ በደቡብ፣ በሰሜን፣ በምዕራብ እና በምስራቅ ሰዎስት በሮች እንደሚኖሩ እናዉቃለን ፡፡ የ12 ሐዋሪያቶች ስም የሚኖራቸዉ 12 መሰረቶች ይኖራሉ (ሉቃ 6፡ 13-16, ኤፌ 2፡ 20) ፤ በማቴ (19፡ 28) ኢየሱስ ሐዋሪያቱን በሰማይ ከእርሱ ጋር ታላቅ የሆነ ስፍራ እንደሚኖራቸው እንደ ነገራቸው እናስታዉሳለን ፡፡
ራዕይ (21፡ 15-16)፡ አንድ የወርቅ ዘንግ ከተማዋን ለመለካት ጥቅም ላይ ዋለ ፤ ማክአርቱር “ ዘንጉ የመደበኛ መለኪያ የሆነ 10 ጫማ ያክል ይረዝም እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡ 12,000 ስታዲያ (ምዕራፍ) ወይም 20ሜትር ያክል የርቀት መለኪያዉ የፍጹምነት ምሳሌ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ 12,000 ፉርሎ/ምዕራፍ(20 ሜት ያክል ርቀት መለኪያው) 1400 ማይል ኪዩብ ወይም 2ሚሊዮን ማይል ካሬ ያክል የሚሆን ለሁሉም ለከበሩት ቅዱሳን የተትረፈረፈ የመኖሪያን ክፍል እንዳቀረበ….. ከተማዋ ፍጹም ሰዎስት በሰዎስት ጎን ያላት ተመሳሳይ ስፋት እንዳላት “ ፅፏል ፡፡ ይህ የምር ትልቅ ነው ፤ በምድር ላይ ተመሳሳይ/ትይዩ የሆነው ሳጥን የቤተ መቅደሱ ዉሰጠኛው መቅደስ ይሆናል ፡፡
ራዕይ (21፡ 17-21)፡ የቅጥሩ ስፋት/ወርድ 73 ያርድ ወይም 216 ጫማ የሚሆን 144 ክንድ ይለካል ፤ ቅጥሩ ከኢያሰጲድ የሚሰራ ነው ፡፡ ምናልባትም ኢያሰጲድ አልማዝ የሚመስል እቃ ነው ፡፡ ከተማዋ ከንጹህ ወርቅ የተሰራች ነች ፤ ወርቁ ንጹህ ስለሚሆን የእግዚአብሔር ብርኃን ሊያበራና ሊያንፀባርቅ ይችላል ፡፡ መሰረቶቿ ያጌጡ የከበሩ ድንጋዮች ይኖሯቸዋል ምናልባትም በሐዋሪያቱ የተሰራ ነገር ይኖራል ፤ 12 የተለያዩ ልፈዩ የሆኑ ድንጋዮች አሉ ከእነዚህ ዉስጥ ስምንቶቹ በታላቁ ካህን የደረት ኪስ ላይ የነበሩ ናቸው ፡፡ እያንዳንዳቸዉ በሮች ከአንድ እንቁ የተሰሩ ናቸው ፤ መንገዱም ንጹህ/ከሚያስተላልፍ ወርቅ የተሰራ ነው ፡፡
ራዕይ (21፡ 22-27)፡ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር አምላክ እና በጉ መቅደሶች ስለሆኑ መቅደስ እና ቤተ መቅደስ አይኖርም ፡፡ የእግዚአብሔር ክብር ሰማያትን ያበራል ፤ አሕዛቦች በብርኃን ይመላለሳሉ ክብራቸዉን ወደ እርሷ ያመጣሉ ፡፡ በሮቹ በፍጹም አይዘጉም በፍጹምም ምሽት/ጨለማ አይሆንም ፡፡ ኃጢዓት አይኖርም የማያምኑም አይኖሩም ፡፡ አይሁዶች እና አሕዛቦች በዙፋኑ በፊት በአንድ ላይ መምጣት ይችላሉ ፤ ይህ እንደ ራዕ (3፡ 5) ተመሳሳይ መልክ ነው ፡፡
መደምደሚያ
ስለዚህ አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር ለምን ዝም ብለን እንቀመጣለን ? ሁልጊዜ ስለ አዲሲቱ ሰማይ እና ስለ አዲስቱ ምድር እዉነት ለማጋራት እድል አለን ፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ቤዛነቱን እና ፍቅሩን አቅርቧል፣ ቃሉን እንድናገር ብቻ ይጠይቀናል ፡፡ የመጽኃፉን ትምህርት መዝጊያ ላይ ድረስ ለመምጣት አንድ ምዕራፍ አለን ፡፡ ነገ እንገናኝ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 2036.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Revelation, p. 339; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/revelation.pdf.
MacArthur, p. 2037.
Constable, p. 349.
MacArthur, p. 2038.
MacArthur, p. 2038.
ጥያቄዎች
-
በራዕ (21፡ 1) መሰረት በአዲሱ ሰማይ እና ምድር ለምን ምንም ባህር አይኖርም ?
-
በራዕ (21፡ 3) ዮሐንስ “ እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል “ የሚል ድምጽ ሰማ ፤ ይሁን እንጂ በቁጥር 22 በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንደሌለ ይነግረናል ፡፡ ይህ ምን ማለት እንደ ሆነ ምን እንደ ምታስቡ ግለፁ ?
-
ራዕ (21፡ 4) “ የቀድሞ ስርዓት/ነገር አልፏል “ ሲል ምን ማለቱ እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ? እነዚህ “ የቀድሞዉ ነገሮች “ ምንድን ናቸው ?
-
በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ዙሪያ ታላላቅ ቅጥሮች እና 12 በሮች ለምን እንደተቀመጡ/እንዳሉ ምን ታስባላችሁ (ራዕ 21፡ 12) ? በፍጹም የማይዘጉ ከሆኑ ለምን በሮቹ ኖሩ ? (ራዕ 21፡ 25)
-
ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም መግባት የሚችሉት እነማን ናቸው (ራዕ 21፡ 27) ? መግባት የማይችሉትስ ?
-
በራዕይ 21 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 21:5b–7
“‘Write, because these words are faithful and true.’ And He said to me, ‘It is done! I am the Alpha and the Omega, the Beginning and the End. I will give water as a gift to the thirsty from the spring of life. The victor will inherit these things, and I will be his God, and he will be My son.’”
ቀድሞ የተነገረው የሙሽራዋና የበጉ ጋብቻ በመጨረሻ ተፈጸመ፡፡ ዮሐንስ ቅድስቲቱ ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባሏ እንደተሸለመች ሙሽራ ሆና ለእግዚአብሔር ተዘጋጂታ ከሰማይ ስትወርድ ተመለከተ፡፡ ዮሐንስ እግዚአብሔር ከሰው ጋር የሚኖርበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድርን ተመለከተ፡፡ ሞት፣ ኃዘን፣ ስቃይና ለቅሶ ከእንግዲህ አይኖርም፡፡ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው እርሱ ዮሐንስን ቃሎቹ የታመኑና እውነት ናቸውና እንድጽፋቸው አዘዘው፡- “ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።”
እነዚህን ነገሮች ለመውረስ ማን ነው ድል የነሳው ? እናንተም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በእምነት ከተቀበላችሁ፣ ከህይወት ውሃ ለዘላለም እየጠጣችሁ አልፋና ኦሜጋ ከሆነው ከእርሱ ጋር አሸናፊዎች ሆናችሁ ለዘላለም በሰማይ መንገስ ትችላላችሁ፡፡ በዚያ አታለቅሱም አትሰቃዩም፣ በዚያ በእግዚአብሔር ክብር ብርሃን በወርቅ መንገድ ላይ ትራመዳላችሁ ስማችሁም በበጉ የህይወት መጽሐፍ ላይ ይጻፋል፡፡ ኢየሱስ ይህን መልካምና ህይወትን የሚቀይር መልዕክት ታካፍሉ ዘንድ ኃይልና ስልጣን ሰጥቷችኋል፡፡ ታዲያ ለምንድን ነው ዝም የምትሉት ? ዛሬ ሂዱና በኢየሱስ የሚያምኑት፣ አሸናፊዎቹ ሰለሚወርሱት የሚያምር ተስፋ ተናገሩ፡፡
“እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።አለኝም፦ ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።”
- ራዕይ 21:5b–7
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ዮሐንስ 5:4–5 — “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?”
ራዕይ 21:3–4 — “ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።”
ራዕይ 21:9b–11 — “ወደዚህ ና፥ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ ብሎ ተናገረኝ። በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፡፡”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።