Wisdom Books Ecclesiastes

What Is It All About?

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Ecclesiastes 10-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 483 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መቼም ቢሆን የእግዚአብሄርን ቃል ስናነብና ስናጠና ስላስተማርነዉ እና ስለሰማነዉ ነገር ተጠያቂዎች ነን ፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ላይ የሆናችሁበትን የመጨረሻዎቹን ጥቂት ጊዜዎች ስታስቡ በተማራችሁት ነገር ምን አደረጋችሁ ? እንዴት ነበር የተበረታታችሁት ? በማህበረሰብ ዉስጥ ቃሉን ከሌሎች ጋር ማጥናት ስለተማርነዉ ነገር ለማዉራት እድልን ይሰጠናል ፡፡ ዛሬ መክብብ መጨረሻዉ ላይ እንመለከታለን ፡፡ በዚህ መፅሀፍ ዉስጥ ለኢየሱስ ቃላችን ዘላለማዊ ነው ፡፡ ከዘላለማዊዉ አምላክ ጋር ብቻ ስንገናኛ ህይወት ትርጉም ይሰጣል ፡፡ ይህ መፅሀፍ አላማችንን በማስታወስ ራሳችንን የተጨነቀ እንዲሆን እንዳንፈቅድለት ይጠራናል ፡፡

ትምህርት

በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ሰዎች “ ስለሁሉም ነገር ይህ ምንድን ነው ? “ የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ የሚሞክሩ ይመስላሉ ፤ የመክብብ ፀሀፊ በአላማ ህይወት ምን ማለት እንደ ሆነ እያብራራ ነበር ፡፡ ዛሬ በመፅሀፉ መጨረሻ ላይ ስለሆንን “ በሁኔታዉ መደምደሚያ ላይ “ እናተኩራለን ፡፡

መክብብ (12፡ 9-14)፡ ሰለሞን በጭፍን ንግግሩን እንደማንቀበል ስለሚያዉቅ “ እግዚአብሄርን ፍራ ትዕዛዙንም ጠብቅ “ (ቁጥር 13) የሚለዉን ትዕዛዙን በደንብ ለመናገር ስለ ነገሮች ከንቱነት ይዘት አልዘለለም ፡፡ እያንዳንዳችን ስለ ትርጉሙ ይህ እዉነት ነበር በማለት ለመፈተን በመሞከር ለመፈለግ በራሳችን እንደምንፈልግ ያውቀናል ፡፡ ሰለሞን ነገሮቹን ረጅም ጊዜ የማይቆዩ እስትንፋስ እንደ ነበሩ/ከንቱ እንደነበሩ ከማጠቃለሉ በፊት ብዙ የተለያዩ ነገሮችን መርምሯል፡

  • መክ (1፡ 17)፡ ጥበብን ማሳደድ ንፋስን ከኋላ እንደማሳደድ ነበር ፡፡
  • መክ (2፡ 1)፡ ደስታን ማረጋገጥ/ማግኘት ከንቱነት ይሆናል ፡፡
  • መክ (2፡ 2)፡ ሳቅና ደስታም ከንቱነትን አረጋግጠዋል ፡፡
  • መክ (2፡ 3)፡ ወይንና ስንፍና በጥበብ ቢመራም ከንቱ ነው ፡፡
  • መክ (2፡ 4-6)፡ ታላቅ ስራዎችን ሰራ ቤቶችን ገነባ፣ የወይን ተክልን መትከል፣ የወይን አትክልትን ተከለ፣ መዝናኛዎችን፣ ፓርኮችን፣ የፍሬ ዛፎችን እና የመዋኛ ገንዳዎችን ሰራ ፤ ከእርሱ የበለጠ ነገርን ለማሳካት ሞከረ ነገር ግን ይህም ደግሞ ከንቱ ነው ፡፡
  • መክ (2፡ 7)፡ ባሪያዎችን ገዛ፣ በጣም ብዙ መንጋዎች እና የመንጋ ጠባቂዎችን ነበሩት ፤ በዙሪያዉ ካሉት ባለጠጋ ሰዉ ነበር ነገር ግን ይህም ቢሆን ከንቱ መሆኑን አረጋገጠ ፡፡
  • መክ (2፡ 8)፡ ወርቅን ብርን እና ኃብትን እንዲሁም ቁባቶችን እና ዘፋኞችን ሰበሰበ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው፡፡
  • መክ (2፡ 9)፡ በኢየሩሳሌም በጣም ኃይለኛና ታላቅ ሰዉ ሆነ፣ ጥበበኛ/አስተዋይም ሆኖ ኖረ ይሁን እንጂ ያም ንፋስን እንደመከተል ነበር ፡፡
  • መክ (2፡ 10)፡ ራሱን ከሚፈልገዉ ማንኛዉም ነገር ሁሉ አልከለከለዉም ከደስታም ራሱን አላራቀዉም ፤ ልቅነትም እንኳን ደስታን አያመጣም ፡፡
  • መክ (5፡ 7)፡ ሰለሞን ህልሞችና ቃላቶች ከንቱዎች እንደነበሩ ማስተዋል ጀመረ እግዚአብሄር ግን መፈራት አለበት ፡፡

መክ (6፡ 2)፡ እግዚአብሄር አንዳንድ ሰዎችን ኃብትን፣ ንብረትን ብልፅግናን እና ክብረን ስለሰጣቸዉ ምንም ነገር አያጡም ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር በእነዚህ መደሰት እንዲችሉ ዋስትና አይሆናቸዉም ይልቁንም ሌሎች ይደሰቱባቸዋል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ ሌላ ሰዎስተኛ አለም ሀገራት የተጓዙ ሰዎች በጥቂቱም ደስተኛ መሆን በቻሉ ሰዎች የተገረሙ ይመስላሉ ፤ ነገር ግን በእነዚያ በሰዎስተኛ አለም ሀገራት የነበሩ ሰዎች በፍፁም እነዚህ ነገሮች ደስተኛ ሊያደርጓቸዉ እንደሚችሉ በማሰብ አልታለሉም ነበር ፡፡

መክ (6፡ 9)፡ የተራበ ሁሉ በመመገቡ የመርካት/የደስታ ትርጉም አይሆንምን ? ነገር ግን በዚህ በምድር ላይ መመገብ የማይቻል ሌላ ርሀብ አለ ፤ መክብብ ከማንኛዉም የምግብ ርሀብ የሚበልጥ ሌላ እንዳለ ያሳየናል ፡፡ ከእግዚአብሄር ዉጪ አለመርካትና ባዶነት ነዉ ያለው ፡፡

በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ላይ መናገር ሰለሞንን “ እግዚአብሄርን ፍራ ትዕዛዙንም ጠብቅ “ (ቁጥር 13) በማለት እንዲያጠቃልል መራው ፤ በዚህ ንግግር ላይ ሁለት የተለያዩ ነገር አድርጋች መመልከት ትችላላችሁ “ እግዚአብሄርን ፍራ “ እና “ ትዕዛዙን ጠብቅ “ ፤ ወይም ደግሞ ይህን እንደ አንድ እንደተያያዘ ፅሁፍ/ንግግር ማንበብ ትችላላችሁ “ ትዕዛዙን በመጠበቅ እግዚአብሄርን ፍራ “ በማለት ፡፡ በዚህ በሁለተኛዉ አገላለፅ እግዚአብሄርን የመፍራት ትርጉሙ ትዕዛዙን መጠበቅ ነው ፡፡

እግዚአብሄርን መፍራት በጥበብ መፅሀፍት/ፅሁፍ (እና በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ) የተገለፀ ነው ፡፡

ኢዮብ (1፡ 9) - ሰይጣንም እንኳን ኢዮብ እግዚአብሄርን እንደሚፈራ ያውቃል ፤ ሰይጣን የኢዮብን ኃብት፣ ንብረት እና ቤተሰቡን መዉሰድ ችሏል ነገር ግን የኢዮብን እግዚአብሄርን መፍራት መዉሰድ አልቻለም ፡፡

መዝ (34፡ 9) - እግዚአብሄርን የሚፈሩ ምንም ነገር አያጡም ፤ ለምን ? ሁሉንም ነገር መከተል ትችላላችሁ ግን እግዚአብሄር እና እናንተ ደስተኛ አትሆኑም ፤ ነገር ግን እግዚአብሄርን ስትፈሩ በደስተኝነት ትጨርሳላችሁ ፡፡ “ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሄርን መንግስት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል “ (ማቴ 6፡ 33) ፡፡

ራዕ (14፡ 7) - እርሱን ክብር በመስጠት እግዚአብሄርን ማክበር ፤ በእዉነት እግዚአብሄርን በማምለክ እና ኑሮአችንን በሙሉ በመስጠት እግዚአብሄርን እንፈራለን ?

እግዚአብሄርን መፍራት ትልቅ ነገር ነው ፡፡ በዘመናዊዉ/በሰለጠነዉ ባህላችን የጥኛዉ የእግዚአብሄር ባህሪይ በደንብ ተብራርቷል ብላችሁ ታስባላችሁ ? አንዳንዶች የእግዚአብሄር ፍቅር ነዉ ይላሉ - የማያልቅ ፍቅሩ፣ ፍፁም ፍቅሩ ነዉ የሚሉት ፤ ነገር ግን ሁሉንም የእግዚአብሄርን ጥራቶች ልናስተዉል/ልንረዳ ያስፈልገናል እግዚአብሄር በፍፁም የማይጠፉ ጥራቶች አሉ ፡፡ ኢየሱስ በእዉነትና በፀጋ ሙሉ ነው ፤ ፀጋው አጭር ያልሆነና እዉነቱን የማያጠፋ ነው ፡፡ እዉነትን ስላብራራ ፀጋዉን አያጠፋዉም ፤ በእግዚአብሄር ፍቅር እና እዉነት/ፍትህ ሁለቱም አሉ ፡፡ እግዚአብሄርን መፍራት ሲኖራችሁ ለእግዚአብሄር ታላቅ የሆነ ፍቅር ሊኖራችሀ ይችላል ፡፡ በማቴ (22፡ 37-39) ይህ ሁሉ ምን ማለት እንደሆነ ኢየሱስ ነግሮናል፡ “ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ዉደድ ፡፡ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትዕዛዝ ይህቺ ናት ፡፡ ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርስዋም ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ዉደድ የምትለዉ ናት “ (ማቴ 22፡ 37-39) ፡፡

በመክብብ ዉስጥ ሁሉም እግዚአብሄርን ስለመፍራት እና ትዕዛዝቱን ስለመጠበቅ ነው ፤ ሁለቱም ፅሁፎች / ንግግሮች በእኩል እዉነት ናቸው ፤ ሁለቱም ሙሉ በሙሉ በአንድ ላይ የሚሄዱ ናቸዉ ፡፡ እግዚአብሄርን መዉደድ አምላክን መፍራት ሲያካትት እግዚአብሄርን መፍራት ደግሞ በላን በሁሉም ነገር እግዚአብሄርን መዉደድ ያይዛል ፡፡ እግዚአብሄርን በመፍራት ከእርሱ ርቆ ከመሄድ ይልቅ ወደ እርሱ እንድትሮጡ ለማድረግ የሚያስችሉ ብዙ መንገዶች አሉ ፡፡ ትዕዛዙን በመጠበቅ እግዚአብሄርን ስትፈሩ በእርሱ ዙሪያ ለመሆን አትፈሩም ፤ በተቃራኒዉ ደግሞ ትዕዛዙን በመጠበቅ እግዚአብሄርን በማትፈሩ ጊዜ እርሱን ትፈሩታላችሁ ፡፡ እግዚአብሄርን የመፍራት አስደናቂዉ ነገር - በእዉነት ይህን በምታገኙት ጊዜ - የእነዚህን ትዕዛዞች ዝርዝር ማድረጉን ማሰብ ብቻ በቂ ነው ምክንያቱም ይወዳችኋል፣ በእናንተ ስለሚያምን፣ ለእናንተ ወደፊትን ስለሚፈልገዉ ለእናንተ ታላቅ ነገር መኖሩ ነው ፡፡ በሚገባ እግዚአብሄርን መፍራት እና ትዕዛዙን መጠበቅ በሙሉ ልባችን እግዚአብሄርን ወደ መዉደድ ይመራናል ፡፡

መደምደሚያ

በመክብብ ያለዉ ሁሉም ነገር ስብስብ/ድምር/አጠቃላይ ሀሳብ - የነገሮች ማጠቃላያዎች/መደምደሚያዎች፡ በፍላጎቶች የምትታለሉ አትሁኑ፣ ደስተኛ በሚያደርጓችሁ በንብረት እና በሀሳብ የተታለላችሁ አትሁኑ እንዲሁም በስራችሁ ወይም በምታደርጉት ነገር የምትታለሉ አትሁኑ ፤ ይልቁንም እግዚአብሄርን በመፍራት እና ትዕዛዙን መጠበቅ በመረዳት ምሪቱን/አቅጣጫዉን መከተል የዚህ ሁሉ ማጠቃለያ ነው ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በመክ (10፡ 1) ሰለሞን ስለ ስንፍናና ሞኝነት ተናገረ ፤ በራሳችሁ ህይወት ወይም በሌላ ሰዉ ህይወት ይህን ጥቅስ የተጠቀመበት/ምሳሌ ያደረገበትን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ? በምን መንገድ ?
  2. ጥበብን ከመፋስ/ከመጥረቢያ እራስ እንዴት ታወዳድሩታላችሁ ? መክ (10፡ 10) ትርጉም ይሰጣል ? ለምን ወይስ ለምን አይሰጥም ?
  3. መክ (11፡ 4) ስታነቡት ወደ አይምሯችሁ ምን ይመጣል ? ይህ የ 2ቆሮ (5፡ 7) ምሳሌ ሊሆን ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይችልም ? የገበሬ ምሳሌዎች እንደሆናችሁ ይሰማችኋል ወይስ በቆሮንቶስ እንዳለዉ ጥቅስ ? ለምን ?
  4. በመክብብ (10-12) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ecclesiastes 12:13–14

“When all has been heard, the conclusion of the matter is: fear God and keep His commands, because this is for all humanity. For God will bring every act to judgment, including every hidden thing, whether good or evil.”

ከምርምሩ በኋላ ሰሎሞን እግዚአብሔርን መፍራትና ትዕዛዙን መጠበቅ የህይወት የመጨረሻ ግብ እንደነበረ ደመደመ ፡፡ ለእኛም እንድሁ ነው ፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት እናም ትዕዛዙን መጠበቅ ብቻውን እውነተኛ የሆነ እርካታን ይሰጣል ፡፡ እግዚአብሔር ፍርድን ይሰጣል ፡፡ ይህ የአንተ ስራ አይደለም ፡፡ የአንተ ስራ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ፡፡ የአንተ ሀላፊነት እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ ፣ ነፍስህ ፣ ኃይልህ እና አሳብህ መውደድ ደግሞም ባልነጀራህንም እንደዚሁ መውደድ ነው ፡፡ ይህንን እንደ ብቸኛ ጉዳይህ አድርገህ ያዝ ፡፡ የእርሱን ትዕዛዝ መጠበቅ እስከሚያስችልህ ድረስ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ይኑርህ ፡፡

ደስታንና እርካታን ለማግኘት ወደ እዚህ አለም ነገሮች ተታለህ እንዳትገባ ፡፡ ከቁጣ ፣ ትዕግስትን ከማጣት ፣ ካለመርካት እራስህን ጠብቅ ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉንም ስለሚመለከት እርሱ ይጠብቅሃል ፡፡ እግዚአብሔርንና ሌሎችን በመውደድ ስትጸና ሌሎች ነገሮች ሲሳኩልህ ታያለህ ፡፡ ጸንተህ ቁም እግዚአብሔርንም ፍራ ፡፡ እግዚአብሔር ምንም እንደማይጎድልብህ ተናግሯል ፡፡ ይህ እውነት አስደነቂ ጸጋ ነው ፡፡ ዛሬ ጠባብ መንገድ በሆነው እግዚአብሔርን በመፍራትና እርሱን በመከተል ላይ አትኩር ፡፡

“ የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና ። “

  • መክብብ 12፡13-14

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 34:9 — “ የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት ። “

ሉቃስ 10:27–28 — “እርሱም መልሶ፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው ። ኢየሱስም፦ እውነት መለስህ፤ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ አለው ። “

ራእይ 14:7 — “ በታላቅ ድምፅም፦ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ ። “