The Source Of Life
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ I AM Revelation 22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ በሪቫይቭ ት/ቤት የመጨረሻዉ ክፍል እንደ ሆነ ማመን አስቸጋሪ ነው ፡፡ በ730 ክፍሎች ዉስጥ አልፈናል ፡፡ ዛሬ ስለዚህ ጥናት ስሜታዊነት እየተሰማኝ ነው ፡፡ ይህ ቡድን በአንድ ላይ የእግዚአብሔር ቃል ስናጠና/ስንጎለጉል ለሁለት አመታት ጠንክሮ ሰርቷል ፡፡ ዕብ (4፡ 12) “ የእግዚአብሔር ቃል ሕያዉ ነዉና የሚሰራም ሁለትም አፍ ካለዉ ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል “ ይላል ፡፡ መጽኃፍ ቅዱስ ህያዉ እና የሚሰራ ስለሆነ ሪቫይቭ ት/ቤት በጀመርን ጊዜ በስራችን፣ በቤተ ክርስቲያናችን እና በሕዝባችን ዉስጥ ህያዉ እና የሚሰራ እንዲሆን ፈለግን ፡፡
ኢየሱስ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ አለ (ማቴ 5፡ 17) ፡፡ ራዕይ 22 የሁሉም መፈጸም ነው ፡፡ ራዕይ እና የክርስቶስ መምጣት በግልጽ ኃጢዓትን እና ሞት ስለማሸነፍ ነው ፡፡ ዝግታችንን በጊዜዉ እንድናነሳሳ/እንድናነቃቃ እና በቃሉ ላይ ጊዜን እንድናሳልፍ እግዚአብሔር እንደ ተናገረን ይሰማኛል ፤ በታማኝነት ለመናገር በዚህ ሂደት ዉስጥ በብዙ የተቀየርኩ እንደምሆን አላሰብኩም ፤ አጠቃላይ መጽኃፍ ቅዱስ ሕይወት ቀያሪ ሲሆን ሁሉም ስለ ክርስቶስ ነው ፡፡ ይህ የሁለት አመት ሂደት ከነበረኝ ጊዜ በጣም አስቸጋሪ የአገልግሎት ጊዜ ነው - የመሲሁን ትልቅ መልክ/ምስል ማየት ለመጀመር በቃሉ ላይ በቂ ጊዜን በመቆየት ታዛዥ መሆንን ይጠይቃል ፡፡
ትምህርት
ራዕይ (22፡ 1-5)፡ ዮሐንስ ከእግዚአብሔር እና ከበጉ ዙፋን ወደታች በመንገዱ መካከል የህይወት ዉኃ ወንዝ ሲፈስ/ሲወርድ ተገልጦለት ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ማክአርቱር “ ይህ ወንዝ በምድር ላይ ማንኛዉንም አይመስልም ምክንያቱም ምን የዉኃ አፈጣጠር ኡደት ስለሌለዉ “ በማለት ይናገራል ፡፡ የሕይወት ዉኃን ሀሳብ በመጽኃፍት ዉስጥ አይተናል (ሕዝቅኤል 47, ዮሐ 7፡ 38-39) ፡፡ የሕይወት ዛፍ በሁለቱም የወንዙ ዳርቻዎች ነበር አስራ ሁለት አይነት ፍሬን ያፈራል በሁሉም ወራትም ፍሬን ይሰጣል (ቁጥር 2) ፡፡ መጀመሪያ የሕይወት ዛፍ የተወከለው በዘፍጥረት (3፡ 22-24) ነው ፡፡ በራዕይ 22 እስከሚታይ ድረስ ማንም ወደ ሕይወት ዛፍ አይደርስም ፡፡ የሕይወት ዛፍ ቅጠሎች ሕዝቦችን ለመፈወስ (ለማደስ) ጥቅም ላይ ይዉላል (ሕዝ 47፡ 12) ፡፡ የእግዚአብሔር እና የበጉ ዙፋን በከተማዋ ዉስጥ ይሆናል ባሪያዎቹም (እንደ አገልጋይ እኛ) ያገለግሉታል (ቁጥር 3) ፡፡ ጌታን ያለማቋረጥ ከማምለካችን ዉጭ ይህ ሁሉ ምን ማለት እንደ ሆነ እርግጠኛ አይደለሁም ፡፡ አገልጋዮቹ ፊቱን ያዩታል ስሙም በግንባራቸዉ ላይ ይሆናል (ቁጥር 4) ፡፡ እንደ አማኝ ግባችን ፊት ለፊት እርሱን ማየት ነው (1ቆሮ 13፡ 12) ፤ ይህ አዲሱን ሰማይ እና አዲሲቱን ምድር የሚገልጽ ነው ፡፡ ምሽት እና ጨለማ አይኖርም ምክንያቱም እግዚአብሔር ብርኃንን ይሰጣል ለዘላለምም ይገዛል (ቁጥር 5) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ጨለማ የለም….ብርኃን የለም “ የሚለዉ የክርስቶስ የራሱን አዋጅ ራሱን “ እንደ አለም ብርኃን “ (ዮሐ 8፡ 12, 9፡ 5, 12፡ 46) የገለፀበት መፈፀም እንደ ሆነ ያመለክታል ፤ ይህ የኤደን ገነት የታደሰች መሆን መልክ ነው ፡፡
ራዕይ (22፡ 6-7)፡ መለዓኩም በአንድ አንባላይ/ነጭ ፈረስ ላይ በሚመለሰው ጌታ “ የታመነ እና እዉነተኛ “ ቃልን (ራዕ 19፡ 11) በመጠቀም ቃሎቹ “ የታመኑ እና እዉነት “ እንደ ነበሩ ተናገሩ (ቁጥር 6) ፡፡ ጌታም በቶሎ ስለሚመጣ “ የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁሕ ነው “ (ቁጥር 7) ፡፡ የራዕይ መጽሐፍ “ ብፁዕ መሆንን “ ሰባት ጊዜ ጠቅሷል ይህ ስድስተኛዉ ነው ፡፡ የእግዚአብሔር በረከቶች በራዕይ መጽኃፍ እና በእግዚአብሔር ተስፋዎች ዉስጥ በመመላለስ ላይ በትምህርት ላይ የሚገኙ ናቸው ፡፡
ራዕይ (22፡ 8-11)፡ ዮሐንስ ይህን ሁሉ ነገር እንዳዬ እና እንደሰማ ይህን ባደረገም ጊዜ ለመስገድ በመለዓኩ እግር ስር ተደፋ (ቁጥር 8) ፤ ይህ ዮሐንስ በስህተት ለመስገድ በመለዓኩ ፊት የተደፋበት ሁለተኛዉ ጊዜ ነበር (ራዕ 19፡ 10)፡፡ መለዓኩም ዮሐንስን ከእርሱ ጋር፣ ከነቢያት እና የራዕይን/የትንቢቱን መጽሃፍ ከሚጠብቁት ጋር በሕብረት የሚያገለግል እንደ ነበር አሳሰበው፡፡ መሰገድ ያለበት ለእግዚአብሔር ብቻ ነው (ቁጥር 9) ፡፡ መለዓኩ ዮሐንስ ጊዜዉ ስለቀረበ የራዕዩን ቃላቶች እንዳይዘጋው ነገረው (ቁጥር 10) ፡፡ በራዕ (10፡ 4) ዮሐንስ ጥቂት ትንቢቶችን በማህተም እንዲዘጋዉ ተነግሮት ነበር ፡፡ ማክአርቱር “ እነዚህ ትንቢቶች የታወጁ ስለሚሆኑ መታዘዝን እና አምልኮን ማምጣት እንደሚችሉ “ ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር “ የእግዚአብሔርን ማስጠንቀቂያዎች የናቁት ለዘላለም ከክፋትና ከቆሻሻ ተፈጥሮአቸዉ ጋር በሚቀመጡበት የዘላለም መዳረሻቸዉን በሲዖል እንደሚሆን “ ይናገራል ፤ ይሁን እንጂ ጻድቁም ጻድቅ ሆኖ ይቀጥላል ቅዱሱም ቅዱስ ሆኖ ይቀጥላል (ቁጥር 11) ፡፡
ራዕይ (22፡ 12-14)፡ ዮሐንስ ጌታ በፍጥነት እየመጣ እንደ ነበር እንዲያስብ ተደረገ (ቁጥር 12) (ራዕ 3፡ 11, 22፡ 7) ፡፡ እግዚአብሔር ከፈተናው ለዘላለም ለተረፈው እያንዳንዱ ላደረገዉ ስራ ይሸልማል/ዋጋዉን ይከፍለዋል ( ቁጥር 12) (1ቆሮ 9፡ 24-27) ፡፡ በጌታ እምነታችን እና ብስለታችን እንዲያድግ ምክንያት የሆነ ስርዓት በሪቫይቭ ት/ቤት አግኝተናል/ተለማምደናል ፡፡ ሰዎች ቃሉን በማስቀመጥ ምንም ነገር ባለማድረግ በመንፈሳዊነት ግዴለሽ ሆነዉ ሊገኙ እንደሚችሉ አምናለሁ ፡፡ እኔ በማለት የሚገልፀው “ አልፋና ዖሜጋ ፊተኛዉና ኋለኛው መጀመሪያውና መጨረሻ ነው “ (ቁጥር 13) ፡፡ እንደ አማኝ ለእግዚአብሔር ቃል እና ለኢየሱስ መንቃት/መዘጋጀት አለብን ፡፡ ቤተ ክርስቲያንለጌታ የተነሳች/የተዘጋጀች ባልሆነች ጊዜ የደከመች/የለሰለሰች ትሆናለች ፡፡ በበጉ ደም ይቅር እንደ ተባልን እና ሰማያዊ አባትን የማግኘት እድል እንደተሰጠን ማስታወስ አለብን ፤ የዘላለም ህይወት ተሰጥቶናል፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የመድረስ እድል አለን እንዲሁም በበሮቿ ወደ ከተማይቱ መግባት እንችላለን (ቁጥር 14) ፡፡ ወደ ገነት የመድረስ/የመግባት እድል በእግዚአብሔር ታድሷል ፡፡
ራዕይ (22፡ 15-21)፡ ቁጥር 15 በብልግና የቆሸሹ እና አስከፊ/የተበላሸ ባህሪይ ያላቸዉ ከበሮቹ ዉጪ እንደሚሆኑ ይናገራል ፤ ከጌታ ጋር አይመላለሱም አይገቡምም ፡፡ ቁጥር 6 ለኢየሱስ ብዙ ርዕሶችን/ስያሜዎችን ይሰጣል፡ የዳዊት ስር፣ የዳዊት ዘር እና የሚያበራ የንጋት ኮኮብ ፤ ማክአርቱር “ ክርስቶስ አምላክነቱን የመሰረተበት የዳዊት ህይወት እና የትዉልዱ መስመር ምንጭ እንደ ሆነ ፤ ሰዋዊነቱን የመሰረተበት የዳዊት ዘር እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፤ በተጨማሪም ማክአርቱር “ የሚያበራ የንጋት ኮኮብ “ “ የቀኑ መድረስን የሚያሳዉቅ የሚያበራ/ከሁሉም የሚበልጥ አብሪ “ እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ በጣም የሚያበራ ስለሆነ ሌላዉ ሁሉም ነገር በእርሱ ይበራል ፡፡ በቁጥር 17 መንፈስ ቅዱስ እና ሙሽራዋ እንዲሁም እዚህ ስፍራ ላይ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳንን እና የክርስቶስ ተከታዮችን ጨምሮ “ ና ! “ ይላሉ ፡፡ ማክአርቱር “ ይህ ጥማታቸዉን ማርካት ለሚፈልጉ ያልተገደበ የጸጋና የድነት ስጦታ እንደሆነ “ ያጋራል ፡፡ ቁጥር 18 ሁሉም በራዕይ መጽኃፍ ላይ እንዳይጨምሩ ያ ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔር በመጽሃፉ ላይ በተገለጹት መቅሰፍቶች እንደሚቀጣቸዉ ማስጠንቀቂያን ይዟል ፤ ቁጥር 19 ከራዕይ ትንቢት አንዳች ነገር እንዳይቀንሱ ያ ከሆነ ደግሞ ከዘላለም ህይወት እንደሚያጎድላቸው ማስጠንቀቂያን ይዟል ፡፡ ራዕይ ጌታ በቶሎ እንደሚመጣ እንዲመሰከር በማስታዎስ ይደመድማል (ቁጥር 2) ፤ ከዚያም በዚህ ይዘጋል፡ “ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን ፤ አሜን “ ፡፡
መደምደሚያ
ዋይርስቤ የክርስቶስን ተመልሶ መምጣት ስንጠብቅ “ ኑሮ አችንን በማንፃት መጠበቅ እንዳለብን “ ይናገራል ፡፡ ለእርሱ ተመልሶ መምጣት የተዘጋጀን እንድንሆን ለማሰልጠን/ለማዘጋጀት በሪቫይቭ ት/ቤት ዉስጥ 66 የመጽኃፍ ቅዱስ መጽኃፍትን አጥንተናል ፡፡ የተዘጋጃችሁ ለመሆን አንድ እርምጃ እንደ ቀረባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 2039.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1767.
MacArthur, p. 2039.
MacArthur, p. 2039.
MacArthur, p. 2040.
MacArthur, p. 2040.
MacArthur, p. 2040.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians–Revelation, v. 11 (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 614.
ጥያቄዎች
-
የፍጥረትን መጀመሪያ በራዕይ 22 ካለዉ የመጨረሻዉ መታደስ ጋር አወዳድሩ ፤ (ዘፍ 1፡ 5, 3፡ 14-17, 24, ራዕ 22፡ 3, 5, 14)
-
የህይወት ዛፍ የምን ምልክት ነው (ዘፍ 2፡ 9) ? ራዕይ 22 የሕይወት ዛፍን እንዴት ይገልፀዋል ?
-
መብራት ወይም ፀሐይም እንኳን ቢሆን በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም መኖሩ ለምን አያስፈልግም ? (ዮሐ 8፡ 12)
-
ሁሉም አማኝ የራዕይን መጽኃፍ ለምን ማጥናት አለበት (ራዕ 1፡ 3, 22፡ 7) ? ልክ እንደ ማቴዎስ 5 የራዕይ መጽኃፍ ጥቂት የተባረኩ/ብጹዖች አሉት ፤ በማግኘት አንብቧቸው ፡፡ (ራዕ 1፡ 3, 14፡ 13, 16፡ 15, 19፡ 9, 20፡ 6, 22፡ 7, 14) እነዚህ እንዴት ያበረታቷችኋል ?
-
የራዕይ መጽኃፍ በጌታ በኢየሱስ ፀጋ መጽኃፉን መጀመሩና መጨረሱ ምንን ያመለክታል ?(ኤፌ 2፡ 8-9, ራዕ 1፡ 4, 22፡ 21) ? በዚህ መጽኃፍ ዉስጥ ባነበባችሁት ሰዉን እንዴት ማበረታታት ትችላላችሁ ?
-
በራዕይ 22 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Revelation 22:20–21
“He who testifies about these things says, ‘Yes, I am coming quickly.’ Amen! Come, Lord Jesus! The grace of the Lord Jesus be with all the saints. Amen.”
የዮሐንስ ራዕይ ሲጠቃልል የእግዚአብሔር መልአክ የተናገረው ቃል ለአማኞች ከክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በፊት ፈጥኖ ሊሆን ያለውን ያሳያቸው ዘንድ የታመነና እውነተኛ እንደሆነ አጸና፡፡ ይህንንም የትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብጹዕ ነው፡፡ ዮሐንስም ለመልአኩ ይሰግድ ዘንድ ሞከረ መልአኩ ግን እንዳያደርገው ለመነው ደግሞም ዮሐንስ ለእግዚአብሔር ብቻ እንድሰግድ አዘዘው፡፡ አማኞች እግዚአብሔርን ሲፈልጉ እርሱን ሲሹ ይቀደሳሉ፡፡ ኢየሱስ የሚሰጠውን ህያው ውሃ ከጠጣ ማንም እንደገና አይጠማም፡፡ ኢየሱስ በቶሎ እንደሚመጣ ተናግሯል፡፡ እኔ ኢየሱስ ታላቅ የሆንኩት፣ አልፋና ኦሜጋው፣ ኃያሉ አምላክ፣ የዳዊት ሥርና ዘር፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ የሆንኩት እኔ በቶሎ እመጣለሁ፡፡
እናንተ ከክርስቶስ ምጽዓት በፊት ባሉት የመጫረሻ ቀናቶች ነው እየኖራችሁ ያላችሁት፡፡ ለመዘጋጀት ፍቃደኛ ናችሁን? ክርስቶስ ለእናንተ ያለውን ፍቅር ተቀበሉ፡፡ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ፣ ነፍሳችሁ፣ አሳባችሁና ኃይላችሁ ውደዱ፡፡ ከዚያም ራሳችሁን እንደምትወዱት አድርጋችሁ ሌሎችን ውደዱ፡፡ ለእግዚአብሔር ብቻ ስገዱ፡፡ ከኢየሱስ ፍቅር ውጭ ምንም ቢሆን መቼም ሊያረካችሁ አይችልም፡፡ ክርስቶስ በቂ ነው፡፡ ና ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና፡፡ እርሱ በቶሎ ይመጣል፡፡ ተዘጋጁ!
“ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።”
- ራዕይ 22፡20-21
ተጨማሪ ጥቅስ
ማቴዎስ 22:37–39 — “ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።”
ኤፌሶን 2:8–9 — “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።”
ራዕይ 22:7–9 — “እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ።ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።