Wisdom Books Song of Songs

The Bridgegroom and the Bride

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Bridegroom Song of Songs 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 484 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ አምስተኛዉ እና የመጨረሻዉ የጥበብ መፅኀፍት እና የመፅሀፍ የግጥም ክፍል ነው ፡፡ በተጨማሪም ይህ መፅኀፍ ሰለሞን ስለፃፈው የሰለሞን መዝሙር በመባል የሚታወቅ ነው ፡፡ 1ነገ (4፡ 32) ከ3,000 በላይ ምሳሌዎችን ከመፃፍ በተጨማሪ ሰለሞን 1,005 መዝሙሮችን ፅፏል ፡፡ ዳዊት የመዝሙሮች አቀናባሪ/ደራሲ ስለነበር ልጁ ሰለሞን መዝሙር መፃፉ የሚያስገርም አይደለም ፡፡ “ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን “ በሚለዉ ርዕስ ይህን መዝሙር የምርጦች ምርጥ በማለት ማሰብ እንችላለን ፡፡ ሰለሞን ይህን መዝሙር በአንድነት መንግስት ላይ ለ40 አመታት ሲያስተዳድር ፃፈው ፤ “ ሰለሞን “ የሚለዉ ስም በመፅሀፉ ዉስጥ ቢያንስ ስለሚገኝ ፀሀፊዉ እንደነበር በእዉነት ጥያቄ የለም ፤ ብቸኛዉ ጥያቄ መቼ ፃፈዉ የሚል ነው ፡፡ ተፅፎ በነበረበት ጊዜ ላይ እንደ ጥቂት ተከታታይ ግጥም ወይም መዝሙር ሳይሆን እንደ አንድ መዝሙር የታዬ ነው ፡፡

በመዝሙሩ ዉስጥ ሁለት ዋና ገፀ ባህሪያት አሉ ፤ ከእነርሱ ዉስጥ አንዱ ሰለሞን ነው ፤ ሌላዉ ደግሞ ሱናማዊቷ ሴት ናት ፤ እሷ ማን ነበረች ? በመጀመሪያ ከኢይዝራኤል ሸለቆ በስተሰሜን 3ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘዉ ሹናሚ ከሚባል ስፍራ ነበረች ፡፡ የኢይዝራኤል ሸለቆ አንድ ቀን የአርማጌድዮን ጦርነት የሚደረግበት ቦታ ይሆናል ፡፡ በዚህ መዝሙር ዉስጥ ሰለሞን ፍቅሩን ለሱናማዊቷ ሴት እና በዙሪያዋ ለምትኖርባቸዉ ስፍራዎችም ገለፀ ፤ የፈርዖል ልጅ ልትሆን ትችላለች (ማስረጃ የለንም) ፤ ምናልባትም ለዳዊት በመጨረሻ ዘመኑ ላይ እንክብካቤ ያደረገችለት ሱናማይቷ አቢሳ ነበረች ፡፡ ነገር ግን ብዙ አዋቂዎች በሰለሞን ተቀጥረዉ ከነበሩት እና በዚያ አካባቢ ቤተሰቦቻ ይኖሩ ከነበሩት ከሱናሚያዊ የማትታወቅ አንድ ወጣት ነበረች ይላሉ ፡፡ በይበልጥ ሰለሞን “ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ “ (መክ 9፡ 9) ያለዉን የምትመስል ነበረች ፡፡ በይበልጥ የመጀመሪያ ሚስቱን ትመስል ነበር ምክንያቱም ሰለሞን 699 ሌሎች ሚስቶችን አግብቶ ስለ ነበር (1ነገ 11፡ 3) ፡፡ እንዲሁም ሰለሞን 700 ሚስቶች እና 300 ቁባቶች ስለነበሩት ይህ የመጀመሪያዉ የፍቅር ደብዳቤ የመሆን ጥሩ እድል አለው ፡፡

በመፅሀፉ ዉስጥ ጥቂት የሚጫወቱ ገፀ ባህሪያት አሉ ፤ አንዳንድ ትርጓሜዎች ከጥቂት ጥቅሶች ከኃላ ኤም እና ደብሊዉ አላቸው ፡፡ በዚህ መዝሙር ላይ ማን እያወራ እንደ ሆነ ለመለየት/ለማወቅ የሚያስቸግርበት ጊዜ አለ ፤ አንዳንድ ጊዜ ሰለሞን ይሆናል ወይም ደግሞ ሱናማይቷ ሴት ሲሆኑ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሌሎች አነስተኛ/ጥቂት ገፀ ባህሪያት ናቸው ፡፡ የሰለሞን ቤት ሰራተኞች አካል ከሆኑት ዉስጥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጆች ተናገሩ ፤ በተጨማሪም በጥቂቱ የእግዚአብሄርን በረከት የያዙ ጥቂት ክፍሎች አሉ ፤ ከዚያም የሱናማይቷ ወንድሞችም ነበሩ ፡፡ መዝሙሩን ማንበብ ከመጀመራችሁ በፊት በመዝሙሩ ላይ በተለያየ መንገድ የተናገሩትን ለመለየት ጊዜ መዉሰድ ፡፡

  • በመኃ (1፡ 2-3፡ 5) ለትዳር የማግባባት ነገር ይከናወናል ፤ ለትዳር ማግባባት ተስፋ የማድረግ መሰረታዊ ባህሪይን ያጠቃልላል ፤ ምል ሊመስል ይችላል ? እንዴት ይገለጣል/ይታወቃል ?
  • ሰርጉ በመኃ (3፡ 6 – 5፡ 1) ላይ የተገለፀ ነው ፤ ይህ ሰርጉን እና ትዳር/ጋብቻ የሚያሟላቸዉን ነገሮች ይይዛል ፡፡

ጋብቻ እና አከባበሩ በመኃ (5፡ 2- 8፡ 14) የተገለፁ ናቸዉ ፤ መዝሙሩ በትዳር ጊዜ ስለገጠሟቸዉ አስቸጋሪ/ጠንካራ ጊዜ ያወራል ፤ ወሲብ እናየጋብቻ ትስስር በእግዚአብሄር የታቀደ/የተሰራ እንደሆነ ለማስታወስ ይጠቅማል ፡፡ ሰይጣን ግን ወሲብን ለብቻው ዋና አላማዉ አድርጉ ለራሱ አላማ ብቻ ይጠቀምበታል ፡፡ ከዚህ መዝሙር ካገባችሁት አንድ ሰዉ ጋር ጤነኛ ወሲባዊ ግንኙነት ምን ማለት እንደሆነ ማየት እንችላለን ፡፡

ስለዚህ በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት ካከል ያለዉ ግንኙነት እንዴት ወደ መሲሁ ያመለክታል ? እንዴት ሙሽራዉ እና ሙሽሪት መስተጋብር እንደሚፈጥሩ ማየት እንጀምራለን ፡፡ የእግዚአብሄር የጋብቻ እቅድ በሁለት ሰዎች መካከል ያለ ወሲባዉ መቀራረብን ያካትታል፣ በመጨረሻም ይህ የቤተ ክርስቲያንን እና የክርስቶስን መልክ ነው ፡፡ ሰለሞን ወደ መጨረሻዉ/ዋናው ሙሽራ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያመለክት የሙሽራ አይነት ነው ፡፡ በ 2ቆሮ (11፡ 2) የክርስቶስ አካል ቤተ ክርስቲያን ለአንድ ባል ለክርስቶስ ተስፋ ተገብታለች ይላል ፤ ራዕ (19፡ 7) የበጉን(ክርስቶስ) ጋብቻ በቅዱሳን የፅድቅ ተግባር በሆነዉ ራሷን በቀጭን የተልብ እግር ልብስ ካዘጋጀችዉ ከሚስቱ ጋር ያለዉን ይገልፃል ፡፡ በፋሲካ በስምንተኛዉ ቀን ላይ አይሁዶች ለእነርሱ ያለዉን የእግዚአብሄርን ፍቅር እና ለእርሱ የእነርሱን ፍቅር ለማስታወስ መኃልየ መኃለይ ዘሰሎሞንን ያነባሉ ፡፡ መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን በሰለሞን እና በሱናማይቷ ሴት መካከል ስላለዉ ግንኙነት ነው ፤ ስለ እስራኤላዊያን እና ከእግዚአብሄር ጋር ስላላቸዉ ግንኙነት መልክ ነው ፡፡ እንዲሁም በመጨረሻ የሙሽራዉ እና ሙሽራዉ ስለሚመጣ መዘጋጀት ስለሚያስፈልጋት ሙሽራ መልክ ነው ፤ ሙሽራዉ ኢየሱስ ነው ፡፡

ትምህርት

መኃለየ መኃልይ ዘሰለሞን (1፡ 2-4)፡ ሱናማይቷ ሴት ተናገረች ፤ ሰለሞን እንዲስማት እንደናፈቀች ፤ ይህ አብሮ መሆንን ተስፋ በማድረግ መጠበቅ ነው ፡፡ ወደ ከንፈሮቹ፣ ወደ ፍቅሩ፣ ወደ ጠረኑ እና ኑሮዉ ተስባ/ተማርካ ነበር ፡፡ የኢየሩሳሌም ሴት ልጆችም “ በአንተ ደስ ይለናል ሐሴትም እናደርጋለን “ (ቁጥር 4) ብለዉ በመዘመር ከኃሏ ተገኝተዋል ፡፡

መኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን (1፡ 5-7)፡ ሱናማይቷ ሴት ማዉራቷን ቀጠለች ፤ በፀሀይ እየሰራች ስለ ነበር ምን እንዴት አጥቁሯት እንደ ነበር በእዉነት እያሰበች ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ሴቲቱ ራሷን ከከተማዋ ወጣት/ኮረዳ ሴቶች ጋር እንዳወዳደረች እና ሰለሞን የሚፈልጋት እንደነበረች እርግጠኛ እንዳልነበረች ገልፆአል ፡፡ ልክ እንደማንኛዉ አብሮ የመሆን/ጊዜ የማሳለፍ ግንኙነት ሱናማይቷ ሴት በሚገባ በቂ እንደሆነች እና እንዳልነበረች ተጨንቃ ነበር ፡፡

መኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን (1፡ 8-11)፡ ሰለሞን ሲናገር ሙሉ በሙሉ የምታምር እንደ ነበረች አረጋገጠላት ፡፡ ከአንዱ የፈርዖን ሰረገላ ፈረስ ጋር ያለዉ ንፅፅር ምስጋና ነበር ፤ 1ነገ (10፡ 26-29) ሰለሞን የብዙ ፈረሶች ባለቤት እንደሆነ ይገልፃል ፡፡ በእርግጥ እርሷን ከፈረሶቹ ጋር ሲያገናኛት ዉበቷል ለመሳል እየሞከረ ነበር ፤ በተጨማሪም ዉበቷን አጉልቶ ለማሳየት የወርቅ እና የብር ጌጣጌጦችን ተስፋ ገባላት ፡፡

መኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን (1፡ 12-14)፡ ሱናማይቷም ሴት ለትዳር ለመግባባት ተስፋ በማድረግ መለሰች ፡፡ መፅኀፍ ስለተለያዩ የፍቅር አይነቶች ያወራል፣ ቁጥር 13 ስለወሲባዊ ፍቅር የሚያወራ ነው ፡፡ ሱናማይቷ በኃይል ሰለሞንን ወደ እርሷ ለመሳብ መዓዛ ያለዉ ልብስ ለመልበስ አሰበች ፤ ፍቅሯን “ ……በዓይንጋዲ ወይን ቦታ እንዳለ እንደ አበባ እቅፍ ነዉ “ (ቁጥር 14) በማለት ትገልጣለች ፡፡ ዓይንጋዲ ዳዊት ከሳዖል ጥበቃን ያገኘበት እንዲሁም ደግሞ መፅናናትን እና መታደስን ያገኘበት ስፍራ ነበር ፡፡ ስለሆነም በሚገባ ጊዜአቸዉን በአንድ ላይ በአስደሳች አሳልፈዉበት የነበረ ነገር አለ ፡፡

መኃለየ መኃልይ ዘሰለሞን (1፡ 15)፡ ሰለሞን ዉበቷን እየተጣራ ምላሽ ሰጠ ፤ የእርግብ አይኖች ጥራቷ፣ ንፁኅነቷን እና ዉበቷን አመለከቱ ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር እነዚህ የእርግብ የጠለቀ ጭሳም ግራጫ አይኖች እንደነበሩ ይናገራል ፡፡

መኃለየ መኃልይ ዘሰሎሞን (1፡ 16-17)፡ ሱናማይቷም ሴት ሰለሞን ምን ያክል ዉብ እንደ ነበር መለሰችለት ፡፡ እዚህ ስፍራ ላይ አብረዉ ጊዜ እያሳለፉ ስለነበር ይህ አንድ ቀን ግንኙነታቸዉ ምን እንደሚመስል እያሰቡት ያለዉ ነገር ነው ፡፡ እግዚአብሄር የሚያስፈልጋቸዉን ሁሉንም ነገር እና አንዱ ለሌላዉ መሆነ የሚፈልገዉንም ሰጥቷቸዋል ፡፡

መደምደሚያ

ግልፅ ለማድረግ እዚህ ስፍራ ላይ ሰለሞን እና ሱናማይቷ ሴት መካከል ምንም ነገር አልተፈጠረም ፤ ይህ ለመጋባት የመግባቢያ ጊዜ ነው ፡፡ ይህን ጥናት ስንቀጥል ከእነዚህ ጥቅሶች ጋር ብዙ ክፉሎችን እናገናኛለን ፡፡ በዚህ መዝሙር ዉስጥ ሙሽራዉ እና ሙሽራዋ የሙሽራዉ እና የሙሽራዋ ማለትም የክርስቶስ እና የቤተ ክርስቲያን መልክ መሆናቸዉን ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፡፡

  1. John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 743.

  2. MacArthur, p. 743.

  3. MacArthur, p. 744.

  4. MacArthur, p. 745.

  5. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 795.

  6. Nelson’s Commentary, p. 797.

  7. Nelson’s Commentary, p. 797.

ጥያቄዎች

  1. መኃ (1፡ 3) ቅባትን የሚያመለክት ነው ፤ ቅባት የመፈወስ ባህሪይ አለዉ ፡፡ ይህ ጥቅስ ወደ ክርስቶስ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይችልም ?
  2. በራዕ (19፡ 9) መልዓኩ ስለ በጉ ሰርግ እራት ተናገረ ፤ በአጠቃላይ ይህ እንዴት ከመኃ (2፡ 4) ጋር ይገናኛል ? “ ሰንደቁ በእኔ ላይ ፍቅር ነው “ ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው ?
  3. መኃ (3፡ 1-4) ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይስ ደግሞ ወደ እስራኤል ሊያመለክት ይችላል ? በታላቁ መከራ ቀን ጊዜ ኢየሱስን በመፈለግ አያገኙትምን ? እስራኤል “ ክርስቶስን “ በተቀበለች ጊዜ በእነርሱ “ ይገኛልን “ ? በዚህ ጥቅስ ላይ ለመመልከት ሌላ መንገድ አለ ? አዎ ከሆነ እንዴት ?
  4. በመኃልየ መኃለይ ዘሰሎሞን (1-3) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Song of Songs 1:15–16

“How beautiful you are, my darling. How very beautiful! Your eyes are doves. How handsome you are, my love. How delightful! Our bed is lush with foliage.”

እርስ በእርሳቸው በመሳሳብና ትዳርን በመመስረት የተጀመረው እንድሁም ሰሎሞን ለመጀመሪያ ሚስቱ ሲነግራትና ፍቅሩን ሲገልጽላት የሚያሳው መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን በቤተክርስቲያንና በሙሽራው በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል ያለውን ፍቅር ይወክላል ፡፡ ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ጌታም አንተን ያይሃል ፡፡ እርሱ አንተን ቆንጆ እንደሆንክ አድርጎ ያይሃል ፡፡ በአይኑ ውድ አድርጎ ያይሃል ፡፡ እርሱ ይረዳሃል ፡፡ እርሱ ጠንካራና ደካማ ጎንህን ያውቃል ፡፡ እርሱ ለይቶ ያይሃል ይከታተልሃልም ፡፡ እርሱ ወደ ታላቅ ፍቅሩ ይስብህ ዘንድ ይናፍቃል ፡፡ ወደ እርሱ እንድትመጣና ወዳጁ እንድትሆን ይፈልጋል ፡፡

ጌታን ተመልከት ፡፡ ለአንተ ያለውን ታላቅ ፍቅር ለመመልከት አይኖችህን ግለጥ ፡፡ ፍቅሩ ስቦ እንድያስገባህ ፍቀድ ፡፡ እርሱ በክንፎቹ ጥላ ስር እንደሚሸፍንህ ይናገራል ፡፡ እርሱ በላባው ይጋርድሃል ፡፡ እርሱ ሰላምህ ፣ ህይወትህ ፣ ረዳትህ ነው ፡፡ ዛሬ ወደ ጥልቅ መገኘቱና ወደ ኢየሱስ ፍቅር ቅረብ ፡፡ እንደምትፈለግ እንደምትወደድ እመን ፡፡ በማያልቅ ፍቅር እንደተወደድክ እመን ፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅ እንደሆንክ እመን ፡፡ አንተ የእርሱ ነህ ፡፡

“ ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፤ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፤ ዓይኖችሽም እንደ ርግቦች ናቸው ። ውዴ ሆይ፥ እነሆ፥ አንተ ውብ ነህ፥ መልከ መልካምም ነህ አልጋችንም ለምለም ነው ። “ - መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 1፡15-16

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 2:4 — “ ወደ ወይን ጠጁም ቤት አገባኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው ። “
  • ኤርምያስ 31:3 — “ እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ ። “
  • ኤፌሶን 5:25 — “ ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ ፤ ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፡፡ “