Restored Marriage
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Bridegroom Song of Songs 6-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በጥበብ መፅኀፍት ዉስጥ ይህ 122 ክፍል ሲሆን በመኃልየ መኃለይ ዘሰሎሞን ደግሞ ሰዎስተኛዉ እና የመጨረሻዉ ነው ፡፡ ንጉስ ሰለሞን ከፃፋቸዉ 1,005 የፍቅር መዝሙሮች ዉስጥ አንዱ ነው ፤ ይህ በኃይለኛው ወድዷት እና ተስቦባት ስለነበረዉ የመጀመሪያ ሚስቱ ሱናማይቷ ሴት ነው ፡፡ ማንኛዉም ግንኙነት በደረጃ ይሄዳል ፤ በመዝሙሩ ዉስጥ ሰለሞን የማግባባት ሁኔታን፣ የሰርግ በዓሉን፣ ጋብቻዉን፣ ትዳር ዉስጥ መምጣት ስለሚችለዉ ስሜት እና ቀጥሎም ስለመዋጀት ይገልፃል ፡፡ በመዝሙሩ ዉስጥ ሌሎች ማለትም የኢየሩሳሌም ሴት ልጆች (መኃ 1፡ 4, 6፡ 1, 6፡ 13, 8፡ 5) እና የሱናማይቷ ወንድሞች (መኃ 8፡ 8-9) ሀሳባቸዉን እና ምስጋናቸዉን ጨምረዋል ፡፡ በምዕራፍ 5 ደግሞ እግዚአብሄር በረከቱን ጨምሮአል (መኃ 5፡ 1) ፡፡
ሰለሞን የሱናማይቷን ሴት የኢየሩሳሌምን እና የሰራዊት ዘይቤአዊ አነጋገር በገለፀበት ጊዜ የሁሉም ነገር ደስታ ነበረች እያለ ነበር ፤ በሱናማይቷ ሴት ፍቅር የወደቀዉም ለዚያ ነው ፡፡ በእነዚህ ቁጥሮች ስንቀጥል ሂደቱን አስታዉሉ ፡፡ ሰለሞን ጋብቻን ተስፋ በማድረግ እና ወሲባዊ ግንኙነት ከእርሷ ጋር እንዲኖረዉ ተከታተላት ፡፡ አንዴ ጋብቻ ከተፈፀመ/ከተሟላ በሽርሽር ጊዜ ዉስጥ አልቆዩም በመጨረሻም ወደ ስሜትን ወደ መጋራት ተጓዙ/ሄዱ (5፡ 2-6፡ 13) ፡፡ ኮንስታብል ቶም ይህንን ሂደት አስቀምጦታል/ዘርዝሮታል፡
- “ በግድየለሽነት ማቆም/ችላ ማለት (5፡ 2-8)
- ፍቅርን ማደስ (5፡ 9-16)
- ወደ እርቅ መሄድ (6፡ 1-3)
- መቀራረብን ማደስ (6፡ 4-13)
- በፍቅር መነጋገር (7፡ 1-10) “ ፡፡
ትምህርት
መኃልየ መኃለይ ዘሰሎሞን (7፡ 1-9)፡ ሰለሞን የሚስቱን ዉበት ሰለሞንን በሚያረካዉ መንገድ በማቅረብ ገለፀ (ቁጥር 1-4) ፡፡ በቁጥር 5 ላይ ሰለሞን ንጉሳዊ እንደ ነበረች አመለከተ ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች መጀመሪያ ሰለሞን የሚመጣዉን የጋብቻ አካላዊ መቀራረብን ተስፋ እያደረገ በነበር ጊዜ ከፃፈዉ ጋር ተደግመዋል ፡፡ ሰለሞን ከሱናማይቷ ሴት የተቀበለዉን ስጦታና በረከት ገልፆአቸዋል (ቁጥር 6-8) ፤ እርሷን መሳም እንኳ ጣፋጭ ወይን እንደመጠጣት ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ በሁሉም ቃል ሰለሞን ልክ እንደ መጀመሪያዉ መሳሳባቸዉ እና እርስ በእርስ እንደ መፈላለጋቸው መለሲ አድሶት እና አነሳስቶት የነበረዉን ግንኙነታቸዉን መልክ ፈጥሮለታል ፡፡
መኃልየ መኃለይ ዘሰሎሞን (6፡ 13)፡ በምዕራፍ ስድስት ሰለሞን ሁለት ሰፈሮችን ወይም ሰራዊቶችን ገልፆአልም የኤሳዉን እና የያዕቆብን ሁለቱንም ታሪክ ተጠቅሞአል (ዘፍ 32፡ 1) ፡፡ ያዕቆብ ሸሽቶ ከነበረ በኋላ ወንድሙን ለመገናኘት በመንገድ ላይ ነበር ፤ እግዚአብሄር የመለዓክት ሰራዊቱን ኤሳዉን እና ሰራዊቱን እንዲያገኙት ላካቸው ፤ ሁለቱም ሰራዊት በአንድ ላይ የመጡበት ይህ ስፍራ መሃናይም ብሎ ሰየመው ፡፡ ይህ የሰለሞን ሚስት እንደ ጠላት ሰራዊት እርሱን የምትዋጋ ሳትሆን ከእርሱ ጋር የምትዋጋ እንደ ረዳት ሰራዊት ታይታ እንደ ነበር ያሳያል ፡፡
መኃልየ መኃለይ ዘሰሎሞን (7፡ 10-12)፡ በቁጥር 12 ሚስቱ “ ታማኝ የሆነዉን ፍቅሯን ለሰዎስተኛ ጊዜ ገለፀች “ ፤ ይህ ፍቅሯን እና ለእርሱ መሰጠቷን ይናገራል - በእርሱ በኩል ያለዉ ወሲባዊ መሳሳብ በእርሷም በኩል ነበር ፡፡ ቀድሞ ጠይቆ እምቢ ተብሎ የነበረዉን ነገር (መኃ 2፡ 8-17) ከእርሷ ጋር ወደ መስክ እንዲሄድ ጋበዘችዉ (ቀጥር 11)፡፡ ሰለሞን ሚስቱን እንደ ወይን ዘለላ ገለፃጽ (ቁጥር 9)፣ ያም ወይን ለፍላጎቱና ለእርካታው ከእርሷ እንዲፈስስ ፈለገች (ቁጥር 9, 12) ፤ ፍቅሯን ተስፋ ገባችለት (1ቆሮ 7፡ 1-7) ፡፡ ሚስቱ ከባሏ ጋር ለወሲብ እየተነሳሳች እና ያለፉ ነገሮችን እና አዲስ ነገሮችን በአንድ ላይ እንደምትሞክር ተስፋ እየገባች ነበር (ቁጥር 13) ፡፡ ሮማን ወሲብ እንደሚቀሰቅስ ንጥረ ነገር/ፍሬ የሚታይ ሀያለኛ የሚጣፍጥ ሽታ ያለዉ ዛፍ ነበር ፡፡ ለእርሱ የሚያድገዉ ፍላጎቷ በጋብቻቸዉ ዉስጥ የወሲብ ግንኙነትን ጨምሯል ፡፡
ከዚህ በፊት መልካም ወይም እግዚአብሄራዊ ያልነበረ ይኖራችሁ ይሆናል ፤ ተቸግራችሁ እና ተገፍታችሁም ይሆናል ፤ ያ ከክርስቶስ የመጣ ፍቅር ስላልሆነ በእንደዚህ አይነት ስፍራ ላይ የሌላ ሰዉ በሚመስል ፍቅር ስር ለመቀበል ራሳችሁን አታስቀምጡ ፡፡
መደምደሚያ
ኦድኔን ሰን ዳግላስ ስለ ጋብቻ ስታስቡ ጋብቻ ንፁኅ መሆን እንዳለበት አመልክቷል፡
“ ንፁኅ ፍላጎት ታጋሽ ነው “ ፤ ትክክለኛ ጊዜን እና ትክክለኛ ሰዉን ይጠብቃል ፡፡
“ ንፁኅ ፍላጎት የሚያስደስት ነው “ ፡፡
“ ንፁኅ ፍላጎት ንፁህ ያልሆነ ፍላጎት መከላከያ ነው “ ፤ ባል እና ሚስት መልካም የሆነ ወሲባዊ ግንኙነት ሲያደርጉ ንፁህ ላልሆነ መነሳሳት ፍላጎት አይኖራቸዉም ፡፡
“ ንፁህ ፍላጎት የመነሳሳት/የፍላጎት ማስታወቂያ ነው “ ፤ በመነሳሳት/በፍላጎት በአንድ ላይ በመምጣት ሙሉ የሆነ የግል/የራስ ፍቅር በትክክል የክርስቶስ ፍላጎትን ያስታዉቃል ፡፡ አለም የግንኙነታችንን/የትስስራችንን ማስተዋል ይወስዳል ! ይህ ሁሉ ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ፡፡
ክርስቶስ ሙሽራዉ ነው ፤ ከቤተ ክርስቲያኑ - ከሙሽራው ጋር ጊዜን ለማሳለፍ የጓጓ ነው ፤ “ ባሎች ሆይ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ዉደዱ ፤ በዉኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ “ (ኤፌ 5፡ 25-26) ፡፡
3 J. Cheryl Exum, Song of Solomon: A Commentary, (Louisville, KY: Westminster John Knox Press, 2005), p. 249; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Exposition Study Notes: Song of Solomon, pp. 48–49.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Exposition Study Notes: Song of Solomon, pp. 40–46; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/song.pdf.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publisher), p. 751.
Constable, p. 49.
Douglas Seam O’Donnell, The Song of Solomon: An Invitation to Intimacy (Wheaton, IL: Crossway Publishers, 2012), p. 81.
ጥያቄዎች
-
መኃ (6፡ 10) ሙሽራዋን “ እንደ ፀሀይ የምታበራ እንደ ነበረች “ ይገልፃታል ፤ ማቴ (5፡ 14-16) አንብቡ ፤ ሙሽሮች ከሆንን በሰማይ ያለዉን አባታችንን ለማክበር እንዴት “ ማብራት “ ይጠበቅብናል ?
-
ሰለሞን የሙሽራዉን ጫማ ያደረጉ የሚያምሩ እግሮቿን ጠቀሰ (መኃ 7፡ 1) ፤ በሮሜ (10፡ 15) እና ኤፌ (6፡ 15) ላይ ተመልከቱ ፤ እግሮቻችሁ በሰላም ወንጌል “ ተጫምታችኋል “ (ኢሳ 52፡ 7) ? እንደ ክርስቶስ ሙሽራ አካል መልካሙን ዜና ወደ ሚያስፈልጋቸዉ እንዴት ነዉ የምታደርሱት ?
-
በመኃ (8፡ 6-7) በሙሽራዋ የተነገረዉ ፍቅር “ ከሞት የጠነከረ “ ስለሆነ ሊጠፋ የማይችልም በላዉ ላይ በልጦት ሊፈስ የሚችል ወንዝ የሌለ ነው ፤ ይህ ከሮሜ (8፡ 38-39) ጋር እንዴት ይነፃፀራል ?
-
በመኃልየ መኃለይ ዘሰሎሞን (6-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Song of Songs 8:6b–7a
“Love’s flames are fiery flames—the fiercest of all. Mighty waters cannot extinguish love; rivers cannot sweep it away.”
በትዳር ውስጥ የፍቅር ትስስር ጠንካራ ነው ፡፡ ሰሎሞን እና ሚስቱ በፍቅር ግንኙነታቸው ውስጥ የመግባባትን እና የወሲባዊ ደስታን ሚዛን ያንጸባርቃሉ ፡፡ እንደጋና ከተገናኙ በኋላ ተመልሰው ልክ እንደ ሰርጋቸው ምሽት አንዳቸው ለአንዳቸው ደስታን ይሰጣጣሉ ፡፡ ይህንን ለማድረግ ቆም ብለው ወደ መጀመሪያ ፍቅራቸው መመለስ ነበረባቸው ፡፡
እግዚአብሔር ትዳርን ለባልና ለሚስት ሲያዘጋጀው በእንድነት ደስታን እንዲያጣጥሙ ፣ የስሜት እና አካላዊ ትስስር እንድኖራቸው ልክ “ ፍቅር ብርቱ ናት ፤ ብዙ ውኃ እንኳ ያጠፋት ዘንድ አይችልም ፡፡ “ በጋብቻህ ውስጥ ስሜታዊና በአካላዊ ግንኙነት ለማድርግ ፤ ልክ እግዚአብሔር እንደሰራው በጥልቀት ለመተሳሳር አንድ ስጋ ለመሆን ጊዜ ትወስዳለህን ? እውነቱን መልስ ፡፡ ቀላል ነው ልጆች ፣ ስራ ደግሞም የተደራረበ ፕሮግራም ከባለቤትህ ጋር ፍቅርን ከመሰጣጠት እንድከለክሉህ መፍቀድ ፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት አይሆንም ፡፡ ዛሬ ለትዳርህ ዳግም መመለስ እንደ ቀድሞ መሆን የምትጸልይበት ቀን ነው ፡፡ እንድህ ተባባሉ እስኪ “ ፍቅርህ/ሽ የታለ ? አንተን ማየት እችል ዘንድ ተመለስ/ሽ ተመለስ/ሽ ፡፡ “ እግዚአብሔር ፍቅራችሁ አንድ እንድሆን ለዘላለም እንድጣመር ይፈልጋል ፡፡ ዛሬ ፍቅራችሁ እንድመለስ ፣ መግባባታችሁ እንድመለስ ደግሞም ትስስራችሁ እንድመለስ ጸልዩ ፡፡ በመጀመሪያ በአንድነት እግዚአሔርን ፈልጉ እርሱም የፍቅርን እሳት እንደጋና ያነደዋል ፡፡ በእምነት ውጡ ልክ ክርስቶስ እንደወደዳችሁም እንዳችሁ ሌላችሁን ውደዱ ፡፡
“ ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው ። ብዙ ውኃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም፥ ፈሳሾችም አያሰጥሙአትም “ - መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 8፡6-7
ተጨማሪ ጥቅስ
- መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 6:1,13a— “ አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከአንቺ ጋር እንፈልገው ዘንድ ውድሽ ወዴት ሄደ? ውድሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ ……….
- ኤፌሶን 5:25–26— “ ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ “
- 1ኛ ዮሐንስ 4:19— “ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።