Wisdom Books Song of Songs

Sex In Marriage

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Bridegroom Song of Songs 4-5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 485 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን በፍቅር የመዉደቅ ሂደትን ያሰፍራል - ማግባባትን፣ እጮኝነትን፣ ሰርግን እና ጋብቻን ፤ በጋብቻ ዉስጥም የወሲብ ስፍራን ያካትታል ፡፡ የመኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን ቋንቋ የተለየ ነዉ በተለይም በዛሬዉ ፅሁፍ ዉስጥ ያለዉ ቋንቋ ፡፡ በሰለሞን እና በሱናማይቷ ሴት ከኢየሩሳሌም ሴቶች፣ ከእግዚአብሄር በከረቶች እና ከሱናማይቷ ሴት ወንድሞች ጋር በአንድ ላይ መመልከታችንን እንቀጥላለን ፡፡ ትናትና ለማግባት ማግባባትን ተመልክተናል - በፍቅር በመዉደቅ ቤተሰብን ትቶ የመሄድ ጊዜን ተስፋ በማድረግ ፤ ዛሬ ወደ ሰርግ እና ጋብቻ ማሟላት ያለበት ነገሮች ላይ እንቀጥላለን ፡፡ እግዚአብሄር የወሲብ ግንኙነትን ለጋብቻ ሰራው/አዘጋጀው ፡፡

ትምህርት

መኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን (4፡ 1-4)፡ ሰለሞን የሴቲቷን ዉበት ገለፀ - አይኖቿን፣ ፀጉሯን፣ ጥርሷን፣ ከንፈሮቿን፣ አፏን፣ የራሷ ግንባር እና አንገቷ (ቁጥር 1-4) ፡፡ ከእዚህ ዉስጥ ጥቂቶቹ ለእኛ እንግዳ ነገር ይመስላሉ ነገር ግን ዋይርስቤ “ የቀድሞ ሰዎች በፍፁም የጥርስ ጤንነት አጠባበቅ ስለማይረዱ ይህ የሚደነቅ ባህሪይ ነው ፤ ጤነኛ ጥርስ አተነፋፈስ ላይ ተፅዕኖ ስለሚያደርግ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ በቁጥር 4 ሰለሞን የአንገቷን ዉበት “ አንገትሽ ለሰልፍ እቃ መስቀያ እንደ ተሰራው እንደ ዳዊት ግንብ ነው ፤ ሺህ ጋሻ የኃያላንም መሳሪያ ሁሉ ተንጠልጥሎበታል “ በማለት ገልፆታል ፤ እነዚህ ሁሉ የማረጋገጫ ቃላቶች ነበሩ ፡፡

መኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን (4፡ 5-7)፡ ሰለሞን ጡቶቿን እንደ ሁለት ሚዳቆ ግልገሎች በመግለፅ “ እንደ ከርቤ ተራራ እና እንድ ዕጣን ኮረብታ “ (ቁጥር 6) በማለት ሰይሟቸዋል ፡፡ ሰለሞን እንደ ፍፁም አያት - “ ነዉር/እንከን እንደሌለባት “ (ቁጥር 7) ፤ ይህ እንከን ወደሌለባት እና ንፁህ ወደ ሆነችዉ ሙሽራዉ የሚመለሰዉ የሙሽራዉ የኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ ነው ፡፡ ቁጥር 7 እግዚአብሄር የክርስቶስ አካል እንድትሆን የሚፈልገዉ እዉነተኛ ትንቢታዊ መልክ ነው - ንፁህነት/ፍፁምነት (2ቆሮ 11፡ 2) ፡፡ በክርስቶስ አይን ሐዋሪያቶች ነን ፤ ኮንስታብል “ ምናልባት ስለሞን እንዳወራለት ፍፁም ባትሆንም እንኳን ፤ ዉበት እንደ ባለቤቱ እይታ ስለሆነ ፤ ለእርሱ ፍፁም ነበረች “ በማለት ይገልፃል ፡፡

መኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን (4፡ 8-10)፡ ጋብቻ መጀመሪያ በቁጥር 8 የተጠቀሰ ነው - “ ሙሽራዬ “ በማለት ፤ ይህ ለጋብቻ በማግባባት እና በሟሟላት ሽግግር መካከል ይጀምራል ፡፡ ሰለሞን በማግባባት ጊዜ እና ለሰርግ ዝግጅት በመጠበቅ ከመሟላቱ በፊት ወሲባዉ ግንኙነት ከማድረግ የታቀቡ እንደ ነበር ግልፅ ነበር ፤ ሰለሞን ሴቲቱን በህይወቷ ሁሉንም ነገር በመተዉ ሙሉ ለሙሉ ከእርሱ ጋር መምጣት እንደምትችል ነገራት ፡፡ ሴቲቱ ልቡን እንደ መጀመሪያ ምልክት ይዛዉ ስለ ነበር ፍቅሯ አስደሳች ነበር (ቁጥር 9-10) ፤ ለእርሷ ከእርሱ ፍቅር ጋር የሚወዳደር ምንም ነገር የለም ፡፡ “ ማርና ወተት “ የእግዚአብሄርን በረከት ይገልፃሉ (ቁጥር 11) ፡፡

መኃለየ መኃለይ ዘሰሎሞን (4፡ 12-15)፡ በቁጥር 12 ንግግሩ በመቀየር በኃይል መቀራረብ ሆነ ፡፡ ሰለሞን እርሱና ሴቲቱ እስካሁን ወሲብ አድርገዉ እንዳልነበር እና ድንግል እንደ ነበረች ( “ የተቆለፈች ገነት ነች “ ) በማለት አመልክቷል ፡፡ ሙሽራዋ ንፁህ ሆና የተቀመጠች ነበረች ፤ ቁጥር 13-14 በኃይል በመነሳሳት ይገልፃጻል ፡፡ የተቆለፈች ገነት እና የታተመ ፈሳሽ ነበረች ፡፡

መኃለየ መኃለይ ዘሰሎሞን (4፡ 16)፡ ሱናማይቷ ሴት በመመለስም በቁጥር 16 ምን እንዲያደርግላት እንደምትፈልግ መግለፅ ጀመረች ፤ ለእርሱ ክፍት ነበረች - ከዚህ በኋላ የተቆለፈ እና የራቀች እንዳልሆነ ፡፡

ሁሉም ጥናቶች ባይስማሙም አንድ ጥናት ያገኘው አንድ ወንድ ድንግልናዉን የሚያጣበት አማካኝ እድሜ 16.9 እንደሆነ እና ለሴት ደግሞ አማካኝ እድሜዉ 17.2 ነው ፡፡ አብዛሀኛዉ የሴቶች ቁጥር (አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከ74 ፐርሰንት የሚበልጡት) ከጋብቻ በፊት በሚደረግ ወሲብ ነው ፤ ብሄራዊዊ የጤና መረጃ ማዕከል በ20 እና በ59 አመት መካከል የሚገኙ ሴቶች 59 ፐርሰንቶቹ ቢያንስ አራት የወሲብ አጋር እንደነበራቸዉ እና ወንዶች ደግሞ ቢያንስ ሰባት እንደነበራቸዉ አግኝቷል ፤ በጣም ብዙ ነው ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያቱ በጋብቻ ዉስጥ ለወሲባዊ ፍላጎትና ለማስረገዝ አንዱ ለአንዱ በሚተማመኑ ሁለት ሰዎች መካከል እግዚአብሄር ወሲባዊ ግንኙነትን መካከል እግዚአብሄር የሚፈልገዉን ጤነኛ ወሲብን አለማስተማራችን እንደሆነ አስባለሁ ፡፡ በማንጠብቅ ጊዜ ወይም ደግሞ ከጋብቻ ዉጪ ወሲብ ሲኖረን እግዚአብሄር የማይፈልጋቸዉ ዉጤቶችን ይደርሱብናል - የአባላዘር በሽጻዎች፣ ያልተፈለገ እርግዝና፣ ምናልባትም አካላዊ ጉዳቶች፣ ስሜታዊ ጉዳቶች እና ለሴቶች ለራስ አነስተኛ ግምት መስጠት/በራስ መተማመንን ማጣት ፡፡ አካላዊ፣ ስሜታዊና ግንኙነታዊዉ ጉዳዮች የተትረፈረቡ/በጣም ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡

መደምደሚያ

ወሲብን በጋብቻ ዉስጥ ለምን እንጠብቃለን ? በሚገባ ለእናንተ የተሰራዉን የተከበረ/የተወደደ ጋርደን ለምን ትጠብቃላችሁ ? መጀመሪያዉ የልብ ትስስር/መገናኘት ፍቅር ስለሚገባችሁ ትጠብቃላችሁ ፤ ሁለተኛው ሁሉም ሰዉ ይህን ስለማያደርግ ትጠብቃላችሁ ፤ ሰዎስተኛ ደህና/ደህንነቱ የተጠበቀ ስላልሆነ ትጠብቃላችሁ ፡፡

አንድ ወንድ ከአንድ ሰዉ ጋር ለመጣመር እናት እና አባቱን ይተዋል (ዘፍ 2፡ 24) ፤ በጋብቻ እና በወሲብ አንድ እንድንሆን ተሰርተናል (ማቴ 19፡ 5-6, ኤፌ 5፡ 31-32) ፡፡ ይህ የክርስቶስ እና የቤተ ክርስቲያንም መልክ ነው ፤ የተከበረዉ/የተወደደዉ ጋርደን እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር እንድንሆን አቅዶትበት ወደ ነበረዉ ስፍራ ወደ ኤደን ገነት መልሶ ይወስደናል ፡፡

4 “American Virgin: First-Time Sex Trends of U.S. Males and Females,” cited by Vera Papisova in “Find Out When Most Teens Are Losing Their Virginity,” Teen Vogue, September 30, 2015; available at https://www.teenvogue.com/story/teens-losing-virginity-age

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 546.

  2. Wiersbe, p. 546.

  3. Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Bible Study Expository Notes: Song of Solomon, p. 37; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/song.pdf.

  4. Guttmacher Institute, “Teenage Sexual and Reproductive Behavior in Developed Countries,” November 2001, p. 9; available at http://citeseerx.ist.psu.edu/viewdoc/download?- doi=10.1.1.295.3589&rep=rep1&type=pdf.

  5. National Center for Health Statistics”; cited in “New survey tells how much sex we’re having,” NBCNews.com; available at http://www.nbcnews.com/id/19374216/ns/health-sexu- al_health/t/new-survey-tells-how-much-sex-were-having/#.XLCU16YpBPM.

ጥያቄዎች

  1. ሙሽራዋ ቤተ ክርስቲያንን እንደምትወክል በመመልከት መኃ (4፡ 7) እንዴት ትገልፁታላችሁ ? (ኤፌ 5፡ 25-27)
  2. በመኃ (4፡ 10) ሙሽራዉ የእርሱን ሙሽራ በመናገር የሽቶዋ መዓዛ ከሁሉም ሽቶ እንደሚሻል ገለፀ ፤ ያ የምን ማጣቀሻ/ማሳያ ይሆናል (ዘጸ 30፡ 34-36, መዝ 141፡ 2, ራዕ 5፡ 8, 8፡ 3-4) ? እግዚአብሄር ፀሎታችንን እንዴት እንደሚያየዉ ያ በምን ይገልጣል ?
  3. መኃ (5፡ 2) ራዕ (3፡ 20) በማንበብ እንዴት የተሻለ መረዳት ይሆናል ?
  4. በመኃ (5፡ 2-6) እና በማቴ (25፡ 5-13) መካከል ምን አንድነት ታያላችሁ ?
  5. በመኃ (5፡ 16) ላይ የሙሽራዉን መግለጫዎች በማንበብ ይህ ኢየሱስን እንደሚገልፅ አስቡ ፤ እርሱን በተመለከተ ይህን አይነት ምላሽ ገጥሟችሁ ያውቃል ? ይህን እንዴት ትገልፁታላችሁ ? እግዚአብሄር ፍቅራችሁን ለእርሱ ለአካሉ ለቤተ ክርስቲያን በምን እንድትገልፁለት ይፈልጋል ? ያ በክርስቶስ ወንድሞቻችሁን እና እህቶቻችሁን እንዴት እንደምታዩ ይቀይራችኋል ?
  6. በመኃልየ መኃለይ ዘሰሎሞን (4-5) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Song of Songs 4:16

“Awaken, north wind—come, south wind. Blow on my garden, and spread the fragrance of its spices. Let my love come to his garden and eat its choicest fruits.”

እግዚአብሔር ጋብቻን ለአንድ ወንድ እና ለአንድ ሴት አድርጎ ሰራው ፡፡ በጋብቻ ኪዳን አንድ ስጋ ይሆኑ ዘንድ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ለአንድ ወንድ እና ሴት አዘጋጀ ፡፡ ይህ ኪዳን መሰበር የለበትም ፣ ከጋብቻ በፊት ይህን በማድረግ ወይም ደግሞ ከብዙ አጋሮች ጋር በማድረግ ፡፡ ከብዙ ተስፋና ጥበቃ በኋላ ሰሎሞንና ሚስቱ በሰርጋቸው ምሽት እርስ በእርስ ደስታን ተሰጣጡ ፡፡ ልክ እግዚአብሔር እንደሰራው በመካከላቸው ያለውን ፍቅርና ትስስር ግንኙነት ለማክበር ለመደሰት ፣ መጠበቅ ያስፈልገው ነበር ፡፡

የእግዚአብሔር የመጀመሪያ እቅድና አሳብ ለንጽህናና ለቅድስና ነበር ፡፡ ከእርሱ የመጀመሪያ እቅድ የሚያፈነግጥ የትኛውም ነገር መንፈሳዊ ደግሞም አካለዊ አደጋ ጣጣ አለው ፡፡ የወሲብን ፈተና እንድሁም የትኛውንም ከጋብቻ ኪዳን ውጪ የሆነ ርኩሰትን ትቋቋሙ ዘንድ ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ኃይል ላይ ታምናችሁ ተራመዱ ፡፡ ውበት ንጽህና የሚመጣው ስትታገሱ ፣ ፈተናን ስትቋቋሙ ደግሞም አቅምን ይሰጣችሁ ዘንድ በጌታ ላይ ስትደገፉ ነው ፡፡ በመጠበቅ በመታገስ ውስጥ ሳላችሁ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሆናል ፡፡ እናም ከዚያ ልክ እግዚአብሔር እንደሰራው ለባልና ለሚስት አብረው “ ወደ መኝታቸው ለመሄድ “ ጊዜው ሲደርስ ፣ እርሱ ውሳኔያችሁን ደግሞም አንዳችሁ ለአንዳችሁ ያላችሁን መሰጠት ይባርካል ደግሞም ያከብራል ፡፡ ጥልቅ ፍቅር መጠበቅ መታገስ ይገባዋል ፡፡

“ የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፤ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱውም ይፍሰስ፤ ውዴ ወደ ገነቱ ይግባ፥ መልካሙንም ፍሬ ይብላ ። “ - መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4፡16

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ማቴዎስ 19:5-6— “ አለም፦ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን ? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው ። “
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 7:2— “ ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት ። “
  • ዕብራውያን 13:4— “ መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል ። “