Wisdom Books Ecclesiastes

How God Sees Us

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Ecclesiastes 7-9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 482 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መቼም ቢሆን የመክብብን መፅሀፍ ሳጠና ከጥናቱ ፊት ለፊት አንድ ቃል አስቀምጣለሁ፡ “ አጥብቆ ማሰብ “ ፤ በመክብብ መፅሀፍ ዉስጥ “ ለምን እና እንዴት “ ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ አስባለሁ ፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ “ ለምን “ የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ በሚሆን እኩልታ/መለኪያ ዉስጥ አቀርበዋለሁ ፤ በዚህ እስማማ እንደሆነ ራሴን እጠይቀዋለሁ ፡፡ ፀሀፊዉ ከየት እንደመጣ እንደማየዉ ወይም እንደማላየዉ እመለከታለሁ፡፡

ትምህርት

መክብብ (7፡ 1-6)፡ ይህ ምዕራፍ እዉነታን በማረጋገጥ ይጀምራል፡ ከሚያስደስት/ከሚያዝናና ነገር ጋር ስታወዳድሩት ለህይወት ምርጡ ነገር ምንድን ነው ? ቁጥር 1 ኃብት ከመኖር ይልቅ መልካም ስም መኖር አስፈላጊ እንደሆነና ከዉልደት ቀን ይልቅ የሞት ቀን የተሸለ እንደሆነ ያነፃፅራል ፡፡ ህይወት አንዱ ከሌላዉ በኋላ የሚመጣበት ቅርብ እስትንፋስ ነው ፤ ስለምንወስደዉ እያንዳንዱ እስትንፋስ/አየር አናስብም ነገር ግን ከእያንዳንዱ እስትናፍስ ዉጪ መኖር ወይም ማንኛዉንም ነገር መፈፀም አንችልም ፡፡ ቁጥር 2-3 በህይወታችን ሀዘንንና አስቸጋሪ ሁኔታ ሲደርስብን/ስንለምድ እናድጋለንም እንበስላለን/ነገሮችን እንችላለን ፡፡ አንዱ ስለሌላዉ ነገር ይመጣል ፤ በሀዘናችን የምንማረዉ ነገር የተሸለና ስንስቅ ከምንማረዉ በላይ የሚቆይ ተፅዕኖ ያለዉ ነው ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ስጓዝ በተማርኩበት ጊዜ መልካም/ጥሩ የሚሆነው ህይወት ቀላልና አስደሳች በሆነች ጊዜ ሳይሆን በአስቸጋሪ ስፍራዎች እየተጓዝኩ በነበርኩበት ጊዜ ነው ፡፡ ሁልጊዜ የህይወት ትምህርት ከመልካም ነገር አይመጣም ከአስቸጋሪ ሁኔታ/ነገርም እንጂ (ቁጥር 4-6) ፡፡

መክብብ (7፡ 7)፡ ግፍ ጥበበኛን ሰዉ ለምን እብድ ያደርገዋል (ቁጥር 7) ? ጥበበኛ ሰዉ በተለዬ እቅድ አለው - ጅማሬዉ፣ ሂደቱና መጨረሻውም አለው ፡፡ የግፍ መሆን/መድረስ የአስተዋይ ሰዉን ጥረት ትቀይራለች - ከእቅዱ ላይ አርቆ ይወስደዋል ፡፡ ስጦታ/ጉቦ ለምን ልብን ያጠፋል (ቁጥር 7) ? ይህ አስተያየታቸዉ የተጣመመ ሊሆን የሚችለዉን በስልጣን ላይ ላሉት ሰዎች ይናገራል ፤ ይህ ሰው ሸጋይ እና ለመጣር የሚስብ ሊሆን ይችላል ፡፡ ሰዉ ሸጋይ ሳይሆን ተጠያቂነት ሊኖረዉ ይገባል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይህን በፖለቲካዉ ዉስጥ እየያነዉ ነዉ ምክንያቱም ገንዘብ ሊያበላሽ ስለሚችል ፤ ይህ የሰዉ ልምድ ነዉ ነገር ግን በዚያ መጠምዘዝ የለብንም ፡፡ ከዚህ ማምለጫችን የዘላለም እይታ ብቻ ነው ፡፡

መክብብ (7፡ 8)፡ የሆነ ነገር መጨረሻ ከመጀመሪያዉ ይልቅ የተሸለ የሚሆነዉ ለምንድን ነው (ቁጥር 8) ? በዚህ ህይወት ዉስጥ በፍፁም ያልተሟላ ነገር ምን ያክል ጊዜ ኖሮን ያውቃል ? ሰዎች ያልተሳካን ነገር ለማድረግ ምን ያክል ጊዜ ሞክረዋል ? የትልቅ አሳብ ምርጡ ነገር ሀሳቡ/አላማው በመጨረሻ ላይ የተፈፀመ/የተሳካ ሲሆን ነው ፡፡ በህይወት መጨረሻ ላይ የነገሮች መሳካት/መፈፀም ህይወት በሚገባ የተኖረ ነበር ብሎ ለማለት ያስችላል ፡፡ መንፈስ ቅዱስን በትዕግስት የሚጠብቁ በትዕቢት መንፈስ ቅዱስ ከመጓዙ በፊት ከሚጓዙ የተሸሉ ናቸው (ቁጥር 8) ፤ ታጋሽ “ በራሱ ጊዜ ይመጣል “ ይላል፣ ትዕቢተኛ ደግሞ “ አሁን መሆን አለበት “ ይላል (ሮሜ 8፡ 28) ፡፡

መክብብ (7፡ 9-10)፡ ግፍ እና ፍትህ መጓደል ሲገጥም ሰለሞን የተቆጣ ለመሆን መቸኮል እንዳይሆን አስጠንቅቋል “ ቁጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና “ (ቁጥር 9) ፡፡ ሁልጊዜ ቁጣ ከባለቤትነት ጋር አገናኘዋለሁ ፤ ቁጣ የሆነ ነገር ይከላከላል - እኔን፣ ግዛቴን፣ ዝናዬን ይከለክላል - ምክንያቱም እነዚህን የኔን ድርሻዎች የከላከል መብት አለኝ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የሚከላከል እና ባለቤት እንደሆነ ስናምን የሚያገጣብሩንን እና ያለአግባብ የሚጠቀሙብንን እንባርካለን ፡፡ “ በቀደመዉ መልካም ዘመን “ (ቁጥር 10) የተሸለ ነበር ብለህ አትጠይቅ ፤ “ የቀደመዉ ዘመን “ በፊት መጥቶ የነበረዉ ጊዜ ነበር ፡፡

መክብብ (7፡ 11-12)፡ ጥበብ ከእግዚአብሄር ይመጣል ፤ ጥበብ ኑሮአችንን የምንታደግበት መጠበቂያችን ነው ፡፡ እነዚህን ዘመናት ትርጉም ያላቸዉ ለማድረግ በእነርሱም ለመስራት መወሰን አለብን ፡፡

መክብብ (7፡ 13-15)፡ የህይወት መንገድ ጠመዝማዛ/አስቸጋሪ ነዉ ነገር ግን እግዚአብሄር ቀጥ ማድረግ ይችላል (ቁጥር 13) ፡፡ የመከራ ቀን እንደሚመጣ ብናዉቅም እንኳን ደስተኞች መሆን አለብን ፡፡ በአጭር/በልጅነት ጊዜ የሚሞቱ መልካም ሰዎች ሲኖሩ ረጅም ጊዜ የሚኖሩ ኃጢዓተኞች ደግሞ አሉ (ቁጥር 15) ፤ ይህ ትክክል የማይመስል የሚያሳስብ ክስተት ነው ፡፡ እግዚአብሄርን ጥበብ እንዲያስተምረን ልንጠይቀዉ ይገባል ፤ ጥያቄዎቻችንን ችላ አይላቸዉም ፡፡ የሰዉን መንገድ አጥብቀን ልንፈልግ ይገባል የእግዚአብሄርን መንገድም እንዲሁ አጥብቀን ልንፈልግ ይገባናል ፡፡

መክብብ (7፡ 19-22)፡ ጥበብ ጠንካሮች ያደርገናል (ቁጥር 19) ፤ ጥበበኛ የሆነ ሰው ከብዙ ሰራዊት የተሸለ መሆን ይችላል ምክንያቱም ከማጥፋት ይልቅ የሆነን ነገር እንዴት መፈፀም እንደሚቻል ስትራቴጅ ስለሚአስቀምጥ/ስለሚስል ፡፡ በምድር ላይ ፃድቅ በፍፁምም ኃጢዓት ያልሰራ ማንም ሰዉ የለም (ቁጥር 20) ፡፡ ሌሎች ለሚሉት ትኩረት አትስጡ ነገር ግን እናንተ ስለምትሉት ትኩረትን ስጡ ፡፡ በሌሎች አስተያየት ላይ ብዙ ዋጋን አታስቀምጡ ምክንያቱም ትክክለኛ አመለካከት በሌላችሁ ጊዜ ዋና/አስፈላጊ ለመሆን ቀላል ስለሆነ ፡፡

መክብብ (7፡ 29)፡ እግዚአብሄር ሰውን ቅኖችና ፃድቆች እንዲሆኑ ሰራቸዉ ነገር ግን ሰው በዚያ ፋንታ ብዙ ሴራዎችን እና ፈጠራዎችን ተከተለ ፤ ለዚያም ነው መክብብ 7 እንዴት እንደምናስብ እዉነትን ማረጋገጫ የሆነው ፡፡

መክብብ (9፡ 11-12)፡ 1ቆሮ (1፡ 26-28) ከቁጥር 11 ጋር ይዛመዳል ፡፡ መክብብ ነገሮች ላይ የምንመለከትበት ተግባራዊ መንገዶችን ይመለከታል - እግዚአብሄር እንዲጠቀምብን በደንብ የተጣራን፣ በደንብ ችሎታ ያለን ወይም በደንብ ባለፀጋዎች መሆን አይጠበቅብንም ፤ ማድረግ የምንችላቸው ወደ እግዚአብሄር አያመጡንም ፡፡ እግዚአብሄር ሊጠቀምብን የሚመርጠው ድክመታችን ነው - ከጥሩነት/ከማጣሪያዉ በታች፣ ከችሎታ በታች እና በድህነታችን ነው ፡፡

መደምደሚያ

ራሳችንን በእነዚህ ምዕራፎች በማስቀመጥ ራሳችንን በሰዉ ልጅ ችግሮች/በሚደርሱ ነገሮች ተሸንፌአለሁ ? ራሴ ባለሁበት ሁኔታዎች ዉስጥ ህይወቴን ስመለከተው ካለሁበት ስፍራ የተነሳ ከፊቴ ላለዉ ነገር ብቁ አልሆንኩም ? በራሴ መመዘኛዉች ራሴን ወስኘዋለሁ ? የሌሎች ግምት በእኔ ላይ እንዲቀመጥ ፈቅጀላቸዋለሁ ወይስ ሰዉ እኔን የሚያጠፋ ነገር እንዲል ፈቅጄለታለሁ ? መክብብ እነዚህን ነገሮች ባለመመልከት የኑሮአችን ልምምድ እንዳይሆኑ ያዘናል ፤ ይልቁንም እግዚአብሄር እንደሚጠቀምብን፣ እንደሚያጠራን እና ወደ ፍፃሜም ስፍራ እንደሚያመጣን በልበ ሙሉነት መጓዝ አለብን ፡፡ ታሪካችንን የሚፅፍ እርሱ እንዲሆን እንፍቀድለት ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በመክ (7፡ 19) “ በከተማ ከሚኖሩ ከአስር ገዢዎች ይልቅ አንድ ጥበበኛ ሰዉ ይበረታል “ የሚለዉ ንግግር እንዴት እዉነት ሊሆን ይችላል ? ይህን ጥቅስ እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
  2. መክ (8፡ 9-14) ስታነቡት ይህ በአሁኑ ጊዜም እዉነት ነዉ ብላችሁ ታምናላችሁ ? ከንጉስ ሰለሞን ጊዜ ነገሮች በብዙ ተቀይረዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይም ለምን አታስቡም ?
  3. በመክ (9፡ 5) ፀሀፊው “ ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና ፤ ሙታን ግን አንዳች አያዉቁም “ ፤ ይህን ለሌላ ሰዉ እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
  4. በመክብብ (7-9) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ecclesiastes 7:9

“Don’t let your spirit rush to be angry, for anger abides in the heart of fools.”

በህይወትህ ስለ ሆነ ነገር ወድያውኑ የምትናደድባቸው ጊዜያቶች ይኖሩህ ይሆናል ፡፡ ይህ የመጀመሪያ ምላሽህ ነው ፡፡ ትበሳጫለህ ፣ ልብህ ሲመታ ይታወቅሃል እናም ፊትህም ደም ይለብሳል ይቀላል ፡፡ በዚህ ጊዜ ለቁጣ ለብስጭት አትቸኩል ፡፡ ትፈልገው ይሆናል ምናልባትም ደግሞ መናደድም ይገባህ ይሆናል ነገር ግን ቁጣ የሚኖረው በሰነፎች ልብ ውስጥ ነው ፡፡ በደንብ ተንፍስ እናም በጸሎት ለሁኔታው ምላሽ የምትሰጥበትን ጥበብ እግዚአብሔርን ለምን ፡፡

እያንዳንዱ ሁኔታ ሁለት ጎን አለው ደግሞም ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር መስራት የሚፈልገው አንተ ማየት ከምትችለው በላይ በሆነ በላቀ መንገድ ነው ፡፡ ስለዚህ አንተ ከመናገርህ በፊት እንድሰራ ለእግዚአብሔር ጊዜን ስጠው ፡፡ ለመረዳት ለመገንዘብ ጊዜን ስጥ ፡፡ ሰነፍ አትሁን ለቁጣም አትቸኩል ፡፡ ቁጣ ብዙውን ጊዜ የሆነን ነገር ይከለክላል ፡- ምናልባት ራስህን ፣ የአንተ የሆነው ግዛት ወይም ደግሞ ስምህን ዝናህን ፡፡ ቁጣ በውስጥህ የሚቀሰቀሰው የራስህን መብት ለማስከበር ስትጥር ነው ፡፡ ምላሽ ከመስጠትህ በፊት ትንስ ቆም በል ፡፡ እግዚአብሔር ተከላካይህ ተሟጋችህ እንድሆን ፍቀድ ፡፡ ቃል ኪዳኑን ፈጽም ፤ እግዚአብሔርም ነገርን ሁሉ አያይዞ ለፍቃዱ እና ለአላማው እንደሚፈጽም እመነው ፡፡ ስራው ድንቅ ነው ፣ ስራው ወደር አልባ ነው እርሱም ታማኝ አምላክ ነው ፡፡ እንደ ሰነፍ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ከመሞከርና አደጋን ከመጋፈጥ ይልቅ እርሱን እመነው ፡፡

“ በነፍስህ ለቍጣ ችኩል አትሁን፥ ቍጣ በሰነፍ ብብት ያርፋልና ። “ - መክብብ 7፡9

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዘዳግም 32:4 — “እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ እርሱ እውነተኛና ቅን ነው ። “
  • ሮሜ 8:28 — “ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ። “
  • 2ኛ ተሰሎንቄ 3:3 — “ ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው ። “