Short But Meaningful
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Ecclesiastes 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ከመክብብ ዉስጥ አንድን ዓረፍተ ነገር ብቻ ለይቶ ማንበብ አደገኛ/መጥፎ ሊሆን ይችላል ፤ አብዛኛዉ የመፅሀፉ ንግግር አሉታዊ ነው ፡፡ በመክብብ መፅኀፍት ዉስጥ በብዛት ጥቅም ላይ የዋለዉ ቃል “ ከንቱ “ የሚለዉ ነው ፡፡ ይህ አንድ ቃል ለመላዉ የመክብብ መፅኀፍ ትርጉም ይሰጣል ፡፡
በዕብራዊ ቃሉ “ ሀቬል “ ተብሎ ይጠራል ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ “ ከንቱ “ የሚለዉ ቃል ከአዳምና ከሄዋን ልጅ አንዱ ለሆነዉ ለአቤል በዘፍ(4፡ 2) እንደ ስም ጥቅም ላይ የዋለ ነው ፡፡ በዕብራዊ የአቤል ስም ቃል በቃል “ አጭር “ እና የእስትንፋስን መልክ የሚሰጥ ማለት ነው ፡፡ ኢሳ (57፡ 13) እንደ “ እስትንፋስ “ የተተረጎመ ተመሳሳይ የእብራዊ ቃል ተጠቅሟል፡ “ ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል ፡፡ በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱ ይገዛል የተቀደሰዉም ተራራዬን ይወርሳል “ ፡፡ ምሳሌ (31፡ 30) እንደ “ ብልጭታ “ የተተረጎመ ተመሳሳይ ቃል ይጠቀማል፡ “ ዉበት ሐሰት ነው ደም ግባትም ከንቱ ነው ፤ እግዚአብሄርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች “ ፡፡
በሚጠቀማችዉ በእነዚህ ሁሉ “ ከንቱ “ በሚለዉ የተለመደ ቃል የሚስለዉ/የሚያሳየዉ ስዕል አጭርነትን ነው ፡፡ በትናትናዉ ትምህርት እንደተካፈልነዉ/እንደተማርነው ለመክብብ ትክክለኛዉ ቃል ዘላለማዊ ነው ፤ መክብብ ለጊዜአዊ ሳይሆን ለዘላለማዊ ነገር እየኖርን ወደ ኢየሱስ እንደንመለከት የሚያበረታታን ማለት ነው ፡፡ ኢዮብ ሰዉ ሁሉንም ነገር ቢያጣም አሁንም በእግዚአብሄር ብቻ ደስታ እንደሚኖረው አስተምሮናል ፡፡ መክብብ ተቃራኒዉን ይነግረናል ፤ ሰለሞን ሰዉ ሁሉም ነገር ቢኖረዉ - ኃብት፣ ንብረት፣ ጥበብ፣ ኃይል ቢኖረው እግዚአብሄርን አጥቶት ከነበረ እርካታን/ደስታን እንደሚያጡ አሳይቷል ፡፡ “ ትርጉም የለሽ “ ወይም “ ከንቱ “ ከሚለዉ በተሻለ ምናልባትም “ አጭር “ የሚለዉን በተረዳን ጊዜ የመክበብ መረዳታችን ይቀየራል ፡፡ መዝ (90፡ 12) “ በልብ ጥበብን እንድንማር ቀኝህን/ቁጥርህን/ዘመንህን እንዲህ አስታውቀን “ ፡፡
ትምህርት
መክብብ (3፡ 1)፡ ጊዜ በተለያዬ መንገድ ይለካል ፡፡ የዘመን ቅደም ተከተል ጊዜ በምልከታችን የተነገረ ሲሆን የተለያዩ ድርጊቶችም በወቅቶች የሚሆኑ/የሚፈፀሙ ናቸው ፡፡
መክብብ (3፡ 2-8)፡ እነዚህ ጥቅሶች ተቃራኒን በመግለፅ በተለያዩ መንገዶች ተመሳሳይ ሀሳብን የሚሰሩ ጥንድ ነገሮችን ይይዛሉ ፤ እያንዳንዳቸዉ ጥቅሶች የተለያዩ ሁኔታዎች የተለያዩ ምላሾችን እንደሚጠሩ ያመለክታሉ ፡፡
መክብብ (3፡ 9-15)፡ ነገሮችን በተገቢዉ ስዓት ጥቅም ላይ ሲዉሉ ነገሮች መልካም ይሆናሉ ፡፡ በወደፊቱ ወቅት የማይኖረን ወቅት ምንም የህይወት ወቅት ይሁን በዚህ የህይወት ወቅት ላይ እግዚአብሄር እድልን ሰጥቶናል ፡፡ ጊዜ በዘላለም ብርሀን ይለካል ወይም ደግሞ የሞኝነት ኑሮ እንኖራለን ፡፡ በእያንዳንዱ ቀን ጊዜያዊ የሆኑ ነገሮችን ወይም ለዘላለም የሚቆዩ ነገሮችን የመምረጥ እድሎች አሉን ፡፡ ጥበብ ለዘላለም የሚቆዩ ነገሮችን ንድንመርጥ ያበረታታናል፡፡
መደምደሚያ
መክብብ ዛሬ ዘላለምን እንዳንተወዉ ያበረታናል ፡፡ በዚህ ህይወት አጭር ጊዜ ብቻ ስላለን በአሁኑ ስዓት በማንኛዉም ወቅት ብንሆን ፤ እነዚህ ከእግዚአብሄር የተሰጡ ናቸው ፡፡ እነዚህን ስጦታዎች እንዴት ከእግዚአብሄር እንደምንቀበላቸዉ እና በእነርሱ እንዴት እንደምንኖር እንመርጣለን ፡፡
Hebrew Aramaic Dictionary of the New American Standard Exhaustive Concordance (La Habra: Lockman Foundation, 1998), 1892. Accessed via Logos Bible Software.
Samuel Prideaux Tregelles, Gesenius’s Hebrew and Chaldee Lexicon (Samuel Ragster and Sons: London), accessed via BlueLetterBible.org, https://www.blueletterbible.org/lang/lexi- con/lexicon.cfm?Strongs=H1892&t=ESV.
ጥያቄዎች
-
የመክብብ 3 ጭብጥ ነገሩ ሁሉም ነገር የተወሰነ/የተመረጠ ጊዜ አለዉ የሚል ነው ፡፡ ኢየሱስ ይህን በምን አይነት መንገድ ደግፎታል (ማቴ 26፡ 18, ማር 1፡ 15, ዮሐ 2፡ 4, 7፡ 6, 30) ? ሌሌች መፅሀፍትስ ? (ዘፍ 18፡ 14, ዘጸ 9፡ 5, ማቴ 8፡ 29, ሮሜ 13፡ 11, 2ቆሮ 6፡ 2, ገላ 4፡ 2, 4)
-
በመክ (3፡ 19) ካለዉ ከሰለሞን ንግግር ጋር ትስማማላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አትስማሙም ?
-
መክ (4፡ 1-3) አንብቡ ፤ የሰለሞንን ምልከታ እንዴት ትገልፁታላችሁ ? የተፃፈ “ የጥበብ “ ቃል ያለዉ ይመስላልን ?
-
ሰለሞን ሁሉም ስራና ችሎታ በሌላዉ ላይ በአንድኛዉ ሰዉ ቅናት እንደሚያመጣ ተናግሯል (መክ 4፡ 4) ፤ በዚህ ትስማማላችሁ ? አዎ ከሆነ፣ ፍላጎት መኖር ስህተት ነው ? ያለ ቅንዐት እየሰራን እንደሆነ እንዴት ልናረጋግጥ እንችላለን ? (ገላ 5፡ 26, ያዕ 3፡ 13-18)
-
5፣ በመክብብ (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ecclesiastes 3:1
“There is an occasion for everything, and a time for every activity under heaven.”
ለራስህ ፡- በዚህ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ ከቻልኩኝ ከዚያ በኋላ መልካም ይሆናል ፣ በማለት አስበህ ታውቃለህ ? ወይም ደግሞ ፡- እዚያ ደረጃ ላይ እስከምደርስ መጠበቅ አልቻልኩም ፣ ልትል ትችላለህ ፡፡ እውነቱ ሁልጊዜም ሌላ ከፍ ያለ ደረጃ ደግሞም ብደርስበት ከምትለው ጊዜ በኋላ ያለ ሌላ ጊዜ መኖሩ ነው ፡፡ ምሽቶችን ከሚያለቅሱ ህጻናት ጋር ፤ ወደ ወጣትነት እየደረሱ ያሉ ልጆች ደግሞም ስሜቶቻቸው ፣ በእድሜ የገፉ ወላጆች እነዚህ ሁሉ የህይወት አካል ናቸው ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው ፡፡ እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ሆንከው ማንነት እንድታድግና ክብርን እንድትሰጠው የህይወትህን ጊዜያቶችና አጋጣሚዎች ወስኗል ፡፡
ዋናው ነገር በእያንዳንዱ ጊዜ አይኖችህን በኢየሱስ ላይ ማድረግ ነው ፡፡ ለዘላለም ከአዳኝህ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመኖር ላይ ለማትኮር ወስን ፡፡ በምሽት የህጻን ልጅ የሽንት ጨርቅ ስትቀይር ፣ እግዚአብሔርን አመስግን ዘላለምንም አስብ ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው ፡- ለማልቀስ ጊዜ አለው ለመሳቅም ጊዜ አለው ፤ ለማዘን ጊዜ አለው ለመደሰትም ጊዜ አለው ፡፡ አሁን ያለህበትን ጊዜ አምነህ ተቀበል ፡፡ ዛሬ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ስጦታ ናት ፡፡ ዛሬ ምክንያት አላማ አላት ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር የሚያስተምርህ ነገር አለው ፡፡ በከባድ ጊዜም ውስጥ ይሁን በተለመደው ጊዜ ውስጥ ሆነህ እግዚአብሔርን አመስግነው ፡፡ እግዚአብሔርን ዛሬ ለአንተ ምን እንዳለው ምን እንዳዘጋጀ ጠይቀው !
“ ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው ። “ - መክብብ 3፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
- መክብብ 3:4 — “ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው “
- ፊልጵስዩስ 4:11 — “ ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና ። “
- 1ኛ ተሰሎንቄ 5:18 — “ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።