Wisdom Books Ecclesiastes

God's Gift Of Sleep

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Ecclesiastes 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 481 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ መክብብ 5 ላይ ጥናታችንን እንቀጥላለን ፤ ለመክብብ ቃላችን ዘላለም ነው ፡፡ ሁሉም ሰዉ በኢየሱስ ብቻ ሊገኝ የሚችለዉን ዘላለምን እየፈለገ ነው ፡፡ ህይወት በራሱ አላፊ/ከንቱ/ጊዜአዊ ነው ፡፡

ትምህርት

መክብብ (5፡ 1-7)፡ ዋይርስቤ ለቁጥር (1-7) ቁልፉ ነገር “ እግዚአብሄርን አትዝረፉት/ያላችሁትን ፈፅሙ/አታታሉ “ የሚል እንደ ሆነ ይናገራል ፡፡ ዋይርስቤ ሰለሞን ወደ ቤተ መቅደሱ በሄደ ጊዜ “ ከሚያመልኩት ዉስጥ አብዛኞቹ በአምልኮአቸዉ ዉስጥ በሙሉ ትህትና እንዳልነበሩ እንዲሁም ገብተዉ በነበሩበት ጊዜ በአስቸጋሪ መንፈሳዊ ሁኔታ ለተቀደሰ ነገር የተለየዉን ስፍራ ትተዉ ይወጡ እንደ ነበር ፅፏል “ ፤ ያ መነሻ በቁጥር 1 የሰለሞንን ምክር ይገልፃል፡ “ ወደ እግዚአብሄር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ “ (1ሳሙ 15፡ 22) ፤ ከምሳሌ ይህ “ የልብን ሁኔታ “ ይገልፃል ፡፡ አምልኮ በመታዘዝ የሚሆን እንጂ ግዴታ አይደለም ፤ ሰለሞንም በፀሎት ጠንቃቆች እንዲሆኑና በትህትና እንዲያደርጉአቸው ትኩረትን ለማግኘት እንዳይነገሩአቸዉ/እንዳያደርጓቸው አስጠንቅቋል (ቁጥር 2-3) ፡፡ ጥሩ ስሜት እንደሚሰማችሁ ከሚያደር እንዲሰማ የምትፈልጉት ፀሎት ከሆነ አትፀልዩ ፤ ለፀሎት ልብ እና ከልባችን የሚፈስስ ቃል ሊኖረን ይገባል (መዝ 141፡ 1-2, ማቴ 6፡ 7, 12፡ 34-37) ፡፡ ቻርለስ ሱፐርገን “ የፀሎታችን እርዝማኔ ሳይሆን የፀሎታችን ጥንካሬ ልዩነት ያደርጋል “ ብሏል ፡፡ በቁጥር 4 ሰለሞን እግዚአብሄርን ስላለመዋሸት አስረግጦ ይናገራል - የማይፈፀም ነገር ከሆነ ለእግዚአብሄር ስለት አታድርጉ በማለት ፤ የማይፈፀም ከሆነ በአጠቃላዩ ለእግዚአብሄር አለመሳል የተሸለ ነው (ቁጥር 5) ፡፡ የተሳላችሁት ስሕተት እንደ ነበር በመናገር አንደበታችሁ ወደ ጥፋተኝነት ዉስጥ እንዲገባ አትፍቀዱ (ቀጥር 6) ፤ በከንቱነትም ማዉራት አቁም (ቁጥር 7) ፡፡

መክብብ (5፡ 8-9)፡ ዋይርስቤ ቁጥር 8-9 “ ሌሎችን አታታል “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ምልከታዉ ከቤተ መቅደሱ ወደ ከተማዋ አዳራሽ ሄደ/ዞረ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ሁሉም ሰዉ በምድር ላይ በእግዚአብሄር ፀጋ ስጦታ ይኖራሉ “ ይላል ፡፡ የፍትህ መጓደል እና መጣመም ስንመለከት በተቃዉሞ መራመድ አለብን ፡፡

መክብብ (5፡ 10-20)፡ ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ ራሳችሁን አታታሉ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ ቁጥር 10 ገንዘብ የሚወድ በፍፁም እንደሚበቃዉ እንደማይሰማው - በፍፁምም እንደማይደስ ያብራራል (2ዜና 9፡ 23-28, መክ 1፡ 8, 4፡ 8) ፡፡ ሰለሞን በእያንዳንዱ አመት ጥበቡን መቀበል ከሚፈልጉት እንደ ስጦታ 25 ቶን ወርቅ ተቀብሏል ፤ “ ምንም ያክል የሰፋ/የበዛ ንብረት ቢኖር ፍላጎት ሁልጊዜ ወደ ኃብት ይሮጣል “ ፡፡ የኃብት መትረፍረፍ ሰዉን ያጠፋል እርሱ/እርሷ መተኛት እንኳን አይችሉም (ቁጥር 11) ፡፡

እንቅልፍ ለምን አስፈላጊ ነው ?

  • እንቅልፍ አይምሮአችን እንዲያርፍ ስለሚያደርግ በማለደ አርፈን እንነቃለን (ዘጸ 34፡ 2, መዝ 5፡ 3, ኢሳ 50፡ 4) ፡፡
  • እግዚአብሄር አዳምን በታላቅ እንቅልፍ ዉስጥ አስቀመጠው (ዘፍ 2፡ 21) ፡፡
  • እግዚአብሄር አረፈ (ዘፍ 2፡ 2) ፡፡
  • ሰንበት ለማረፍ ነበር (ዘጸ 31፡ 15, ዘሌ 23፡ 3) ፡፡
  • እንቅልፍ ከእግዚአብሄር የተሰጠ ነው (መዝ 4፡ 8, ምሳ 3፡ 24) ፡፡

መደምደሚያ

በአንድ ምሽት የአሜሪካዊያን አማካኝ የመተኛ ጊዜ ሰባት ሰዓት ከሰላሳ ስድስት ደቂቃ ሲሆን ፤ አማካኝ የመተኛ ጊዜ ከምሽቱ 4፡ 55 ሲሆን አማካኝ የመንቂያ ጊዜ ደግሞ ከጥዋቱ 12፡ 38 ነው ፡፡ በዕረፍት ቀናቶች አማካኝ የአሜሪካዊያን የመተኛ ጊዜ 40 ደቂቃ ይረዝማል ፡፡ ከ50 እስከ 70 ሚሊዮን አሜሪካዊያን የእንቅልፍ መዛባት አለባቸው ፤ ከ40-80 ፐርሰንት ያንኮራፋሉ ፤ 60-70 ፐርሰንት አሜሪካዊያን ከጥሩ እንቅልፍ ያነሰ እንደሚተኙ ሪፖርት ሲደረግ 37.9 ፐርሰንቶቹ ደግሞ በቀን ጊዜ በእንቅልፍ ይወድቃሉ/ይያዛሉ ፡፡ አምስት ፐርሰንት ያክሉ ደግሞ ሲያሽከረክሩ በእንቅልፍ የሚወድቁ ናቸው ፤ 30 ፐርሰንቶቹ ደግሞ በእንቅልፍ እጦት ዉስጥ ሲሆኑ 25 ሚሊዮን በእንቅልፍ ዉስጥ ትንፋሽ በማጣት ይቸገራሉ ፡፡

ኢየሱስ እግዚአብሄርን/አባቱን/አብን ስለተደገፈ/ስለታመነ ተኛ (ማቴ 8፡ 24) ፡፡ ሸክማችንን ለክርስቶስ በሰጠን ጊዜ ማረፍ እንችላለን (ማቴ 11፡ 28-30) ፡፡ መዝ (121፡ 3-4) እግዚአብሄር በፍፁም እንደማያንቀላፋና እንደማይተኛ ይናገራል ፡፡ በእርሱ ላይ ስናርፍ ለዘላለም እየተዘጋጀን ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 502.

  2. Wiersbe, p. 502.

  3. Wiersbe, p. 504.ol

  4. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999) p. 786.

  5. Wiersbe, p. 504.

  6. Nelson’s Commentary, p. 786.

ጥያቄዎች

  1. መክ (5፡ 10) ገንዘብን ስለሚወዱ ያወራል ፤ 1ጢሞ (6፡ 10) ገንዘብን ስለመዉደድ ምን ይላል ? አንድ ሰዉ እንዴት “ ስሩን “ ማጥፋት ይችላል ?
  2. መክ 5፡ 13, ማቴ 6፡ 19-21 እና ሉቃ 12፡ 13-21 አንብቡ ፤ የሰለሞን ቃል ሰዉን እንዴት ወደ ተሸለ መንገድ ያመለክታል ? ኢየሱስስ ?
  3. በመክብብ 5 እና በማቴዎስ 6 መካከል ምን ያክል ተመሳሳይነቶችን ማግኘት ትችላላችሁ ?
  4. በመክብብ 6 መሰረት ሰለሞን ያለዉን ሁሉንም ነገር ሁሉንም እንዴት ተመለከተው ? ለእይታዉ ምክንያት የሆነዉ ምንድን ነው ? (1ነገ 3፡ 3, 11፡ 1-6)
  5. በመክብብ (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ecclesiastes 5:10

“The one who loves money is never satisfied with money, and whoever loves wealth is never satisfied with income. This too is futile.”

ሰሎሞን በጥበብ ገንዘብ ፈጽሞ አርካታን አይሰጥም አለ ፡፡ ምናልባት ብዙ በጣም ብዙ ገንዘብ ልታገኝ ትችላለህ ነገር ግን ፈጽሞ የእውነት ሊያረካህ አይችልም ፡፡ ገንዘብ እንደሚበቃህ ልታስብ ትችላለህን ? በዚህ አለም ሁልጊዜ ሌላ የሚቀር ያልተደረሰበት ነገር አለ ፡፡ ነገር ግን ወድያውኑ አንድኛውን ነገር እንዳገኘህ አይኖችህ በሌላ አድስ በሆነ ነገር ላይ ያተኩራሉ ፡፡ ገንዘብ እንኳ ሳይቀር ከንቱና ጠፊ ነው ፤ ዛሬ እዚህ ነው እና ነገ ደግሞ ይጠፋል ፡፡ እግዚአብሔር ነፍስህን ለዘላለም ፈጥሯታል ፡፡ በህይወትህ ብቸኛው 100 % የማያከስር ኢንቨስትመንት ራስህን ሙሉ በሙሉ ለጌታ መስጠት ነው ፡፡ በእርሱ ሰላም አለህ ፡፡ በእርሱ መገኘት ደስታ አለ ፡፡ እርሱ ሁሉንም ፍላጎትህን ያሟላል ፡፡

ገንዘብና ሃብት የምትፈልገውን እርካታ ፈጽሞ መስጠት አይችሉም ፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ከሚገኘው ፍጹም የሆነ ሰላምና ተስፋ ይልቅ ገንዘብ በሚሰጠው ሰላም ላይ መደገፍ ቃላል እንደሆነ የምታስብባቸው ጊዜያቶች ይኖሩ ይሆናል ፡፡ ዛሬ ልብህን መርምር እናም እውነተኛ ለሆነ እርካታ እግዚአብሔርን ፈልግ ፡፡

“ ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው ። “ - መክብብ 5፡10

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 2ኛ ዜና 9:23 — “ የምድርም ነገሥታት ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበቡን ይሰሙ ዘንድ የሰሎሞንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር ።
  • ሉቃስ 12:15 — “ የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው ። “
  • 1ኛ ጢሞቴዎስ 6:9–10 — “ ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ ። ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ ። “