The Power Of The Gospel
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Justifier Romans 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ጳዉሎስ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ ከ21 ደብዳቤዎች/መልዕክቶች ዉስጥ ከግማሽ በላዩን ፅፏል ፡፡ የዛሬዉ ትምህርት ስለዚህ አዲስ ክፍል ስለ ጳዉሎስ ደብዳቤዎች እና ስለ ሮሜ እንዲሁም ስለ ራሱ ሮሜ 1 አጠቃላይ ዕይታን/ዳሰሳን ያካትታል ፡፡ የጳዉሎስ ደብዳቤዎች ለአካባቢዉ ሰዎች በእጅ የተሰጡ ናቸው ፤ ሁሉም ደብዳቤ ተደራሽ እና ፍሬ ነገር ነበረው ፡፡ ጳዉሎስ ሮሜን በሮሜ ላሉ አማኞች በመፃፍ በዚህ ደብዳቤም ለእነርሱ ራሱን በግልፅ ገልፆአል ፡፡ በመጀመሪያ ጳዉሎስ ሳዎል በመባል የሚታወቅ የብንያም ነገድ ነበር ፤ የሮማዊ ዜጋም ነበር (ሐዋ 16፡ 37) ፡፡ ጳዉሎስ ክርስቶስ ተወልደቦት በነበረዉ ጊዜ አካባቢ በጠርሴስ የተወለደ ነበር ፡፡ ከክርስቶስ ሞት 33-34 በኋላ ጳዉሎስ ራሱ ኢየሱስን ባገኘዉ ጊዜ ኢየሱስን ያመኑትን አይሁዶች እያሳደደ በደማስቆ መንገድ ላይ እየተጓዘ ነበር ፤ ወዲያዉኑም በምኩራብ ላይ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ መናገር ጀመረ (ሐዋ 9፡ 20) ፡፡ ገላ (1፡ 17-19) ኬፋን እና ያዕቆብን (የኢየሱስን ወንድም) ወዳገኘበት ስፍራ ወደ ኢየሩሳሌም ከመጓዙ በፊት ወደ አረብ እንደሄደና ከዚያም ለሰዎስት አመታት ደማስቆ እንደተመለሰ ይናገራል ፡፡
ጳዉሎስ ከኢየሱስ መገለጥ በተቀበለ ጊዜ ለሰዎስት አመታት ጠፍቷል (ገላ 1፡ 11-12) ፡፡ ጳዉሎስ በአጠቃላይ በሮማዊያን ግዛት ዉስጥ ክርስትና እንዲስፋፋ ኃላፊነት ነበረበት ፤ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ሰዎስት የጳዉሎስን የአገልግሎት ጎዞዎችን ይገልፃል - ከተቀየረ በኋላ የሕይወቱ ጊዜ ሰሌዳ/የጊዜ ዕቅዱ ነው ፡፡ ሁሉም የፃፋቸዉ መልዕክቶቹ (ልክ ዳዊት ስሜቱን እንደሚገልፅበት ) የደረሱበትን የሚገልፁ መዝሙሮች ነበሩ ፤ በመልዕክቶቹ ጳዉሎስ ከዚህ በፊት ጎብኝቷቸዉ የነበረዉን መልሶ ወይም ወደ ፊት ሊጎበኛቸዉ የሚፈልጋቸዉን ፅፏል ፡፡ 2ቆሮ (10፡ 10) የጳዉሎስ “ መልዕክቶቹስ ከባድና ኃይለኛ ናቸው ሰዉነቱ ግን ሲታይ ደካማ ነው ንግግሩም የተናቀ ነዉ ይላሉ “ በማለት ይናገራል ፡፡ ጳዉሎስ ያገኘዉ ኃይሉና ጥንካሬዉ ምንጩ እግዚአብሄር ነው (ፊል 4፡ 13) ፤ ጳዉሎስ አግኝቶት የነበረዉ የእግዚአብሄር ፀጋ በቂዉ ነበር (2ቆሮ 12፡ 9-10) ፡፡ ይህ ሁሉ ጳዉሎስ ሩጫዉን/ዉድድሩን በሚገባ እንዲጨርስ አስቻለዉ (2ጢሞ 4፡ 7) ፡፡
ሮሜ በጳዉሎስ የሰወስተኛ አገልግሎት ጉዞ መጨረሻ ላይ አካባቢ በቆሮንቶስ እያገለገለ በነበረበት ጊዜ ተፃፈ (ሮሜ 16፡ 1, 23) ፡፡ ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ቢሄድም ሮሜን መጎብኘት ፈለገ (ሮሜ 15፡ 25) ፤ ቆይቶም ወደ ሮም ይህን አላደረገም/አልሄደም ነገር ግን ይህን ደብዳቤ/መልዕክት በፌበን በኩል ላከ (ሮሜ 16፡ 1) ፡፡ በኢየሩሳሌም እያለ ጳዉሎስ በሮማዉያን ተደብድቦ ታሰረ ፤ ጳዉሎስ ጥፋተኛ እንዳልነበር ቢያዉቁም እንኳን ለሁለት አመታት በእስር ቤት አስቀመጡት (ሐዋሪያት ስራ 21) ፡፡ ጳዉሎስ ጉዳዩን ለቂሳርያ ይግባኝ ለማለት/ለማቅረብ ወደ ሮም ለመሄድ በመርከብ ላይ ተቀምጦ ነበር ነገር ግን በጉዞ ላይ የመርከብ አደጋ ተፈጠረ/ነበር ፡፡ አንድ ጊዜ በሮም እንደ ገና ከመታሰሩ በፊት አንድ ጊዜ እንዳገለገለ እና ከክርስቶስ ሞት 65-67 በኋላ የቀደሙት ቤተ ክርስቲያናት ተሰዉቶ ነበር ይላሉ (2ጢሞ 4፡ 6) ፡፡
ሮሜ የሮማዉያን ግዛት ዋና ከተማ ነበረች በጊዜዉም በጣም አስፈላጊ/ጠቃሚ ከተማ ነበረች ፤ ከክርስቶስ ልደት 753 በፊት ላይ ተመሰረተች … ከተማዋ አዲስ ኪዳን እስኪመጣ ድረስ በአጠቃላይ በመፅሀፍ ላይ የተጠቀሰች አልነበረችም ፤ ሮሜ ከባህር 15 ማይል ከሚርቅ ከአንድ ወንዝ አጠገብ የምትገኝ ስፍራ ነበረች ፤ በጳዉሎስ ዘመን በሮም 1ሚሊዮን ህዝብ እንደሚኖሩና አብዛኞቹም ባሪያዎች እንደ ነበሩ ይገመታል ፡፡ ቀደምት ቤተ ክርስቲያን ጳዉሎስ በኔሮ ዘመን ጊዜ ከሮም ዉጪ በዖስቴን መንገድ ላይ እንደተሰዋ/እንደተገደለ ያቀርባሉ ፡፡ ምናልባትም በሮም የነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን በበዓለ ሀምሳ ቀን በኢየሩሳሌም (ሐዋሪያት ስራ 2) በነበሩት የተጀመረች ነበረች ፡፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን/ደብዳቤዉን ወደ ሮም መምጣት እንደፈለገ ነገር ግን ለመምጣት እንደተከለከለ በመናገር መልዕክቱን ጀመረ (ሮሜ 1፡ 13) ፡፡ ሮሜ ለማጥናት ብዛት ያለዉ እና ትልቅ ሊሆን ይችላል ፤ ማክአርቱር የጳዉሎስ ዋና አላማ ሮሜን በመፃፉ “ ሐዋሪያታዊ ትዕዛዞችን በፍፁም ተቀብለዉ ላልነበሩት አማኞች የፀጋዉን ወንጌል ታላቅ እዉነት ማስተማር ነበር “ ይላል ፡፡ ከሌሎቹ መልዕክቶች በተለዬ ሮሜ ለተበላሸ/ለመጥፎ አስተምሮ ምላሽ እንዲሆን አልተፃፈም ነበር ምክንያቱም ሰዎች እግዚአብሄራዊ በሆነ አኗኗር እየኖሩ ስላልነበር ፡፡ ይህ በሮም ላሉት አማኞች በስልጣን እዉነትን የማካፈል የጳዉሎስ ንግግር ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በአራት ምክንያቶች ፃፈላቸው፡ ሊያፀናቸው (ሮሜ 1፡ 11)፣ ወንጌልን ሊያስተምራቸዉ/ሊሰብካቸው (ሮሜ 1፡ 15)፣ በመተዋወቅ እርሱን ሊያበረቱት ስለሚችሉት (ሮሜ 1፡ 12)፣ ለእርሱ እንዲፀልዩለት (ሮሜ 15፡ 30) እና አገልግሎት መስራቱን እንዲቀጥል ጳዉሎስን እንዲረዱት (ሮሜ 15፡ 28) ፡፡
የመፅኀፍ ቅዱስን እያንዳንዱን መፅሀፍት ስናጠና በዚያ መፅሀፍት ዉስጥ ክርስቶስን ይገልፀዋል ብለን ባመነዉ አንድ ቃል ወይም ሀረግ መጥተናል ፤ ለሮሜ መፅሀፍት አንድ ቃላችን አፅዳቂ የሚል ነው (ሮሜ 4፡ 23-25) ፡፡ በግልፅ ኢየሱስ በእኛ ስፍራ ላይ የመጣ አየሚፀድቀን መልሳችን ስለሆነ ህይወት ሊኖረን ቻለ ፡፡ የዚህን ነፃ አዉጪ እና አፅዳቂ ፍሬ ነገር/ጭብጥ በእግዚአብሄር አብ ቀኝ ባስቀመጠን በኢየሱስ ላይ ታዩታላችሁ ፡፡ ስለመስቀሉ በምታስቡ ጊዜ እንደ አፅዳቂ ስለ ኢየሱስ ማሰብ ትጀምራላችሁ ፡፡
ትምህርት
ሮሜ (1፡ 1-7)፡ በመጀመሪያዎቹ አራት ቁጥሮች ዉስጥ ጳዉሎስ ራሱን እንደ ክርስቶስ አገልጋይ፣ ሐዋሪያ እና አስተማሪይ ያስተዋዉቃል ፤ ጳዉሎስ “ ለእግዚአብሄር ወንጌል የተለዬ ነበር “ (ቁጥር 1) ፤ በተጨማሪም ጳዉሎስ ለአሕዛቦች ምዕክተኛም ነበር ፤ በህይወቱ ሙሉ ጥሪዉ ከእነርሱ ጋር ወንጌልን ለመነጋገር/ለማጋራት ነበር (ቁጥር 5)፡፡
ሮሜ (1፡ 8-15)፡ እንደ ዋረን ዋይርስቤ አገላለፅ ለእነርሱ ጳዉሎስ የገለፀዉ ፍላጎቱ/ሀሳቡ ስለ እነርሱ ያመሰግን እንደ ነበር (ቁጥር 8)፣ ስለ እነርሱ እንደሚፀልይ (ቁጥር 9-10)፣ እንደሚወዳቸው (ቁጥር 11-12)፣ ስለ እነርሱም እዳ እንደነበረበት (ቁጥር 13-14) እና ሊያያቸዉ ጓጉቶ እንደ ነበር (ቁጥር 15) ነው ፡፡
ሮሜ (1፡ 16-17)፡ ጳዉሎስ በወንጌል ያፍር ስላልነበረ መጀመሪያ ወደ አይሁዶች ከዚያም ቀጥሎ ወደ አሕዛብ ተናገረ/አደረሰ (ቁጥር 16) ፡፡ ስለ ወንጌል “ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተፃፈ የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣል “ (ቁጥር 17) ፡፡ ጳዉሎስ ያመነዉን ከመናገር የሚያስቆመዉ ምንም ነገር አልነበረም ስደት ቢሆን፣ ግርፋት ቢሆን የመርከብ አደጋም ቢሆን እንኳን አያስቆመዉም ነበር ፡፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን ሰበከ/አስተማረ ነገር ግን ስራዉን የሰራዉ (አሁንም የሚሰራዉ) የእግዚአብሄር ኃይል እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ ጳዉሎስ ወንጌልን ለመናገር ጓጉቶ ስለነበር ሰዎቹ ከመንፈሳዊ አላዋቂነታቸዉ እና በራሳቸዉ ከሚያደርጉት ክፋት እንዴት ነፃ መዉጣት እንደሚችሉ እና ከእግዚአብሄር ቁጣ እንዴት እንደዳኑ ማየት ቻሉ ፡፡ በሚገባ ወንጌል ሰዎችን ነፃ ማዉጣት ይችላል ነገር ግን የእግዚአብሄር ኃይል ብቻ የሰዉን ልጅ የኃጢዓት ተፈጥሮ የሚቋቋም እና አዲስ ህይወት መስጠት ይችላል ፡፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ በእነዚህ ምክንያቶች በወንጌል ሙሉ እምነት እንደነበረዉ ያመለክታል፡ “ የወንጌል መነሻ የክርስቶስ ወንጌል ስለሆነ ፤ የወንጌል መስሪያ/ማከናወኒያ የእግዚአብሄር ኃይል ስለሆነ ፤ የወንጌል ዉጤት ለድነት የእግዚአብሄር ኃይል ስለሆነ ፤ የወንጌል መዳረሻዉ ሁሉም እንዲያምኑ ስለሆነ “ ፡፡
የጳዉሎስ አገልግሎት መጀመሪያ ለአይሁድ ቀጥሎ ለአሕዛብ ነበር ፡፡ የክርስቶስ አገልግሎት መጀመሪያ ለእስራኤል እና በእስራኤል ዉስጥ ነበር፣ ወንጌልም ለአለም መጣ ፤ ይህ ወንጌል ወደ ሁሉም ሰዉ ይሄዳል ማለት ነው ፡፡
መደምደሚያ
ሮሜ 1 በማንበብ ጊዜ አሳልፉ ፤ ስታነቡት እንዳትቸኩሉ/እንዳትጣደፉ ነገር ግን በሚገባ ለማንበብ እና ለማብላላት ለራሳችሁ ጊዜ ስጡ ፡፡ በትክክል ጳዉሎስ የፃፈዉን መኖር በምትጀምሩ ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ትችላላችሁ ? ማህበረሰባችን ሙሉ ለሙሉ የተለየ ይሆናል ፤ በክርስቶስ በሆነዉ ሙሉ ለሙሉ ያፈርን ካልነበር ሰዎች “ ያ እብድ ሰዉ መጣ “ ወይም የሰዎች ኑሮ ሙሉ ለሙሉ ተቀየረ ይላሉ ፡፡ በወንጌል አትፈሩ - ምንም ነገር አታጡም ፤ አንድ ሰዉን ስለ ወንጌል ስትናገሩ በእናንተ ዉስጥ የእግዚአብሄር ኃይል ስለሚሰራ ድነትን ሊቀበሉ ይችላሉ ፡፡
John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1499.
MacArthur, p. 1499.
MacArthur, p. 1499.
MacArthur, p. 1500.
MacArthur, p. 1500.
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 411.
Wiersbe, p. 412.
Wiersbe, p. 412.
ጥያቄዎች
-
ሮሜ (1፡ 1) ጳዉሎስን ቀድሞ እንደ ተለዬ አገልጋይ ይገልፀዋል ፤ የተለዬ አገልጋይ ምንድን ነዉ ጳዉሎስ ራሱን ለምን እንደ አንዱ ሐዋሪያ እንደጠቀሰ ምን ታስባላችሁ ? ለኢየሱስ ክርስቶስ ራሳችሁን እንደ ተለዬ አገልጋይ ትመለከታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታዩም ?
-
ጳዉሎስ “ በደማስቆ መንገድ “ ላይ ገጥመቶ በነበረዉ ነገር ለእግዚአብሄር ሳይታዘዝ ቀርቶ በነበር ለአሕዛቦች ምን ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ሐዋ 9፡ 3-9) ሐናንያ ሳይታዘዝ ቀርቶ በነበር ምን ይፈጠር ነበር ? እግዚአብሄር ሳዖልን ወንጌልን ለአሕዛብ እንዲያደርስ ለምን እንደመረጠዉ ምን ታስባላችሁ ?
-
በሮሜ (1፡ 16) ጳዉሎስ “ በወንጌል አላፍርም “ አለ ፤ እንደሱ ተመሳሳይ ማለት ትችላላችሁ አዎ ከሆነ ድርጊታችሁ ይገልጠዋል ?
-
ሮሜ (1፡ 20) ምን ማለት ነው ? ይህ አንድ ሰዉ አምላክ የለሽ ለመሆን በሚናገር ጊዜ ለመጠቀም ጥሩ ጥቅስ ይሆናል ? እግዚአብሄርን በተፈጥሮ ዉስጥ ታዩታላችሁ ?
-
ሮሜ (1፡ 24, 26) እግዚአብሄር “ ለሚያስነዉር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው “ እርስ በእርሳቸዉም በመካከላቸዉ “ ባህሪያቸዉን ለወጡ “ ይላል ፤ ይህ ማለት እግዚአብሄር እርስ በእርሳቸዉ ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ወሲብ እንዲያደርጉ ፍላጎት ሰጣቸዉ/አሳደረባቸዉ ማለት ነው ? (ዘሌ 18፡ 22, መሳ 17፡ 6, 21፡ 25, ሮሜ 1፡ 21, 1ጢሞ 1፡ 9-10፣ ይሁዳ 7)
-
የጽድቅ ህይወት ባለመኖር ምክንያት የሚመጡ በሮሜ የጠቀሳቸዉን ጥቂት ሌላ ነገሮችን ተናገሩ ፤ ከሌሎቹ “ በይበልጥ ስህተት “ የሆኑ ሌላ ነገሮች አሉ ? (ዘጸ 20፡ 1-17, ያዕ 2፡ 10)
-
በሮሜ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Romans 1:15–16
“So I am eager to preach the good news to you also who are in Rome. For I am not ashamed of the gospel, because it is God’s power for salvation to everyone who believes, first to the Jew, and also to the Greek.”
መግቢያ
ጳዉሎስ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ ከ21 ደብዳቤዎች/መልዕክቶች ዉስጥ ከግማሽ በላዩን ፅፏል ፡፡ የዛሬዉ ትምህርት ስለዚህ አዲስ ክፍል ስለ ጳዉሎስ ደብዳቤዎች እና ስለ ሮሜ እንዲሁም ስለ ራሱ ሮሜ 1 አጠቃላይ ዕይታን/ዳሰሳን ያካትታል ፡፡ የጳዉሎስ ደብዳቤዎች ለአካባቢዉ ሰዎች በእጅ የተሰጡ ናቸው ፤ ሁሉም ደብዳቤ ተደራሽ እና ፍሬ ነገር ነበረው ፡፡ ጳዉሎስ ሮሜን በሮሜ ላሉ አማኞች በመፃፍ በዚህ ደብዳቤም ለእነርሱ ራሱን በግልፅ ገልፆአል ፡፡ በመጀመሪያ ጳዉሎስ ሳዎል በመባል የሚታወቅ የብንያም ነገድ ነበር ፤ የሮማዊ ዜጋም ነበር (ሐዋ 16፡ 37) ፡፡ ጳዉሎስ ክርስቶስ ተወልደቦት በነበረዉ ጊዜ አካባቢ በጠርሴስ የተወለደ ነበር ፡፡ ከክርስቶስ ሞት 33-34 በኋላ ጳዉሎስ ራሱ ኢየሱስን ባገኘዉ ጊዜ ኢየሱስን ያመኑትን አይሁዶች እያሳደደ በደማስቆ መንገድ ላይ እየተጓዘ ነበር ፤ ወዲያዉኑም በምኩራብ ላይ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ መናገር ጀመረ (ሐዋ 9፡ 20) ፡፡ ገላ (1፡ 17-19) ኬፋን እና ያዕቆብን (የኢየሱስን ወንድም) ወዳገኘበት ስፍራ ወደ ኢየሩሳሌም ከመጓዙ በፊት ወደ አረብ እንደሄደና ከዚያም ለሰዎስት አመታት ደማስቆ እንደተመለሰ ይናገራል ፡፡
ጳዉሎስ ከኢየሱስ መገለጥ በተቀበለ ጊዜ ለሰዎስት አመታት ጠፍቷል (ገላ 1፡ 11-12) ፡፡ ጳዉሎስ በአጠቃላይ በሮማዊያን ግዛት ዉስጥ ክርስትና እንዲስፋፋ ኃላፊነት ነበረበት ፤ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ሰዎስት የጳዉሎስን የአገልግሎት ጎዞዎችን ይገልፃል - ከተቀየረ በኋላ የሕይወቱ ጊዜ ሰሌዳ/የጊዜ ዕቅዱ ነው ፡፡ ሁሉም የፃፋቸዉ መልዕክቶቹ (ልክ ዳዊት ስሜቱን እንደሚገልፅበት ) የደረሱበትን የሚገልፁ መዝሙሮች ነበሩ ፤ በመልዕክቶቹ ጳዉሎስ ከዚህ በፊት ጎብኝቷቸዉ የነበረዉን መልሶ ወይም ወደ ፊት ሊጎበኛቸዉ የሚፈልጋቸዉን ፅፏል ፡፡ 2ቆሮ (10፡ 10) የጳዉሎስ “ መልዕክቶቹስ ከባድና ኃይለኛ ናቸው ሰዉነቱ ግን ሲታይ ደካማ ነው ንግግሩም የተናቀ ነዉ ይላሉ “ በማለት ይናገራል ፡፡ ጳዉሎስ ያገኘዉ ኃይሉና ጥንካሬዉ ምንጩ እግዚአብሄር ነው (ፊል 4፡ 13) ፤ ጳዉሎስ አግኝቶት የነበረዉ የእግዚአብሄር ፀጋ በቂዉ ነበር (2ቆሮ 12፡ 9-10) ፡፡ ይህ ሁሉ ጳዉሎስ ሩጫዉን/ዉድድሩን በሚገባ እንዲጨርስ አስቻለዉ (2ጢሞ 4፡ 7) ፡፡
ሮሜ በጳዉሎስ የሰወስተኛ አገልግሎት ጉዞ መጨረሻ ላይ አካባቢ በቆሮንቶስ እያገለገለ በነበረበት ጊዜ ተፃፈ (ሮሜ 16፡ 1, 23) ፡፡ ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ቢሄድም ሮሜን መጎብኘት ፈለገ (ሮሜ 15፡ 25) ፤ ቆይቶም ወደ ሮም ይህን አላደረገም/አልሄደም ነገር ግን ይህን ደብዳቤ/መልዕክት በፌበን በኩል ላከ (ሮሜ 16፡ 1) ፡፡ በኢየሩሳሌም እያለ ጳዉሎስ በሮማዉያን ተደብድቦ ታሰረ ፤ ጳዉሎስ ጥፋተኛ እንዳልነበር ቢያዉቁም እንኳን ለሁለት አመታት በእስር ቤት አስቀመጡት (ሐዋሪያት ስራ 21) ፡፡ ጳዉሎስ ጉዳዩን ለቂሳርያ ይግባኝ ለማለት/ለማቅረብ ወደ ሮም ለመሄድ በመርከብ ላይ ተቀምጦ ነበር ነገር ግን በጉዞ ላይ የመርከብ አደጋ ተፈጠረ/ነበር ፡፡ አንድ ጊዜ በሮም እንደ ገና ከመታሰሩ በፊት አንድ ጊዜ እንዳገለገለ እና ከክርስቶስ ሞት 65-67 በኋላ የቀደሙት ቤተ ክርስቲያናት ተሰዉቶ ነበር ይላሉ (2ጢሞ 4፡ 6) ፡፡
ሮሜ የሮማዉያን ግዛት ዋና ከተማ ነበረች በጊዜዉም በጣም አስፈላጊ/ጠቃሚ ከተማ ነበረች ፤ ከክርስቶስ ልደት 753 በፊት ላይ ተመሰረተች … ከተማዋ አዲስ ኪዳን እስኪመጣ ድረስ በአጠቃላይ በመፅሀፍ ላይ የተጠቀሰች አልነበረችም ፤ ሮሜ ከባህር 15 ማይል ከሚርቅ ከአንድ ወንዝ አጠገብ የምትገኝ ስፍራ ነበረች ፤ በጳዉሎስ ዘመን በሮም 1ሚሊዮን ህዝብ እንደሚኖሩና አብዛኞቹም ባሪያዎች እንደ ነበሩ ይገመታል ፡፡ ቀደምት ቤተ ክርስቲያን ጳዉሎስ በኔሮ ዘመን ጊዜ ከሮም ዉጪ በዖስቴን መንገድ ላይ እንደተሰዋ/እንደተገደለ ያቀርባሉ ፡፡ ምናልባትም በሮም የነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን በበዓለ ሀምሳ ቀን በኢየሩሳሌም (ሐዋሪያት ስራ 2) በነበሩት የተጀመረች ነበረች ፡፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን/ደብዳቤዉን ወደ ሮም መምጣት እንደፈለገ ነገር ግን ለመምጣት እንደተከለከለ በመናገር መልዕክቱን ጀመረ (ሮሜ 1፡ 13) ፡፡ ሮሜ ለማጥናት ብዛት ያለዉ እና ትልቅ ሊሆን ይችላል ፤ ማክአርቱር የጳዉሎስ ዋና አላማ ሮሜን በመፃፉ “ ሐዋሪያታዊ ትዕዛዞችን በፍፁም ተቀብለዉ ላልነበሩት አማኞች የፀጋዉን ወንጌል ታላቅ እዉነት ማስተማር ነበር “ ይላል ፡፡ ከሌሎቹ መልዕክቶች በተለዬ ሮሜ ለተበላሸ/ለመጥፎ አስተምሮ ምላሽ እንዲሆን አልተፃፈም ነበር ምክንያቱም ሰዎች እግዚአብሄራዊ በሆነ አኗኗር እየኖሩ ስላልነበር ፡፡ ይህ በሮም ላሉት አማኞች በስልጣን እዉነትን የማካፈል የጳዉሎስ ንግግር ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በአራት ምክንያቶች ፃፈላቸው፡ ሊያፀናቸው (ሮሜ 1፡ 11)፣ ወንጌልን ሊያስተምራቸዉ/ሊሰብካቸው (ሮሜ 1፡ 15)፣ በመተዋወቅ እርሱን ሊያበረቱት ስለሚችሉት (ሮሜ 1፡ 12)፣ ለእርሱ እንዲፀልዩለት (ሮሜ 15፡ 30) እና አገልግሎት መስራቱን እንዲቀጥል ጳዉሎስን እንዲረዱት (ሮሜ 15፡ 28) ፡፡
የመፅኀፍ ቅዱስን እያንዳንዱን መፅሀፍት ስናጠና በዚያ መፅሀፍት ዉስጥ ክርስቶስን ይገልፀዋል ብለን ባመነዉ አንድ ቃል ወይም ሀረግ መጥተናል ፤ ለሮሜ መፅሀፍት አንድ ቃላችን አፅዳቂ የሚል ነው (ሮሜ 4፡ 23-25) ፡፡ በግልፅ ኢየሱስ በእኛ ስፍራ ላይ የመጣ አየሚፀድቀን መልሳችን ስለሆነ ህይወት ሊኖረን ቻለ ፡፡ የዚህን ነፃ አዉጪ እና አፅዳቂ ፍሬ ነገር/ጭብጥ በእግዚአብሄር አብ ቀኝ ባስቀመጠን በኢየሱስ ላይ ታዩታላችሁ ፡፡ ስለመስቀሉ በምታስቡ ጊዜ እንደ አፅዳቂ ስለ ኢየሱስ ማሰብ ትጀምራላችሁ ፡፡
ትምህርት
ሮሜ (1፡ 1-7)፡ በመጀመሪያዎቹ አራት ቁጥሮች ዉስጥ ጳዉሎስ ራሱን እንደ ክርስቶስ አገልጋይ፣ ሐዋሪያ እና አስተማሪይ ያስተዋዉቃል ፤ ጳዉሎስ “ ለእግዚአብሄር ወንጌል የተለዬ ነበር “ (ቁጥር 1) ፤ በተጨማሪም ጳዉሎስ ለአሕዛቦች ምዕክተኛም ነበር ፤ በህይወቱ ሙሉ ጥሪዉ ከእነርሱ ጋር ወንጌልን ለመነጋገር/ለማጋራት ነበር (ቁጥር 5)፡፡
ሮሜ (1፡ 8-15)፡ እንደ ዋረን ዋይርስቤ አገላለፅ ለእነርሱ ጳዉሎስ የገለፀዉ ፍላጎቱ/ሀሳቡ ስለ እነርሱ ያመሰግን እንደ ነበር (ቁጥር 8)፣ ስለ እነርሱ እንደሚፀልይ (ቁጥር 9-10)፣ እንደሚወዳቸው (ቁጥር 11-12)፣ ስለ እነርሱም እዳ እንደነበረበት (ቁጥር 13-14) እና ሊያያቸዉ ጓጉቶ እንደ ነበር (ቁጥር 15) ነው ፡፡
ሮሜ (1፡ 16-17)፡ ጳዉሎስ በወንጌል ያፍር ስላልነበረ መጀመሪያ ወደ አይሁዶች ከዚያም ቀጥሎ ወደ አሕዛብ ተናገረ/አደረሰ (ቁጥር 16) ፡፡ ስለ ወንጌል “ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተፃፈ የእግዚአብሄር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣል “ (ቁጥር 17) ፡፡ ጳዉሎስ ያመነዉን ከመናገር የሚያስቆመዉ ምንም ነገር አልነበረም ስደት ቢሆን፣ ግርፋት ቢሆን የመርከብ አደጋም ቢሆን እንኳን አያስቆመዉም ነበር ፡፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን ሰበከ/አስተማረ ነገር ግን ስራዉን የሰራዉ (አሁንም የሚሰራዉ) የእግዚአብሄር ኃይል እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ ጳዉሎስ ወንጌልን ለመናገር ጓጉቶ ስለነበር ሰዎቹ ከመንፈሳዊ አላዋቂነታቸዉ እና በራሳቸዉ ከሚያደርጉት ክፋት እንዴት ነፃ መዉጣት እንደሚችሉ እና ከእግዚአብሄር ቁጣ እንዴት እንደዳኑ ማየት ቻሉ ፡፡ በሚገባ ወንጌል ሰዎችን ነፃ ማዉጣት ይችላል ነገር ግን የእግዚአብሄር ኃይል ብቻ የሰዉን ልጅ የኃጢዓት ተፈጥሮ የሚቋቋም እና አዲስ ህይወት መስጠት ይችላል ፡፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ በእነዚህ ምክንያቶች በወንጌል ሙሉ እምነት እንደነበረዉ ያመለክታል፡ “ የወንጌል መነሻ የክርስቶስ ወንጌል ስለሆነ ፤ የወንጌል መስሪያ/ማከናወኒያ የእግዚአብሄር ኃይል ስለሆነ ፤ የወንጌል ዉጤት ለድነት የእግዚአብሄር ኃይል ስለሆነ ፤ የወንጌል መዳረሻዉ ሁሉም እንዲያምኑ ስለሆነ “ ፡፡
የጳዉሎስ አገልግሎት መጀመሪያ ለአይሁድ ቀጥሎ ለአሕዛብ ነበር ፡፡ የክርስቶስ አገልግሎት መጀመሪያ ለእስራኤል እና በእስራኤል ዉስጥ ነበር፣ ወንጌልም ለአለም መጣ ፤ ይህ ወንጌል ወደ ሁሉም ሰዉ ይሄዳል ማለት ነው ፡፡
መደምደሚያ
ሮሜ 1 በማንበብ ጊዜ አሳልፉ ፤ ስታነቡት እንዳትቸኩሉ/እንዳትጣደፉ ነገር ግን በሚገባ ለማንበብ እና ለማብላላት ለራሳችሁ ጊዜ ስጡ ፡፡ በትክክል ጳዉሎስ የፃፈዉን መኖር በምትጀምሩ ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ትችላላችሁ ? ማህበረሰባችን ሙሉ ለሙሉ የተለየ ይሆናል ፤ በክርስቶስ በሆነዉ ሙሉ ለሙሉ ያፈርን ካልነበር ሰዎች “ ያ እብድ ሰዉ መጣ “ ወይም የሰዎች ኑሮ ሙሉ ለሙሉ ተቀየረ ይላሉ ፡፡ በወንጌል አትፈሩ - ምንም ነገር አታጡም ፤ አንድ ሰዉን ስለ ወንጌል ስትናገሩ በእናንተ ዉስጥ የእግዚአብሄር ኃይል ስለሚሰራ ድነትን ሊቀበሉ ይችላሉ ፡፡
1 John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1499.
2 MacArthur, p. 1499.
3 MacArthur, p. 1499.
4 MacArthur, p. 1500.
5 MacArthur, p. 1500.
6 Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 411.
7 Wiersbe, p. 412.
8 Wiersbe, p. 412.
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።